Logo
SeledaPost
ትራዎሬ ከ 23ተኛ የግድያ ሙከራ ተረፈ

የቡርኪናፋሶው ጥቁር አልማዝ ካፒቴን ኢብራሂም ትራዎሬ ከ22ተኛ የግድያ ሙከራ በተዓምረኛ የደህንነት መዋቅሩ በህይወት መትረፍ ችሏል።

የቡርኪና ፋሶን ማዕድናት ያለከልካይ በመቦጥቦጥ ሀገሪቷ ላይ እንደ ጥገኛ ፓራሳይት ተጣብተው ደሟን ሲመጡ የነበሩት ምዕራባውያንን እርዳታችሁንም ድጋፋችሁንም አንፈልግም፣ እናንተ ካልሰረቃችሁን የሀገሬ ቡርኪና ማዕድን ከህዝቧ አልፎ ለመላ አፍሪካውያን ይተርፋል፣ ፊታችሁን ሳታዞሩ ሀገሬን ለቃችሁ ውጡ ብሎ በቀጭን ትዕዛዝ ጠራረጎ ባባረራቸው ትራዎሬ ጥርስ ነክሰው በሳለፍነው ሳምንት 22ኛቸው የሆነውን ኦፕሬሽን ለመፈጸም በቅድመ ዝግጅት ላይ የነበሩ ቅጥረኛ ሰላዮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ የሆላንድ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም በአስተዳዳሪውና በምክትሉ እንዲሁም በሰራተኞቹ በኩል ትራዎሬን ማስገደልና ከስልጣን ለመገርሰስ ሲንቀሳቀሱ በደህንነት ተቋሙ መያዛቸውን ተከትሎ የቡርኪናፋሶ የደህንነት ተቋም በምርመራው ያገኘው መረጃ እጅግ አስገራሚና በእርግጥም ትራዎሬ ከምዕራቦቹ አቅም በላይ የሆነ የዚህ ትውልድ ቶማስ ሳንካራ ነው አስብሏል።

seledadotio
seledadotio
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.