1 month ago
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ10 ወራት ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
*****************
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት ውስጥ ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) የ10 ወራት የእቅድ አፈጻጸምን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ተቋሙ የሪፎርም እና በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በመከተሉ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ በሪፎርም ስራዎች እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረጉ፣ በማጭበርበር ምክንያት ሊጠፋ የነበረና ሀገር ልታጣው የነበረ 256.7 ቢሊዮን ብር በጥቅሉ ወደ ገቢ መቀየር መቻሉን ገልጿል።
በበጀት ዓመቱ 725 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ፣ በ10 ወራት ውስጥ ብቻ ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል። ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ258 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተመላክቷል።
ለዚህ ስኬታማ አፈጻጸም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እና የተቋሙ አዲስ አደረጃጀት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተጠቅሷል።
በሌላ በኩል፣ ከገቢ እና ወጪ ኮንትሮባንድ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ 23.1 ቢሊዮን ብር ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች (አልባሳት፣ ማዕድናት፣ መድኃኒቶች፣ ኮስሞቲክስና ኤሌክትሮኒክስ) ተይዘው ገቢ ተደርገዋል። በድንገተኛ ፍተሻና ቁጥጥር ብቻ 2.8 ቢሊዮን ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።
የሕግ ማስከበር ስራውን በተመለከተም፣ በሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማሩ 1,295 ኮንትሮባንዲስቶችን በቁጥጥር ስር በማዋል ለሕግ ማቅረብ መቻሉ ተረጋግጧል።
ኮሚሽኑ የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ለማበረታታትና ኢንቨስትመንትን ለመደገፍ በሚያደርገው ጥረት፣ ለዘርፉ የሚውል 328.5 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉንም ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በቀሪዎቹ የበጀት ዓመቱ ወራትም ሕገ-ወጥ ዝውውርን በመከላከል እና የመንግስትን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ ረገድ የተጀመረው ውጤታማ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በሂሩት እምቢአለ
#ebcdotream #customscommission #revenue

Comments