4 months ago
አንድ ሺህ ዜማ ዜሮ ዲግሪ - የካሙዙ ካሳ የሹመት ጥማት እና የአለም መሪዎች ስም ማጥፋት
ፖለቲካ በ 'Auto-tune' አይሰራም የካሙዙ ካሳ የድፍረት ቅንብር እና የተገላቢጦሽ ምሳሌዎቹ
የአቀናባሪ ካሙዙ ካሳ ጽሁፍ በውጪ ሀገራት ስኬታማ የነበሩ ግለሰቦችን እንደ ምሳሌ በማቅረብ የራሱን የፖለቲካ ተሳትፎ ትክክለኛነት ለማስረዳት ቢሞክርም የቀረቡት ማስረጃዎች ግን ካለበት ተጨባጭ ሁኔታ (የትምህርት ዝግጅት ማነስ እና የሙያ አይነት) አንጻር ሲመዘኑ እርስ በርሳቸው የሚጋጩና የሱን ሃሳብ የማይደግፉ ናቸው።
የካሙዙ ካሳን "የአለም ተሞክሮ" ድርሰት ስንመለከተው ሰውየው ቅንብሩ ላይ እንጂ መረጃ ፍለጋው ላይ ጭንቅላቱን እንዳልተጠቀመበት በግልጽ ያስታውቃል።
ሊቅ ያወቀውን ይናገራል ካሙዙ የሰማውን ይዘበዝባል እንደሚባለው የጠቀሳቸው ሰዎች ታሪክ የሱን ድንቁርና እንጂ የሱን ብቃት አያረጋግጥም።
ካሙዙ ሆይ እስቲ የቀረጽከውን የውሸት ሲቪ በትንሹ እንፈትሽው
1. ባለንድራ ሻህ (Balen Shah) - የኔፓሉ መሪ
ካሙዙ የጠቀሰው ባለንድራ ሻህ ራፐር ስለሆነ ብቻ የመሪነት ወንበር ላይ የወጣ ይመስለዋል ነገር ግን እውነታው ይሄ ነው
• የትምህርት ማስረጃው ባለንድራ ሻህ በ Structural Engineering (የህንፃ ስትራክቸር መሐንዲስ) የመጀመሪያ ዲግሪውን የያዘ ሲሆን በማስተርስ ዲግሪው ደግሞ በ Infrastructure Engineering ተመርቋል።
• ለካሙዙ መልእክት፦ ካሙዙ ሆይ የቤት ስራህን ስትሰራ ራፐር መሆኑን ብቻ ሳይሆን መሐንዲስ መሆኑንም ብታነብ ኖሮ አንተ "High School" እንኳን ሳትጨርስ እሱን ለመምሰል ባልዳዳህ ነበር።
ኔፓል ሀገር እንጂ የሙዚቃ ስቱዲዮ አይደለችም!
2. ቮሎዲሚር ዘለንስኪ (Volodymyr Zelenskyy)
"ኮሜዲያን ነበር" ብሎ ካሙዙ ሊያጽናናን ይሞክራል ግን አንድ ነገር ረሳ
• የትምህርት ማስረጃው፦ ዘለንስኪ ከኪዬቭ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ዩኒቨርሲቲ በ ህግ (Law Degree) የተመረቀ ባለሙያ ነው።
• ለካሙዙ መልእክት፦ ዘለንስኪ በድራማው ላይ ፕሬዝዳንት ሆኖ ከመጫወቱ በፊት የህግ መጽሐፍትን ገልጦ ያጠና ሰው ነው። አንተ ግን በገሃዱ ዓለም የፓርላማ ወንበር ላይ ተቀምጠህ "ቅንብሩን እንዴት ላሳምረው?" እያልክ ልታቀነቅን ነው ወይስ በ "Autotune" ልታስተዳድረን?
3. ቫችላቭ ሃቬል (Václav Havel)
ካሙዙ የጠቀሰው የቼክ ሪፐብሊክ መሪ ታሪክማ ለካሙዙ ጭራሽ አይሆንም
• የትምህርት ማስረጃው፦ ሃቬል በድራማቲክ አርትስ የተመረቀና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ ፈላስፋ (Philosopher) እና ደራሲ ነው።
• ለካሙዙ መልእክት፦ ሃቬል አምባገነንነትን በብዕሩና በፍልስፍናው ያሸነፈ ሰው ነው። አንተ የ 12ኛ ክፍል ማትሪክን እንኳን ሳታልፍ እንዴት ብለህ ነው የሃቬልን ስም ለመጥራት የደፈርከው? ድፍረት ወይስ ድንቁርና?
4. ሮናልድ ሬገን እና አርኖልድ ሽዋርዜኔገር
እነዚህ ሰዎች ወደ ፖለቲካ ከመግባታቸው በፊት ምን እንደነበሩ ካሙዙ ሳያጣራ ተዋናይ ነበሩ ብሎ ዘለለው
• ሮናልድ ሬገን፦ በኢኮኖሚክስ እና ሶስዮሎጂ (Economics and Sociology) ዲግሪ የነበረው ሰው ነው።
• አርኖልድ፦ በቢዝነስ እና ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክስ (Business and International Economics) ዲግሪ አለው።
• ለካሙዙ መልእክት፦ እነዚህ ሰዎች ሆሊዉድ ከመግባታቸው በፊትና ከገቡም በኋላ የተማሩ ሰዎች ናቸው።
"High School" ያላጠናቀቀ ሰው የአሜሪካን ፕሬዝዳንቶች እንደ ምሳሌ ሲጠቅስ "ድንገት ፊልም ውስጥ ያለን" ነው የሚመስለው።
5. ጆርጅ ዌአ እና ኢሱኑ ንዱር
• ጆርጅ ዌአ፦ ፕሬዝዳንት ከመሆኑ በፊት ወደ ትምህርት ቤት ተመልሶ በቢዝነስ ማኔጅመንት እና በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን (Master's in Public Administration) ተመርቋል።
• ለካሙዙ መልእክት፦ ጆርጅ ዌአ ለሀገር መሪነት እግር ኳስ ብቻ አይበቃም ብሎ የተማረ ሰው ነው። አንተ ግን "ከ 10ኛ ክፍል በላይ እውቀት አያስፈልገኝም ብለህ ፓርላማ ለመግባት መመኘትህ ለታዛቢ ግርምት ነው።
ካሙዙ ሆይ የጠቀስካቸው ሰዎች በሙሉ የጋራ መለያቸው "ተምረው ማለፋቸው" ነው።
አንተ ግን ትምህርት ቤት በር ላይ እንኳን ሳታልፍ "እነዚህን ሆነናል" ማለትህ የኢትዮጵያን ህዝብ መወከል እንደ ሙዚቃ ቅንብር መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል።
ፖለቲካ "Key-Note" አይደለም እውቀትና ብቃት ይጠይቃል።
ቢያንስ ቢያንስ ምሳሌ ስትጠቅስ የሰዎቹን የትምህርት ታሪክ ጎግል (Google) ማድረግ እንኳን አለመቻልህ ምክር ቤት ብትገባ ምን አይነት "ጥናት" ልታቀርብ እንደምትችል ከወዲሁ ያሳብቃል።
የፓርቲ አባል መሆን መብት ቢሆንም ሀገር መምራት ግን "ሰባት ድምፅ" መደርደር አይደለም።
Via belayneh Kassa

5 months ago
#ቃለየሱስ በቀለ - የአቪየሽን ወርቃማው ጋዜጠኛ
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
#በዚህ የስነዳ ሥራችን ውስጥ በቅፅ 3 ከተካተቱት 20 ዘርፎች ውስጥ የሥራ ዘርፎች ውስጥ ሚድያ አንዱ ነው። በአሁኑ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች እየተሰነዱ ይገኛሉ። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
#ዛሬን ሰንደን የምናስነብባችሁ የሚድያ ባለሙያ የቃለየሱስ በቀለን የሙያ ታሪክ ነው። በሚድያው ሥራ ሩብ ክፍለ- ዘመን የዘለቀው ቃለየሱስ በአቬሽን እና ማዕድን ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመዘገብ ትልቅ አሻራ አኑሯል። በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ በአገራችን በአንድ ርዕስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ወይም ተክኖ መዘገብ ባልተለመደበት ሁኔታ ቃለየሱስ ችሎ አሳይቷል። ከባለታሪኩ የተገኘውን መረጃ በማግኘት፣ የቅርብ ሰዎቹን በማነጋገር የሙያ ታሪኩ ተሰንዷል። ዕዝራ እጅጉ እና ታደሠ ማሞ አጠናክረውታል።
፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ትውልድና ዕድገት
‹‹የትኛውም አውሮፕላን ወደ አየር አኮብኩቦ መነሳቱ የተለመደ የጉዞው አማራጭ ቢሆንም አውሮፕላኑ ካሰበበት ደርሶ ማረፉ ደግሞ የግድ መሆን ያለበት ተግባር ነው፡፡››የሚል የአቪየሽን አባባል አለ፡፡በዚህ አባባል ተንደርድረን ወደ ውስጥ እንዝለቅ፡፡ሁሉም ዘርፍ የየራሱ አነፍናፊ ጋዜጠኞች እንዳሉት ሁሉ ቃለየሱስ በቀለ የተባለ ህልመኛና ደፋር ጋዜጠኛ በአቪየሽኑ ዘርፍ በተለየ መንገድ የራሱን የብዕር አሻራ ማኖር መቻሉ የዚህ ፅሁፋችን መነሻ ነው፡፡
#ቃለየሱስ በቀለ የውልደቱም ሆነ የእድገቱ መነሻ የምስራቅ ሸዋ አዳማ (ናዝሬት) ከተማ ናት፡፡ሀምሌ 18/1967 ዓ.ም በአዳማ ሀይለ ማሪያም ማሞ ሆስፒታል ቃለየሱስ የተባለ ብላቴና ከተፋፋመ ምጥ ውስጥ ወቅቱ አብዮታዊ ለውጥ ኢትዮጵያን በሚንጥበት በዚያ ጊዜ የለውጥ አየሩን እየማጉ ድምፃቸውን በማሰማት ይቺን ምድር ከተቀላቀሉት ጨቅላዎች አንዱ ሆኖ ተመዝግቦ በስሙ የልደት ካርድ ወጣለት፡፡
