2 months ago
"እኔና ጣሊያን ፎቶ ለመነሳት ማንንም አንለምንም!"
በሜሎኒና በትራምፕ መካከል የተቀሰቀሰው ፍጥጫ
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በቡድን 7 ጉባኤ ወቅት የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ፎቶ ለመነሳት እንደለመኗቸውና አዝነውላቸው አብረዋቸው ፎቶ መነሳታቸውን ለጣሊያኑ ላ7 ቲቪ መናገራቸውን ተከትሎ.፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል።
በትራምፕ ንግግር ክፉኛ የተቆጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ በቪዲዮ ባስተላለፉት ምላሽ፣ የትራምፕ ንግግር ሙሉ በሙሉ የፈጠራ ወሬ መሆኑን በመግለጽ.፣ "እኔና ጣሊያን ፎቶ ለመነሳት ማንንም አንለምንም" ሲሉ በቁጣ አጣጥለውታል።
ፕሬዝደንቱ በአጋር ሀገራት ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት ሲፈጽሙ ይህ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነም ሜሎኒ አክለው ገልጸዋል።
ይህንን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየሻከረ የመጣ ሲሆን፣ የጣሊያኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ይፋዊ ጉዞ ወዲያውኑ ሰርዘዋል።
ሚኒስትሩ ከአሜሪካው አቻቸው ማርኮ ሩቢዮ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ቀጠሮ የተሰረዘው በዚህ እያገረሸ በመጣው አለመግባባት ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።
#giorgiameloni #donaldtrump #italy #usa #diplomacydrama #breakingnews #g7 #worldpolitics

4 months ago
ጣሊያን ለአሜሪካ "የጦር ሰፈሬን አትጠቀሚም" አለቻት
#ethiopia | አሜሪካ በኢራን ላይ ለምታቅደው ወታደራዊ ዘመቻ የጣሊያንን ትብብር ብትጠይቅም፣ የሮም መንግስት ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ተሰማ። በተለይም በሲሲሊ የሚገኘውን ስልታዊው የሲኞኔላ (Sigonella) የአየር ኃይል ጣቢያ አሜሪካ ለጥቃት እንዳትጠቀምበት ታግዳለች።
በዚህም ምክንያት ወደ ጣሊያን ለመግባትና ስምሪት ለመጀመር ተዘጋጅተው የነበሩ የአሜሪካ የቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ባሉበት እንዲቆሙ መታዘዛቸው ተነግሯል። ጣሊያን ይህን ውሳኔ ያሳለፈችው ከብሪታንያ እና ስፔን በመቀጠል ሲሆን፣ ይህም በኢራን ላይ ለሚሰነዘር ጥቃት ፈቃደኛ ያልሆነች ሦስተኛዋ የአውሮፓ ሀገር አድርጓታል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ እንደዚህ ያሉ ወታደራዊ ውሳኔዎች የሀገሪቱ ፓርላማ እውቅና እና ጥልቅ ውይይት እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ የአሜሪካን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል። ይህ እርምጃ በኔቶ አባል ሀገራት መካከል በኢራን ጉዳይ ላይ ያለውን ከፍተኛ የፖሊሲ ልዩነት በግልጽ ያሳየ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #italy #usa #iran #breakingnews #military #geopolitics #giorgiameloni #sigonella #europe

Comments