25 days ago
ብሔራዊ የእደ ጥበብ ሙዚየም እና የሀስትካላ አካዳሚ
(National Crafts Museum & Hastkala Academy)
የጉዞ ማስታወሻ ( ክፍል - 2 )
#ethiopia |በኒው ዴልሂ በሚገኘው ብሔራዊ የዕደ-ጥበብ ሙዚየምና ሀስትካላ አካዳሚ (National Crafts Museum & Hastkala Academy) ዘለቅን። የብሪክስ ባዛር (BRICS Bazaar - ከመስከረም 10–15, 2026) እየተካሄደ ነው።
የብሪክስ ባዛር፦ ባህሎችን መቅረጽ፣ ሕዝቦችን ማገናኘት (BRICS Bazaar: Crafting Cultures, Connecting People) መሪ ቃል ይዟል። የንግድ ትርኢቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በጨርቃጨርቅ ሚኒስቴር አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፣ አማርኛ፣ ህንዲ፣ አረብኛ፣ እስፓንኛ፣ ፖርቱጋልኛ፣ ቻይንኛ ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክቶችን ያካተተ ነው።
Ms. Shakshi Gupta - አስጎብኚያችን ስለሙዚየሙ መተንተን፤ ማስረዳት ጀመረች።
የቤንጋል መንደር ገጽታ (ምዕራብ ቤንጋል)
በ'ኩምሃር' (የሸክላ ሰሪ) ባለሙያዎች ማህበረሰብ ከተሰሩ የክሪሽናናጋር (ናዲያ ዞን) የሸክላ ምስሎች፣ ከሳርና የቀርከሃ ጎጆዎች እንዲሁም ከጌጣጌጥ ስራዎች ጋር የገጠር ሕይወትን ያሳያል።
የኪንሃል አሻንጉሊቶች (ካርናታካ)
ከኪንሃል የመጡ በእጅ በእንጨት የተቀረጹ አሻንጉሊቶች ሲሆኑ፣ በኮምጣጤ ፍሬ የተወለወሉና በደማቅ የከለር ቀለም የተሸለሙ ናቸው፤ በታሪክ ለሙሽሮች በስጦታ መልክ ይሰጡ ነበር።
የፓታቺትራ ስዕል (ኦዲሻ)፦ ከፑሪ፣ ራጉራጅፑር እና ቡባኔስዋር የመነጨ ባህላዊ የጨርቅ ላይ ስዕል (ፓታ + ቺትራ) ሲሆን፣ ከራማያና፣ ማሃባራታ እና ባጋቫታ ታሪኮችን ያቀርባል።
የናጋ ጥበብ (ናጋላንድ / ሰሜን-ምስራቅ ህንድ)፦ የጎሳ ባህል ያላቸው የእንጨት የቀደመ አባቶች ምስሎች፣ የተሸመኑ የሸንበቆና ቀርከሃ ቅርጫቶች፣ እንዲሁም በዐጥንት፣ ቀንድ እና ፀጉር ያጌጡ የትንባሆ ማጫሻዎች፣ ጦሮች እና ባርኔጣዎች ናቸው።
የፓቡጂ ፋድ (Phad of Pabuji - ራጃስታን)
በታጠበ የጥጥ ጨርቅ ላይ የሚሳሉ የመጠቅለያ (ስክሮል) ስዕሎች ሲሆኑ፣ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በምዕራብ ራጃስታን ኮሉ (ማርዋር) ይኖር የነበረውን የፓቡጂ የተባለ የህዝብ ጀግና ህይወትና ተረቶች ያሳያሉ።
ታሪኩ ሙሉ ሌሊት በሚከናወኑ ስነ-ስርዓቶች ላይ 'ቦፓስ' (ከናያክ ማህበረሰብ የተወጣጡ ዘማሪዎች) በትልልቅ የሸክላ ማማዎች እየታጀቡ 'ፓቡጂ ራ ፓንዋራ' የተሰኙ የጀግንነት ዜማዎችን ሲዘምሩ ይተረካል።
ስዕሎቹ በቢልዋራ (ሜዋር) ሻህፑራ በሚገኙ የ'ጆሺ' ቤተሰብ ባለሙያዎች ብቻ የሚሳሉ ሲሆን፣ ጨርቁን አዘጋጅተው መልካም ቀን በመጠበቅ በባህላዊ ተፈጥሯዊ ቀለሞች ይስሏቸዋል።
አስጎብኚያችን Ms. Shakshi Gupta - ፈትፍታ የማጉረስ ትህትና ያላት ናት።
ጥያቄ አለ? - አለች።
የዶክራ ብረታ ብረት ዕደ-ጥበብ (Dhokra Metal Craft - ቻቲስጋርህ እና ማዕከላዊ/ምስራቅ ህንድ) ጥበብ ማውጋት ቀጠለች።
