5 months ago
የራይድ ትራንስፖርት እና የቦስተን ፓርትነርስ (ኩሪፍቱ) ታሪካዊ የሥራ ስምምነት ተፈራረሙ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፖርት ፈር ቀዳጅ የሆነው ራይድ ትራንስፖርት፣ በቱሪዝምና መስተንግዶ ዘርፍ ግዙፍ ስም ካለው ቦስተን ፓርትነርስ ጋር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በጋራ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተፈራርሟል።
የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎት፦
ራይድ የኤሌክትሪክ መኪኖቹን እንደ እንጦጦ ፓርክ፣ አፍሪካ ቪሌጅ እና ኩሪፍቱ ቢሾፍቱ ባሉ የቱሪስት መስህቦች በመመደብ ከቦስተን ፓርትነርስ ጋር በጋራ ይሰራል።
ለታላላቅ ሁነቶች አስተማማኝ ትራንስፖርት፦
በኩሪፍቱ ሪዞርቶች በሚካሄዱ ትልልቅ ስብሰባዎች፣ የጋብቻ ሥነ ሥርዓቶችና ኮንሰርቶች ወቅት ራይድ በቂና አስተማማኝ ትራንስፖርት ያቀርባል።
ዘመናዊ የቱሪስት ትራንስፖርት፦
ለኩሪፍቱ ሪዞርትና ለቦስተን ስፓ ደንበኞች ያለምንም እንግልት የሚንቀሳቀሱበት ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ይቀርባል።
የጋራ የገበያ ትስስርና ፕሮሞሽን፦
ሁለቱ ተቋማት የጋራ የገበያ ትስስር፣ የማስተዋወቅና የብራንድ ግንባታ ሥራዎችን በትብብር ያከናውናሉ።
አዳዲስ ፓኬጆች፦
የገበያ ተደራሽነትን የሚያሰፉ አዳዲስ የጋራ ፓኬጆችን በማዘጋጀት ለተጠቃሚዎች ያቀርባሉ።
የራይድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሳምራዊት ፍቅሩ ስምምነቱ ሰዎችን ከዕድሎች ጋር የማገናኘት ራዕያቸውን ይበልጥ እንደሚያሳልጠው ገልጸዋል።
የቦስተን ፓርትነርስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታዲዎስ ጌታቸው በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው ላለፉት 24 ዓመታት የጀመረውን አዳዲስ የቱሪዝም አገልግሎቶችን የማቅረብ ጉዞ ይህ ስምምነት ይበልጥ እንደሚያዘምነው ተናግረዋል።
#getu #ethiopia #ride #bostonpartners #kuriftu #tourism #digitaltransport #businessnews #samrawitfikru #tadiwosgetachew #ራይድ #ኩሪፍቱ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments