" ውጤት ባይመጣም ተስፋ አለ"
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤት ግራ ተጋብቻለኹ። 91 በመቶዎቹ የማለፊያ ውጤት እንዳላገኙ ተዘግቧል።
በግልፅ ክፍተቱ የማነው የሚለው ሰፊ ስራ ይጠይቃል። የሌሎች አገራት ተሞክሮ ምን ይመስላል? የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ መጣር በዚኽ ልክ ተማሪዎችን ይጥላል ወይ ?በየአመቱ የተፈታኝ ቁጥር ማሽቆልቆሉስ ? የቀጣይ ትውልድ እጣ ፋንታ ያሳስባል።
በኖርዌይ ኢንስቲትዩት ኦፍ ፐብሊክ ኼልዝ በተካሄደ የቅርብ ጊዜ ጥናት መሰረት የሁለተኛ ደረጃ ውጤት ከተማሪዎች የአእምሮ ጤና መታወክ ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለው።
ጥናቱ እንዳረጋገጠው ውጤት ካልመጣላቸው 21 በመቶ የሚኾኑት ተማሪዎች ከፍተኛ ለኾነ ለአእምሮ ጤና መታወክ ተጋልጠዋል።
በእኛም አገር ጥናት ይፈልጋል። ነገር ግን በርካታ ልጆቻችን ውጤቱን ተከትሎ ተስፋ መቁረጥ፣ ግራ መጋባት፣ ድባቴ፣ ቀደም ሲል የነበረ ተነሳሽነት መቀዛቀዝ፣ ራስ ምታት፣ መጨነቅና ብቸኝነትን የመምረጥ ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላል።
ይህ የስነልቦና ጫናና የስሜት ስብራት ለአጭር እና ለረዥም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፤ በዚህ ወቅት ድጋፍና እንክብካቤ ይሻሉ።
ተስፋ አለ፤ ከታሪክ ምን እንማራለን ?
ቶማስ ኤዲሰን በ12 አመቱ ከትምህርት ቤት ተባረረ። መምህሩ ለእናቱ ተስፋ አስቆራጭ መልእክት ይልካል። "ልጅሽ የማይገባው ዘገምተኛ ነው፤ ከትምህርት ቤት ተባሯል" የሚል ነበር።
ጀግናዋ እናቱ ( ናንሲ ኢሊዮት ኤዲሰን) ይኽንን መልእክት ፈፅሞ አልተቀበለችም። ልጇን 'አንተ ምጡቅ አእምሮ አለህ' እያለች በቤቷ ማስጠናቷን (Homeschooling ) ቀጠለች።
ያወጀችበት ፍሬ አፈራና ቶማስ ኤዲሰን የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ አምፖል ግኝት ባለቤት ኾነ። መላው አለማችንን ከ "ጨለማ" ወደ "ብርሃን" አሸጋገረ።
ሌላው አልበርት አንስታይን በትምህርት ቤቱ ለምንም የማይጠቅም ስለኾነ ኹላችንንም ሳያደክመን ትምህርት ቢያቋርጥ የሚል ሃሳብ ቀርቦ ነበር። ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደገባ ትምህርት አስጠልቶት ነበርና በአንዳንድ ትምህርቶች ደኽና ቢያመጣም በተቀሩት ግን በጣም ዝቅተኛ ውጤት አመጣ።
ይኹንና ታሪክ ተቀይሮ አልበርት አንስታይን በ1921 በፊዚክስ የኖቤል ተሸላሚ ኾነ።
💡 ምክረ ሃሳብ
✅ ተማሪዎች ከካርድ ውጤት በላይ ናቸው።
✅ውጤት ባለመምጣቱ ፈተና ሊወድቁ ይችላሉ ነገር ግን ውዳቂ አይደሉም። ይኽ ጊዜያዊ የህይወት ገጠመኝ አካል እንጂ ማንነታቸው አድርገው ሊወስዱት አይገባም።
✅ውጤት አለማምጣት የህይወት መጨረሻ አይደለም፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ተስፋ አለ። ከታሪክ የምንማረው ይኽን ነው።
መውጫ
ተማሪዎች ምንም ዓይነት ውጤት ቢያስመዘግቡም ለራሳቸው ያላቸውን ክብርና ራስ መተማመን አንውሰድባቸው፤ እንደምንወዳቸውና ከጎናቸው እንደሆንን እናረጋግጥላቸው። ይህ የወጣቶቹን አለም ይቀይራል።
[ https://t.me/childdevtnetw... ]
✍️ ብርሃኑ በላቸው አሰፋ
የክቡር ልጆች ደራሲ (የሕንጸት 2017 አዋርድ ተሸላሚ መጽሐፍ )

9 months ago