በሸክላ ቅርጾች ላይ በሚቀልጥ ሰም (cire perdue) የሚሰራ የ5,000 ዓመታት ዕድሜ ያለው የብረት ማቅለጥና ማፍሰስ ጥበብ ሲሆን፣ የተጠላለፈ ወይም የተጠቀለለ የላይኛው ገጽታ ቅርፅ በመያዙ ይታወቃል።
በቻቲስጋርህ (ባስታር)፣ ኦዲሻ፣ ጃርካንድ፣ ምዕራብ ቤንጋል እና አንድራ ፕራዴሽ ባሉ ከፊል-ዘላን የጎሳ ብረት ሰሪዎች የተሰራ ሲሆን፣ የእህል መለኪያ ማሰሮዎችን፣ የከብት ቃጭሎችን እና የነሐስ የጎሳ ምስሎችን (እንደ ከአደን የሚመለሱ አደንኞችን ምስል) ያመርታሉ።
የኮንድሃ / ኮንድ ነሐስ ስራዎች
(Kondha Bronzes - ኦዲሻ)
በኦዲሻ የራያጋዳ እና ጋጃፓቲ ዞኖች በሚኖሩ የኮንድሃ (ዶንጋሪያ ኮንድሃ) የጎሳ ቡድኖች በብረት ሰሪዎች ለዘመናት የተከናወነ የነሐስ ማፍሰስ ጥበብ ነው።
ሙሉ በሙሉ በማፍሰስና ሰም በማቅለጥ ቴክኒኮች ለ'ዳራኒ ፔኑ' (የምድር አምላክ) የመስዋዕት ስጦታዎች፣ የክብረ-በዓል ምልክቶች፣ የተለያዩ ቅርሶች እና በስጦታ (ሚዜ) የሚሰጡ አሻንጉሊቶችን ለመስራት ያገለግላል።
የካርናታካ የቡታ እምነት ቅርጻ ቅርጾች
(Bhuta Cult Sculptures - ካርናታካ)
በባህር ዳርቻይቱ ካርናታካ ኡዱፒ ዞን ከ19ኛው ክፍለ ዘመን የመጡ በእንጨት የተቀረጹ ምስሎችና የነሐስ ጭንብሎች ሲሆኑ፣ ከ'ቡታራዳኔ' (የመንፈስ አምልኮ ስነ-ስርዓት) ጋር የተያያዙ ናቸው።
በ'ጉዲጋር' የእደ-ጥበብ ማህበረሰብ ከጽኑ የጃክፍሩት እንጨት የሚቀረጹ ሲሆን፣ እንደ 'ፓንጁርሊ' (የዱር አሳማ መንፈስ)፣ 'ፒሊቻንዲ' (የነብር መንፈስ)፣ 'ጁማዲ' እና እንደ 'ኮቲ እና ቼናያ' ያሉ የአባቶች ጀግኖችን ይወክላሉ።
በወፍ በረር ማጠቃለያ ላይ ደረሰች
የማዱባኒ ስዕል (Madhubani Painting - ቢሃር)
በሰሜን ቢሃር የሚቲላ አካባቢ የሚገኝ ጥንታዊና መስመራዊ የህዝብ ስዕል ዘይቤ ሲሆን፣ በባህላዊ መልኩ በመንደር ሴቶች በግድግዳዎችና ወለሎች ላይ ይሳላል።
'ኮህባርቺትራ' (ለአዲስ ተጋቢዎች የመኝታ ክፍል ግድግዳ ስዕል) እና 'አሪፓና' (ለስለትና ባህላዊ ስነ-ስርዓቶች የሚሰራ የወለል ጌጣጌጥ) የሚያካትት ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በወረቀትና በሸራ ላይ ይሰራል።
ጠቅላላ የብረታ ብረት ዕደ-ጥበብ
(General Metal Crafts)
ከዕለት ተዕለት ቁሳቁሶች፣ የማስቀመጫ ሳጥኖችና የአልጋ እግሮች እስከ ባህላዊ ምስሎችና የወፍ እና የእንስሳት ቅርጽ ያላቸው የሱፓሪ መቁረጫዎች (sarota) ድረስ ያሉትን ባህላዊ የህንድ የነሐስና የብረት ጥበቦችን ያጎላል።
***
ከሙዚየም ወደ ባዛር ዘለቅን
ኢትዮጵያውያን የእደ ጥበብ ባለሙያዎች በBRICS Bazaar 2026 ላይ ተሳትፈዋል
በሕንድ ኒው ዴልሂ በሚገኘው ብሔራዊ የእደ ጥበብ ሙዚየም እና ሀስትካላ አካዳሚ (National Crafts Museum & Hastkala Academy) ከመስከረም 10 እስከ 15 ቀን 2026 እየተካሄደ ባለው BRICS Bazaar 2026 ላይ ኢትዮጵያውያን የእደ ጥበብ ባለሙያዎች ሀገራቸውን ወክለው ተሳትፈዋል።
ዝግጅቱ “Crafting Cultures, Connecting People” — “ባህሎችን መቅረጽ፣ ሕዝቦችን ማገናኘት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፣ የተለያዩ የBRICS አገራትን ባህላዊ የእደ ጥበብ፣ ፋሽን፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ሸክላ ስራ እና ሌሎች ባህላዊ የእጅ ሥራዎችን ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ያስተዋውቃል።
