1 month ago
Abebe Tilahun culture & Sport:
ለፈረንጅ ሚስቶች የቆመች ሐውልት‼️
የመጽሐፉ ርዕስ፦ የፈረንጅ ሚስት
ደራሲት፦ እስከዳር ግርማይ
የገጽ ብዛት ፦ 119
የመጽሐፉ ዋጋ ፦ 150 ብር
እትም፦ 3ኛ /2017 ዓ.ም
ዘውግ፦ ግለ ማስታወሻ (Memoir)+
አርታኢያን፦ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል እና አርቲስት አዜብ ወርቁ
👉መንደርደሪያ
ካርል ሮጀርስ (Carl Rogers) የተባለው ታዋቂው አሜሪካዊ የሥነ-ልቦና ባለሙያ "On Becoming a Person" በተሰኘ መጽሐፉ ላይ በሰዎች መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት በማጥናት እንዲህ ይላል። “What is most personal is most universal.” ፦ “እጅግ ሲበዛ ግላዊ የሆነው ነገር፣ እጅግ ሲበዛ ዓለማቀፋዊ ነው።”
ግለ-ማስታወሻ (Memoir)፤ ከሕይወት ውስጥ አንድን ወሳኝ ክስተት፣ ስሜት ወይም ጭብጥ (Theme) መርጦ ይተነትናል። ትኩረቱ "ከገጠመኝ ነገር ምን ተማርኩ? ምን ተሰማኝ?" የሚል ነው። በሌላ አነጋገር ግለ-ማስታወሻ ከታሪክ ይልቅ ትርጓሜና ስሜት ላይ ያተኩራል።
አንድ ሰው ለብቻው የሚሰማው፣ ለሌላ ሰው ለመናገር የሚፈራው ወይም "እኔ ብቻ ነኝ እንዲህ የሚሰማኝ" ብሎ የሚያስበው የግል ስሜት (ለምሳሌ፦ የፍርሃት፣ የብቸኝነት ስሜት፣ ወይም የናፍቆት፣ የመበሳጨትና የመብከንከን ስሜት) በሚገርም ሁኔታ ሌሎች ሰዎችም በውስጣቸው የሚሰማቸው ነው።
ስለሆነም ጸሐፊዋ እስከዳር ስለ ራሷና በዙሪያዋ ስላሉ ተመሳሳይ ሰዎች እጅግ ጥብቅና ግላዊ የሆኑ ጉዳዮችን በሐቀኝነት ስትናገር፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች በታሪኳ ውስጥ የራሳቸውን ስሜት አግኝተውታል። የሥነ-ልቦና ጠበብት አንድ ሰው ወደ ራሱ ማንነት (Inner self) በጥልቀት በወረደ ቁጥር፣ ከግል ማንነቱ ባለፈ የሰው ልጅን የጋራ ማንነት (Collective Human Experience) ያገኛል ብለው ያምናሉና በፈረንጅ ሚስት የሆነውም ይሄው ነው።
ሌላኛው ጄምስ ጆይስ (James Joyce)የተባለ ምሁር "በተለየው (in the particular) ውስጥ ሁልጊዜም ዓለማቀፋዊውን (the universal) ነገር እናገኛለን።" በማለት በሥነ-ጽሑፍ ሥራዎቹ የግል ተሞክሮን ማዕከል ማድረጉን ገልጿል። እንዲሁም ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን (Ralph Waldo Emerson) "በገዛ ልብህ ውስጥ የምታምነው እውነት ለሁሉም ሰዎች እውነት ነው።" በሚል ሀሳብ ተመሳሳይ ፍልስፍናን አራምዷል።
