Logo
Getu Temesgen
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለመቄዶንያ ከ4.6 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አበረከተ
#ethiopia | አዲስ አበባ | ኢትዮጵያ – የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የመስሪያ ቤቱን ማኔጅመንት፣ ሰራተኞች እና ታራሚዎች በማስተባበር ለመቄዶንያ አረጋውያንና ህጻናት መረዳጃ ማህበር ከ4.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አበርክቷል።

ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በገባው ቃል መሰረት በየዓመቱ ሐምሌ 28 መቄዶንያን የመጎብኘት ልማዱን በመቀጠል፣ በዚህ ዓመትም 547 ሺህ 65 ብር ጥሬ ገንዘብ እና ከ4.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለማህበሩ አስረክቧል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ዋና ኮሚሽነር የኑስ ሙሉ፣ መቄዶንያ ለሚያከናውነው ሰብዓዊ አገልግሎት በኮሚሽኑ ስም ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የኮሚሽኑ የህክምና ልዑካን ቡድን ከ770 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶችን በማበርከት ብቻ ሳይሆን፣ ለማህበሩ ተገልጋዮች የህክምና አገልግሎትም ሰጥቷል።

በተጨማሪም በኮሚሽኑ ስር የሚገኙ ታራሚዎች በእጃቸው ያመረቷቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች በስጦታ በማበርከት ከመልካም ምኞት መልዕክታቸው ጋር ለማህበሩ አስረክበዋል።

የመቄዶንያ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ዶ/ር ቢንያም በለጠ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ የማህበሩ ተገልጋይ አረጋውያንም በተደረገላቸው ጉብኝትና ድጋፍ ያላቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ጌጡ ተመስገን
#ethiopia #federalprisoncommission #macedonia #charitysupport #givingback #humanitarianassociation #getutemesgen #ጌጡተመስገን

16 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.