5 months ago
የ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ዓርብ መጋቢት 11 እንደሚከበር ተረጋገጠ
#ethiopia | የዘንድሮው የ1447ኛው የረመዷን ጾም 30 ቀናት ተሟልቶ ነገ ሐሙስ እንዲጠናቀቅና የዒድ አል-ፈጥር በዓል ደግሞ ዓርብ (ጁምዓ) መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲከበር በይፋ ተወስኗል።
የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የሸዋል ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ ምክንያት ነገ ሐሙስ የረመዷን 30ኛው ቀን ሆኖ እንዲጾም፣ በዓሉ ደግሞ ዓርብ ዕለት እንዲከበር በይፋ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች "እንኳን አደረሳችሁ" በማለት በቅዱሱ የረመዷን ወር የታየው የመረዳዳትና የደግነት ተግባር በበዓሉ ዕለትና ከዚያም በኋላ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤቱ አሳስቧል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
ጌጡ ተመስገን ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽንስ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!
#ethiopia #eidalfitr #ramadan30 #eidmubarak #breakingnews #moonsighting #islamicholiday

Comments