በአጠቃላይ አባባሉ "የሰው ልጅ ስሜትና ተፈጥሮ በየትኛውም ቦታ አንድ ነው" የሚለውን መሠረታዊ እውነት የሚያሳይ ነው። የፈረንጅ ሚስት የሚለው ግለ-ማስታወሻ በራስ ሕይወት መስኮትነት ዓለምን የማሳያ ጥበብ ሆኖ ብቅ ብሏል። ጸሐፊዋ በራሷ ሕይወት ውስጥ ያለውን ትርጉም ስትፈልግ፣ አንባቢው ደግሞ በጸሐፊው ታሪክ ውስጥ የራሱንና የማኅበረሰቡን ሕይወት ያያል፣ ይታዘባል።
የፈረንጅ ሚስት
👉ግላዊና ዓለማቀፋዊ ሀሳብ፤ ጸሐፊዋ ስለ ራሷ ብቻ ስታወራ ለአንባቢው አሰልቺ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በግል ሕይወቷ በፈረንጅ ሚስትነቷ፣ በኢትዮጵያዊነቷ፣ የደረሰባትን ሐዘን፣ ፍቅር፣ ክህደት ወይም መገለል በሐቀኝነት ስለገለጠችው፣ አንባቢያን በራሳቸው ሕይወት ውስጥ ተመሳሳይ ስሜት አጋጥሟቸው ስለሚያውቅ ከጸሐፊዋ ጋር፣ እንደግል በሀሳብ፣ እንደማኅበረሰብ በአባልነት ይቆራኛሉ።
ሰው ወደ ራሱ ውስጠት በጥልቀት በቆፈረ ቁጥር፣ የሁሉንም ሰው የጋራ ምንጭ ያገኛል። የራስን እውነተኛ ስሜት፣ ስቃይ እና ደስታ መፈለግ እና እዚያ ጥልቀት ላይ ሲደርሱ የምናገኘው ራስን ብቻ ሳይሆን መላውን የሰው ልጅ የሚያገናኘውን የጋራ ክር ነው። ለዚህ ነው ግላዊ ማስታወሻዎች (Memoirs) በሚገባ ተቆፍረው ሲጻፉ ዓለምን ሁሉ የመንካት አቅም የሚኖራቸው።
በሥነ-ጽሑፍ እና በፈጠራ ድርሰት ዓለም ውስጥ በስፋት የምትታወቀው አሜሪካዊት ጸሐፊ ማያ አንጄሉ (Maya Angelou) “In the particular is contained the universal.” ፦ በተለየው/በግል ታሪክ ውስጥ፣ ዓለማቀፋዊው እውነት ይገኛል። ብላለች ።
ይህች የፈረንጅ ሚስት መጽሐፍ ከኢትዮጵያዊ ወንድ ውጭ ላገባችሁ ቀወል ስም የፈረንጅ ሚስት ለምትባሉ ሁሉ ሴቶች የቆመች ቅልብጭ ያለች ሐውልት ናት።
👉በፈረንጅ ሚስት መጽሐፍ ውስጥ ፤
ሐቀኝነት (Honesty)አለ፦ ግለ-ማስታወሻ ጸሐፊዋ ራሷን ብቻ ያሞግሰችበት ሳይሆን፣ ድክመትና ስህተቶችንም ጭምር የገለጥችበት መጽሐፍ ነው። ሐቀኝነት ከሌለ አንባቢው በታሪኩ አይመሰጥም።
የራስ መተማመኗን ፈረንጅ የማግባት ውጤት ሲያደርጉት፤ ሐበሻ ብታገባ ኖሮ በዚህ የራስ መተማመኗ ድሮ እንደሚፈታት ሲያሙላት በስላቅ ሐቋን ትጠይቃለች።
"እውነት የሀገሬ ሴቶች ታዋቂ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ እና በራሳችሁ
የምትተማመኑ ከሆናችሁ ትዳራችሁ አይጸናም?
ደመወዛችሁ ከባለቤታችሁ ደመወዝ ሲበልጥ፣ ሥልጣናችሁ ከትዳራችሁ በላይ ሲገዝፍ ትፋታላችሁ?
ወይስ ትዳራችሁን መርጣችሁ፣ የመጣላችሁን ዕድል አሳልፋችሁ ለወንድ እና ላላገቡ ሴቶች ትሰጣላችሁ?
የሀገሬ ወንዶችስ? በሥራ፣ በደመወዝ ወይም በሥልጣን የምትበልጣችሁን ሴት ማግባት ትፈራላችሁ እንዴ?"
