Logo
Getu Temesgen
የ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ዓርብ መጋቢት 11 እንደሚከበር ተረጋገጠ
#ethiopia | ​የዘንድሮው የ1447ኛው የረመዷን ጾም 30 ቀናት ተሟልቶ ነገ ሐሙስ እንዲጠናቀቅና የዒድ አል-ፈጥር በዓል ደግሞ ዓርብ (ጁምዓ) መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲከበር በይፋ ተወስኗል።

​የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የሸዋል ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ ምክንያት ነገ ሐሙስ የረመዷን 30ኛው ቀን ሆኖ እንዲጾም፣ በዓሉ ደግሞ ዓርብ ዕለት እንዲከበር በይፋ አሳውቋል።

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች "እንኳን አደረሳችሁ" በማለት በቅዱሱ የረመዷን ወር የታየው የመረዳዳትና የደግነት ተግባር በበዓሉ ዕለትና ከዚያም በኋላ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤቱ አሳስቧል።

​በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።

ጌጡ ተመስገን ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽንስ ​ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

​ዒድ ሙባረክ!

​#ethiopia #eidalfitr #ramadan30 #eidmubarak #breakingnews #moonsighting #islamicholiday

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.