3 months ago
ኢጋድ የጋራ የውሃ ሀብቶችን ለትብብርና ለጋራ ብልጽግና ለማዋል ቁርጠኛ መሆኑን አስታወቀ
**************************
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በቀጣናው የሚገኙ የጋራ የውሃ ሀብቶች የውጥረት ሳይሆን የትብብር ድልድይ እንዲሆኑ ከአባል ሀገራት ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገለጸ።
ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ውሃ ድንበር እንደማያውቅ ጠቅሶ፤ በኢጋድ ቀጣና ውስጥ የሚገኙ የውሃ ሀብቶች ማህበረሰቦችን፣ መተዳደሪያን፣ ስነ-ምህዳርንና ኢኮኖሚን የሚያስተሳስሩ ወሳኝ መሰረቶች መሆናቸውን አመልክቷል።
በቀጣናው የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ የድርቅና የጎርፍ አደጋዎች፣ የአየር ንብረት ለውጥ ጫና እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የውሃ ፍላጎት ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ትብብርን አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንዳደረጉትም ተገልጿል።
ይህ ትብብር ለማህበረሰቦች ጽናት፣ ለቀጣናዊ ሰላም እና ለጋራ ብልጽግና ወሳኝ ሚና እንዳለው ኢጋድ አስገንዝቧል።
ተቋሙ በውይይት፣ በመረጃ ልውውጥ፣ በጋራ እቅድና በትብብር ማዕቀፎች አማካኝነት የጋራ የውሃ ሀብቶች ዘላቂ አስተዳደር እንዲጠናከር ከአባል ሀገራት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ይህም ውሃ የውጥረት ምንጭ ከመሆን ይልቅ የትብብር ድልድይ እንዲሆን ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
ኢጋድ በቀጣናዊ መፍትሄዎች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የጋራ የውሃ ሀብቶችን ወደ የጋራ እድሎች ለመለወጥ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በድጋሚ አረጋግጧል።
በላሉ ኢታላ
#igad #watercooperation #eastafrica #regionalintegration #watermanagement #peaceandprosperity

Comments