11 days ago
በ660 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር የማጓጓዣ ጊዜን በ80% ይቀንሳል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና የዳንጎቴ ግሩፕ በጋራ አክሲዮን (Joint Venture) የሚያለሙት የ660 ሚሊዮን ዶላር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ በትላንትናው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት "ይህ ታሪካዊ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት የሎጂስቲክስ ወጪዎችንና መዘገየቶችን የሚቀንስ፣ የኢነርጂ ደህንነትን የሚያጠናክር እንዲሁም የኢትዮጵያ-ጂቡቲ የንግድ ኮሪደርን ውጤታማነትና ጽናት የሚያሳድግ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅቡቲ በተካሄደው የመሰረት ድንጋይ ማኖሪያ ሥነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ነዳጅ በጭነት መኪና ሲገባ አምስት ቀናት እንደሚወስድ አንስተው፣ አዲሱ የቧንቧ መስመር ይህንን ጉዞ ወደ አንድ ቀን ዝቅ እንደሚያደርገው አስረድተዋል።
ለመሆኑ ይህ ፕሮጀክት ምን ያካትታል ?
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ቢልሌኔ ሥዩምን ጠቅሶ ብሉምበርግ እንደዘገበው፤ በፕሮጀክቱ ፥
- የ120 ኪሎሜትር የቧንቧ መስመር ዝርጋታን፤
- በዳሜርጆግ 375,000 ኩቢክ ሜትር እንዲሁም በደወሌ 800,000 ኩቢክ ሜትር የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናሎችን ግንባታ ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ብሩክ ታዬ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የቧንቧ መስመሩ በተቋሙ እና በናይጄሪያው ዳንጎቴ ግሩፕ በጋራ አልሚነት የሚገነባና እንደሚተዳደር አንስተዋል።
ከጂቡቲ ዳሜርጆግ ወደብ እስከ ኢትዮጵያ ደወሌ የሚዘረጋው ይህ የ120 ኪሎሜትር መስመር፤ በጭነት መኪኖች ይካሄድ በነበረው ረጅም የጉዞ ሂደት ላይ ይታይ የነበረውን ቅሸባ፣ ብክነት እና ህገ-ወጥ አሰራር በዘላቂነት እንደሚቀርፍም ገልጸዋል።
ዶክተር ብሩክ አክለውም፥ ኢትዮጵያ የራሷ ዴፖ ባልነበራት ጊዜ መርከቦች ቦታ ጠብቀው ለማራገፍ ከሁለት ቀን እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ ይወስዱባት የነበረውን መዘግየትና አሁንም ድረስ የምትከፍለውን የዲሞሬጅ (የመጠበቂያ) ወጪ እንደሚያስቀር ነው የተናገሩት።
በደወሌ የሚገነባው ሁለተኛው ዴፖ ደግሞ ከአዋሽ በተጨማሪ ለወራት የሚበቃ ስትራቴጂካዊ የነዳጅ ክምችት ከመፍጠሩም ባሻገር፣ ከኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ሃዲድ ጋር በመገናኘቱ ነዳጅ በቧንቧ ከተቀበለ በኋላ በባቡርና በጭነት መኪኖች ወደ አገር ውስጥ ለማሰራጨት የሚያስችል ነው።
ፕሮጀክቱ በመጪዎቹ ሁለት አመታት እንደሚጠናቀቅም ነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ብሩክ ታዬ የገለጹት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለፕሮጀክቱ የፋይናንስ ድጋፍ ላደረጉት ለአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (Afreximbank) ፕሬዝዳንት ዶክተር ጆርጅ ኤሎምቢ ምስጋና አቅርበዋል።
@TikvahethMagazine

