5 months ago
1,447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት ተከበረ
#ethiopia | በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ጉጉት ሲጠበቅ የቆየውና የረመዳን ጾም ማጠናቀቂያ የሆነው 1,447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል፣ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ15 በላይ በሚሆኑ ዋና ዋና የመስገጃ ስፍራዎች የሶላት ስነ-ሥርዓቱ የተከናወነ ሲሆን፣ ከማለዳው ጀምሮ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች "አላሁ አክበር" እያሉ ወደ አደባባዮች በመሄድ በዓሉን በጋራ አክብረዋል።
በዕለቱ የተገኙት የሃይማኖቱ ተከታዮች ባለፈው የአንድ ወር የጾም ወቅት የታዩ የመረዳዳት እና የመተሳሰብ እሴቶች ከበዓሉ በኋላም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በተለይም አቅመ ደካሞችን በመርዳት እና ማዕድ በማጋራት ረገድ የታየው አንድነት ለሀገር ሰላምና እድገት ያለውን ፋይዳ ምዕመናኑ በአጽንኦት ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በሁሉም ክልሎች፣ በዋና ዋና ከተሞችና በገጠር ቀበሌዎች በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በኢስላማዊ አደብ የሶላት ስነ-ሥርዓታቸውን አከናውነው በዓሉን በደስታ አክብረዋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #eidalfitr #eidmubarak #addisababa #1447theid #peaceandunity #ramadan2026 #celebration #islamicholiday

የ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ዓርብ መጋቢት 11 እንደሚከበር ተረጋገጠ
#ethiopia | የዘንድሮው የ1447ኛው የረመዷን ጾም 30 ቀናት ተሟልቶ ነገ ሐሙስ እንዲጠናቀቅና የዒድ አል-ፈጥር በዓል ደግሞ ዓርብ (ጁምዓ) መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲከበር በይፋ ተወስኗል።
የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የሸዋል ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ ምክንያት ነገ ሐሙስ የረመዷን 30ኛው ቀን ሆኖ እንዲጾም፣ በዓሉ ደግሞ ዓርብ ዕለት እንዲከበር በይፋ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች "እንኳን አደረሳችሁ" በማለት በቅዱሱ የረመዷን ወር የታየው የመረዳዳትና የደግነት ተግባር በበዓሉ ዕለትና ከዚያም በኋላ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤቱ አሳስቧል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
ጌጡ ተመስገን ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽንስ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!
#ethiopia #eidalfitr #ramadan30 #eidmubarak #breakingnews #moonsighting #islamicholiday

Comments