20 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በ2021 አቤል በላይ ከሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ በህግ የባችለር ዲግሪውን ሲቀበል እና በአሜሪካ የሞክ ትሪያል ውድድር አንደኛ በመውጣት ትልቅ ታሪክ መስራቱን በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወሳል። የዚያን ጊዜ "ታዋቂ የወንጀል ጠበቃ መሆን እና ማህበረሰቤን ማገልገል ህልሜ ነው" ያለው አቤል፣ ዛሬ ቃሉን ጠብቆ እና ህልሙን አሳክቶ አስደሳች ዜና አድርሶናል። አቤል ባደረሰን መረጃ መሰረት፣ የህግ ትምህርቱን በከፍተኛ ማዕረግ በማጠናቀቅ የዶክትሬት (Juris Doctor) ዲግሪውን በክብር ተቀብሏል።
በህግ ትምህርት ቤቱ ቆይታው አቤል በርካታ ታላላቅ ስኬቶችን አስመዝግቧል። በትምህርት አፈጻጸሙ በክፍሉ አንደኛ ደረጃን በማምጣት፣ በህግ ተማሪዎች ዘንድ ትልቅ ክብር ያለውን የ'ካሊ' (CALI Award) ሽልማት አሸናፊ ለመሆን በቅቷል። ከዚህም ባሻገር በሶስተኛ ዓመት የህግ ትምህርቱ ላይ እያለ፣ በወንጀል ተከላካይ እና የታራሚዎች ጥብቅና ክሊኒክ ውስጥ በተማሪ ጠበቃነት አገልግሏል። በዚህም የራሱን ደንበኞች በመወከል እና ፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኞች ፊት ባደረገው የህግ ክርክር፣ አምስት የተለያዩ ሰዎችን ከእስር ነጻ ማስወጣት ችሏል። ገና ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ይህን መሰል ተግባራዊ ስኬት ማስመዝገቡ ትልቅ የወደፊት ተስፋውን የሚያሳይ ነው።
በተጨማሪም ፍርድ ቤት በመቅረብ ከሚያደርገው የጥብቅና ስራ ጎን ለጎን፣ በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚ ሴቶች የህግ ጽሁፍ አዘገጃጀትን በማስተማር ማህበረሰባዊ ግዴታውን በከፍተኛ ሁኔታ ተወጥቷል።
እነዚያ ባህሉን እና ቋንቋውን አውቆ እንዲያድግ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ወላጆቹ፣ ከበደ በላይ፣ ሙሉ ጸጋዬ፣ ልዑል ሰገድ ደምሴ ዛሬ ልጃቸው የደረሰበትን የዶክትሬት ማዕረግ እና ተግባራዊ የስኬት ጉዞ ሲመለከቱ ኩራታቸው እጥፍ ድርብ ሆኗል።
አቤል ለደረስክበት የዶክትሬት ማዕረግ እንኳን ደስ አለህ፤ በቀጣይ የጥብቅና የስራ ዓለምህም የተሻለ ስኬትን እንመኝልሃለን!

2 months ago
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ዶ/ር ዮሐንስ ዘሪሁንን የአመቱ ምርጥ ሲል ሰየመ
#ethiopia | የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ7ኛው የምርምር ጉባዔው በተለያየ ዘርፍ የአውቅና ሽልማት ሰጥቷል፡፡ ኮሌጁ የዓመቱ ምርጥ የቀድሞ ተመራቂ (Alumni) ሆኖ የተመረጡት ዶ/ር ዮሐንስ ዘሪሁን ናቸው፡፡
ዶ/ር ዮሀንስ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በሕክምና (Doctor of Medicine) ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፣ በትምህርትና በተግባር ዘርፎች ከፍተኛ ብቃት አሳይተዋል።
በኢንተርንሺፕ የተግባር ልምምድ ግዜአቸው በተለያዩ ሙያዊ ክፍሎች ሰፊ የክሊኒካል ልምድ በማግኘት፣ በታካሚዎች እንክብካቤ እና በሕክምና ውሳኔ ሂደት ንቁ ተሳትፎ አድርጎዋል።
ከሁሉ በላይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ያደረጉት አገልግሎት በኒራቅ ጤና ጣቢያ እንደ አጠቃላይ ሐኪም፣ ከመደበኛ ሕክምና ተግባራቸው በተጨማሪ ዝቅተኛ ወጪ ያለው የሚጠቅም ፈጠራ አቀረበዋል፤ ይህም ተጣጣፊ የሆነ በግድግዳ ላይ ተለጣፊ የህጻናት የድንገተኛ አልጋ እና ከርሱ ጋር የተያያዘ የአስተማሚ መቀመጫ፣ ከተቀናጀ መደገፊያ እና የሚነቀል አነስተኛ የሂደት መሳሪያ ትሬይ ጋር የተያያዘ፣ ኮሎስቶሚ አፕሊያንስና የተሻሻለ እስፓይካ ቴብል ነው።
ይህ የፈጠራ ስራ የጤና አገልግሎቱን ተደራሽና እንዲሻሻል አስተዋጻኦ አድርገዋል። ከሕክምና አገልግሎታቸው በተጨማሪ፣ በ3D ፕሪንቲንግ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመታገዝ በማህበረሰቡ ውስጥ ትምህርትንና ፈጠራን ለማበረታታት “መቅድም ቤተ መፃህፍት እና የፈጠራ ማዕከል” መመስረት ችለዋል።
በሙያቸውና በፈጠራ ስራቸው ከፍተኛ አስተዋጽዎ ላደረጉት ዶ/ር ዮሐንስ ዘሪሁን የዓመቱ ምርጥ አልሙናይ (የቀድሞ ተመራቂ) እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

3 months ago
ዛሬ የዶክተሮች ቀን ነው።
#fastmereja I ዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (March 30, 2026) በመላው ዓለም የሃኪሞች ቀን (Doctors’ Day) የህክምና ባለሙያዎች ለሰው ልጅ ህይወት መታደግ የሚያደርጉትን ተከታታይ ተጋድሎ በማሰብ በታላቅ ክብር እየተከበረ ይውላል።
ይህ በየዓመቱ መጋቢት 21 ቀን የሚከበረው የሃኪሞች ቀን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንጆቹ 1933 በዊንደር ጆርጂያ መከበር የጀመረ ሲሆን፣ ዕለቱ የተመረጠውም ዶክተር ክራውፎርድ ደብሊው ሎንግ ለመጀመሪያ ጊዜ "ኢተር" (Ether) የተሰኘውን ማደንዘዣ ለህክምና አገልግሎት ያዋሉበትን አንደኛ ዓመት መታሰቢያ በማድረግ ነበር።
በየደቂቃው በሚታደሱ የህክምና ግኝቶች ውስጥ ሆነው፣ ዕውቀታቸውንና ጉልበታቸውን መስዋዕት በማድረግ በታማሚዎችና በሞት መካከል ቆመው ለሚያገለግሉ የህክምና ባለሙያዎች ዕውቅና መስጠት የዕለቱ ዋነኛ ዓላማ ነው። ማህበረሰቡም በየደረጃው የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን "ስለ አገልግሎታችሁ እናመሰግናለን" በማለት የሞራል ድጋፍ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

የስልጤ ዞን የሀይረንዚ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የመጀመሪያዎቹን 17 የሕክምና ዶክተሮች አስመረቀ
#fastmereja I በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪ በሕክምና ሳይንስ (Doctor of Medicine) ሲያጠኑ የቆዩ 17 የስልጤ ዞን የሀይረንዚ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የበኩር ልጆች በደመቀ ሁኔታ ተመርቀዋል።
ተመራቂዎቹ በ2010 ዓ.ም በሀይረንዚ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተፈትነው በተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከተሰማሩት ተማሪዎች መካከል የመጀመሪያዎቹ ፍሬዎች መሆናቸው ተገልጿል።
#ጤና #ልዩ_ልዩ

Sponsored by
Surafel
7 months ago
ነስርን ለማስቆም የሚረዱ ቀላል ምክሮች | Stopping a Nosebleed: A Quick Guide
ነስር ወይም የአፍንጫ መድማት (ኤፒስታክስ) (Epistaxis) ሲያጋጥም ሊያስደነግጥ ይችላል፤ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ከባድ የጤና ችግርን አያመለክትም።
ነስር ወይም የአፍንጫ መድማት ሲያጋጥምዎ ምን ማድረግ እንዳለብዎ እና በምን ጊዜ መጨነቅ እንዳለብዎ እንጠቁምዎ።
ምን ማድረግ አለብን? | What to Do
1️⃣ መረጋጋት (Stay Calm):- ቀጥ ብለው ይቀመጡ፣ እና በትንሹ ወደፊት ያዘንብሉ። ይህ ደም ወደ ጉሮሮዎ እንዳይወርድ ይረዳል።
2️⃣ አፍንጫን መያዝ (Pinch):- አውራ ጣት እና አመልካች ጣትዎን ተጠቅመው ከአፍንጫዎ አጥንት በታች ያለውን ለስላሳ የአፍንጫ ክፍል አጥብቀው (ቆንጥጠው) ይያዙ።
3️⃣ ይዞ መቆየት (Hold):- መድማቱ መቆሙን ለማየት (ለማረጋገጥ) የያዙትን ሳይለቁ ከ 10 እስከ 15 ደቂቃዎች ያህል ይቆዩ።
4️⃣ መተንፈስ (Breathe):- በአፍዎ ይተንፍሱ።
ማድረግ የሌለብን ነገሮች | What to Avoid
ወደ ኋላ አይተኙ ወይም ራስዎን (ጭንቅላትዎን) ወደ ኋላ አያድርጉ። አፍንጫዎን በሶፍት አይሙሉት ወይም አይጠቅጥቁት።
መቼ ወደ ሐኪም መሄድ አለብን? | When to See a Doctor
የሚከተሉት ከተከሰቱ በአፋጣኝ የሕክምና ዕርዳታ ያግኙ፤
🔹 ደም መፍሰሱ ከ20 ደቂቃ በላይ ከቀጠለ።
🔹 የማዞር፣ የድካም ስሜት ከተሰማዎ።
🔹 የአፍንጫ መድማቱ በደረሰብዎ ጉዳት ለምሳሌ በጭንቅላትዎ ላይ በደረሰ ምት የተከሰተ ከሆነ።
የመከላከያ ምክሮች | Prevention Tips
🔹 ቤትዎ ደረቅ ከሆነ አየርን እርጥበት አዘል የሚያደርግ መሳሪያ (humidifier) ይጠቀሙ።
🔹 የአፍንጫዎን መድረቅ ለመከላከል ቀለል ያለ ቫዝሊን በአፍንጫዎ ቀዳዳ ውስጥ ይቀቡ።
🔹 አፍንጫዎን ከመጎርጎር ይቆጠቡ።
seledadotio

8 months ago
የጤና ሚኒስቴር የህይወት ዘመን ተሸላሚ ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማርያም
#ethiopia | የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ሽልማት ተሰጣቸው።
በጉራጌ ዞን በሙህርና አክሊል ወረዳ ተወለዱ።