መልስ አትፈልግም።
ይልቁንስ ደራሲዋ ጥያቄዎቹን የምታቀርበው ምላሽ ፈልጋ ሳይሆን፣ ማኅበረሰቡን በመስታወት ፊት አቁማ ራሱን እንዲታዘብ ለማድረግ ነው።
ጭብጥ (Theme)አለ፦ ታሪኳ የሚሽከረከርበት አንድ ማዕከላዊ እውነት አለው ። ማዕከላዊ እውነቷ በማኅበረሰባችን ዘንድ ለፈረንጅ ሚስት ያለውን ስሁት አመለካከት ማረም፣ እውነቷንና ጽናቷን በመግለጽ ማንነቷን ማሳየት ነው። ለእያንዳንዱ ገጠመኟ በተግባር የተፈጸመ ምሳሌ ያልደበዘዘ ትውስታ ተቀምጧል ።
በማኅበረሰባችን ዘንድ የፈረንጅ ሚስትን ከሚያራክስበት ዝቅጠታዊ ልማድ የባሰ የሀብታም ቅምጥን የሚያሞግስበትና የሚያከብርበት የስብእና ንጥፈት እንዴት እንዳብከነከናት በሚቆጠቁጥ መልኩ የማዕከላዊ ጭብጡ ማጠንጠኛ ሆኗል ።
ደሞ ለምን ፈረንጅ አገባሽ ? እያሉ የጅል ጥያቄ ለሚጠይቁ አድርቅ ጋዜጠኞች ጥያቄን በጥያቄ በመመለስ በጥያቄያቸው እንዲያፍሩ የምታደርግበት ጥበብ የፈረንጁ ባሏ ምክርና የጭብጧ ማጠናከሪያ ነበር።
"ባለቤቴ ሁል ጊዜ የማይደረስ ጥያቄ ለሚጠይቅሽ ሰው፤ የጠየቀሽን ጥያቄ መልሰሽ ራሱን ጠይቂው። መልሱ ካላጠገበሽ ምን ማለትህ ነው? ብለሽ ይበልጥ እንዲያብራራልሽ እንደገና ጠይቂው። ስህተቱን
እስኪረዳው ተፋተኚው። እንደዚህ ዐይነት ሰዎች ከአምስት
ጥያቄዎች በላይ መመለስ አይችሉም፤ የሚለኝን ሳስበው ተግባራዊ እያደረግኩ።" ትለናለች። (ገጽ34)
ጥበባዊ አቀራረብ አለ፦ ምንም እንኳን እውነተኛ ታሪክ ቢሆንም፣ እንደ ልብ-ወለድ (Fiction) የታሪክ አወቃቀር፣ ገጸ-ባህሪያት አሳሳል እና የቃላት ምርጫ (Imagery) ተጠቀማለች። እንደ ገጸ ባሕርይ ራሷን እና በዙሪያዋ ያሉ ተመሳሳይ ሕይወት የሚጋሩ ወዳጆቿን፣ ቤተሰቦቿን እና በመንገዷ የገጠሟትን አካታለች። የታሪክ አወቃቀሩ ከአንዱ የሕይወት ገጠመኝ ወደ ሌላኛው የሕይወት ገጠመኝ እየተሻገረች፣ በትውስታ እያጀበች በምሳሌ አዋቅራ የልቧን እውነት የሕይወቷን ትርክት ቀንጭባ አቅርባዋለች።
የቃላት አመራረጧ ትኩሳቷን በመግለጥ እንደ እሳት የሚጋረፉ ፣ ስታዝን የሚለዝቡ፣ ስትቆጣ የሚንጣጡ ቃላት ናቸው።
ለምሳሌ የሀብታም ቅምጥን የገለጠችበትን ቃላት ተመልከቱ፦ "የሀብታም ቅምጥ የከተማው ሁሉ ወንድ የሚመኛት፣ ያሳደጓት የሰፈር ጎረምሶች ዓይናቸው እያየ ለባለጸጋ አሳልፈው በመስጠታቸው የሚቆጩባት፣ ዘመድ አዝማዶቿ የእሷ ስኬት የልጆቻቸው ባለመሆኑ የሚቀኑባት፣ የሰፈሩ ሰዎች ለአቅመ ሔዋን ላልደረሱ ልጆቻቸው "አርአያነቷን" እንዲከተሉ ጀብዳቸውን የሚነግሩላት፤ በየቦታው ትንሽዬ "ፈጣሪ" ሆና ብዙ "ደቀ መዛሙርት" ያፈራች ሴት ናት።" (ገጽ 27)
ውስጣዊ ሙግት (Internal Dialogue/ አለ፦ በሆነባት በተደረገባት ነገር ብቻ ሳይሆን፤ የወጣችበት ማኅበረሰብ ግንዛቤ ባለበት ቆሞ መቅረት ጭምር ሲያብሰከስካት ፤ እንደግል መብቷን፣ እንደማኅበረሰብ ውበቷን ስትገፈፍ የምትናገራቸው ቃላት የውስጧን መብከንከን ይገልጻሉ።
