" የፋይናንስ ባለሙያዎችን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ
➡️ " ግለሰቦቹ ቀድሞ ተዘጋጅቶ ቮይድ በተደረገ ቼክ ተመሳሳይ አሳትመዉ ነበር ለማጭበርበር የሞከሩት " - የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ/ም ድንገት ተከስቶ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ የተከሰተውን አጠቃላይ ጉዳት ለማካካስና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ድጋፍ ሲሰበሰብ እንደነበር ይታወሳል።
ለተጎጂዎች የተሰበሰበ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ የተወሰኑ ግለሰቦች ተመሳጥረው በተጭበረበረ መንገድ ከባንክ ለማውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት እና ገፅታ ግንባታ ዘርፍ ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር አሸናፊ ሃይለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ገንዘቡን ከፋይናስ ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች ጋር በመመሳጠር በአንድ ግለሰብ አማካኝነት በአዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸገር ቅርንጫፍ ለማስወጣት ሲሞክሩ ባንኩ በሰጠው ጥቆማ መሰረት የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ግለሰቡን በቁጥጥር ስር በማዋል ለክልሉ ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል " ሲሉ ገልፀዋል።
ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸዉን የፋይናስ ባለሙያዎችን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር መዋላቸዉን ገልፀው በአሁኑ ወቅት ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
የዞኑ መንግስት ምን ይላል ?
የጎፋ ዞን መንግስት 60 ሚሊዮን 276 ሺህ 383 (ስልሳ ሚልዮን ሁለት መቶ ሰባ ስድሰት ሺ ሶስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ) ቀደም ሲል ተሠርቶ ቮይድ በተደረገ ቼክ ቁጥር ' 42221123 ' ተመሳሳይ በማሳተም ገንዘቡን ለመዝረፍ ካመቻቹ በኋላ ከአዲስ አበባ ንግድ ባንክ ሸገር ቅርንጫፍ ለጎፋ ዞን አስተዳደር በተደረገ ጥቆማ ከአዲስ አበባ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር ገንዘቡ ሳይወጣ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።
" በተለያዩ ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ ትክክለኛና ተጨባጭ መረጃ ከመስጠት ይልቅ ሐሰተኛና የተዛባ መረጃ የሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ " ሲል አሳስቧል።
በቀጣይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የምርመራው ሂደት ሲጣራ ለሕብረተሰቡ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባደረገው ማጣራት የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ገንዘቡን ሲያጭበረብሩ የተያዙት ግለሰቦች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንደሆኑ የገለፁ ሲሆን ፖሊስ እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠዉ መረጃ የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#tikvahethiopiafamilyhawassa
tikvahethiopia

8 months ago