እጂጋየሁ ኃይለጊዮርጊስ አራርሶ
ከኢትዮጵያ በHandweaving – የእጅ ጨርቃ ጨርቅ ሥራ የተሳተፈችው እጅጋየሁ ኃይለጊዮርጊስ አራርሶ የፋሽን ዲዛይነርና ሥራ ፈጣሪ ስትሆን፣ Ejig Tibeb መስራች እና Ethiopian Fashion Designers Association ተባባሪ መስራች ናት።
የኢትዮጵያን ቡና ለታዳሚዎቹ በክብር አጠጥታለች።
መዓዛ አሰግድ አሰፋ
በሌላ በኩል መአዛ አሰግድ አሰፋ (Meaza Asegid Assefa) በHand Modelling / Pottery – የእጅ ሸክላ ሥራ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክላለች።
“Meaza Pottery – መአዛ ሸክላ ሥራ” በሚል የንግድ ስም ትሠራለች። በእጅ የተሰሩ ባህላዊ የሸክላ እቃዎችንና መያዣዎችን በማምረት የባህላዊ የሸክላ ጥበብን ለመጠበቅና ለማስቀጠል እየሰራች መሆኑ ተናግራለች።
የኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ውበት በዓለም መድረክ
የኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ባለሙያዎች በዚህ ዓይነት ዓለም አቀፍ መድረክ መሳተፋቸው፣ የአገሪቱን ባህላዊ የእጅ ሥራዎች፣ ፋሽንና የፈጠራ ሥራዎችን ለዓለም ማስተዋወቅ ከመቻሉ ባሻገር ለእደ ጥበብ ምርቶች አዳዲስ የገበያና የትብብር ዕድሎችን የሚከፍት አጋጣሚ ነው።
የጉዞ ማስታወሻ
ከፍል ( 3 ) ይቀጥላል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
Special thanks :
#india in Ethiopia (Embassy of India, Addis Ababa) #indiaethiopia #brics #financialcooperation #banking #economiccooperation #ministry of External Affairs, #government of IndiaIndia in Ethiopia (Embassy of India, #addis Ababa)Press Information Bureau - PIB, #government of IndiaDiaspora India ConnectMinistry of Information & Broadcasting, #government of #indiamygovindiaddnewsliveasian News #international (ANI)All India Radio News #india in ethiopia (embassy of india addis ababa) #manohar Lal #ethiopian Airlines #ministry of External Affairs
Government of India
# India - External Publicity & Public Diplomacy Division External Language Media Section #mr . Amit Raghav, Publicity Officer (XLM) #unesco #brics2026 #bricsbazaar2026 #ethiopia #india #newdelhi #crafts #handicraft #handweaving #pottery #ethiopianfashion #getutemesgen

Comments