#ይህ ሰው ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ያለውን የትምህርት ጉዞውን ያሳለፈው በናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ነው፡፡ትምህርት ቤቱ ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎችን በግብረ ገብና በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት አንፆ በማብቃት ረገድ የተዋጣለት እንደነበር ቃለየሱስና አብረውት የተማሩት ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው፡፡
#በ1986 ዓ.ም ውጤታማ ሆኖ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅን ደጃፍ መርገጥ የቻለው ቃለየሱስ በኮሌጁ ሁለት ዓመታት በአካውንቲነግ ሙያ ተምሮ ቢያሳልፍም የሂሳብ ባለሙያ ሆኖ መቀጠሉ ስላልተዋጣልኝ ከልጅነቴ ጀምሮ አልመውና እፈልገው የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያ ለመቀላቀል መንከራተት የየዕለት ተግባሬ ሆነ ይላል፡፡ያኔምደፋር ብዕሩን ስሎ አሰሳውን የጀመረውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ አርቲክሎችን እየዘጋጀ ለዴይሊ-ሞኒተር እና ዘ-ሪፖርተር ጋዜጦች ማቅረብ መጀመሩ የምኞት ጭላንጭሉን ወገግ አደረገለት፡፡
#ጋዜጠኝነት
እንደምኞትና ፍላጎቱም መንከራተቱ ፍሬ አፍርቶ ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ በሆነው ፎርቹን ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ተቀጥሮ ማገልገል ጀመረ፡፡ምኞትና ህልሙ መሬት እንዲረግጡ ቀዳሚውን ዕድል ያመቻቸለት የፎርቹን ጋዜጣ መስራችና ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው አቶ ታምራት ሀይለ ጊዮርጊስ በቃለየሱስ የህይወት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡የጋዜጠኝነት ሀ ሁን ከማስቆጠር ጀምሮ ከዚያም ባሻገር አንደ ዓለም ባንክ፣የአሜሪካ ኤምባሲና ብሪቲሽ ካውንስል ያሉ ተቋማት በሚያዘጋጁት የሚዲያ ስልጠናዎች ላይ ተሳታፊ እንድሆን ዕድሉን ከማመቻቸት አልፎ ጠንካራ የጋዜጠኝነት ሰብዕናን እንድላበስ ያደረገኝ ባለውለታዬ ታምራት ነው ይላል ቃለየሱስ፡፡
#ወትሮም ለጋዜጠኝነት ታላቅ ጉጉት የነበረው ቃለየሱስ ዜና እንዴት ይፃፋል፣የዜና ግብዓቶች እንዴት ይሰበሰባሉ፣የዜና አስተማማኝ ምንጮችን እንዴት ማዳበር ይቻላል፣ፊቸር አርቲክል እንዴት ይፃፋል የሚሉና ሌሎችም ስልጠናዎችን አግኝቶ በብዕሩ መጠንከር የቻለው በፎርቹን ጋዜጣ ቆይታው እንደሆነ ያስታውሳል፡፡መች ይሄ ብቻ ከሀገር ውጪም በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት በኤር ባስ አማካኝነት ከበረራና የበረራ ደህንነት መረጃ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ስልጠናዎችን በስፋት በመውሰድ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ተቀብሏል፡፡
#ቃለየሱስ ባለውለታዎቼ ብዙ ናቸው ይላል፡፡የፎርቹን ጋዜጣ ኤዲተር የነበሩት መላኩ ደምሴና ይበቃል ጌታሁን በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ኮትኩተው ለውጤት አብቅተውኛል ካለ በኋላ በአጠቃላይ የፎርቹን ኤዲተሮች እኔን ጠፍጥፈው ሠርተውኛል ብል ማጋነን አይሆንም በሚል ያለፈበትን የጋዜጠኝነት ህይወት በአጭሩ ገልፆታል፡፡
#ከፎርቹን የሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ሪፖርተር ጋዜጣን በመቀላቀል ለ18 ዓመታት ከከፍተኛ ሪፖርተርነት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለው ቃለየሱስ ከሪፖርተር ጋዜጣ መሥራች አቶ አማረ አረጋዊ ጋር መሥራት መታደል ነው ይላል፡፡ከአቶ አማረ ጋዜጠኝነትን ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና ብሔራዊ ጥቅምን (National Interest)፣ደግነትንና ለሠራተኞቹ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም ለጋዜጠኞች የሙያ ነፃነት ሰጥቶ ሠርቶ የሚያሠራበትን መልካም ትምህርት ቀስሜያለሁ ብሏል፡፡በሪፖርተር ሳለሁም በርካታ የሙያ ማሻሻያዎችንና የአጭር ጊዜ ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገሮች አግኝቻለሁ በማለት ትናንቱን ያመሰግናል፡፡
#በዘ -ሪፖርተር እንግሊዝኛ ጋዜጣ የማቀርባቸው ዘገባዎቼ በአብዛኛው ቢዝነስ ተኮር ነበሩ የሚለው ቃለየሱስ በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድን ዘርፎች ላይ አተኩር ስለነበር፤በእነዚህ ዙሪያ በሚሠሩ የውጭ መጽሔቶች ለእኛም ጻፍልን የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ኤርላይን ፍሊት ማኔጅመንት፣ወርልድ ኤር ኒውስ፣ኤርላይን ኢኮኖሚክስ፣አፍሪካን ኤሮስፔስና ዓረቢያን ኤሮስፔስ፣አቪዬሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ፣አፍሪካን ቢዝነስ እና አፍሪካን ማይኒንግ ጆርናል ለተባሉ መጽሔቶች በፍሪላንስነት ለረዥም ዓመታት ሠርቻለሁ ይላል፡፡
እ.ኤ.አ.በ2008 በእንግሊዝ አገር በሚካሄድ “Best Aerospace Journalist of the Year” ሽልማት ታጭቼና ለንደን ተጋብዤ ዋናውን ሽልማት ባላሸንፍም፣"How Safe Are African Airlines?" በሚል ርዕስ በኤርላይን ፍሊት መጽሔት ላይ ያሳተምኩት ጽሑፍ ከ500 ለውድድር ከቀረቡ ጽሑፎች አምስቱ ምርጥ ውስጥ ለመግባት በመቻሉ፣ሰርተፊኬት ተበርክቶልኛል ብሏል፡፡
#በ2007 ዓ.ም. በትግራይ ሽመልባ የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ካምፕ ጉብኝት በማድረግ፣ ስለኤርትራዊያን ስደተኞች አሳዛኝ ሕይወት "The Woes of Eritrean Refugees” በሚል ርዕስ በዘ- ሪፖርተር ጋዜጣ ያሳተምኩት ሰፊ ጽሑፍ ጄኔቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ዋና መሥሪያ ቤት ተመርጦ፣ለረዥም ጊዜ በድረ ገጻቸው ላይ ለንባብ ተቀምጦ ነበር፡፡በሻሸመኔ መልካ ኦዳ ስለሚገኙ የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰቦች በቦታው ተገኝቼ የሠራሁት "The Plight of Rastafarians in Ethiopia" ዘገባ ከራስ ተፈሪያን ማኅረሰብ ምሥጋናና ዕውቅና አስገኝቶልኛል ይላል፡፡
ቃለየሱስን አንባቢያን የሚያውቁት ስለኢትዮጵያ አየር መንገድና በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ስለሚካሄዱ የማዕድንና የነዳጅ ፍለጋዎች ተከታታይ በርካታ ዜናዎችን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በመሥራቱ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ጋር የመሥራት ዕድሉን አግኝቷል፡፡
#የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ወቅትም እነሱን በማገዝ የተለያዩ ሥራዎችን ከውኗል፡፡ከእነዚህም መካከል “CNN, Aljazeera, SKY News, The Economics, National Geographic, Los Angeles Times, News Week, New York Times, Christian Science Monitor, Chicago Tribune…” እና ሌሎችም ከተሳተፈባቸው ውስጥ ይገኙበታል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2019 አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በተመለከተ ሲኤንኤን (CNN) በሠራቸው ዘገባዎች ላይ በረዳት ፕሮዲዩሰርነት የሠራ ሲሆን፣በወቅቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከሲኤንኤን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምሥጋና ተችሮታል፡፡በዘገባዎቹ ላይም ሙሉ ስሙን በማስፈር ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተውታል፡፡የአሜሪካው አልጄዚራ ኢንግሊሽ ቡድን ስለአውሮፕላን አደጋው ዶክመንተሪ ለማዘጋጀት አደጋው ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅትም፣አብሮ የአገር ውስጥ ፕሮዲዩሰር (Local Producer) ሆኖ ሠርቷል፡፡
መቼ ይሄ ብቻ ቃለየሱስ የ”Fault Lines” ፕሮግራም አዘጋጅ ከሆነው ጆሽ ረሺንግ (Josh Rushing) እና ፕሮዲዩሰሯ ካቢታ ቺኩሩ ጋር የሠሩት ዶክመንተሪ የተለያዩ አህጉሮችን የሸፈነ ሲሆን፣ለኤሚ አዋርድ ዕጩ ሆኖ ቀርቦም ነበር፡፡
#ከ18 ዓመታት አገልግሎት በኃላ እ.ኤ.አ. በ2020 ሪፖርተር ጋዜጣን ተሰናብቶ ኦሪጅንስ ሚዲያን በማቌቋምና ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት በመውሰድ፣‹‹ኢትዮ የንግድና የኢንቨስትመንት መድረክ››የተሰኘ ፕሮግራም በሳምንት ለሁለት ቀናት እያዘጋጀ ለሦስት ዓመታት ያህል አቅርቧል፡፡ኦሪጅንስ የሚል የጉዞ (Travel Magazine) ለማሳተም እየንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም፣በኮቪድ ወረርሽኝና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ለፍሬ ሊበቃለት እንዳልቻለ በቁጭት ያስታውሳል፡፡
#ገጠመኞቹ
#ቃለየሱስ በጋዜጠኝነት ሙያ የገጠሙኝ ፈተናዎች ብዙ ናቸው ይላል፡፡ሙያው ራሱ የሚያስደስት ነገር እንዳለው ሁሉ ብዙ የሚያስጨንቁና የሚከብዱ ነገሮችም አሉት።ጋዜጠኛው ከህሊናው ጋር ተሟግቶና ሚዛኑን ጠብቆ የሚሰራው ነገር አንዱ ሲሆን።ዘገባን ወቅት ጠብቆ መስራትም የራሱ ፈተና አለው። ሚዛናዊነቱ ሳይጓደልም እንኳን ስለአንድ ነገር ሲፃፍ ወይም ሲዘገብ በዜናው ምከንያት የሚጠቀሙ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ።
ወዲህ ደግሞ ጉዳቱም የዛን ያህል ነው።አንድ ሚዲያ በሚሰራው ዘገባ ባለስልጣንም ሆነ ካምፖኒ ሊሆን ይችላል የነበረውን አቅም ሊያጣ ይችላል።ይህ የሚዲያ ባህሪ ነው።ፈተናዎቹ የበዙ ቢሆኑም ጋዜጠኛው ሲፅፍ ሚዛናዊነት የተለበሰ መሆን አለበት ባይ ነው ቃለየሱስ።
#ቃለየሱስ ረጅም ዓመት የሠራው ህትመት ሚዲያ ላይ ነው።በአንድ ወቅት ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛ ጋር ወደ ትግራይ በማቅናት በኢትዮ ኤርትራ ስላለው ሁኔታ ለመዘገብ አመሩ፡፡ሽሬ አካባቢ ሽመልባ የሚባል የኤርትራ ስደተኞች ያሉበትን ስፍራ ጎብኝተውና አነጋግረዋቸው ወደ ሽራሮ ሄዱ፡፡የጦርነቱ ከተማ ወደነበረችው ባድመ ሄደውም ነዋሪዎችን፣አርሶ አደሮችና የከተማውን አስተዳደር ቃኝተውና ቃለመጠይቅ አድርገው ወደ ኤርትራ ድንበር ተጠጉ፡፡
#የኤርትራን መሬት ከወንዝ ባሻገር እያዩና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲያስጎበኟቸው የተቀበሩ ፈንጂዎች ስለነበሩ በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል አማካኝነት የፈንጂ ማስወገድ ስራው እየተሰራ ስለነበር የምንረግጠውን መንገድ ጠቆሙን ካለ በኋላ ቀይ ቀይ የተደረገባቸውን ድንጋዮች አሳይተውን ለእግር ፉካ የምትሆን ድንጋይ አሳዩን።ቀይ ምልክት የተደረገባቸውን ድንጋዮች ትተን ሌላ ከረገጥን ልንሞት እንደምንችል ነገሩን።በፈንጂ መሀከል በጭንቅና በዝግታ ያሳለፍንውን ምንጊዜም አልረሳውም ይላል ቃለየሱስ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ በአቬየሽን፣በነዳጅ እና ማዕድን ፍለጋ ስራዎች ዙሪያ ለመዘገብ ወደ ሱማሌ ክልል ይሄዳል፡፡ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ጋር የነበሩ ውጊያዎች ስለነበሩ አንድ ጊዜ አቦሌ ከሚባል በደቡብ ምዕራብ በሚገኝ ኩባንያ የነዳጅ ስራ ፍለጋ በሚያደረግ ካምፕ ላይ ታጣቂዎቹ ጥቃት ሰንዝረው 9 ቻይናውያን እና ወደ 65 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ህይወት ያልፋል።
ያንን ለመዘገብ ወደ አካባቢው የሄደው ቃለየሱስ ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛው ፖልስ አሎቤ ጋር ያለ እንቅልፍ ረጅም ቀናት በማሳለፋቸው በሀሩራማው ኦጋዴን ውስጥ ለረጅም ሰአታት ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በህክምና የነቃበትን ጊዜም ያስታውሳል።ቃለየሱስ ገጠመኞቹ የትየለሌ ናቸው፡፡በችሎት ዘገባ እንዲሁም ጋምቤላ ለዘገባ ሄዶ ያጋጠሙትንም ሁሌ እያስታወሰ ይገረምባቸዋል፡፡ በተለያዩ የአቪዬሽን ስብሰባዎችና እንዲሁም በአውሮፕላን አምራች ካምፓኒዎች በአካል እየተገኘም የሚያማልሉ ዘገባዎችን አስነብቧል፡፡
#ስለ ቃለየሱስ የታላላቅ ሰዎች ምስክርነቶች
"ቃለ ኢየሱስ በቀለ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በትጋት ከሠሩ ባለሙያዎች አንዱ ነው።" ይላል የሪፖርተር ጋዜጣ መስራች አማረ አረጋዊ። ምስክርነቱንም በመቀጠል፦
"... ቃለ ኢየሱስ በአቬሽን እና በማዕድን ዘገባዎች ላይ ያተኩር እንጁ የተሰጠውን ደስ ብሎት የሚሠራ ጋዜጠኛ ነው። የጋዜጠኝነት የሥነ ምግባር ደንብን አውቆ የሚተገብር ባለሙያ ነው። ፕሮፌሽናሊዝም እንዲሰፍን የሚታገል ጠንቃቃ ባለሙያ መሆኑን መመስከር እወዳለሁ።" በማለት ገልጿል
፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#የአቶ ግርማ ዋቄ ምስክርነት
#ቃለ ኢየሱስ በቀለን ረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ። ለአቬሽን የተለየ ፍቅር አለው። አለምአቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። ከዚያም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ፅሁፍ ያቀርባል።ብስለቱ ይደንቃል። ከሌሎች የስሚ ስሚ ሰምቶ ሳይሆን አንድን ጉዳይ ከስር ከመሠረቱ አውቆ የመዘገብ ችሎታውን አደንቅለታለሁ። ስለ አፍሪካ አየር መንገድ ፣ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በወጉ ተረድቶ ስለሚፅፍም ፅሑፉ ተነባቢ ለመሆን ችሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አቬሽን ጋዜጠኝነት በጥልቀት ሲሠሪ የማውቀው እርሱን ነው።ሌሎችም አሉ። እርሱ ግን ከፍ አድርጎ በልህቀት የሚሠራ በመሆኑ ይለያል።
ገና አየር መንገድ ሲመጣ መረጃ ለማግኘት ፍላጎት ያሳያል። ዕውነትን ለማግኘት ይጎለጉላል። አፍሪካም ውስጥ ፈጠን ብሎ አቬሽን ጋዜጠኝነት ላይ የገባ በመሆኑ ይህም ግንባር ቀደም ያደርገዋል። ቃለኢየሱስ ካለበት ካናዳ ሆኖ የአቬሽን ጋዜጠኝነትን ሙያ እንዲያሳድግ ምክሬን እለግሰዋለሁ።
