5 months ago
የቻይና ነገር
''የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም''
#ethiopia | የቴህራንን ሰማይ እንዲጠብቁ የተተከሉት የቻይና እና የሩሲያ ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርዓቶች፣ የአሜሪካና የእስራኤልን ጥቃት መከላከል አለመቻላቸው የጦር መሳሪያዎቹን ብቃት ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል።
የ"ኤችኪው-9ቢ" (HQ-9B) ዳግመኛ ውድቀት
ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ይዞት በወጣው ዘገባ መሰረት፣ በቅርቡ አሜሪካና እስራኤል በኢራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ የሰነዘሩት የተቀናጀ ጥቃት የኢራንን የአየር መከላከያ አውታር በእጅጉ አሳጥቶታል። በተለይም ኢራን በከፍተኛ ወጪ ከቻይና የገዛችው HQ-9B የተሰኘው የሚሳኤል መከላከያ ስርዓት፣ የአጥቂዎቹን የጦር አውሮፕላኖች ማቆም ሳይችል መቅረቱ ታላቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
ይህ የቻይና መከላከያ ስርዓት ሲከሽፍ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በፓኪስታንና በህንድ መካከል በነበረው ግጭት የህንድን ጥቃት መከላከል ሳይችል መቅረቱ ይታወሳል።
ራዳሮችን "የሚያሳውረው" የአጥቂዎቹ ስልት
የመከላከያ ስርዓቱ ለምን ሊከሽፍ ቻለ? ለሚለው ጥያቄ ዘገባው የሚከተሉትን ምክንያቶች አስቀምጧል፦
* የኤሌክትሮኒክስ ውጊያ፦ አጥቂዎቹ የተራቀቁ የራዳር ማሳወሪያ (Jamming) ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀማቸው፣ የቻይናው HQ-9B እና የሩሲያው S-300 ኢላማቸውን ማየት ተስኗቸዋል።
* የስውር አውሮፕላኖች ሚና፦ እንደ F-35 ያሉ በራዳር የማይታዩ (Stealth) የጦር አውሮፕላኖች እና በርካታ ድሮኖች የኢራንን የዕዝ ማዕከል በመምታት መላውን ስርዓት "ዓይነ ስውር" አድርገውታል።
* የከፍታ ገደብ፦ የቻይናው መከላከያ በከፍተኛ ከፍታ ላይ የሚበሩ ኢላማዎችን ለመምታት ታስቦ የተሰራ ቢሆንም፣ ዝቅ ብለው ለሚበሩና ፈጣን ለሆኑ የሚሳኤል ጥቃቶች ተገቢውን ምላሽ መስጠት አልቻለም።
የቤጂንግ ስጋት
ይህ ክስተት የቻይና የጦር መሳሪያዎች በጦር ሜዳ ያላቸውን ተዓማኒነት ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል። ቀደም ሲል ህንድ በፓኪስታን ላይ ባደረገችው "ኦፕሬሽን ሲንዶር" ወቅትም በተመሳሳይ የቻይና መከላከያ ስርዓቶች በህንድ ድሮኖች በቀላሉ መደምሰሳቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የአሁኑ የኢራን ክስተት ለቤጂንግ የጦር መሳሪያ ንግድ መጥፎ ዜና እንደሚሆን ተገምቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #iran #china #militarytech #airdefense #middleeastupdate #hq9b #israel #usa

Comments