5 months ago
በአዲስ አበባ የሕዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን ለውጥ ተከትሎ፣ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። ይህ አዲስ የታሪፍ ጭማሪ ከነገ ሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
ማሻሻያው ሚኒባስ ታክሲዎችን፣ ሚዲባሶችን (ሃይገርና ቅጥቅጥ) እንዲሁም የከተማ አውቶብስ አገልግሎቶችን ያጠቃልላል።
1. የሚኒባስ ታክሲ አገልግሎት
የሚኒባስ ታክሲ ታሪፍ እንደ ርቀቱ ከ5 እስከ 10 ብር የሚደርስ ጭማሪ ታይቶበታል።
* እስከ 2.5 ኪ.ሜ፡ 10.00 ብር (ያለ ለውጥ ይቀጥላል)
* ከ 2.6 - 5 ኪ.ሜ፡ 20.00 ብር (የ5 ብር ጭማሪ)
* ከ 7.6 - 10 ኪ.ሜ፡ 35.00 ብር (የ10 ብር ጭማሪ)
* ረጅሙ ርቀት (17.6 - 20 ኪ.ሜ)፡ 55.00 ብር ደርሷል
2. የሚዲባስ (ሃይገርና ቅጥቅጥ) አገልግሎት
* እስከ 8 ኪ.ሜ፡ 15.00 ብር
* ከ 12.01 - 16 ኪ.ሜ፡ 30.00 ብር
* ከ 24.01 - 28 ኪ.ሜ፡ 45.00 ብር ሆኗል
3. የከተማ አውቶብስ አገልግሎት
* እስከ 7.5 ኪ.ሜ፡ 10.00 ብር
* ከ 30.01 - 45 ኪ.ሜ፡ 60.00 ብር
* ከ 40.01 - 50 ኪ.ሜ፡ 70.00 ብር እንዲሆን ተወስኗል
ልዩ ማሳሰቢያ፡ የሸገር ትራንስፖርት አገልግሎት በተስተካከለው ታሪፍ መሠረት በሁሉም መስመሮች 10 ብር ሆኖ እንደሚቀጥል ቢሮው አረጋግጧል።
ሕገ-ወጥ አሰራርን እንዴት እንከላከል?
አገልግሎት ሰጪዎች ከተቀመጠው ታሪፍ ውጪ ሲያስከፍሉ ወይም እንግልት ሲያደርሱ ከተገኙ፣ የሰሌዳ ቁጥራቸውንና ሰዓቱን በመያዝ በነፃ የጥሪ መስመር 9417 ላይ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #መናኸሪያFm #አዲስ_አበባ #ትራንስፖርት #ታሪፍ_ማሻሻያ #ኢትዮጵያ #የታክሲ_ታሪፍ #addisababa #ethiopia #transportupdate

Comments