11 days ago
ውድቀት ሳይሆን ያልሰሩ 10ሺህ መንገዶችን አግኝቻለሁ
#ethiopia | ኤዲሰን የኤሌክትሪክ አምፖልን ለመስራት በሚያደርገው ሙከራ 10,000 ጊዜ ሳይሳካለት ቀርቷል።
ሌሎች ሰዎች ይህን እንደ ትልቅ ውድቀት ሲቆጥሩት እሱ ግን እኔ አልወደቅኩም ይልቁንም የማይሰሩ 10,000 መንገዶችን አግኝቻለሁ አለ።
በማለት ለነገሩ ያለው አዎንታዊ አመለካከት እና ተስፋ ያለመቁረጥ ባህሪ ምን ያህል ጠንካራ እንደነበር አሳይቷል።
ኤዲሰን ለስራ ያለው ፍቅር ልዩ ነበር።
ኤዲሰን በምርምር ላቦራቶሪው ውስጥ በቀን 18 እስከ 20 ሰአታት ይሰራ እንደነበር ታሪክ የሚነግረን።
እንቅልፍ እንደ ጊዜ ማባከን ይቆጥር ስለነበር በስራ መካከል ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ እረፍት ያደርግ ነበር።
ኤዲሰን ስለስኬቱ በተደጋጋሚ ያለመሰላቸት መስራቱ እንደነበር ይጠቀሳል።
እሱም እንዲህ የሚል አስተሳሰብ ነበረው "ስኬት የሚመጣው 1 በመቶ በተጸጥሮ ጥበብ ሲሆን 99 በመቶው በጥረት በላብህ በትጋትህ የሚመጣ ነው" የሚል።
ቶማስ ኤዲሰን ተአምር ወይም እድል የሚባሉ ነገሮችን በእሱ ዘንድ ቦታ አልነበራቸውም።
ጭራሹም በእነዚህ አስተሳሰቦች አያምንም ነበር።
ታላቅነት ችሎታ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነት ባለው ጥረት ተስፋ ባለመቁረጥ እና ችግሮችን ወደ እድል በመቀየር የሚገነባ መሆኑን የኤዲሰን መንገድ ያስተምረናል።
ኤዲሰን በህይወት ዘመኑ 1,093 የፈጠራ መብት ፓተንቶች በስሙ ማስመዝገብ የቻለ ታላቅ የፈጠራ ባለቤት ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #thomasedison #history #engineering #technology

Comments