"የማዝነው፤ ማኅበረሰባችን በየመንገዱ መሰደቧን እንዳላየ እንዳልሰማ ሆኖ ስለሚያልፋት ብቻ አይደለም ። ከሐበሻ ወንድ ወጭ ሲሆን በፍቅር የማትወድቅ፣ ከሀገሯ ቋንቋ በቀር የፍቅር ቃላት የማትሰማ፣ ጠረን ለምዳ የማትሸነፍ ናት፤ ብለው በመወሰናቸውና የስሜት ሕዋሳቷ ለሌላ ሀገር ዜጋም ቢሆን እንደሚሠሩ ባለማወቃቸውም እንጂ!" (ገጽ16)
"ውጭ ሀገር ስንኖር አለመከበራችን በምንም መልኩ ልክ አይደለም፤ በሰው ሀገር ስንከፋ የሚሰማን ስሜት ፣ ከራሳችን ሀገር ከሚደርስብን የጥቃት ስሜት ጋር ካነጻጸርነው ግን፣ የሕመሙ ክብደት በሰው ሀገር
ሲሆን ይቀንሳል።
ሀገር ያስከፋን ጊዜ ግን ወዴት አቤት ይባላል? የራስ ሕዝብስ ለማን ይከሰሳል?" እያለች ምሯን ትናገራለች።
እናቴ አሳዛኝና አንጀት ቆራጭ ነገሮች ሲገጥሟት፦ "ከቀላድም ባይረዝም ከመጫኛም ባይበልጥ፤
አንጀት ያልቅ የለም ወይ ሲቆረጥ ሲቆረጥ።" ትላለች ።
የማኅበረሰባዊ መገፋት አንጀት ይቆርጣል ፤ አይመልሰኝ አሰኝቶ ድንጋይ ያስወረውራል። በጊዜ ሊታረም ከዘመኑ ጋርም ሊዘምን የሚገባ እንጅ የምናጌጥበት ነውር መሆን የለበትም ።
👉በፈረንጅ ሚስት መጽሐፍ
ደራሲዋ እስከዳር ግርማይና መሰል የፈረንጅ ሚስቶች ያለፈና ያለን ቁስል በቃላት አስጊጣ በመግለጧ ግላዊ እፎይታ ፣ ሕሊናዊ ፈውስ አግኝተውበታል፤ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ።
በመሰል ፈተና ውስጥ ያሉ ሰዎች የግለ ማስታወሻዎቹን ሂደትና መፍትሔ አይተው ተስፋ የሚሰጥ ትምህርት ያገኛሉ። በማኅበረሰባዊ ሂሷም ብዙዎች ራሳቸውን እንዲታዘቡ ራሳቸውን እንዲመረምሩና እንዲታረሙ ኮርኩራለች።
እስከዳር በራሷ የተወሰነ ዘመንና ማኅበረሰብ ውስጥ ለፈረንጅ ሚስት የነበረን አመለካከት ለትውልድ በማስተላለፍ የታሪክ ምስክር በመሆን፤ ለፈረንጅ ሚስቶች ሐውልት አቁማለች።
ማጠቃለያ
ደራሲ እስከዳር ግርማይ በመጽሐፏ ውስጥ 'የፈረንጅ ሚስት' የሚለውን ስም ከስድብነት ወደ ማንነት (Identity)፣ ከማንነትም ወደ ተጋድሎ (Resistance) ቀይራዋለች። ይህ መጽሐፍ የአንድን ግለሰብ ሕይወት ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያዊነትን እና የዘመናዊነትን (Modernity) ግጭት፣ እንዲሁም የሴትነትን ነፃነት የሚፈትን፣ ማኅበረሰባዊ ሕጸፅን ነቅሶ የሚያሳይ መስታወት ነው።
👉እስከዬ አሁንም ያላወጣሽው ብዙ ግላዊ "የመሬማውያን ጉዳይ" አለና በጥልቀት ቆፍረሽ ታወጭው ዘንድ አደራ እላለሁ 🙏
👉የፈረንጅ ሚስት በዶክመንተሪ ቢዘጋጅ ደግሞ ከንባብ የራቀውና የስድብ መጋዘን ከሆነው የማኅበረሰብ ክፍል ውስጥ በእጁ ላይ ገብተሽ ትነግሪዋለሽ። የፈረንጅ ሚስት ማለት በምን የሕይወት ሸለቆ ውስጥ አልፋ ምርጫዋን የምታስከብር እንደሆነች ታሳያቸዋለሽ።
የሀብከ ብርሃኔ ጥላሁን

5 months ago
300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር በስህተት ወደ አካውንታችሁ ቢገባ ምን ታደርጋላችሁ?