አቶ ግርማ ዋቄ
የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
‹‹እኔ ቃለየሱስ በቀለን የማውቀው ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ፎርቹን ጋዜጣ አብረን ስንሠራ ጀምሮ ነው›› የሚለው የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው መላኩ ደምሴ ነው፡፡‹‹ከዚያም በኌላ ለ18 ዓመታት አብረን በሪፖርተር ጋዜጣ ሠርተናል፡፡ከጀማሪ ሪፖርተርነት አንስቶ እስከ አርታኢነት በዘለቀው የሥራ ጉዞው በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድናት ዘርፍ እጅግ በጣም በርካታ ዘገባዎችን የሠራ ሲሆን፣በሁሉም ሥራዎቹ አንጀት አርስ የሚባል ጋዜጠኛ ነው፡፡ጋዜጠኝነትን ከልቡ ከማፍቀሩ የተነሳ አብረው ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ጭምር የሙያውን ፍቅር የማጋባት ችሎታ ያለው ነው፡፡ቃለየሱስ ዘገባዎችን ሲሠራ የሁሉንም ባለጉዳዮች ደምፅ ከማካተት በተጨማሪ፣አንባቢያን ለርዕሰ ጉዳዩ ቅርበት እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስሜትን የተካነ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአቪዬሽን ዘገባ በግንባር ቀደምነትነት የሚጠቀስ ጋዜጠኛ ማነው ቢባል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኘው ቃለየሱስ ነው፡፡በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ አውሮፕላን አምራች ኩባንያዎችን፣አየር መንገዶችን፣በአቪዬሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ የሥራ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን ሳይቀር በተለያዩ አገሮች በማግኘት በሪፖርቶቹ ውስጥ ድምፃቸውን ከማካተቱም በላይ በቃለ ምልልስ ጭምር ለአንባቢያን ተደራሽ በማድረግም ወደር የለውም፡፡የአውሮፕላን አደጋዎች ሲያጋጥሙም ሆነ የተለዩ ክስተቶች ሲኖሩ ከሚሠራቸው ዘገባዎች በተጨማሪ፣በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማብራሪያ የሚፈለገው ቃለየሱስ ነው፡፡በውጭ ለሚዘጋጁና ቁጥራቸው ቀላል ለማይባል የአቪዬሽን መጽሔቶች በርካታ ዘገባዎችን በመሥራትም ታዋቂ ነው፡፡
‹‹በማዕድናት ዘርፍም ከካሉብ ነዳጅ የጀመረው የጋዜጠኝነት ህይወቱ በተለያዩ ክልሎች የሚደረጉ የነዳጅ፣የወርቅ፣የብረት፣የፖታሽ፣የታንታለም፣የኦፓልና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ ሥራዎችን በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታዎች፣በጂኦ ተርማል ፕሮጀክቶች፣ በፀሐይና በንፋስ ኃይል ማመንጫዎች፣በሲሚንቶና በሌሎች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችም ሰፋፊ ዘገባዎችን በማበርከት ስመጥር ሆኖ ዘልቌል፡፡በፖለቲካው መስክ ደግሞ በተለያዩ አገራዊ ምርጫዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በክልሎች ተሰማርቶ አመርቂ ሪፖርቶችን በማቅረብ ችሎታውን ማስመስከር የቻለ ነው፡፡ከሪፖርተር በገዛ ፈቃዱ ከተሰናበተ በኃላም በኤፍኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት ወስዶ ያቀርባቸው የነበሩ የቢዝነስ ፕሮግራሞቹ፣የቃለየሱስን ችሎታ ከጋዜጣ አንባቢያን ወደ ሬዲዮ አድማጮች በማዝለቅ ረገድ ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው ነበሩ፡፡
‹‹ቃለየሱስ ግልጽ፣ ቅን፣ ሰብዓዊነትን የሚያስቀድም፣ኃላፊነት የሚሰማው፣ በአስገራሚ ትውስታው የረሳናቸውን ጉዳዮች የማስታወስ ችሎታ ያለው፣በቀልድም ሆነ በቁምነገር የሚታወቅ፣ ከማንኛውም ሰው ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ምንጊዜም ዝግጁ የሆነ፣በተለይ በሪፖርተር የሥራ ባልደረቦቹ ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ምሥጉን ጋዜጠኛ ነው፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ሰፊና ጥልቅ ትንተናዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ብዙዎችም በዚህ መጠን ለነገሮች ትኩረት ሰጥቶ የማስረዳት ብቃቱን በአድናቆት የሚመሰክሩለት ነው፡፡እኔም ከሁለት አሠርት ዓመታት በላይ አብሬው ስለሠራሁ ችሎታውን በዚህ መጠን ስገልጽ በከፍተኛ ስሜት ሲሆን፣ይህንን ከመሰለ ብርቱና ታታሪ ጋዜጠኛ ጋር የመሥራት ዕድል በማግኘቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ›› በማለት መላኩ ምስክርነቱን አጠቃሏል፡፡
ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው ስለ ቃለየሱስ በሰጡት ምሥክርነት ‹‹እኔ እሱን ለአየር መንገዱ ልዩ እንደ ሆነ ሰው አየዋለሁ።በጣም ትሁት፣አዳማጭ የሆነ ሰው ነው።ከየት እንዳመጣው ባላውቅም ልዩ የሆነ የኢንግሊዘኛ ፀሀፊ ነበር።በሁለት ምክንያት የሱን ፅሁፍ አነብ ነበር፡፡አንዱ በፅሁፉ ለመደሰትና እንደ ግጥም ስለምወደው ነው።ሌላው ከእውቀቱ ወይም አንብቦም ይሁን ባላውቅም የፅሁፎቹ ይዘት በሚያውቀው ነገር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው።በዚህም በጣም አበረታታዋለሁ።
‹‹ከተዋወቅን 15 ዓመታት ሆኖናል።በውጪ ህትመቶች ላይ የሚያወጣቸው ስራዎች ቃለየሱስ ብሎ ስሙ ይገለፅ ይሆናል እንጂ ማንም ነጭ የሚፅፈው አይነት ፅሁፍ ነው።የፅሁፉ ይዘትና አያያዝ ደረጃውን የጠበቀ ነው።የሚፅፍባቸው መፅሄቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ትላልቅ ናቸው።ነገር ግን ደረጃቸውን ጠብቀዋል የሚባሉትም አንዳንዴ ትርኪምርኪ ሲፅፉም ይታያል።ግን የሱ ፅሁፍ በጣም የሚያኮራ ነው።ሌላው ዜግነቱን የሚወድ ሰው ነው።ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ በቦታው ካሉት ህዝብ ግንኙነቶች እሱ ብዙ የሰራ ይመስለኛል።እውቅናና ሽልማት ሊሰጠው በርታ ሊባል የሚገባው ልጅ ነው።ወገቡን ይዞ ነበር ለአየር መንገዱ ይሰራ የነበረው።አሁንም ቢሆን ባለበት ሆኖ ለአየርመንገዱ ነገሮችን መስመር የሚያሲዝ ሰው ነው››ብለዋል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨
የቀድሞ የሲቪል አቬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው ‹‹ከተዋወቅን ከ7 ዓመት በላይ ይሆነናል።እኔ ከማቃቸው የሚዲያ ሰዎች በጋዜጠኝነት የሱን ያህል ብዙም አቬሽን ዘርፉ ላይ ገብቶ እያንዳንዱን ነገር አይቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን የግል ኦፕሬተሮቹም ጋር እንደሱ የሚፅፍ አላየሁም።እሱ ነው የተሻለ ጠይቆ አንብቦ ተረድቶ አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚጥረው።በዛ ወቅት ቃለ እየሱስ ጥሩ ዘጋቢ ነበር።ብዙ መፅሄቶች ላይ ይሳተፋል አንዳንድ አለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሄዳል። በኢትዮጵያ አየርመንገድና በሲቪል አቬየሽን ላይ የተለየ እውቀት ያለው ነው።ምክንያቱም በየእለቱ ስለሚከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አቬየሽን ኢንዱስትሪ በደንብ ያውቀው ነበርና ነው።
