Logo
FIDEL POST NEWS
መራራ ጣዕምን የሚመርጡ ሰዎች የሳይኮፓትነት ባህሪ የማሳየት ዕድላቸው ሰፊ ነው። - ጥናት።

መራራ ጣዕሞችን (ጥቁር ቡና፣ ጥቁር ቸኮሌት፣ ቶኒክ እና የመሳሰሉትን) የሚመርጡ ሰዎች ከጨለማው ትሪያድ ፣ጭካኔ ፣  ሳይኮፓቲ| የስነልቦና መታወክ ያለበት ሰው) እና ማኪያቬሊያኒዝም - ጋር የተያያዙ ባህሪያትን የማሳየት ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው ሲል  በኦስትሪያ የተሰራ ጥናት ያሳያል።

"የጥናቱ ውጤቶች ... መራራ ጣዕምን መውደድ ከተንኮል የተሞሉ የባህሪይ መገለጫዎች ጋር አዎንታዊ ተዛምዶ እንዳለው አረጋግጠዋል፤ በተለይ ደግሞ የዕለት ተዕለት ጭካኔን  እና የሳይኮፓቲ ባህሪን የማሳየት ጠንካራ ግንኙነት አሳይተዋል" ሲሉ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

ሳይንቲስቶች የሚያምኑት ችግሩ ራሱ ጣዕሙ ሳይሆን የነዚህ ሰዎች ለአዲስ ነገር የመፈለግ ፍላጎት እና ደስ የማይል ነገርን ለመጋፈጥ ፈቃደኝነታቸው ነው።

መራራ ነገርን መውደድ የበላይነት ዝንባሌን ሊያመለክት እና ለአሉታዊ ልምዶች መቻቻልን ሊያንፀባርቅ ይችላል።
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.