የመጀመሪያ ደረጃና መልስተኛ 2ኛ ደርጃ ትምህርታቸውን በዲላ ከተማ አጼ ዳዊት ት/ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በይርጋዓለም ከተማ ራስ ደስታ ዳምጠዉ ክፍተኛ 2ኛ ድርጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡
የመጀመሪያና የማስተርስ ድግሪያቸውን በፋርማሲ ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ፣ የፒ.ኤች ዲ. ድግሪያቸውን ከUniversity of Wales በፋርማሲ ዘርፍ በማዕርግ አግኝተዋል።
በጀርመን ሀገርም post-doctoral ምርምር አካሂደዋል።
የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረጋቸውን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡
ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ ከ30 ዓመታት በላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ የፋርማሲቲካል ዲፓርትመንት በኃላፊነት፣ የፋርማሲቲካል ትምህርት ቤት በዲንነት፣ የድህረ ምረቃ ጥናትና ምርምር በም/ፕሬዝዳንትነትነት ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ በፋርማሲቲካል ቴክኖሎጂ ዘርፍ በምርምር፣ በማስተማር እና በማማከር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
የቂሊንጦ ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ፓርክ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ላይ፣ የባዮቴክኖሎጂ R&D እቅድ እና ግብይት ስትራቴጂ ዝግጅት፣ የ10 ዓመት የኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ ብሔራዊ የምርምር ካውንስል ማቋቋሚያ ላይ የጋራ ስምምነት ጥናት፣ የብሔራዊ መድሃኒቶች ፖሊሲ ክለሳ ላይ ተሳትፈዋል፣ ባላቸው የላቀ የስራና የትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ብሔራዊ እና ክልላዊ ስትራቴጂዎችን ለመቅረጽ አስተዋፅዖ ያደረጉ ቴክኒካል ሰነዶችን አዘጋጅተዋል።
በአ/አ/ዩ 50ኛ ኢዩቤልዩ በዓል በምርምር የወርቅ ሚዳልያ እና ሰርተፊኬት፣ የታዋቂዉና ታላቅ ክብር ያልዉን የጆርጅ ፎርስተር የምርምር ሽልማት፣ ከአሌክሳንደር ቮን ሁምቦልት ፋውንዴሽን ሽልማት አግኝተዋል፣ AAU የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህይወት ዘመን ምርጥ ተመራማሪ ሽልማት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የላቀ የፋኩልቲ ሽልማት፣ ሁምቦልት አምባሳደር ሳይንቲስት የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት፣ ከኢትዮጵያ ፋርማሲዩቲካል ማኅበር ሽልማትንም አግኝተዋል፡፡
ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር የረጅም ጊዜ አቅም ግንባታን በድህር/ምረቃ ፕሮግራሞችን ምርምር ላይ አመቻችተዋል፡፡
ከ175 በላይ የምርምር ውጤቶችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መሥራችና አባል፣ የአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የሳይንስ አማካሪ ቦርዱ ናቸው፡፡
ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማርያም፤ የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡
ከጤና ሚኒስቴር

9 months ago
ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ (ከ1922-2018)
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል። ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ቅፅ 3 መዝገበ አእምሮ ከ20 በላይ ዘርፎች ይኖሩታል። እዚህ ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ የአገር ባለውለታዎችን መሰነዳችን ይቀጥላል። ዲፕሎማሲና የመንግስት ኃላፊነት በሚለው መደብ ታሪካቸውን የምንሰንድላቸው ዶክተር ምናሴ ኃይሌ ሲሆኑ ታሪካቸውንም ዕዝራ እጅጉና ሲሳይ ገብረማሪያም እንደሚከተለው አጠናክረውታል
ህልፈታቸው በዩናይትድስቴትስ ኒውጀርሲ እ.ኤ.አ መስከረም 2025 (ጳጉሜ 5, 2017 ዓ.ም) ነበር።እንደ አንድ የመንግስት ኃላፊ ፣ዲፕሎማት ፣የህግ ምሁር ለማይታረቁና ለተለያዩ የዓለም አስተሳሰቦች የሚጋሩትን ድልድይ በመገንባት ይህን ዓለም ተሠናብዋል። ከልጅነት እስከዕውቀት ዶ/ር ምናሴ ህይወትን እንዴት ኖሯት?
