Logo
YenetaTube
የአለማችን በርካታ ሃገራት በእስራኤል ላይ ተቆጡ !

የእስራኤል የባህር ኃይል ሃይሎች በጋዛ ለሚገኙ የረሀብ አለንጋ እየተገረፉ ለሚገኙ በሽዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ሰብአዊ ርዳታ ለማድረስ 450 በላይ በጎ ፈቃደኞች የጫኑ የግሎባል ሱሙድ ፍሎቲላ መርከቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ተከትሎ በመላው አለም ከባድ ተቃውሞ ገጠማት ።

‎እስራኤል የጋዛን ርዳታ ፍሎቲላ መያዙን ተከትሎ ረቡዕ ረፋድ ላይ የተቀሰቀሰው ሰፊ ተቃውሞ እስከ ሐሙስ ድረስ በመቀጠል በፈረንሳይ በጣልያን ስዊዘርላንድ ‎ፖርቱጋል ስፔን ዋና ከተሞች እንዲሁም በሌሎች የአውሮፓ ከተሞች እንደ ጄኔቫ፣ ሄልሲንኪ፣ ዘ ሄግ፣ ብራስልስ፣ ኒኮሲያ እና ኢስታንቡል እንዲሁም ኒውዮርክ፣ ኩዋላ ላምፑር፣ ሲድኒ፣ ካራቺ፣ ቦነስ አይረስ እና ሜክሲኮ ሲቲ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል። ።

እሮብና ሐሙስ ዕለት በአውሮፓ እና በዓለም ዙሪያ ባሉ ዋና ዋና ከተሞች ጎዳናዎች የወጡ ሰልፈኞች ‎እስራኤል ወደጋዛ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳይገባ ለረጅም ጊዜ የጣለችውን እገዳ በማንሳት ወደ ሰርጡ ሰብአዊ ዕርዳታ ያለከልካይ እንዲገባ እንድትፈቅድ እንዲሁም የጋዛ ርዳታ ለማድረስ ከ40 በላይ መርከቦችን እና ወደ 500 የሚጠጉ አክቲቪስቶችን ያቀፈዉ በእስራኤል ቁጥጥር ስር የሚገኙት የፍሎቲላ ብድን አባላት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል ።

በፓሪስ ሪፐብሊክ አደባባይ ተሰባስበው እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ጥቃት፣ ፍሎቲላውን ጣልቃ መግባቷን እና የታሰሩትን አክቲቪስቶች በቁጥጥር ስር ማዋልን አውግዘዋል።
‎ሰልፈኞች "ፍልስጤምን ነፃ ውጡ!" የሚል መፈክር አሰምተዋል ።

በ‎ጣሊያን፡ በመላው ኢጣሊያ በዋና ዋና ከተሞች ማለትም በሮም፣ ሚላን እና ኔፕልስ ባሉ ትላልቅ ከተሞች በርካታ ሰዎች የተሳተፉባቸዉ ትላልቅ ሰልፎች ተካሂደዋል።

‎በሚላን ከተማ 20,000 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ በሮም ደግሞ ከኮሎሲየም ተነስተው ፖርታ ሳን ፓኦሎ በደረሰው ሰልፍ 10,000 ሰዎች መገኘታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በስፔን በባርሴሎና ፖርቶ እና ኮይምብራን ጨምሮ በዘጠኝ ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል
በሰልፉ የመብት ተሟጋቾችና በጎ ፍቃደኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል ።

በሽታዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በእስራኤል ኤምባሲ ፊት ለፊት ተገኝተው "ነፃነት ለፍልስጤማውያን " "በእስራኤል የተጣለው ማዕቀብ" እና "በፍልስጤም ላይ ያለውን ከበባ ይቁም" የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል ።

በስዊዘርላንድ በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል ። በጄኔቫ በተካሄደዉ ሰልፍ የእስራኤል ተግባር ያወገዙ ተቃዋሚዎች ጎማ በማቃጠል በኮርናቪን ባቡር ጣቢያ ላይ የባቡር ሀዲዶችን ለአጭር ጊዜ በመዝጋት ተቃዉሞአቸዉን አሰምተዋል ።

በአቴንስ ተሰባስበው ወደ እስራኤል ኤምባሲ
በከባድ ተቃዉሞ ካመሩት መካከል አንዱ የሆነዉ ጴጥሮስ ቆስጠንጢኖው በግሪክ የተባበሩት ዘረኝነት እና የፋሺስት ስጋት (KEERFA) ንቅናቄ ተቃዋሚዎች “የእስራኤል ጦር በፍሎቲላ ላይ የወሰደው ተግባር የባህር ላይ ወንበዴ ተግባር ነዉ” ብለዋል።

በማርሴይ ወደ መቶ የሚጠጉ የፍልስጤም ደጋፊ ሰልፈኞች ሃሙስ እለት ከሰአት በኋላ ወደ እስራኤል ወታደራዊ ጥቃትን አዉግዘዋል ።ለ ቴላቪቭ ወታደራዊ ቁሳቁስ አቅርቧል ብለው የከሰሱትን የጦር መሳሪያ ኩባንያ ዩሮሊንክስን ሊዘጉ ሲሞክሩ ፖሊስ አስቁሟቸዋል ።

አለምአቀፋዊ ሚዲያዎች በፊት ገፃቸው እንዳስነበቡት ከሆነ ትላንትና ዛሬ እነዚህና ‎በፍልስጤም ላይ ያለው ከበባ መቆም አለበት ያሉ በሌሎች የአውሮፓ ከተሞች እንደ ጄኔቫ፣ ሄልሲንኪ፣ ዘ ሄግ፣ ብራስልስ፣ ኒኮሲያ እና ኢስታንቡል እንዲሁም ኒውዮርክ፣ ኩዋላ ላምፑር፣ ሲድኒ፣ ካራቺ፣ ቦነስ አይረስ እና ሜክሲኮ ሲቲ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል። ሲሉ የዘገቡት ሮይተርስ አልጀዚራ ኒዮርክ ታይምስ ኤፒ እና ሌሎችም አለምአቀፋዊ የዜና አዉታሮች ናቸዉ ።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.