‹‹አቬየሽን ኢንዱስትሪው በእነዚህ መፅሄቶች በብዙ መንገድ ይጠቀማል።ህብረተሰቡ አቬየሽኑም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን ከማስተዋወቁ በላይ ምን ላይ እንዳለ እና በተለየ አካል እንዲሰራለት ትክክለኛነቱን ይረጋገጣል።እንዲሁም ምን ያህል የግል ኦፕሬተሮች ምን ያህል በኢኮኖሚው ይሳተፋሉ የሚለውንም ለህብረተሰቡም ለመንግስትም መረጃ ይሰጣል።ስራዎቹ ለብዙ ነገሮች የመረጃ ምንጮች ሆነው ያገለግላሉ ።
‹‹ቃለእየሱስ በዚያ ወቅት የሚያደርገው የኢትዮጵያን አቬየሽን ኢንዱስትሪ ከሌላው እያነፃፀረ በሚያውቀው ልክ ለህብረተሰቡ ሙሉ መረጃ ይሰጣል።ለግል ኦፕሬተሮችም ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ግብዐት የሚሆኑ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል።በተዘዋዋሪም ያስተዋውቃል።እውነተኛ መረጃ ሲያቀርብ ሰው ስለ አቬየሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እውቀት ያዳብራል።አብዛኛው ሰው ስለ ግል ኦፕሬተር አያውቅም አውሮፕላን አላቸው ወይ ? ብሎ የሚጠይቅም ብዙ ሰው ነው።በዚህ ጉዳይ ላይ በብዛት የሚሰራው ቃለእየሱስ ነበር››ብለዋል፡፡
‹‹በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ የቃለየሱስ አስተዋፅኦ ትልቅ ነው።››ብለው ምስክርነታቸውን መስጠት የጀመሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡‹‹ቃለየሱስና እኔ ለረጅም ጊዜ እንተዋወቃለን በ«Reporter» ጋዜጣ ሲሰራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜናዎችንና እድገቶችን ይዘግብ ነበር።በቀጣይ የአቪዬሽን ዘርፍ ላይ ጥልቅ ፍላጎት አሳየ፤እኛም ከIATA ጋር እንዲገናኝ አደረግነው፣በተለይም በየዓመቱ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚካሄዱ የIATA አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤዎች (AGM) ላይ የፕሬስ ኮንፈረንሶች ላይ ይሳተፍ ነበር።
‹‹በአፍሪካ አየር እና አቪየሽን (African Aerospace and Aviation) መጽሔት እና በሌሎች ከአቪየሽን ጋር የተያያዙ መጽሔቶች ላይ ጽሁፎችን ይጽፍ ነበር።በአጋርነትም ብዙ ፕሮጀክቶችን አከናውነናል። እኔም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቦርድ ሊቀመንበር በነበርኩበት ሰዓት፣የራሱን የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት እንዲጀምር ወይም እንዲያስብበት ሀሣብ አቀርብለት ነበር፤እርሱም ይህን ሀሳብ በአዎንታ ይመልከተው ነበር።
‹‹በአጠቃላይ፣ ይህ ዘርፍ እስከዛሬም በቂ የሚዲያ ሽፋንና የማስተዋወቂያ መድረክ ስላልነበረው፣ ቃለየሱስ ይህን ክፍተት ልብ ብሎ በማጤን በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ልማት ላይ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።በእኔ አመለካከት፣ያበረከተው አስተዋፅኦ አስደናቂ ነው፣ለሥራውም እውቅናና ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል››ብለዋል፡፡
ሲጠቃለል ከ15 አመት በላይ በአለም አቀፍ የአቪየሽን ስብሰባዎችን በአሜሪካ፣አውሮፓ፣አፍሪካ፣ መካከሉኛው ምስራቅ እና ኤሽያ ተሳትፌያለሁ 36 ሃገሮችንም የማየት እድል ገጥሞኛል የሚለው የአቪየሺን ባለወርቃማ ብዕሩ ቃለየሱስ በቀለ እ.ኤ.አ.ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ ኑሮውን በካናዳ ያደረገ ሲሆን፤ለአፍሪካ ኤሮስፔስና አቪየሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ በፍሪላንስነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

💰የትራምፕ አዲሱ የ2,000 ዶላር ስጦታ ወይስ የፖለቲካ ተስፋ?
📌ዕቅዱ ሲፈተሽ
#ethiopia | ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአሜሪካውያን "የታሪፍ ትርፍ ድርሻ" (Tariff Dividend) በሚል ስያሜ ለእያንዳንዱ ዜጋ 2,000 ዶላር ለመስጠት ማቀዳቸውን መግለጻቸው መነጋገሪያ ሆኗል። ይሁንና ይህ ተስፋ ምን ያህል ወደ መሬት ይወርዳል? ዝርዝሩን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
📌 የዕቅዱ ዋና ዋና ነጥቦች
* ምንጩ ከየት ነው? ክፍያው የሚፈጸመው ከውጭ ሀገራት (በተለይም ከቻይና) በሚገቡ ምርቶች ላይ ከሚጣለው ከፍተኛ ታሪፍ ወይም ቀረጥ በሚሰበሰብ ገቢ እንደሆነ ተገልጿል።
* መቼ ይጀምራል? ፕሬዚዳንቱ እንደጠቆሙት ከሆነ ክፍያው በ2026 አጋማሽ ወይም ማብቂያ ላይ ለዜጎች ሊደርስ ይችላል።
* ዓላማው፡ የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና የአሜሪካን ምርት ለማበረታታት የታለመ "የኢኮኖሚ ማነቃቂያ" ተደርጎ ተወስዷል።
⚠️ ሊታለፉ የማይገቡ "ግን"ዎች
ምንም እንኳን ዜናው ለብዙዎች አስደሳች ቢሆንም፣ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ትልልቅ መሰናክሎች ይጠብቁታል።
* የኮንግረስ ይሁንታ፡ ፕሬዚዳንቱ በራሳቸው ፍቃድ ገንዘቡን ማከፋፈል አይችሉም። ጉዳዩ በሕግ አውጪው ምክር ቤት (Congress) መጽደቅ አለበት። እስካሁን ግን ምንም ዓይነት የጸደቀ ሕግ የለም።
* የባለሙያዎች ስጋት፡ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች "ሂሳቡ አይገጥምም" ይላሉ። ከታሪፍ የሚሰበሰበው ገቢ፣ ለእያንዳንዱ አሜሪካዊ 2,000 ዶላር ለመስጠት ከሚያስፈልገው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ጋር ሲነጻጸር እጅግ አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ።
* የIRS ዝምታ፡ የአሜሪካ የገቢዎች አገልግሎት (IRS) እስካሁን ስለ ክፍያው ሂደትም ሆነ ስለ ተቆረጠ ቀን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።
ባጭሩ፡ ክፍያው በአሁኑ ወቅት "ዕቅድ" ወይም "ተስፋ" እንጂ ገና የጸደቀ ውሳኔ አይደለም። ስለዚህ አሜሪካውያን ገንዘቡ እጃቸው እስኪገባ ድረስ መጠበቅ ይኖርባቸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #trump2026 #tariffdividend #economics #usnews #menaheria #thiqah

6 months ago
የቁጥሮች ፍልሚያና የኢኮኖሚው ሕልውና፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሪፖርት ትንተና
ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የብሔራዊ ባንክ የግማሽ ዓመት ሪፖርት፣ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕበል ውስጥ ላለችው ኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም አለው። ሪፖርቱ የተሳካ የፖሊሲ ውጤቶችን ቢያሳይም፣ ዘላቂነታቸው ላይ ግን ከባድ ስራ ይጠብቃል።
1. የዋጋ ግሽበት ስባሪ፡ የፍሪድማን ድል ወይስ የኬይንስ ስጋት?
