Logo
Getu Temesgen
300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር በስህተት ወደ አካውንታችሁ ቢገባ ምን ታደርጋላችሁ?

* "የሰው ሀቅ ለኔ አይገባም!" - ወጣት እመቤት መኮንን
#ethiopia | ​​ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ አያት አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ወጣት እመቤት መኮንን (በጓደኞቿ እሙ)፤ ያልጠበቀችው መልዕክት ስልኳ ላይ ገባ። መልዕክቱ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር ወደ ሂሳቧ መግባቱን የሚያበስር ነበር።

​ገንዘቡ የሷ እንዳልሆነ ያወቀችው እመቤት፤ ለአፍታም ሳታመነታ "ይህ የሰው ሀቅ ነው፤ የኔ አይደለም" በማለት ለራሷ ወሰነች።

​ከደቂቃዎች በኋላ ገንዘቡን በስህተት የላከውና በአላማጣ ከተማ የሚኖረው ወጣት መሐመድ መኪ ደውሎ ሲያናግራት፤ በፍጥነት እና በቅንነት ገንዘቡን ለመመለስ ተባበረችው።

​የወጣት እመቤት መልእክት፡-
​"እኔም በላቤ የምኖር ሰው ነኝ። ሰው በላቡ ለፍቶ ያገኘውን ገንዘብ በስህተት ወደ ሌላ ሰው መላክ ሊያጋጥም ይችላል፤ የራስ ያልሆነን ነገር መመለስ ግን ለኅሊና ዕረፍት ነው።"

​የባለቤቱ ምስጋና፡-
ከአላማጣ ሆኖ በጭንቀት ይደውል የነበረው መሐመድ፤ በወጣቷ ምላሽ ተደናቋል። "ደውለን ስናናግራት የሰጠችን ምላሽ እምነቷንና ታማኝነቷን እንድገነዘብ አድርጎኛል። አላህ ሀቋን ይክፈላት" ሲል መርቋታል።

​ክብር ለእንደዚህ አይነት ቅን ኢትዮጵያውያን! 👏

​እናንተስ በወጣት እመቤት ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር? ሀሳባችሁን አጋሩን! 👇

​#honesty #integrity #ethiopia #addisababa #alamata #gooddeed #inspiration

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.