ልደት፣ ዕድገትና ትምህርት
ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ ከእናታቸው ከወይዘሮ እሌኒ ኃይሌ እና ከአባታቸው ከአቶ ኃይሌ ድብነህ በ1922 ዓ.ም በሐረር ተወለዱ። የልጅነት ዘመናቸውን በሐረር ያሳለፉት የያኔው አዳጊው ምናሴ ቤተሰባቸው ኑሮውን በአዲስ አበባ ሲከትም የእርሳቸው የትምህርት ህይወት በኮተቤ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቀጠለ። በኮተቤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ሳሉ በሀገረ- አሜሪካ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸውን እድል አገኙ።
በአሜሪካ በቀጠለው ትምህርታቸው እ.ኤ.አ በ1950 ከዊስኮንሲን ማዲሰን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አገኙ። እ.ኤ.አ በ1954 ደግሞ በኒውዮርክ ወደሚገኘው ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ በማቅናት የህግ ትምህርት ለማጥናት ጥርጊያውን ያመቻቸላቸውን ለህግ ትምህርት ቅድመ ዝግጅት ብቁ የሚያደርገውን የ (Juris Doctor) ወረቀት አገኙ። ባልተገታው የትምህርት ጉዟቸው እ.ኤ.አ በ1957 ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሲጎናፀፉ ከ4 አመት በኋላ በ1961 ሦስተኛው ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) ያዙ።
ሀገራዊ ኃላፊነት እና ሙያዊ አበርክቶ
በዛው ትምህርታቸውን ባጠናቀቁበት ዓመት ምቾት ይበልጥብኛል ሳይሉ እ.ኤ.አ በ1961 ወደ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመለሱ።
በተመለሱበት ቅፅበትም የኢትዮጵያን ፒስ ኮርፐስ ከአሜሪካ ጋር በጋራ እንዲሠሩ ሁለቱን ሀገራት ያፈራረሙት ዶክተር ምናሴ ነበሩ። በጊዜውም እርሳቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የህግ አማካሪ ሆነው በተቀጠሩበት ጊዜ ነው። ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ በተመደቡበት የውጭ ጉዳይ ስራ ሳይታጠሩ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ደንብ የሚል ረቂቅ በማዘጋጀት በረቂቅ ደንቡ አማካይነት የኢትዮጵያ ፐርሶኔል አስተዳደራዊ ኤጀንሲ ተብሎ የሚጠራውን ተቋም አቋቋሙ ።
ከዚህ መንግስታዊ ኃላፊነት በኋላ እ.ኤ.አ በ1962 ዶ/ር ምናሴ የንጉሠ ነገስቱ የግል ካቢኔ አባል ተደርገው ተሾሙ። በዚሁ ኃላፊነታቸው የውጭ ፣የፍትህ ፣የኢኮኖሚ ፣የውጭ ደህንነት እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ቅኝት እንዲያደርጉ እና ስትራቴጂካዊ በሆኑ ሀሣቦች ዙሪያ እንዲያማክሩ በንጉሡ የግል ካቢኔ አባል ሆነው ሥራቸውን ቀጠሉ።
ከተሠጣቸው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችን ማማከር እና ቅኝት የማድረግ ኃላፊነት ባሻገር እ.ኤ.አ በ1964 ሌላ ድርብ ኃላፊነት ተጣለባቸው። የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። በዚህ ኃላፊነታቸው በሃገሪቱ በወቅቱ በነበሩት ሚዲያ ዎች ማለትም በኢትዮጵያ ሬድዬ ፣ቴሌቪዥን እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላይ ስርነቀል ለውጥ እንዲመጣ በማድረግ በእርሳቸው መሪነት ተቋማቱ የተሻለ ሙያዊ ነፃነት እንዲጎናፀፉ አድርገዋል።በተመሣሣይ ጊዜም በሀገሪቱ በተነባቢነት ሁለተኛ ደረጃነት ይዞ የነበረው የዛሬይቱን ኢትዮጵያ ጋዜጣን መስርተዋል።