* "የሰው ሀቅ ለኔ አይገባም!" - ወጣት እመቤት መኮንን
#ethiopia | ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ አያት አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ወጣት እመቤት መኮንን (በጓደኞቿ እሙ)፤ ያልጠበቀችው መልዕክት ስልኳ ላይ ገባ። መልዕክቱ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር ወደ ሂሳቧ መግባቱን የሚያበስር ነበር።
ገንዘቡ የሷ እንዳልሆነ ያወቀችው እመቤት፤ ለአፍታም ሳታመነታ "ይህ የሰው ሀቅ ነው፤ የኔ አይደለም" በማለት ለራሷ ወሰነች።
ከደቂቃዎች በኋላ ገንዘቡን በስህተት የላከውና በአላማጣ ከተማ የሚኖረው ወጣት መሐመድ መኪ ደውሎ ሲያናግራት፤ በፍጥነት እና በቅንነት ገንዘቡን ለመመለስ ተባበረችው።
የወጣት እመቤት መልእክት፡-
"እኔም በላቤ የምኖር ሰው ነኝ። ሰው በላቡ ለፍቶ ያገኘውን ገንዘብ በስህተት ወደ ሌላ ሰው መላክ ሊያጋጥም ይችላል፤ የራስ ያልሆነን ነገር መመለስ ግን ለኅሊና ዕረፍት ነው።"
የባለቤቱ ምስጋና፡-
ከአላማጣ ሆኖ በጭንቀት ይደውል የነበረው መሐመድ፤ በወጣቷ ምላሽ ተደናቋል። "ደውለን ስናናግራት የሰጠችን ምላሽ እምነቷንና ታማኝነቷን እንድገነዘብ አድርጎኛል። አላህ ሀቋን ይክፈላት" ሲል መርቋታል።
ክብር ለእንደዚህ አይነት ቅን ኢትዮጵያውያን! 👏
እናንተስ በወጣት እመቤት ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር? ሀሳባችሁን አጋሩን! 👇
#honesty #integrity #ethiopia #addisababa #alamata #gooddeed #inspiration

✅ ተገኝተዋል! | "ፓስፖርታችንን በክብር ተረክበናል!"
#ethiopia | የጠፉት 5 ፓስፖርቶች፣ መታወቂያዎች እና የውጭ ሀገር ገንዘብ ለባለቤቶቹ ተመለሰ! 👏🇪🇹
ትናንትና ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ወድቆ በወንድማችን ዲንሰፋ በሽር (Dinsefa Beshir) እጅ ገብቶ የነበረው የካናዳ እና የኢትዮጵያ ፓስፖርቶች እንዲሁም ጠቃሚ ሰነዶች ዛሬ ለባለቤቶቹ ተመልሰዋል።
ከ9 ዓመታት በኋላ ከካናዳ፣ ባለቤቱን እና ልጆቹን ይዞ ለሦስት ሳምንት ለእረፍት ወደ ሀገር ቤት የገባው አቶ ሚኪያስ ንብረቱን ተረክቧል።
ዲንሰፋ በሽር፤
ለአቶ ሚኪያስ የስፖርት ትጥቅ መሸጫ ሱቁ ድረስ በመጥራት፡-
4 የካናዳ ፓስፖርት 🇨🇦
1 የኢትዮጵያ ፓስፖርት 🇪🇹
የካናዳ መኖሪያ ፈቃድ፣ መንጃ ፈቃድ እና ዶላሩን ጨምሮ ምንም ሳያጎድል አስረክቧል።
የክብር ምስጋና!
ይህ መረጃ በፍጥነት እንዲደርስ እና ቤተሰቡ ከጭንቀት እንዲገላገል መረጃውን #ሼር (SHARE) ላደረጋችሁ የጌጡ ተመስገን ሚዲያ ቤተሰቦች በሙሉ "ምስጋና ውሰዱ" ተብላችኋል!
በጎነት ለራስ ነው!
ክብር ለወንድማችን ዲንሰፋ! 🙏
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #honesty #goodnews #lostandfound #boleairport #getutemesgenmedia

11 months ago
ለዩኒቨርሲቲ መምህሩ አስናቀ ብርሃኑ እንድረስለት
Lets support Our Teacher
Yilkal Andualem is organizing this fundraiser.
