4 months ago
የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ወደ 2028 ሊራዘም ይችላል? ኬንያ የጸጥታ ስጋት እንዳለባት ገለጸች
#ethiopia | በጋራ አዘጋጅነት የተረከቡት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት (ኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ) ታሪክ ለመስራት እየተዘጋጁ ቢሆንም፣ ውድድሩ የአንድ ዓመት መራዘም ሊገጥመው እንደሚችል ፍንጮች እየታዩ ነው።
ለምን ሊራዘም ይችላል?
ዋናው ምክንያት የኬንያ ሀገራዊ ምርጫ ነው። እ.ኤ.አ በ2027 ኬንያ ጠቅላይ ምርጫ የምታካሂድ በመሆኑ፣ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ለትልቅ ስፖርታዊ ውድድር አስተማማኝ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።
የኬንያ የአዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኒኮላስ ሙሶንዬ በጉዳዩ ላይ ሲናገሩ፦
> "በምርጫ ወቅት የደህንነት ሁኔታው አስተማማኝ ስለማይሆን፣ ውድድሩ ወደ 2028 ቢራዘም ለኬንያ መልካም ነው" ብለዋል።
>
የካፍ (CAF) ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል?
የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ በታንዛኒያ ዳሬሰላም በሚያደርገው ስብሰባ በዚህ አጀንዳ ላይ በጥልቅ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። ካፍ የኬንያን ጥያቄ ተቀብሎ ውድድሩን ያራዝመዋል ወይንስ ሌሎች አማራጮችን ይፈልጋል? የሚለው ጉዳይ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
ውድድሩ የሚራዘም ከሆነ በዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ዝግጅት ላይም የራሱ የሆነ ጫና ማሳረፉ አይቀሬ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #afcon2027 #caf #kenya #tanzania #uganda #africanfootball #sportsnews #pamojabid #የአፍሪካዋንጫ #ኬንያ