እ.ኤ.አ ከ1969 እስከ 1971 የነበረው ወቅት የአሜሪካ ትኩረት በቬትናም ጦርነት እና የቀዝቃዛው ጦርነት ትኩረት ያየለበት ጊዜ ነበር።ለዶ/ር ምናሴ ይኸው ወቅት ቀጣይ የሙያ ማረፊያቸው ሆኖ በአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉበት ጊዜ ነበር።
ከአሜሪካ አምባሳደርነት መልስ እ.ኤ.አ በ1971 ዶ/ር ምናሴ ዳግም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ሆነው ተሾሙ።በዚህ የውጭ ጉዳይ ቆይታቸው ቦታው የሚጠይቀውን ታላላቅ የዲፕሎማሲ ስራዎችን ያከናወኑ ሲሆን በዚሁ ጊዜ የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ልዑክ በተባበሩት መንግስታት ፣በአፍሪካ አንድነት፣ በወቅቱ የዓለም ገለልተኛ አባል ሃገራት ንቅናቄ እየተባለ ከሚጠራው ተቋምና እና በሌሎች የሁለትዮሽ ትብብር መድረኮች ኢትዮጵያ እንድትከብር አድርገዋል።
እ.ኤ.አ ከ1971 -1972 ባለው ጊዜም ሀገርን በሌላ ሙያዊ አቅም ወደሚያገለግሉበት ወደአፍሪካ አንድነት ድርጅት በማቅናት በድርጅቱ ውስጥ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል አገልግሎታቸውን ቀጠሉ። እርሳቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል በነበሩት ዘመንም አህጉሪቱ በታላቅ ተስፋ እና ስጋት ውስጥ ነበረች። ዶ/ር ምናሴም በድርጅቱ በነበራቸው ቆይታ ስጋትን ወደተስፋ በመቀየር ካሳኳቸው ተግባራት መካከል እ.ኤ.አ በ1972 በአዲስ አበባ የተካሄደው ስምምነት ሲሆን ስምምነቱም የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቋጭ ያደረገ ነበር። ከዚሁ ጎን ለጎን ለረዥም ጊዜ አጨቃጫቂ የነበረው የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር እንዲካለል አድርገዋል። በተመሳሳይ ወቅት ከንጉሰ ነገስቱ ጋር ወደቻይና ተጉዘው ጉብኝት አድርገው ከወቅቱ የቻይና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዞ ኔሊያ እና ከሊቀመንበሩ ማኦ ዜዱንግ ጋር ተገናኝተው ሁለቱ ሃገራት በጋራ ስለሚሠሩባቸው ጉዳዮች መክረዋል።
የጋራ እሳቤ መስራቹ ምናሴ ሀይሌ!
ሀሙስ ግንቦት 16 1965 ዓ.ም ፡፡ የአፍሪካ ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና ርዕሳነ መንግስታት የወቅቱን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ 10ኛ አመት በአል ለማክበር በአዲስ አበባ ታድመዋል፡፡
ለአዲስ አበባ ይህ ክብረ በአል የድርጅቱ ጉዞ 10 ዓመት ላይ መድረሱ ብቻ አይደለም ትርጉሙ።ዕለቱን ልዩ ያደረገው በዚህ ቀን የተፃፈው አይረሴ ታሪክ ነው።
በአፍሪካ አንድነት ምስረታ 10ኛ ዓመት ላይ
ቅዳሜ ግንቦት 18 1965 ዓ.ም የድርጅቱን ምስረታ በማስመልከት የሚደረጉ ንግግሮች ቀጥለዋል፡፡በወቅቱ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ከሚሉ መልዕክቶች ባሻገር የበዓሉን ዐውድ የሚለውጡ ንግግሮች መደመጥ ጀመሩ፡፡ ቀዳሚው ደግሞ ከሶማሌያው ተወካይ የተደመጠው ንግግር ነበር፡፡በአፍሪካ አንድነት 10ኛ አመት በዓል ላይ የወቅቱ የሀገራቸውን ፕሬዚዳንት የሆነትን ዚያድ ባሬን ወክለው የተገኙት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ኮለኔል