2 months ago
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ወደ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ተሸጋገረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) በይፋ"ፋይዳቨርስ" በመባል ወደ የመንግሥት የልማት ድርጅት ማዕቀፍ ማደጉ ተገለጸ።
ይህ አዲስ ድርጅት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ሥር የተጠቃለለ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ከነበረበት ማዕቀፍ ወጥቶ በንግድ አሠራር የሚመራ እና ዘላቂ ዲጂታል መሠረተ ልማት አቅራቢ ሆኖ እንዲቀጥል ታስቦ የተቋቋመ መሆኑ ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ እንደገለጹት፤ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ለቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ወሳኝ ድርሻ አለው።
ፕሮግራሙ አሁን ላይ ከ50 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን መመዝገብ የቻለ ሲሆን፣ 150 የሚደርሱ የንግድ ተቋማት የደንበኛ ማረጋገጫ (eKYC) ውህዶችን አከናውኗል። በተጨማሪም ከ190 ሚሊዮን በላይ ደህንነታቸው የተጠበቁ የማረጋገጫ ሂደቶችን በማከናወን ከ15 ሚሊዮን በላይ ዲጂታል መታወቂያ ምስክር ወረቀቶችን መስጠቱ ተገልጿል።
ተቋሙ አሁን የያዘውን አዲስ መዋቅር በመጠቀም የዲጂታል መታወቂያ መፍትሔዎችን ከአህጉራዊ አጀንዳዎች ማለትም ከአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና እና ከስማርት አፍሪካ ጋር ለማስተሳሰር እና አገልግሎቱን በክልሉ ለማስፋፋት ተነግሯል።
Seledadotio

4 months ago
","work_is_company_qa_poll":false,"options":{"nodes":[{"profile_voters":{"count":4},"id":"3295754563932202","text":"u1265u122bu12dau120d","viewer_has_voted":false,"unique_votes_count_company_qa_polls":4,"grouped_option_votes":[],"sample_voters":{"count":4,"nodes":[{"__typename":"User","id":"100004689856132","name":"Miftah Bearings","profile_picture":{"uri":"https://scontent-lhr6-1.xx...
7 months ago
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በጅቡቲ ግዙፍ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ሊገነባ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) በጅቡቲ ዳመርጆግ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ 150 ሺህ ኩቢክ ሜትር ነዳጅ የማከማቸት አቅም ያለው ግዙፍ ማጠራቀሚያ ለመገንባት የሚያስችለውን የ10 ሄክታር መሬት ጥያቄ በይፋ አቅርቧል።
ይህ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መለከት ሳህሉ ከጅቡቲ ወደቦችና ነፃ ቀጠናዎች ባለሥልጣን ሊቀመንበር ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው።
ይህ ግንባታ አሁን ላይ የማከማቸት አቅሙ ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀው የሆራይዘን ተርሚናል የተሻለ አማራጭ ሆኖ የቀረበ ነው። በዓመት 25 ሚሊዮን ቶን የማስተናገድ አቅም ባለው በአዲሱ የዳመርጆግ ወደብ የሚገነባው ይህ ማጠራቀሚያ፤ በባቡር መስመርና በነዳጅ ማስተላለፊያ አቅራቢያ መሆኑ ነዳጅን ወደ ሀገር ውስጥ በፍጥነት ለማጓጓዝ ምቹ ያደርገዋል።
ከዚህም ባሻገር፥ በባህረ ሰላጤው አካባቢ ያለውን ወቅታዊ ቀውስ ተከትሎ ሀገሪቱ አስተማማኝ የነዳጅ ክምችት እንዲኖራት ከማስቻሉም በላይ፤ መርከቦች ወደብ ላይ ለረጅም ጊዜ በመቆየታቸው ምክንያት የሚከፈለውን የቅጣት ክፍያ (ዲመሬጅ) በእጅጉ እንደሚቀንሰው ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #djibouti #eih #investment #energysecurity #economy #newsupdate #dailynews

