16 days ago
የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል “ጊፋታ” ድምቀት የሆነው "ሹሃ ዎጋ"
******************
በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ተምዝግቦ የዓለም ቅርስ የሆነው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በብሔሩ ዘንድ እጅግ የተለየ ትኩረት የሚሰጥ የብሔሩ መገለጫ ነው።
ለበዓሉ ከዓመት እስከ ዓመት የእርድ በሬ መግዣና የእናቶች የቅቤ ቁጠባን የመሳሰሉ ዝግጅቶች የሚደረጉ ሲሆን፣ በዓሉ ሲቃረብ ግን ሳምንታት እና ቀናቶች የየራሳቸው ስያሜ አሏቸው።
በገበያዎች "ሀረ-ሀይቆ፣ ቦቦዳ እና ጎሻ" ቀናት "ኮሴታ ሐሙሳ፣ ሱልዓ አርባ፣ ባጭራ ቄራ እና ሹሃ ዎጋ" የሚባሉ የበዓሉ መዳረሻዎች ናቸው። የቀናቱ ስያሜ ከበዓሉ ማግስት "ታማ ሰኞ" ጀምሮ እስከ "ጎሏዋ እጌታ" ወደሚባልበት የበዓሉ ለቀጣይ ዓመት መልካም ምኞት ቀን ይቀጥላሉ።
በዚህ መሠረት ዛሬ በወላይታ ብሔር ዘንድ ቀኑ የዕርድ እሁድ" ሹሃ ዎጋ" በመባል ይጠራል። የዕርድ እሁድ አባቶች በ"Amuwaa" (በቡድን) አንድ ላይ ሆነው ከወራት በፊት ለእርድ የሚሆን በሬ ገዝተው ከቡድኑ አባላት በአንዱ ቤት የተቀለበው በሬ የሚታረድበት የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ነው።
የዕርድ በሬው በእሸት፣ በቆሎ፣ ስኳር ድንች እና በሌሎች እህልና ስራስሮች አባለቱ በየተራ እያዋጡ ይቀለባል። በሬ የሚታረደው "በአሙዋ" አባላት ውስጥ በሬ ሲቀለብ የቆየው አባወራ ደጅ ሲሆን፣ አባላት በዕርድ ቀን ጠዋት ተሰብስበው ከእርድ አስቀድመው በቦታው ባህላዊ ምግቦችን ይበላሉ፣ መጠጦችንም ይጠጣሉ።
በእርድ ቦታ ከስጋ ዓይነቶች የተወሰነ ወስደው የቡድኑ አባላት የአብሮነት መገለጫ ብለው በቦታው ይቋደሳሉ። የየራሳቸው ቅርጫ ከተከፋፈሉ በኋላ በእርጥብ ቆዳ ለሚቀጥለው ዓመት ጊፋታ በዓል የዕርድ በሬ መግዣ ተቀማጭ ገንዘብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ።
ዕጣ ጥለው የተከፋፈሉትን ስጋ ወደየቤታቸው ከወሰዱ በኋላ እናቶች ቆጮ፣ ቂጣና ዳጣ በርበሬ በማዘጋጀት ሥጋውን የቤተሰቡ አባለት በጋራ በኮባ ቅጠል በመሬት ዘርግፈው ለማዕዱ ፈጣሪን በማመስገን በደስታ የበዓሉ ድግስ በጋራ ይበላሉ።
የዘንድሮ ጊፋታ በዩኔስኮ የተመዘገበበት የመጀመሪያ ዓመት በዓል በመሆኑ በወላይታ ሶዶ ከተማ በተለዬ ድምቀት “የትውልድ ቅርስን እንጠብቅ፣ የጊፋታን ውርስ እናስቀጥል” በሚል መሪ ቃል በአደባባይ እየተከበረ ይገኛል።
በትዕግስቱ ቡቼ
#ethiopia #ebc #gifata #yoogifata #wolaita #ethiopianculture

"ጊፋታ" በዓል ማህበራዊ አንድነትንና ወድማማችነትን በማጠናከር ለሀገራዊ አንድነት መሰረት ይጥላል፡- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
********************
የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡
በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እንደገለፁት፣ በወላይታ ሕዝብ ዘንድ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው 'ጊፋታ' በዓል የሰላም፣ የአንድነት እና የመሻገር ምልክት ነው።
"ጊፋታ" በዓል የተራራቁና የተነፋፈቁ የሚገናኙበት፣ ቂምና ቁርሾን በዕርቅና በይቅርታ በመሻገር እንዲሁም የጥላቻን ግንብ በፍቅር በማፍረስ ሰላም ነግሶ በአንድነት ወደ አዲስ ዘመን መሸጋገሪያ ተደርጎ የሚወሰድ ድንቅ የክልላችን እሴት ነው ብለዋል፡፡
የወላይታ ሕዝብ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በጋራ የሚያከብረው የ'ጊፋታ' በዓል አብሮነትና ወንድማማችነት የሚጎለብትበት፣ ኅብረ-ብሔራዊነት የሚያድግበት እና የሕዝቦች ትስስር ይበልጥ የሚጠናከርበት በዓል መሆኑን ገልጸዋል።
የበዓሉን እሴቶች ለሀገር ሰላምና አንድነት፣ ለሕዝቦች የጋራ ልማትና ዕድገት መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ የሚከበረው ጊፋታ፣ የሕዝቦች አንድነትን ከማጠናከርና የሀገራችንን በጎ ገፅታ ለዓለም ከማስተዋወቅ ባለፈም፣ በቱሪዝም መስህብነት የጎላ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ በዓሉን ዋነኛ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን ለማስቻል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
‘የጊፋታ’ በዓል ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፍ የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት መመዝገቡ የሚታወስ ነው፡፡
በሐይማኖት ከበደ
#ebc #gifata #wolaitanewyear #ethiopianheritage #unescoculturalheritage

20 days ago
የናፍቆት ማሳረጊያው የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘ጊፋታ’
*****************
በመስከረም ወር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ 'ጊፋታ' በዓል አንዱ ሲሆን፣ ጥልቅ ማህበራዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ እና ሞራላዊ እሴቶችን በውስጡ አቅፎ የያዘ ነው፡፡
"ኪያዳ ኪያዳ ሞካ ታና ታዬ!" መጥቼልሻለሁ ወጥተሸ ተቀበይኝ እናቴ! የሚል ትርጉም ያለው የድምፃዊት ትዕግስት ወይሶ ሙዚቃ፤ ድምፅ የናፍቆት ነው፤ ዜማው የርቀት ነው፤ ጥሪው የልጅነት ትዝታን አዝሎ፣ የኑሮን ውጣ ውረድ ተቋቁሞ፣ ከወራት መለየት በኋላ ወደ እናት ጉያ የሚደረግን ጉዞን የሚያሳይ ነው።
መስከረም ጠባ ማለት ኑሮን ለማሸነፍ ሲል ከትውልድ ቀዬው ለራቀው ወጣት የልብ ትርታው የሚጨምርበት ወቅት ነው። ‘ጊፋታ’ የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን፣ የቤተሰብ መገናኛ ድልድይም ጭምር ነው።
ወጣቱ በአካል ተገኝቶ የናፈቀችውን እናቱን ሲስም፣ መከታ የሆነውን አባቱን ሲያቅፍ፣ በስስት የሚያያቸውን እህት ወንድሞቹን እና የልጅነት አብሮ አደግ ጓደኞቹን ሲያገኝ ደስታው እጥፍ ድርብ ይሆናል። ድምፃዊት ትዕግስት ወይሶ በዜማዋ እንዳንቆረቆረችው፣ የጊፋታ ወቅት 'ተናፋቂ' የሚሆነውም ለዚህ ነው።