ኢስማኤል አቡበከር ሲሆኑ ንግግራቸው ኢትዮጵያን በመክሰስ ጀመረ ፡፡በሶማሊያው ፕሬዚዳንት ዚያድ ባሬ ተፅፎ በምክትሉ በቀረበው ንግግር ኢትዮጵያ ሶማሊያን ልትወር ነው የሚል ሀሜት ያዘለ ዲስኩርን አሰሙ፡፡ የሶማሌውን ምክትል ፕሬዚዳንት ተከትሎ መድረኩን ቀጥለው የተረከቡት ደግሞ የወቅቱ የሊቢያ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት አቡ ዘይድ ነበሩ፡፡ አቡዘይድ “ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጥቂት ነጭ ገዢዎች ስርዓት እንዲሰፍን ትፈልጋለች፡፡” በማለት ለሰደድ እሳቱ ክብሪቱን በመጫር
ንግግራቸውን ጀመሩ፡፡ በማስከተልም “ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጥቂት ነጭ ገዢዎች ስርዓት እንዲሰፍን የምታደርገው እስራኤልን በመርዳት ነው፡፡” ሲሉ ክሳቸውን አጠናከሩ፡፡በዚህ ያልተገታው ተንኳሽ ንግግራቸው “ኢትዮጵያ ለአሜሪካ የጦር ሰፈር ፈቅዳለች፡፡ለሰሜን ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶም ትሰልላለች፡፡ይኸው የስለላ ሥራዋ በደቡብ አፍሪካ እና በሮዴዥያ ያለውን ሥርአት የሚመግብ ነው፡፡ይህ የኢትዮጵያ ተግባር ከአፍሪካ አንድነት ዓላማ ጋር የማይሄድ በመሆኑ ፤ በዚህ በዓል ላይ የታደማችሁ የአንድነት ድርጅቱ አባላት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቀመጫ ከአዲስ አበባ እንዲነሳ” የሚል ክስ አቀረቡ፡፡ ይኸው ንግግር በአዳራሹ የነበረውን አውድ ቀየረው፡፡ ክብረ-በዓሉ ወደሃሣብ ጦርሜዳነት ተቀየረ። በወቅቱ ንጉሰ ነገስቱን ወክለው ለሶማሌ ፕሬዚዳንት እና ለሊቢያው ፕሬዚዳንትተወካዮች የወቅቱ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አክሊሉ ሀብተወልድ በፈረንሳይኛ መልስ ሰጡ።ነገሩ ግን በዚህ አልተቋጨም መሠል ጥያቄን በታሪክ ሲነሣም ሁሌም መልስ ሊሆን የሚችል ንግግር በሌላኛው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ተሰማ፡፡
ስለሁኔታው በማግስቱ ጉዳዩን ለዓለም አንባብያን ያደረሠው “The New York Times” በዘጋቢ ቶማስ ጆንሰን ፅሁፍ እንዲህ ሲል ገለፀው። “AFRICAN NATIONS CLASH AT PARLEY” ወይም “በሰርግ መሀል የቀለጠው ጦርነት” የሚል ስሜት ያለው ፅሁፍ ፃፈ፡፡በዚሁ ግንቦት 19 1965 ዓ.ም ለንባብ ባዋለው ፅሁፍ በአፍሪካ አንድነት 10ኛ ዓመት ክብረ-በአል ላይ የኢትዮጵያ እና ሊቢያ ዱላ ቀረሽ ፀብ ማስተናገዳቸውን፡፡
የፀቡ ፊትአውራሪ የሊቢያው ተወካይ አቦዙድ ዱዋርዳ በአረበኛ ባደረገው ንግግር የኢትዮጵያን መሪዎች “ፅዮናውያን እና ቅኝ ገዢዎች” ብሎ መዝለፉን። “ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ከአሜሪካ እና ከፅዮናውያን ጋር ጥብቅ ቁርኝት” ያላቸው መሆኑን ይህን ተከትሎም “የአፍሪካ አንድነት ዋና መዲናነት ወደሌላ ሥፍራ ይዘዋወር” ብሎ መጠየቁ መሆኑን አትቷል፡፡
አፀፋዊ ምላሹ በጣም ትዕግስተኛ እና ሆደሰፊ እንደመሆናቸወ ከሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያን የማይገመት ነበር ያለው "ዘ ኒውዮርከ ታይምስ" በወቅቱ መብረቃዊ የሆነ አፀፋዊ ምላሽ የሰጡትን የኢትዮጵያው የወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ምናሴ ሀኃይሌ ምላሽ 'No Dictation From Libya' ብለው ጀመሩ ይላል፡፡