Sponsored by
Surafel
9 months ago
የኢትዮጵያ "ወርቃማው ቁማር"፡ በቢሊዮን ዶላሮች የሚለካው የኃይል ሚዛን ሽግግር
በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ "የመሬት መንቀጥቀጥ" እየተከሰተ ነው። ለዘመናት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የነበረው ቡና፣ቢጫው ብረት — ወርቅ — ወንበሩን እየፎካከረው ነው።
ነገር ግን ይህ ሽግግር ዝም ብሎ የንግድ ለውጥ አይደለም፤ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የገባችበት ግዙፍ እና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ የኢኮኖሚ ቁማር እንጂ!
📊 ቁጥሮቹ የሚነግሩን ድብቅ እውነት
ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው 37 ቶን ወርቅ ለዓለም ገበያ አቅርባለች። ይህ ቁጥር ሲታይ አስደናቂ ቢሆንም፣ በውስጡ ግን አንድ የሚያስቆጭ "የሀብት መፍሰስ" (Wealth Leakage) ደብቆ ይዟል።
ኢትዮጵያ ወርቋን የምትልከው ከ70-90% ንጽህና ባለው በ"ዶሬ" (Dore) መልክ ነው። ይህ ማለት ግን፦
በየዓመቱ እስከ 15% የሚደርስ ገቢ (በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር) በማጣራት ሂደት ስም ለውጭ ሀገራት በገጸ-በረከትነት ይሰጣል።
እንደ ብር እና ፕላቲነም ያሉ ውድ ተረፈ-ምርቶች በነጻ አብረው ይላካሉ።
ሀገሪቱ የራሷን ወርቅ መልሳ በውድ ዋጋ ለማጣራት ትገደዳለች።
🏗️ የስትራቴጂው እምብርት፡ "የእሴት ሰንሰለት አብዮት"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይፋ ያደረጉት የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ግንባታ፣ ይህንን "የሀብት ደም መፍሰስ" ለማቆም የተቃጣ ሰይፍ ነው። ፋብሪካው ወርቁን ወደ 99.99% ንጽህና (Standardized Bullion) ሲያሳድገው፦
ቀጥተኛ ትርፍ፦ ከጥሬ ወርቅ ሽያጭ ይልቅ ከ 10-30% ተጨማሪ ገቢ ይገኛል።
የገበያ የበላይነት፦ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የለንደን የወርቅ ገበያ (LBMA) ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን የዋጋ ተመጋቢ ሳይሆን "የዋጋ ወሳኝ" ትሆናለች።
🌍 የሀገራት ፍልሚያ፡ ከጋና ትምህርት፣ ከዱባይ ብልሃት
ኢትዮጵያ በዚህ ጉዞዋ ላይ ሁለት ትልልቅ ትምህርቶች ከፊቷ ተቀምጠዋል፦
የጋና ስጋት፦ ጋና በአፍሪካ ቀዳሚ አምራች ብትሆንም፣ ህገወጥ የማዕድን ቁፋሮ (Galamsey) የአካባቢዋን ደህንነትና የታክስ ገቢዋን አናግቶታል። ኢትዮጵያም በየዓመቱ የምታጣውን ከ300-700 ሚሊዮን ዶላር የኮንትሮባንድ ገቢ ለማስቆም ከባድ ጦርነት ይጠብቃታል።
የዱባይ ስኬት፦ ዱባይ ወርቅ ባይኖራትም የአለም ማዕከል የሆነችው በፋይናንስ ስርአቷ ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) የጀመረው የክሪፕቶ ማይኒንግ እና የገንዘብ ህትመት ስራ፣ ወርቅን ከዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር በማቀናጀት ሀገሪቱን የአፍሪካ "ዙሪክ" የማድረግ ራዕይ አለው።
⚡ ልበ-አንጠልጣዩ ጥያቄ፡ ቁማሩ ይሳካ ይሆን?
የዚህ ሁሉ እንቅስቃሴ ውጤት የሚወሰነው በአንድ ወሳኝ ነጥብ ላይ ነው፡ "ተዓማኒነት" (Trust)።
የኢትዮጵያ ማጣሪያ ፋብሪካ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ካላገኘ፣ ወይም በጥቁር ገበያው እና በህጋዊው ገበያ መካከል ያለው የዋጋ ልዩነት ካልጠበበ፣ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠረው ኢንቨስትመንት "ነጭ ዝሆን" (White Elephant) ሆኖ ሊቀር ይችላል።
💡 ማጠቃለያ፦ ወደ አዲሱ የኢኮኖሚ አድማስ
ኢትዮጵያ ወርቅን እንደ "ስትራቴጂያዊ ከለላ" (Strategic Hedge) በመጠቀም፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረቷን ለመቅረፍና ብሔራዊ ኩራቷን ለማስመለስ ቆርጣ ተነስታለች። ይህ ጉዞ ስኬታማ ከሆነ፣ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ የወርቅ ገቢ ብቻውን የሀገሪቱን አጠቃላይ የኤክስፖርት ገቢ በእጥፍ ሊያሳድገው ይችላል።
ወርቁ በእጃችን ነው፤ ጥበቡ ግን ከምድር በታች ካለው ማዕድን ይልቅ በፖሊሲው ጠረጴዛ ላይ በሚደረገው ድርድር ይወሰናል!

