Logo
YenetaTube
የግብፅ ወታደሮች በምስራቅ አፍሪካ እግራቸው ተከሉ !

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በዲፕሎማሲያዊ መድረኮች ተወስና የቆየችዉ ግብፅ በቀጠናው ያላትን ተሳትፎ ወደ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፍ በማሳደግ በሚቀጥሉት ሳምንታት ጦሯ በጎረቤት ሀገር ሱማሊያ እንደምሚሰማራ ተናገረ ።

ወደ ሶማሊያ የሚሰማራው የግብፅ ጦር በሚቀጥሉት ሳምንታት የቡሩንዲ ጦርን በመተካት በመካከለኛው ሸበላ ክልል ሴክተር አምስትን እንደሚቆጣጠር የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ረቡዕ አስታዉቀዋል ።

መሃሙድ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በሽዎች የሚቆጠሩ ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቁ ወታደሮቹ በባድማ እና ማሃዳይ ወረዳዎች መካከል እንደሚሰፍሩ አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንቱ ሶማሊያ በካይሮ እና በአዲስ አበባ መካከል ለሚካሄደው የውክልና ጦርነት የጦር አውድማ እንድትሆን እንደማትፈቅድ ገልጸው፣ በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገኘውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በተፈጠረ አለመግባባቶች ቢኖሩም ግንኙነታችን ቀጥሏል። ብለዋል

መሃሙድ "በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ, ነገር ግን በሶማሊያ ውስጥ አይደለም." “ከምንም ተነስቶ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የሚሄድ የግብፅ ወታደሮች የሉም፣ ግብፅም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንድንሄድ የጠየቀን የለም ያሉት ፕሬዘዳንቱ አክለዉም ። ኢትዮጵያ እና ግብፅ በሶማሊያ ውስጥ የሚዋጉበት ምንም ምክንያት የለም" ብለዋል. ።

የግብፅ ጦር በሶማሊያ በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ስር በሶማሊያ ከሚሰማራዉ ጦር በፊት ለስለላ ተልእኮ ሞቃዲሾ ገብቷል።

በሜጄር ጄኔራል እስላም ራድዋን የሚመራው የልዑካን ቡድን በሞቃዲሾ እና በመስክ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎችን በመመልከት የስምምነት ሁኔታዎችን፣ የወታደሮች ማረፊያ እና የሎጂስቲክስ ዝግጅቶችን በመገምገም ላይም ይገኛል ።

እንደ AUSSOM ዘገባ ግብፅ 1,100 የሚጠጉ ወታደሮችን ለማሰማራት በዝግጅት ላይ ትገኛለች እነዚህም በመካከለኛው ሸበሌ ክልል በሶስት ቦታዎች ላይ የሚሰፈሩትን የቡሩንዲ ወታደሮችን ለመተካት ነው።

በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ ተገንጣይ ግዛት መካከል የተደረገውን አወዛጋቢ ስምምነት ተከትሎ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ውጥረት ከቅርብ ወራት ወዲህ ወደ መባባስ ያመራ ሲሆን በቀጠናዉ እግሯን መትከል የምትፈልገዉ ግብፅ የሶማሊያን መንግስት ስምምነቱን ውድቅ ማድረጉን በጠንካራ ሁኔታ ስትደግፍ ቆይታለች ፣ ይህም በካይሮ እና ሞቃዲሾ መካከል አዲስ የወታደራዊ እና የፀጥታ ትብብር እንዲኖር መንገድ ከፍቷል።

"በሶማሊያ የግብፅ ኃይሎች መኖራቸው በኢትዮጵያ ላይ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ጫና አሳድሯል" ሲሉ የቀጠናው የፖለቲካ ተንታኞች በአባይ ውሃ ላይ እየጨመረ የመጣው ቁርሾ ወደ ሰፊ ቀጠናዊ ጥምረት እየገባ መሆኑን ይገልጻሉ። ሲል ያስነበበው ሃራሬ የዜና ወኪል ነዉ ።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.