“ቀድሞ ዲስኩር ያሰማው ሰው ንግግሩ የፈላስፋ መስሏችሁ ከቁብ እንዳትቆጥሩ፡፡…የአንድ የዞረበት እና ግራ የገባው ሰው ንግግር ነው፡፡” ሲሉ ቀጠሉ “በዚህ አዳራሽ ያላችሁ የአፍረካ ርዕሳነ ብሔራት እና ርዕሳነ መንግስታት፤በተነሣው ርዕስ ላይ ማናችሁም በሊቢያ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ትቀበላላችሁ ብዬ አላምንም፡፡ሊቢያ የቱን ያህል አማላይና የተትረፈረፈ ሀብት ቢኖራትም አፍሪካ ለሽያጭ የቀረበች ቁስ አይደለችም። የሊቢያ ሀብት ለአፍሪካውያን ምናቸውም ነው፡፡ ” ሲሉ ጠንካራ ቅስም ሰባሪ ምላሽ ሰጡ፡፡አዳራሹ በጭብጨባና ጩኸት ተሞላ።
አክለውም የኢትዮጵያን አቋም በግልፅ እንዲህ በድፍረት አስቀመጡ “ሊቢያ ከነዳጅ የምታገኘው 13 ቢሊየን ዶላር ዓለምን ለመቀየር በቂ ይመስላታል።” በማለት የኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲናነት መለወጥ እንደማይችል የወቅቱ ደፋር እና የአድዋ ልጅ መሆናቸውን ያስመሰከሩበትን ንግግር አደረጉ። ይህንኑ ታሪክም ዘ ኒውዮርከ ታይምስ ለታሪክ እንዲቀመጥ አድርጎታል።
ይህ የዶክተር ምናሴ መርህ አዘል ንግግር በመድረኩ ብቻ ተቀብሮ አልቀረም።የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ እንደሚባለው ኢትዮጵያ ዛሬም ድረስ በአፍሪካና በዓለም ጭቁን ህዝቦች ፊት በአርአያነት ለመታየትና ለአፍሪካውያንም የቁርጥ ቀን ቤታቸው ልትሆን የቻለችው ትናንት በተከፈለው ዋጋ ነው። የትናንቱ ዋጋ ለዛሬ መሰረት ሆኖ ነገ እንዲገነባባት አድርጓል፡፡ የአፍሪካ ህብረት መዲና መሆንም እንዲሁ በዋዛ ያልተገኘ እና በየጊዜው እጅግ የከበረ ዋጋ የሚከፈልበት መሆኑ በታሪክ አጋጣሚ የሚከሰቱ ክስተቶች ማሳያ ሆነው አልፈዋል፡፡ እዚህ ላይ ትናንት የህብረቱ መቀመጫ በኢትዮጵያ እንዲሆን ለማድረግ ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ እና ጓዶቻቸው ገጥሟቸው የነበረው ፈተና ራሱን በታሪክ የደገመበትን አጋጣሚ እናንሳ፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቶጎ ሎሜ በ1991 ዓ.ም ለህብረቱ ስብሰባ ታድመዋል። ይኸው በትውልድ መፈራረቅ ያልተገታው ጥያቄ በቶጎ ሎሜ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ከመቃብር ተነስቶ ብቅ አለ። ለውይይት ከቀረቡ አጀንዳዎች በ24 ኛ ደረጃ ላይ የአፍሪካ ህብረት መዲናነትን ከአዲስ አበባ እንዲነሳ በወቅቱ አንድ ጉዳይ ሆኖ መጣ። ኢትዮጵያን ወክለው በመድረኩ የተገኙትት አቶ መለስም ለአጀንዳው መልሳቸው የእነዶክተር ምናሴ ኃይሌ አርአያነትን የተከተለ ነበር፡፡ “….በአፍሪካ ጉዳይ መንግስቱ ኃይለማርያም ልክ እንደቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሁሉ የፀና አቋም ነበረው፡፡ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያላት ቁርጠኝነት መንግስታት በተለዋወጡ ቁጥር የሚቀየር አይደለም፡፡” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው መድረኩ ላይ ተናገሩ።
ይህን የመለስ አባባል ከባለታሪኩ ዶ/ር ምናሴ ሀይሌ ስም ትርጉም ጋር ስናሰናኘው ስምና ግብራቸው የገጠመላቸው ሰው ያስብላቸዋል፡፡ በቅዱስ መፅሀፍ ምናሴ፦ማስረሻ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ለዘመናት እኛ ኢትዮጵያውያን ስርአት መጥቶ ስርአት ሲተከል በውስጥ ጉዳያቸው መለያየታችን ያለና የኖረ ቢሆንም በአፍሪካ ጉዳይ ዶ/ር ምናሴ ኃይሌና ባልደረቦቻቸው በዘመናቸው ለሀገራቸው የከፈሉት ዋጋ በዓለም መድረክ የውስጥ ልዩነታችንን ያስረሳ ተብለው ቢገለፁ የሚያንስባቸው አይሆንም፡፡ ህያው ሥራቸው በርዕዮትም በግብርም በማይመስሏቸው የኢትዮጵያ መሪዎች መመስከሩም ይህንኑ ያስረዳል፡፡