🏨 ሒልተን አዲስ አበባ በትርፍ አደገ📈
* የ308.6 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ተመዘገበ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ስር የሚተዳደረው አንጋፋው ሒልተን አዲስ አበባ፤ በተጠናቀቀው የ2017 የሒሳብ ዓመት አስደናቂ የፋይናንስ አፈጻጸም ማስመዝገቡን አስታወቀ።
የሪፖርቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
💰 የተጣራ ትርፍ፡ 308.6 ሚሊዮን ብር (ባለፈው ዓመት 140.4 ሚሊዮን ብር ነበር)።
💵 ጠቅላላ ገቢ፡ 506.4 ሚሊዮን ብር።
📊 የዕድገት መጠን፡ ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ 97% ዕድገት አሳይቷል።
🏦 ጠቅላላ ሀብት፡ የሆቴሉ ሀብት 1.98 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
የስኬቱ ሚስጥር ምንድን ነው?
የሆቴሉ ማኔጅመንት እንደገለጸው፤ ለዚህ ከፍተኛ ትርፍ ዋና ምክንያቶች፡-
የአዲስ አበባ የቱሪዝም ዘርፍ ማገገም፣
በከተማዋ የሚካሄዱ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች መጨመር እና
የሆቴሉ የአሠራር ቅልጥፍና መሻሻል ናቸው።
ለመንግስት የሚከፈለው ድርሻ
ኩባንያው ካገኘው ላይ 317 ሚሊዮን ብር የሚሆነውን ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በትርፍ ድርሻ (Dividend) መልክ ገቢ ያደርጋል።
የቱሪዝም ዘርፉ ማገገም ለኢኮኖሚው ትልቅ ተስፋ ነው!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#hiltonaddis #businessnews #ethiopia #tourism #revenue #economy #eih

10 months ago
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአመራር ለውጥ አደረገ
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) ከፍተኛ ሹመቶች እና በአመራር ምደባ ዙሪያ የተነሳ አለመግባባትን ተከትሎ፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራር በአዲስ መልክ ተዋቅሯል።
ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ብሩክ ታዬ ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል።
ፎርቹን ባየው መግለጫ እና የውስጥ ደብዳቤ ላይ ዶ/ር ብሩክ የአመራር ለውጡን ያደረጉት “ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማስመለስ እና የልማት ባንኩን ከብሔራዊ ልማት ቅድሚያዎች ጋር ለማጣጣም ያለመ ሰፊ የማሻሻያ አጀንዳ” አካል መሆኑን ገልጸዋል።
የቀድሞ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ እና ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር እመቤት መለሰ (ዓርብ፣ ታኅሣሥ 3 ቀን 2018 ዓ.ም.) የተተኩት፣ በምክትል ፕሬዝዳንቶች ሹመት እና ለከፍተኛ ሠራተኞች የብቃት ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ በቦርዱ እና በዋና ሥራ አስፈጻሚው መካከል የነበረው አለመግባባት ከጠነከረ በኋላ ነው። ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ የተካረረ ልዩነት ስትራቴጂያዊ የውሳኔ አሰጣጥን እያደናቀፈ ነበር። ለባንኩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳሉት፣ አለመግባባቱን ለማርገብ የመጨረሻ ጥረት የተደረገው ከአንድ ሳምንት በፊት ሲሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ እና የማዕከላዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በአቶ ተክለወልድ እና በዶ/ር እመቤት መካከል ስብሰባ ጠርተው ነበር። ሆኖም ውይይቱ ልዩነቱን ማጥበብ እንዳልቻለ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ሲመሠረት በዶ/ር ብሩክ ይመራ የነበረው መስራች ሥራ አስፈፃሚ አካል ውስጥ ነበሩ። የዶክትሬት ዲግሪያቸውን የተከታተሉት ደግሞ በአሜሪካ ዋልደን ዩኒቨርሲቲ ነው። ከ2010 እስከ 2011 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። በተጨማሪም በኢንተለጀንስ እና ደህንነት መረጃ መረብ ኤጀንሲ (INSA) የስትራቴጂ እና የሳይበር ምርምር ዳይሬክተር እንዲሁም የሕግ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል።
አዲስ ፎርቹን

