Logo
Getu Temesgen
✅ ተገኝተዋል! | "ፓስፖርታችንን በክብር ተረክበናል!"
#ethiopia | ​የጠፉት 5 ፓስፖርቶች፣ መታወቂያዎች እና የውጭ ሀገር ገንዘብ ለባለቤቶቹ ተመለሰ! 👏🇪🇹

​ትናንትና ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ወድቆ በወንድማችን ዲንሰፋ በሽር (Dinsefa Beshir) እጅ ገብቶ የነበረው የካናዳ እና የኢትዮጵያ ፓስፖርቶች እንዲሁም ጠቃሚ ሰነዶች ዛሬ ለባለቤቶቹ ተመልሰዋል።

​ከ9 ዓመታት በኋላ ከካናዳ፣ ባለቤቱን እና ልጆቹን ይዞ ለሦስት ሳምንት ለእረፍት ወደ ሀገር ቤት የገባው አቶ ሚኪያስ ንብረቱን ተረክቧል።

​ዲንሰፋ በሽር፤
ለአቶ ሚኪያስ የስፖርት ትጥቅ መሸጫ ሱቁ ድረስ በመጥራት፡-
​4 የካናዳ ፓስፖርት 🇨🇦
​1 የኢትዮጵያ ፓስፖርት 🇪🇹
​የካናዳ መኖሪያ ፈቃድ፣ መንጃ ፈቃድ እና ዶላሩን ጨምሮ ምንም ሳያጎድል አስረክቧል።

​የክብር ምስጋና!
ይህ መረጃ በፍጥነት እንዲደርስ እና ቤተሰቡ ከጭንቀት እንዲገላገል መረጃውን #ሼር (SHARE) ላደረጋችሁ የጌጡ ተመስገን ሚዲያ ቤተሰቦች በሙሉ "ምስጋና ውሰዱ" ተብላችኋል!

​በጎነት ለራስ ነው!
ክብር ለወንድማችን ዲንሰፋ! 🙏

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

​#ethiopia #honesty #goodnews #lostandfound #boleairport #getutemesgenmedia

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.