የባንግላዴሽ የግብርና ዩኒቨርሲቲ ለምርምር ያመጣቸው 14 በጎች ተሰረቁ
በባንግላዴሽ የግብርና ዩኒቨርሲቲ (BAKU) የምርምር ፕሮጀክት እርሻ ውስጥ ይራቡ የነበሩ አስራ አራት የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው በጎች ተሰርቀዋል።
ባለስልጣናት እንደተናገሩት በጎቹ የ'ዳርፓር' እና 'ጋሮል' ዝርያዎች ናቸው።
ከበጎቹ ዘር በመሰብሰብ ተግባራዊ ስልጠና ለተማሪዎቹ ለመስጠት ታስቦ ነበር።
" ከስርቆቱ በኋላ የዩኒቨርሲቲው የቅድመ ምረቃ፣ የድህረ ምረቃ እና የዶክትሬት ተማሪዎች ምርምርም በእጅጉ ተጎድቷል" ሲሉ የባንግላዴሽ የግብርና ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ሃላፊ የሆኑት ናዝሙል ኢስላም ተናግረዋል።
በጎቹ ታርደው ተበልተዋል ወይስ አንድ ድብቅ ቦታ ላይ ይገኛሉ የሚለውን ለማወቅ ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

11 months ago