የዋጋ ግሽበት ወደ 9.7% ዝቅ ማለቱ፣ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ አቅርቦትን ለመቆጣጠር የወሰደው የቁጥጥር እርምጃ (Tight Monetary Policy) ውጤት መሆኑን ያሳያል።
የፖሊሲው ስኬት፡ የሚልተን ፍሪድማን የገንዘብ መጠን ቀመር MV = PQ እንደሚያሳየው፣ የገንዘብ ስርጭትን መገደብ ዋጋን ያረጋጋል።
ስጋቱ፡ ግሽበቱ የቀነሰው በምርት ብዛት ሳይሆን፣ በህዝቡ የመግዛት አቅም መዳከም (Low Consumption) ከሆነ፣ ይህ የኢኮኖሚ መቀዝቀዝን ሊያስከትል ይችላል። የኬይንስ ስጋትም ይኸው ነው—ያለ ፍጆታ እድገት የለም።
2. የሐዋላው “ወርቃማ ዝናብ” እና የሪካርዶ ስጋት
የ4.6 ቢሊዮን ዶላር ሐዋላ (36.5% እድገት) ትልቅ የምስራች ነው። ይህ የሚያሳየው የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ በጥቁር ገበያና በህጋዊው መስመር መካከል ያለውን ግንብ ማፍረሱን ነው።
ሚዛኑ፡ አዳም ስሚዝ እንዳለው ሰዎች በህጋዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ማበረታቻ (Incentive) መፍጠር ተችሏል።
አደጋው፡ በዴቪድ ሪካርዶ እይታ ግን ሀገር መቆም ያለባት በወጪ ንግድ (Export) እንጂ በስጦታ አይደለም። ሐዋላ እንደማይለዋወጥ ዝናብ ነው፤ ነገ በዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ምክንያት ቢቋረጥ የውጭ ምንዛሪ ክምችቱ አደጋ ላይ ይወድቃል።
3. የብድር ስርጭት እና የፋይናንስ ጤናማነት
ለግሉ ዘርፍ የተሰጠው ብድር 94.5% መድረሱ መንግስት ከንግድ ባንኮች ብድር መውሰዱን ቀንሶ ለግል ባለሀብቱ እድል መስጠቱን ያሳያል። ሆኖም የሐይማን ሚንስኪ "የፋይናንስ አለመረጋጋት መላምት" (Financial Instability Hypothesis) እዚህ ጋር ጥንቃቄን ይጠይቃል፦
የብድር አረፋ ስጋት፡ ባንኮች ብድርን በ 45% እድገት ሲያሰራጩ፣ የብድሩ ጥራት ካልተጠበቀ ወደፊት የባንኮች ቀውስ ሊፈጠር ይችላል።
የምርት አለመመጣጠን፡ ብድሩ ወደ ማምረቻ ዘርፍ ሳይሆን ወደ ሪል-እስቴት ግምት (Speculation) ካዘነበለ፣ ውጤቱ ዘላቂ እድገት ሳይሆን የዋጋ ግሽበት አዙሪት ይሆናል።
ቀይ መብራት፡ የማይመለሱ ብድሮች (NPL) መጠን መጨመር የፋይናንስ ዘርፉን ጤናማነት አደጋ ላይ ይጥላል።
4. የዲጂታል ክፍያ አብዮት
የ 14.56 ትሪሊዮን ብር የዲጂታል ዝውውር የጆሴፍ ሹምፔተርን “Creative Destruction” ሃሳብ በግልጽ ያሳያል።
ቴክኖሎጂው አሮጌውን የጥሬ ገንዘብ አያያዝ እየቀየረው ነው። ይህ ለታክስ አሰባሰብ እና ለገንዘብ ቁጥጥር ቢረዳም፣ የሳይበር ደህንነት ስጋት እና የገንዘብ ዝውውር ፍጥነት ከምርት እድገት ጋር ካልተጣጣመ አዲስ ግሽበት ሊቀሰቅስ ይችላል።
5. መዋቅራዊ መፍትሄዎች፡ ከሪፖርት ወደ ተግባር
ለቀጣይ ጊዜያት ሚዛናዊ እድገት ለማምጣት የሚከተሉት ነጥቦች ወሳኝ ናቸው፡
የምርት አብዮት (Supply-Side Economics): በፖሊሲ የገንዘብ ዝውውርን ከመቀነስ ባለፈ፣ ግብርናና ኢንዱስትሪው ላይ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ።
የሐዋላ ገቢን ወደ ኢንቨስትመንት መቀየር: ሐዋላው ለፍጆታ ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ ፕሮጀክቶች እንዲውል የዲያስፖራ ቦንድና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስፋፋት።
የፖሊሲ ቅንጅት: ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጥጥር ሲያደርግ፣ የፌዴራል መንግስት ደግሞ የበጀት ጉድለቱን በመቀነስ የፖሊሲ ቅራኔ እንዳይፈጠር ማረጋገጥ አለባቸው።
ማጠቃለያ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሁን ባለበት ሁኔታ እንደ ደቡብ ኮሪያ ወደ ምርታማነት የመሸጋገር ወይም እንደ ናይጄሪያ በሪፖርት አሃዞች ተታሎ ወደ እዳ አዙሪት የመግባት አጣጥ ላይ ነው። የብሔራዊ ባንክ ስኬት እውነተኛ የሚሆነው በምክር ቤት ቀርቦ ሲመሰገን ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ እናቶች በገበያ ውስጥ የኑሮ ውድነት ሳይፈትናቸው በሰላም ሲሸምቱ ነው።

🇷🇺 ''የግሪንላንድ ዋጋ 1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነው!" ፑቲን
#ethiopia | የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ አሜሪካ ግሪንላንድን ለመቆጣጠር ያላትን ፍላጎት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ያልተጠበቀ እና ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። ፑቲን የትራምፕን ዕቅድ እንደማይቃወሙ በመጠቆም ዴንማርክን ክፉኛ ተችተዋል።
🔍 ዋና ዋና ነጥቦች፦
* "የእኛ ጭንቀት አይደለም"፦ ፑቲን በሩሲያ የፀጥታ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ "በግሪንላንድ የሚፈፀም ማንኛውም ጉዳይ የእኛ ጭንቀት አይደለም" በማለት ሩሲያ በጉዳዩ ጣልቃ እንደማትገባ ገልጸዋል።
* ዴንማርክ ላይ የተሰነዘረ ትችት፦ ዴንማርክ ግሪንላንድን የያዘችበትን መንገድ "እንደ ቅኝ ግዛት እና ጭካኔ የተሞላበት" ሲሉ ኮንነዋል። ይህ ትችት ዴንማርክ ለዩክሬን የምታደርገውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ተከትሎ የመጣ የበቀል አስተያየት ይመስላል።
* የዋጋ ግምት፦ ሩሲያ በ1867 አላስካን ለአሜሪካ በ7.2 ሚሊዮን ዶላር መሸጧን ያስታወሱት ፑቲን፤ ግሪንላንድም ዛሬ ብትሸጥ ዋጋዋ 1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ብቻ እንደሆነ በፌዝ መልክ ተናግረዋል።
* የአውሮፓ ስጋት፦ የትራምፕ ግሪንላንድን የመቆጣጠር ግፊት በአሜሪካ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያሻከረው ይገኛል።
💡 ለምን አሁን?