የኑሮ ግዴታ ሆኖበት በአካል ወደ ቤተሰቡ መሄድ ላልቻለው ወጣት ጊፋታ የኃላፊነት መወጫ ነው። ካለበት ሆኖ፣ በላቡና በትጋቱ ካገኘው ገንዘብ ቀንሶ ለቤተሰቦቹ በመላክ በዓሉ ደምቆ እንዲውል ያደርጋል። ይህ ድርጊት በወላይታ ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ጠንካራ የቤተሰብ ትስስር እና መረዳዳት የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው።
በዓሉ ከመድረሱ በፊት ያለው የቅድመ ዝግጅት ድባብ ራሱን የቻለ አንድ በዓል ነው። እናቶችና ሴቶች ባህላዊ ምግቦችን ለማሰናዳት ይዘጋጃሉ። ሙቾ፣ ቆጮ፣ ቂጣ፣ ባጭራን የመሳሰሉ ባህላዊ ምግቦችን እና ጠረኑ የሚያውደውን ዳጣ ሲያዘጋጁ፤ እነዚህን ምግቦች ለማወራረድ ደግሞ 'ቦርዴ' የተሰኘው ባህላዊ መጠጥ ይጣላል።
የጊፋታ በዓል ትልቁ ዕሴት ደግሞ አብሮነትን ማጉላት ነው፡፡ ማህበረሰቡ ለበዓሉ የሚታረዱትን ከብቶች በጋራ ይገዛል፣ የሥጋ ማከፋፈሉ ሥራ በወንዶች በኩል በፍትሃዊነት ይከናወናል። ቤተሰብ እና ጎረቤት በአንድነት ተሰባስቦ በአንድ ማዕድ ይቋደሳል። ይህ ሥርዓት፣ በዘመናዊው ዓለም እየጠፋ የመጣውን 'አብሮነትን' እና 'ጉርብትናን' በተግባር ያሳያል።
ጊፋታ ትዝታ ቀስቃሽ እና ዘመድ አስታዋሽ ብቻ አይደለም፤ ዕርቅ አንጋሽም ነው። በወላይታ ባህል ማንም ሰው በልቡ ቂም ይዞ፣ ወንድሙን አስቀይሞ ወይም ከጎረቤቱ ጋር ተጣልቶ ጊፋታን አያከብርም።
አዲሱ ዓመት ሲመጣ የተጣላ ይታረቃል፤ የተቀያየመ ይቅርታ ይደራረጋል። ቂምና በቀልን በአሮጌው ዓመት ጥሎ፣ አዲሱን ዓመት በንፁህ ልብ መቀበል የሕዝቡን አንድነትና ሰላም የሚያስጠብቅ፣ የማህበራዊ ትስስር ዋልታ ነው። አባቶችም አዲሱን ዓመት አዲሱ ትውልድ በሰላም እንዲያልፈው ይመክራሉ፣ ይመርቃሉም።
የበዓሉ ሌላው ማሳረጊያ እና ድምቀት የ'ጉልያ' ወይም የችቦ ማብራት ሥርዓት ነው። ችቦ ሲበራ ተምሳሌታዊ ትርጉሙ ጥልቅ ነው። ማህበረሰቡ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሐዘን ወደ ደስታ፣ ከክረምት ጭቃ ወደ በጋው ፀዳል መሸጋገሩን ያበስራል።
በዚህ የብርሃን ጅማሮ ወቅት "ሃያያ ለኬ" የተሰኘው የጊፋታ ባህላዊ ዘፈን በወጣቶች እና በጎልማሶች አንደበት ይንቆረቆራል። ወጣቶች በየቤቱ እየዞሩ መልካም ምኞታቸውን በዘፈን ይገልጻሉ። ሁሉም በአንድ ድምፅ፡ "ሃሹ ላይታፔ ላይታ ሰሯን ጋቲስ!" (ከዓመት ወደ ዓመት እንኳን በሰላም አሸጋገረን) እያሉ ሀገርን በሰላም ላቆየው ፈጣሪ ምስጋና ያቀርባሉ።
ጊፋታ በቀን መቁጠሪያ ላይ ያለ አንድ ዕለት ብቻ አይደለም። ጊፋታ የወላይታ ሕዝብ ፍቅርን፣ ሰላምን፣ መተሳሰብን እና ኩራቱን ለትውልድ የሚያስተላልፍበት ትልቅ የህይወት መድረክ ነው።
ብርሃን ሲፈነጥቅ ጨለማ እንደሚገፈፈው ሁሉ ጊፋታ ሲመጣ ቂም ይረግፋል፤ ፍቅር ያብባል፤ አብሮነት ይፀናል።
በሲሳይ ደበበ
#ethiopia #ebc #gifata #wolaita #culturalheritage

1 month ago
የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" የዋዜማ ክዋኔዎች መካሄድ ጀመሩ
*******************
በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት የተመዘገበው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በመቃረቡ፣ የበዓሉ ዋዜማ በልዩ ልዩ ማኅበራዊና ባህላዊ ክዋኔዎች በደመቀ ሁኔታ መከበር ጀምሯል።
በወላይታ የዘመን አቆጣጠር ቀመር መሠረት የዓመቱ የመጀመሪያ ወር የሆነው እና ‘ታላቅ፣ በኩር ወይም የመጀመሪያ’ በሚል ትርጓሜ የሚታወቀው የጊፋታ በዓል፤ ከአሮጌ ወደ አዲስ ተስፋ፣ ከክረምት ወደ በጋ፣ እንዲሁም ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገሪያ ነው።
የበዓሉን መድረስ ተከትሎ በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ በዓሉን ለመቀበል ደማቅ የዝግጅት ክዋኔዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።
የበዓሉ ዋዜማ የኅብረተሰቡን አብሮነት፣ አንድነትና የመተሳሰብ እሴት የሚያጎሉ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች የሚከናወኑበት ወቅት ነው።
በዚህም እናቶች በቅቤ እቁብ የጀመሩትን ቁጠባ ሲያጠናቅቁ፤ አባቶች ደግሞ ዓመት ሙሉ የቆጠቡትን ገንዘብ ሰብስበው ከሦስት ወር በፊት የገዟቸውን የእርድ በሬዎች የማስቀለብ ሥርዓት በመፈጸም ላይ ናቸው።
በተጨማሪም ወጣቶች ለጉሊያ (ደመራ) የሚሆን እንጨት በመሰብሰብ እና በመከመር፣ እናቶች ደግሞ የእንሰት መፋቅ ሥነ-ሥርዓት በመከወን የበዓሉን መድረስ በማብሰር ላይ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ከበዓሉ አስራ አምስት ቀናት ቀደም ብሎ ልዩ ግብይት የሚከናወንባቸውና የበዓሉ ድምቀት የሆኑት “ሀሬሀይቆ”፣ “ቦቦዳ” እና “ጎሻ” የተሰኙ ባህላዊ ገበያዎች ደምቀው መዋል ጀምረዋል።
ምርት በገፍ የሚቀርብበት የሀሬሀይቆ ገበያ፣ ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቁሳቁሶች የሚሸጡበት የቦቦዳ ገበያ፣ እንዲሁም የማህበረሰቡ አባላት በማለዳ ተነስተው የመጨረሻ ግብይት የሚያካሂዱበት የጎሻ ገበያ ለዋዜማው ልዩ ድምቀት ሰጥተውታል።
ጊፋታ የዕርቅ እና የሰላም በዓል በመሆኑ፣ ማኅበረሰቡ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ ዕዳዎችን በመክፈል እና አካባቢውን በማጽዳት በዓሉን በሙሉ ደስታ ለማክበር ዝግጅቱን አጠናክሯል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የዋዜማው አከባበር አካል የሆነው እና በወላይታ ዞን የሚገኙ የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎችን የማስጎብኘት ዓላማ ያለው የ"ጊፋታ ቱር" መርሐ ግብር በዚህ ሳምንት እየተካሄደ ይገኛል።
በትዕግስቱ ቡቼ
#ethiopia #gifata #wolayita #unesco #culturalheritage #ethiopianculture

Sponsored by
Surafel
1 month ago
Comments