ሰበር ዜና : የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) የአመራር ለውጥ አደረገ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) ከፍተኛ ሹመቶች እና በአመራር ምደባ ዙሪያ የተነሳ አለመግባባትን ተከትሎ፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራር በአዲስ መልክ ተዋቅሯል።

ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ሲመሠረት በዶ/ር ብሩክ ይመራ የነበረው መስራች ሥራ አስፈፃሚ አካል ውስጥ ነበሩ። የዶክትሬት ዲግሪያቸውን የተከታተሉት ደግሞ በአሜሪካ ዋልደን ዩኒቨርሲቲ ነው። ከ2010 እስከ 2011 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። በተጨማሪም በኢንተለጀንስ እና ደህንነት መረጃ መረብ ኤጀንሲ (INSA) የስትራቴጂ እና የሳይበር ምርምር ዳይሬክተር እንዲሁም የሕግ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል ሲል አዲስ ፎርቹን ዘግቧል።

1 year ago
የኢትዮጵያ መንግስት እና ዳንጎቴ ግሩፕ በጎዴ ዩሪያ ፋብሪካ የ40/60 ድርሻ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ መንግስት የኢንቨስትመንት ክንድ የሆነው ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና የዳንጎቴ ግሩፕ በጎዴ ለሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ትልቅ የባለአክሲዮኖች ስምምነት ተፈራረሙ።
ዛሬ የተደረገዉ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 40 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ የዳንጎቴ ግሩፕ ደግሞ ቀሪውን 60 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ እንደሚይዝ ያመላክታል።
የፋብሪካው ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪ 2.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን፣ ዓመታዊ የማምረት አቅሙም እስከ 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ፕሮጀክት ከተጠናቀቀ በኋላ በዓለም ላይ ካሉ ትላልቅ የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካዎች መካከል አንዱ ይሆናል።
የፋብሪካው ግንባታ ከጀመረ በኋላ በ40 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከቃሉብ እና ሂላላ ጋዝ ማሳዎች ጋዝን ለማጓጓዝ የሚያስችል የቧንቧ መስመር ዝርጋታን ጨምሮ ተጨማሪ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችንም ያካትታል።
ይህ ፕሮጀክት የአገር ውስጥ ጋዝ ክምችቶችን በመጠቀም የማዳበሪያ ዋጋን ተወዳዳሪ በማድረግ፣ የግብርና ምርታማነትን እንደሚያሳድግ እና ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ የማዳበሪያ ምርት ማዕከል እንድትሆን እንደሚያግዛት ተጠቁሟል።

#ethiopia | የኢትዮጵያ መንግስት የኢንቨስትመንት ክንድ የሆነው ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና የዳንጎቴ ግሩፕ በጎዴ ለሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ትልቅ የባለአክሲዮኖች ስምምነት ተፈራረሙ።

ይህ ፕሮጀክት የአገር ውስጥ ጋዝ ክምችቶችን በመጠቀም የማዳበሪያ ዋጋን ተወዳዳሪ በማድረግ፣ የግብርና ምርታማነትን እንደሚያሳድግ እና ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ የማዳበሪያ ምርት ማዕከል እንድትሆን እንደሚያግዛት ተጠቁሟል ሲል ካፒታል በገጹ አስነብቧል።

Comments