Donation protected
መምህራችን_ታሞብናል
ወደ ካንሰር ሊቀየር ይችላል....ሀኪሞች
ወጣት መ/ር አስናቀ ብርሃኑ አላምነህ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቅንነትና በታማኝነት እያገለገለ ያለ በሙያውም አንቱታን ያተረፈ በሥነ ምግባሩ ምስጉን ሰው አክባሪ፣ ለተቸገሩ ፈጥኖ ደራሽ ወንድማችን ነው::
በሒሳብ ትምህርት ክፍል የኑሜሪካል አናላይሲስ መምህር ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ቆይታውም ከማስተማር ስራው ጎን ለጎን በጥናትና ምርምር ዘርፍ በሙያው አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው 6 (ስድስት) ጥናትና ምርምሮችን በማሳተም ለአንባቢያን አድርሷል::
ወንድማችን መ/ር አስናቀ ድንገት በገጠመው የጤና እክል በህይወት እና በሞት መካከል ሆኖ የድረሱልኝ ተማፅኖውን እያሰማ ይገኛል:: በገጠመው የጤና ዕክል በተለያዩ ስድስት (6) ሆስፒታሎች ህክምና ሲያደርግ ቆይቷል::
ከነዚህም ውስጥ በአንዱ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሰርጀሪ ተሰርቶ ሊሻለው ባለመቻሉ ወደ አዲስ አበባ አለርት ኮምፕርሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለት ክትትል እያደረገ ይገኛል::
በመሆኑም የአለርት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቦርድ 30% አጠቃላይ ቋሚ የአካል ጉዳተኛ እንደሆነና የሚከተሉትን ውሳኔዎችን ወስኗል::
1ኛ. በግራ እግሩ ላይ ስድስት (6) ዓመት የቆየ ከባድ ቁስለት ወደ ካንሰር የመቀየር እድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን፣
2ኛ. ሁለቱም እግሮቹ ነርቫቸው የተጎዳና ስሜት አልባ መሆናቸውን፣
3ኛ. የግራ እግሩ ሙሉ አጥንቶቹ የተጎዱና ይዘታቸውን የቀየሩ መሆናቸውን
4ኛ. ቁሞ ማስተማርም ሆነ በእግሩ መንቀሳቀስ እንደማይችል የአለርት ሆስፒታል ሜዲካል ቦርዱ አረጋግጧል
መምህር አስናቀ ባለብዙ ተስፋና ብዙ ህልም የነበረዉ ሩጦ ያልጠገበ ወንድማችን እግሮቹ ደክመው እቤት እንዲውል ተገዷል::
የህመሙ ሁኔታ አሳሳቢ እና ለህይወቱም አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ ወደ ህንድ አገር ሂዶ ህክምና እንዲያደርግ ሪፈር ተፅፎለታል:: የህክምና ወጭውም ከሁለት ሚሊየን (2,000,000) ብር በላይ እንደሚያስፈልገው ተነግሮታል::
ወንድማችንን ለማገዝ አነሰ በዛ ሳንል በአገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ ትዉልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የእርዳታ እጃችሁን ትዘርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን::
Asinake Birihanu Alamneh
ስልክ_ቁጥር 09 23 53 45 01
Lecturer Asnake Berhanu, who has been serving Hawassa University with integrity and honesty, is a respected, respectful, and helpful person who has earned a reputation in his profession.
He is a Numerical Analysis Lecturer in the Department of Mathematics.
During his time at the university, he has published 6 (six) internationally recognized studies and research papers in his field, and has reached readers.
Our brother,Teacher Asnake is suddenly in the middle of life and death due to a health problem he encountered.
He has been receiving treatment in six (6) different hospitals for his health problem. In one of them, he underwent surgery at Hawassa University Referral Hospital and was referred to Addis Ababa Alert Compressive Specialized Hospital for follow-up.
Therefore, the Alert Specialized Hospital Medical Board has determined that he is 30% permanently disabled and has made the following decisions:
1st. The six (6) year old severe ulcer on his left leg has a very high chance of turning into cancer,
2nd. Both his legs are nerve damaged and numb,
3rd. The entire bones of his left leg are damaged and their contents have changed,
4th. The Alert Hospital Medical Board has confirmed that he cannot stand or walk.
Our brother, Teacher Asnake, who had many hopes and dreams, has been forced to stay home due to tired legs. His condition is serious and life-threatening, so he has been referred to India for treatment. He has been told that the medical expenses will cost more than $15000 .
Please help support this visionary teacher as they navigate through an incredibly difficult time. The funds raised will go towards the cost of surgical treatment , and to help to cover the loss of income while taking some much needed time to recover.
Thank you for your generosity.
I am grateful for your help and wishes.
Thank you
"Let's save the life of the visionary teacher with sincere hearts and united hands!
Show your support for this GoFundMe