የፑቲን ንግግር ዴንማርክን ለማሳጣት እና አሜሪካ ከአውሮፓ አጋሮቿ ጋር ያላትን ልዩነት ይበልጥ ለማስፋት ያለመ ስትራቴጂ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#russia #putin #greenland #donaldtrump #denmark #worldpolitics #usa #breakingnews #ethiopia #economics

Sponsored by
Surafel
7 months ago
የአይኤምኤፍ 261 ሚሊዮን ዶላሩ ብድር እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እጣ ፋንታ
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የ261 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር እንዲለቀቅ መወሰኑን በይፋ አስታውቋል። ይህ ውሳኔ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ሥር አራተኛው የግምገማ ምዕራፍ መጠናቀቁን የሚያበስር ሲሆን፣ ኢትዮጵያ እስካሁን ከድርጅቱ ያገኘችውን ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ወደ 2.183 ቢሊዮን ዶላር አሳድጎታል።
ሆኖም ይህ የገንዘብ መርፌ ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ህመም ፈውስ ይሆን ወይስ የዕዳ አዙሪት? የሚለው ጥያቄ የሁለቱንም ወገን መከራከሪያዎች በሚዛናዊነት መመልከትን ይጠይቃል።
1. የኢኮኖሚ ንድፈ-ሐሳቦች ግብግብ
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ በሁለት ተቃራኒ የኢኮኖሚ ንድፈ-ሐሳቦች መካከል የሚደረግ ፍልሚያ ይመስላል፦
ኒዮ-ክላሲካል ኢኮኖሚክስ (Neoclassical Economics): አይኤምኤፍ የሚመራበት ይህ ንድፈ-ሐሳብ፣ የገበያ ኃይሎች (ፍላጎትና አቅርቦት) ያለ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ዋጋን እንዲወስኑ ያሳስባል። "የማይታየው እጅ" (The Invisible Hand) ገበያውን ያስተካክላል የሚለው ይህ አስተሳሰብ፣ የብር ዋጋ በገበያ እንዲወሰን ማድረጉን ይደግፋል።
የስትራቴጂክ ንግድ ቲዮሪ (Strategic Trade Theory): ይህ ደግሞ ታዳጊ ሀገራት የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎቻቸው እስኪጠነክሩ ድረስ መንግሥት ጥበቃና ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል ይላል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ስትከተለው የነበረው "ልማታዊ መንግሥት" ፍልስፍና ከዚህ ይመነጫል። አሁን ላይ ሀገሪቱ ከለጋሽ ድርጅቶች ጫና የተነሳ ከዚህ ፍልስፍና ወጥታ ወደ ነፃ ገበያ መግባቷ "የመዋቅር ሽግግር ድንጋጤ" (Structural Adjustment Shock) ፈጥሮባታል።
2. የአራት ሀገራት ተሞክሮ፡ ስኬት፣ ውድቀት እና ትምህርት
አይኤምኤፍ በሌሎች ሀገራት የነበረው ሚና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ሲታይ ሁለት መልክ አለው፦
ደቡብ ኮሪያ (የስኬት ተምሳሌት): በ1997 የኤዥያ የፋይናንስ ቀውስ ወቅት ኮሪያ ከአይኤምኤፍ ጋር መራራ ስምምነት አድርጋ ነበር። ሀገሪቱ መዋቅራዊ ለውጦችን በብቃት በመተግበሯ እና ትኩረቷን በኤክስፖርት ላይ በማድረጓ በአጭር ጊዜ ውስጥ አገግማለች። ይሁን እንጂ ስኬቷ የመጣው በጠንካራ የሀገር ውስጥ ምርታማነት እንጂ በብድሩ ብቻ አልነበረም።
አርጀንቲና (የዕዳ አዙሪት): አርጀንቲና ከአይኤምኤፍ ጋር ከአርባ ጊዜ በላይ የብድር ስምምነት አድርጋለች። ሆኖም ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና ሙስና በታከለበት ሁኔታ የሚወሰድ ብድር ሀገሪቱን ለከፍተኛ የዋጋ ግሽበት (Hyperinflation) ዳርጓታል። ይህ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው።
ግብፅ (የመካከለኛ መንገድ): ግብፅ በቅርቡ ያደረገችው የገንዘብ ምንዛሬ ማሻሻያ የውጭ ኢንቨስትመንትን ቢያነቃቃም፣ የኑሮ ውድነቱ ግን ማኅበራዊ ቀውስ አስከትሏል። ይህ ተሞክሮ "ኢኮኖሚው ሲያገግም ሕዝቡ ሊቆስል ይችላል" የሚለውን እውነታ ያሳያል።
ጋና (የቅርብ ጊዜ ፈተና): ጋና በከፍተኛ የዕዳ ጫና ምክንያት ብድር መክፈል አቁማ ነበር። ከአይኤምኤፍ ጋር ያደረገችው ስምምነት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማረጋጋት ቢረዳም፣ ዜጎቿ ግን አሁንም በከባድ የበጀት ቅነሳ ውስጥ ይገኛሉ።
3. የባለሙያዎች እይታ እና የዋጋ ግሽበት እውነታ
ለጉዳዩ ሚዛናዊ ምላሽ ለመስጠት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ሁለት ተቃራኒ አስተያየቶች ከወቅታዊ ዳታ ጋር እንመልከት፦
የደጋፊዎች እይታ: "ይህ ብድር ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት እንድትቀላቀል የሚያስችል ድልድይ ነው። የውጭ ምንዛሬ ተመን መስተካከሉ 'የገበያ መዛባትን' ያስቀራል፤ ይህም የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲመጣ ያደርጋል።"
የተቺዎች እይታ: "ምርታማነት ባልጨመረበት ሁኔታ የገንዘብ ዋጋን ማርከስ የዋጋ ግሽበትን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ነው። በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት (Inflation) አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ መቀጠሉ የዚሁ ማረጋገጫ ነው።"
የቅርብ ጊዜ ዳታ፦ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መረጃ እንደሚጠቁመው፣ የምግብ ዋጋ ግሽበት አሁንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። የብር ዋጋ መርከስን ተከትሎ የሚመጡት የነዳጅ እና የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ መጨመር የመግዛት አቅምን በእጅጉ እየተፈታተኑት ነው።
4. ምርታማነት እና ሰላም፦ ያልተመለሱ ጥያቄዎች
የአይኤምኤፍ ፕሮግራም ስኬታማ የሚሆነው ሀገራዊ ምርታማነት ሲጨምር ብቻ ነው።
የአቅርቦት ማነቆ: የገንዘብ ዋጋ መቀነሱ ኤክስፖርትን በጣም ያበረታታል ተብሎ ቢታሰብም፣ በሀገሪቱ ሰላም ባለመኖሩ ምክንያት አድገቶች ቢኖሩም ምርታማነት በታሰበው ያክል ሊጓዝ አልቻለም ። አቅርቦት ሳይጨምር የገንዘብ ዋጋ መቀነሱ ደግሞ የዋጋ ግሽበቱን አባብሶታል።
የዕዳ ሸክም: የሚወሰደው ብድር በምርት ላይ ካልዋለ፣ ሀገሪቱን ወደ ባሰ የዕዳ አዙሪት ውስጥ የመክተት ዕድል አለው።
ማጠቃለያ፦ ወደፊት ምን ይጠበቃል?
