3 months ago
ባርሴሎና ለኤል ክላሲኮ ልዩ ማልያ ይዞ ይቀርባል
#ethiopia | የካታላኑ ኩራት ባርሴሎና ከዋነኛ ተቀናቃኙ ሪያል ማድሪድ ጋር ለሚያደርገው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ፣ የአሜሪካዊቷን ዝነኛ አቀንቃኝ የኦሊቭያ ሮድሪጎን (Olivia Rodrigo) አርማ የያዘ ልዩ ማልያ እንደሚጠቀም ታወቀ።
ይህ አሰራር ክለቡ ከዋና ስፖንሰሩ ስፖቲፋይ (Spotify) ጋር ባለው ስምምነት መሰረት የሚከናወን ሲሆን፣ በታላላቅ ጨዋታዎች ላይ የዓለም አቀፍ አርቲስቶችን አርማ በማልያው ላይ በማድረግ ማስተዋወቂያ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህኛው ጨዋታም የአርቲስቷን መጠሪያ የመጀመሪያ ፊደላት የያዘው "OR" የሚል አርማ በባርሴሎና ማልያ ደረት ላይ ደምቆ ይታያል።
ይህ ልዩ እትም የሆነ ማልያ ለገበያ የቀረበ ሲሆን፣ ዋጋውም እንደ ይዘቱ ከፍ ያለ ነው። መደበኛው ልዩ ማልያ በ400 ዩሮ እየተሸጠ ሲሆን፣ የአርቲስቷ ኦሪጅናል ፊርማ ያረፈበት ማልያ ደግሞ በ3,000 ዩሮ ለሽያጭ ቀርቧል።
ባርሴሎና ከዚህ ቀደም እንደ ድሬክ፣ ሮሊንግ ስቶንስ እና ካሮል ጂ ያሉ ታዋቂ አርቲስቶችን አርማ በተመሳሳይ መልኩ መጠቀሙ ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#fcbarcelona #elclasico #oliviarodrigo #spotify #barcanews #footballfashion #laliga #oliviarodrigoor #barcajersey

''የሮድሪ ጉዳት ለአርሰናል ብስራት ነው''ጋሪ ኔቭል
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ሽሚያ ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በባለሙያዎችና በቀድሞ ተጨዋቾች መካከል የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ትኩረትን እየሳቡ ይገኛሉ። በተለይም የማንቸስተር ሲቲው የቁልፍ ሰው ሮድሪ ጉዳት በፉክክሩ ላይ ሊያመጣ የሚችለው ተፅዕኖ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል።
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ጋሪ ኔቭል እንደገለጸው፣ የሮድሪ ከሜዳ መራቅ ለለንደኑ ክለብ አርሰናል ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው። "ሮድሪ ለሁለት ወይም ለሦስት ሳምንታት እንኳን ቢርቅ፣ በዋንጫ ፉክክሩ ለአርሰናል ትልቅ ብስራት ሊሆን ይችላል" ሲል ኔቭል ተናግሯል።
ኔቭል አክሎም የአርሰናሉን አማካይ ዴክላን ራይስን እንቅስቃሴ በተለየ መንገድ ተመልክቶታል። ራይስ "ፉክክሩ ገና አላበቃም" የሚል ተስፋ ያለው ንግግር ቢያደርግም፣ ኔቭል ግን የተጫዋቹን የፊት ገጽታና የሰውነት ቋንቋ በመጥቀስ "ሁሉም ነገር አብቅቷል" የሚል ስሜት ውስጥ እንዳለ ገምቷል።
"ራይስ ቡድኑን ለማነሳሳት ሲሞክር ቢታይም፣ እኔ ግን የተሰማኝ ተስፋ የቆረጠ ይመስለኛል" ብሏል።
በተቃራኒው የአርሰናሉ የምንግዜም ኮከብ ኢያን ራይት አሁንም በክለቡ ላይ ያለውን ፅኑ እምነት አጋርቷል። ራይት ምንም እንኳን ፉክክሩ ጠንካራ ቢሆንም፣ "አሁንም ቢሆን እኛ አርሰናሎች ሊጉን እንደምናሸንፍ አምናለሁ" በማለት ለደጋፊዎች ያለውን ተስፋ ገልጿል።
የሮድሪ ጉዳት ማንቸስተር ሲቲን ዋጋ ያስከፍል ይሆን ወይስ አርሰናል የተፈጠረለትን አጋጣሚ ተጠቅሞ የዓመታት የዋንጫ ጥማቱን ያረካል? የሚለው ጥያቄ በሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታዎች ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#arsenal #mancity #premierleague #garyneville #ianwright #rodri #footballnews #declanrice #epl #titlerace

8 months ago
በሳምንቱ መጨረሻ እንደተለመደው አትሌቶቻችን በተለያዩ ሀገራት በተለያየ ርቀት አሸንፈዋል።
2025 Incheon marathon, South Korea
Men's
1. Gerba Dibaba 2:06:52 🇪🇹
2. Gilbert Kibet 2:06:54 🇰🇪
3. Felix Kibitok 2:06:57 🇰🇪
4. Abdisa Tola 2:08:40 🇪🇹
5. Robert Ngeno 2:09:02 🇰🇪
2025 ETHIOPIAN GREAT RUN 10KM
Men's
1. Yismaw Dillu 28:25 🇪🇹
2. Eyob Simegn 28:28 🇪🇹
3. Dinkalem Ayele 28:29 🇪🇹
4. Beniyam Melak 28:30 🇪🇹
5. Jerata Lensa 28:31 🇪🇹
6. Negesa Dekeba 28:34 🇪🇹
7. Adisu Negash 28:39 🇪🇹
8. Chim'sa Debele 28:40 🇪🇹
9. Zenebe Ayele 28:47 🇪🇹
10. B. Gatahun 28:48 🇪🇹
WOMEN
1. Likina Amebaw 27:25 🇪🇹
2. Sheila Jebet 27:55 🇰🇪
3. V. Gemetto 28:11 🇮🇹
4. Idaira Suarez 28:19 🇪🇸
5. Noshim Kimuge 28:33 🇰🇪
Men
1. Mathew Kipsang 23:10 🇰🇪
2. Rodrigue Kwizera 23:11 🇧🇮
3. Mathew Kipkoech 23:13 🇰🇪
4.T. Ndikumwenayo 23:13 🇪🇸
5. Naibei Kiplimo 23:45 🇰🇪
NBF Fujairah 10km (Émirats arabes unis)
1. Abu Salim Mayanja UGA 28:28, 2. Dagne Demsie ETH 28h30,
3. Feyisa Tadese ETH 28:31,
6.7km Cross Cinque Mulini, Italy
Winner: Yenenesh Shimket 19:11 🇪🇹
Via: Toprun news
#athletics #running #5km #10km #15km #halfmarathon #worldathletics #followers #highlight #ethiorunners #ethiorunnersfan #ethiopianathletics #ethiopianathleticsfederation
✍️
Wondmagegn Getachew Yigezu

Sponsored by
Surafel
Comments