ከጦር መሳሪያ ድምፅ የፀዳች አፍሪካን ለመፍጠር ቆርጠናል !/ዩጋንዳ /
ዩጋንዳ በአህጉሪቱ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን ግጭት ለመቀነስ እልፎችን ለሞት ለስደት ለረሀብና ማህበራዊ ቀዉስ እየዳረገ የሚገኘዉን የጦር መሳሪያ ድምፅ ለማጥፋት
የጦር መሳሪያዎችን እያቃጠለች መሆኑ ተሰማ ።
"የአፍሪካ የምህረት ወር መታሰቢያ"በሚል መርህ ዩጋንዳ እና የአፍሪቃ ህብረት በጋራ በመሆን በአህጉሪቱ የስጋት አደጋ የሆነዉን እና የበርካቶችን ህይወት ያመሰቃቀለዉን የጦር መሳሪያዎች ስርጭትን ለመግታት ባዘጋጁት ዝግጂት በርካታ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ማውደማቸው ተገልጿል ።
የዩጋንዳ የመከላከያ እና የአርበኞች ጉዳይ ሚኒስትር ጃኮብ ማርክሰንስ ኦቦዝ በኡጋንዳ ምስራቃዊ ጂንጃ በሚገኘው የጋዳፊ ጦር ሰፈር በመገኘት ይህን ምሳሌያዊ የሆነ ተግባር የጦር መሳሪያ ቃጠሎን መርተዋል።
ልምምዱ ዘጠነኛው የአፍሪካ የምህረት ወር አካል ሲሆን "ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰቦችን ለመፍጠር በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ትጥቅ ማስፈታት" በሚል መሪ ቃል ተሰጥቶታል ።
በዩጋንዳ በተዘጋጀው የአፍሪካ የምህረት ወር መታሰቢያ ዝግጂት ላይ የተገኙት መሪዎቹ ይህን በፈቃደኝነት ትጥቅ የመፍታት ሂደት ከጥይት እሩምታ ከሽጉጥ ኳኳታ ከመድፍ ድምታ የፀዳች አህጉር ለማድረግ መሳርያዎችን ዝም ማሰኘት አለብን" ሲሉ አርብ በሰጡት የጋራ መግለጫ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት ሰብሳቢ ተበሌሎ ቦአንግ "መሳርያዎቹ መውደማቸውን፣ዉዱን የሰዉ ህይወትን ማዳን እና የመኖር ተስፋ ያደሰ" ነዉ ብለዋል።
"በጋራ ትጥቅ መፍታትን እናስቀድማለን፣ ሽጉጡን ጸጥ እናደርጋለን እና በ2030 ለሁሉም ሰላም እንገነባለን" ሲሉም አክለዋል።
የኡጋንዳ የመከላከያ እና የአርበኞች ጉዳይ ሚኒስትር ጃኮብ ማርክሰንስ ኦቦዝ ሁሉም ሀገራት የኡጋንዳን ፈለግ እንዲከተሉ የተናገሩ ሲሆን አሁንም ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዘው የሚገኙ ግለሰቦች ለሰላምና ደህንነት ሲባል በገዛ ፈቃዳቸው እንዲያስረክቡ ኦቦት ጠይቀዋል።
ከዚህ የምህረት ዝግጂት በፊት በካምፓላ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን ባለሙያዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት በአፍሪካ የጦር መሳሪያዎችን መስፋፋት ወግታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ. በ2017 መስከረምን የአፍሪካ የምህረት ወር ብሎ ማወጁን ተከትሎ ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ መኖሩን የገለፀዉ በአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ይህን አህጉሪቱን ወደ ሰላም የሚያሸጋግር ተግባር ከአፍሪካ ህብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ)፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ)፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የወጣቶች፣ የሴቶች ማህበራት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን በማድረግ የትጥቅ ጥቃትን ለማስቆም አህጉራዊ አጀንዳ እንዲያደርጉት ጥሪ አቀርቧል።
ለጥንቅሩ ፦ Eastleigh Voice Xinhua የዜና ወኪሎችን ተጠቅመናል ።
#የኔታ_ቲዩብ ዘጋቢ ፦ #ታዴ_የማመይ_ልጅ

10 months ago