የ261 ሚሊዮን ዶላሩ ብድር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ "የመተንፈሻ ቱቦ" ነው። ሀገሪቱን ከውጭ ክፍያ እዳ (Default) ታድጓታል። ሆኖም ዘላቂ ስኬት የሚመጣው ከብድር ባለፈ ሀገራዊ ሰላም ሲረጋገጥ፣ ሙስና ሲቀንስ እና የአገር በቀል ምርታማነት ሲጨምር ብቻ ነው። የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፋንታ የሚወሰነው በዚህ መራራ የሪፎርም ጉዞ እና በማኅበራዊ መረጋጋት መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅ ላይ ነው።

9 months ago
መልህቁን የሚደግፉ ሌሎች ህልዩቶች
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር ጥያቄን ለመደገፍ ከዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዮት አንፃር ከዚህ በፊት አጭር ሀሳብ ማቅረቤ ይታወሳል።ሀሳቡን ይበልጥ ለማዳበር እና በተለይም በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ምንም ግንዛቤ ሌላቸው ሰዎች ይረዳ ዘንድ ሌሎች ንድፈ-ሐቦች ምን ይላሉ የሚለውን ለመመልከት የተለያዩ የጥናት እና ምርምር ወረቀቶችን እና (Article Review) ለማድረግ ሞክሪያለሁ፤እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪዩን አለምአቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ እንደ አጠና ሰው በተጨማሪም የተለያዩ ከፍተኛ ሥልጠናዎችን፤አለምአቀፍ ጉዳዬችን እንደ ሚከታተል ባለሙያ በድጋሚ ሌሎች መልህቁን ሊደጋፉ የሚችሉ ህልዩቶችን ተመልክቻለሁ ።
እንደ አንድ ዜጋ የሀገር እና የብሔራዊ ጥቅም (National Interest )ጉዳይ ሲነሳ በምንም ሁኔታ እና አስተሳሰብ ወደ ጎን የሚተው ነገር እንዳልሆነ አምናለሁ።ይህ አጀንዳ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አማካኝነት በመንግስት ደረጃ መነሳቱ በዘላቂነት አጥተነው(በሆነ ዘመን) የነበረውን እድል እና ባለቤትነት በትውልድ ቅብብሎሽ መሳካቱ እንደማይቀር በማመን(በኢትዮጵያ ልጆች፥ለታላቁ ህዳሴ ግድብን በተባበረ ክንድ ገንብተን እንደጨረስነው ሁሉ)ይህም የዚህ ዘመን ትውልድ አሻራ የሚጠይቅ እንደመሆኑ ታሪክ ስንመረምር ደግሞ የጥንት ስልጣኔዎች ከአክሱም(አዱሊስ)ጀምሮ የኢትዮጵያ መርከቦች በቀይ ባህርና ወደብ ናኝተውበታል።እኛ የጥንት ህዝቦች እና የአባቶቻችን ልጆች ነን ለዚህም እንደ ሀገር ልጅነት በጋራ እና በትብብር በመቆም መስራት ይጠበቅብናል።
በዛሬው አጭር ሀሳቤ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች በማቅረብ ይበልጥ መረዳትን ለማሳደግ እና በተለይ በአንዳንድ የመረጃ ምንጮች የሚተላለፉ ጥሬ መረጃዎች በእውቀት እና በግንዛቤ ላይ ያልተመሰረቱ እና የተሳሳቱ መሆኑን ባደረኩት ቅኝት ለመረዳት ችያለሁ።
ዛሬ የምንመለከተው የጂኦ-ፖለቲካዊ እና የጂኦ-ኢኮኖሚያዊ ህልዮቶች መሰረት በማድረግ እነዚህ ንድፈ-ሐሳቦች መልካምድራዊ አቀማመጥ እና የኢኮኖሚ ጥቅሞች በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸውን ሚና መሰረት በማድረግ እንፈትሻለን:-( ሌሎች በመስኩ የምርምር ስራ የሰራችሁ ሊቃውንት ሀሳባችሁን ወደ መድረክ በልዩ ልዩ አማራጮች በማቅረብ ለሀገር እና ለብሔራዊ ጥቅም የሚደረጉ ጥረቶችን በእውቀትና ሳይንስ ተኮር በሆኑ አስረጂዎች በማቅረብ ለሀገር እና ለህዝብ ያላችሁን አጋርነት አሳዩ)። (የተረዳነውን እናስረዳ)
🔴.የባህር ኃይል ፅንሰ-ሀሳብ (Sea Power Theory/ Mahanian Thought):-ይህ ንድፈ-ሀሳብ የሚያጠነጥነው የሀገር ልማትናብልጽግ እንዲሁም ኃይል የሚወሰነው በባህር ላይ ባለ ቁጥጥር እና አጠቃቀም ላይ ነው ብሎ ያምናል።የባህር መንገድን መቆጣጠር እና ነፃ የባህር ላይ ንግድ ማካሄድ ለብሔራዊ ደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ወሳኝ መሆኑን ያስረዳል።ይህ ንድፈ ሀሳብ ለጥያቄው በተለያ መንገድ ድጋፍ ይሰጣል።ኢትዮጵያ ለንግድ እና ለሌሎች አገልግሎቶች ቀይ ባህርን መድረስ፣መጋራት መፈለጓ፣የባህር በር እንደ "ህልውና ጉዳይ"(Existential Matter) መታየቱ፣ይህ ንድፈ-ሐሳብ እንደሚደግፈው፣አንድ ሀገር ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ለመፍጠር ተሰሚነትን ለማሳደግ የባህር ላይ አቅም (Sea Power) ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል።
🔴.የሪምላንድ ፅንሰ-ሀሳብ (Rimland Theory - Spykman):-የዚህ ህልዮት ዋና ሀሳብ በአህጉር ዳርቻ የባህር ጠረፎችን(ሪምላንድን) የሚቆጣጠር ሀይል የአለምን እጣ ፈንታ ይወስናል የሚል እምነት አለው።የባህር ዳርቻ አካባቢዎች በየብስ እና በባህር ኃይሎች መካከል ድልድይ በመሆናቸው ስልታዊ ጠቀሜታ አላቸው የሚል እይታ አለው።አስረጅ ሲያቀርብ ቀይ ባህር ከአፍሪካ ቀንድ፣ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከእስያ ጋር የሚያገናኝ "ወሳኝ የንግድ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ መስመር"(Chokepoint)በመሆኑ፣በዚያ አካባቢ ተሳትፎና እንቅስቃሴ ማድረጉ የኢትዮጵያን አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሚና ለማሳደግ ስልታዊ ጠቀሜታ አለው።
🔴.ጂኦ-ኢኮኖሚክስ(Geo-economics):-የዚህ ንድፈ ሀሳብ መነሻ የሀገሮች ተሰሚነት፣ስልጣንና ግንኙነት በዋነኛነት የሚወሰነው በኢኮኖሚ አቅማቸው እና ንግድን በሚጠቀሙበት መንገድ ነው።የንግድ መስመሮችን እና የገበያ ተደራሽነትን መቆጣጠር ከወታደራዊ ኃይል የበለጠ ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል ይላል።ለኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር አቅርቦት ጥያቄን ሲያስረዳ ቀይ ባህር በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ያለው ወሳኝ ሚና (As the gateway to the Suez Canal and Bab el-Mandab)፣ለኢትዮጵያ ነፃ የባህር በር ማግኘቷ የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ወደ ውጭ መላክን ለማሳደግ እና በሌሎች ሀገሮች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ወሳኝ ነው።
🔴.ዓለም አቀፍ የህግ እና ትብብር ንድፈ-ሐሳቦች:-እነዚህ ንድፈ-ሐሳቦች ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ትብብር እና የህግ ማዕቀፎችን አስፈላጊነት ያመለክታሉ።የዓለም አቀፍ ሊብራሊዝም እና ተቋማዊነት (International Liberalism and Institutionalism)ሀገሮች በጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በመመርኮዝ በትብብር (Cooperation) እና በዓለም አቀፍ ተቋማት (እንደ የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ኮንቬንሽን-UNCLOS) አማካኝነት ግጭቶችን በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነትን ማስፈን ይችላሉ የሚል እይታ አለው ።
🔴.የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ስምምነት (UNCLOS) እና የባህር-በር የሌላቸው ሀገራት መብቶች:-የዚህ ህልዮት ዋና ሀሳብ (በህጉ ላይ የተመሠረተ አቀራረብ) ይህ ኮንቬንሽን (A landlocked Country) የተዘጉ ወይም ወደብ አልባ ሀገራት ወደ ባህር የመድረስ መብት (Right of Access to and from the Sea) እና በጎረቤት ሀገራት በኩል በነጻ የመጓጓዝ መብት (Freedom of Transit) እንዳላቸው በግልጽ ይደነግጋል (አንቀጽ 125-127)። ይህ መርህ ታዲያ የኢትዮጵያን ወደብ የመጠቀም ፍላጎት "በዓለም አቀፍ ህግ የተደገፈ" መሆኑን ያረጋግጣል።
✍️እንደ መውጫ ⁉️:-
የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ "የባህር ኃይል እና የጂኦ-ኢኮኖሚክስ" ንድፈ-ሐሳቦች በሚደግፉት መሠረት ለብሔራዊ ጥቅም እና ህልውና ወሳኝ ነው።በተመሳሳይ ጊዜ፣ "የሊብራሊዝም እና ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች" (እንደ UNCLOS) ይህንን ጥያቄ በሰላማዊ እና በትብብር መንገድ ለመፍታት መነሻ መሆን እንደሚችሉ ያመለክታሉ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia 🇪🇹
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-tps://x.com/HDebasu?t=WkEcsELrZrHGV1UGX3oSMg&s=09
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

Comments