ይህ ሁሉ ሀገራዊ አበርክቶ ግን በምስጋና አልተቋጨም። ጊዜ ሲለወጥ ነገሮችም አብረው ተቀየሩ። አንዱ ሾተል የሆነው የታሪክ አካልም በ1966 አብዮት ብቅ አለ። በወቅቱ በሀገራችን የተካሄደውን የ1966 ቱ አብዮት ተከትሎ ዶ/ር ምናሴ ከስልጣን ለቀቁ።
ከስልጣን በኋላ ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ ስለነበሩበት ሁኔታ ቤተሰቡን በቅርበት የሚያውቁት ዶ/ር ጌታቸው ተድላ እንዲህ ያስታውሱታል።"በወቅቱ ዶ/ር ምናሴና ቤተሰባቸው ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ትምባሆ ሞኖፖል በታች ቪላ ተከራይተው ይኖሩ ነበር።እኔ ስለቤተሰቡ የማስታውሰው ልጅ እያለን ወ/ሮ አይሬስ ሀይሌ እሁድ እሁድ በራቸው ላይ ብስኩት ይሰጡን ነበር። ወይዘሮ አይሬስ መልከ መልካም ጥቁር አሜሪካዊት እናት ነበሩ።ሁለት መንታ ወንድ ፣አንድ ሴት እና ሌላ አንድ ወንድ ልጅ ነበራቸው።መንቶቹ ዴቪድ እና ዳንኤል ሲባሉ።ሴቷ ሱዛን የመጨረሻው ወንድ ልጅ ስም ማይክ ነው።ሶስቱም ወንዶች ፕሮፌሽናል ዶክተሮች ናቸው ።ሴት ልጃቸው ሱዛን የአባቷን ፈለግ በመከተል የጥብቅና ሙያ ላይ ታገለግላለች። ዶ/ር ምናሴን ደርግ አንድ አመት ከሁለት ወር አስሯቸዋል።ልክ መስከረም 1ቀን ተፈቱ።ኮሎኔል ዳንኤል አስፋው ከ4ኛ ክፍለጦር ወደቤተ-መንግስት ወሰዳቸው።ከዚያም ተፈቱ። እንደተፈቱም ኒውዮርክ መሄድ እፈልጋለሁ ሲሉ ልቀቋቸው ይሂዱ የተከበሩ ሰው ናቸው አለ።ወደአሜሪካ ሄዱ ።" በማለት ዶክተር ጌታቸው መስክረዋል።
ከእስር እንደተፈቱ ህይወታቸውን በስደት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መምራት ቀጠሉ። በስደት እያሉ ህይወታቸውን በአላማ መምራታቸውን አላቆሙም።በተግባር የቀሰሙትን እውቀት በትምህርት ማካፈል ጀመሩ። በቀዳሚነት የማስተማር ስራ የጀመሩት ደግሞ በቪላኖቫ ዩንቨርስቲ ሲሆን ከጥቂት ቆይታ በኋላ ወደኒውዮርክ በማቅናት ካርዶዝ ዩኒቨርሲቲ ለ26 ዓመታት በማስተማር እና በተለያዩ የህግ፣በዲፕሎማሲ እና የአፍሪካ ሉአላዊነት ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን ሲያሳትሙ ቆይተዋል።
ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ እንዳሰቡት የኖሩ፣በታላቅ ክብር ፣በማይናወፅ ትጋት እና በኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር እንደተነደፉ በ95 ዓመታቸው የህይወታቸው ጉዞ ተፈፅሟል።ዶ/ር ምናሴ ከወ/ሮ አይሪስ ሀይሌ ጋር 71 አመት የትዳር ህይወት ነበራቸው።ከትዳር አጋራቸውም አራት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን ጠቃና የህግ ምሩቅ የሆነችው ሱዛን ሀይሌን ፣ዶ/ር ዳዊት ፣ዶ/ርዳንኤል ፣ዶ/ር ሚካኤል ሀይሌ እና 8 የልጅ ልጅ እና የአንድ የልጅ ልጅ ልጅ ቅድም አያት ነበሩ።
የአሁን ዲፕሎማቶች ከዶ/ር ምናሴ ሀይሌ ምን ይማሩ?
ክቡር አምባሳደር ነብዩ ተድላ
"አንድ ዲፕሎማት በየትኛውም ጊዜና ወቅት የሃገሩን ጥቅም ከማስከበር አኳያ ስትራቴጂክ የሆነ ትዕግስት ባለቤት ሊሆን ይገባል ተብሎ ይታሰባል። በዲፕሎማሲ አንዳንድ ጊዜ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች በአጭር ጊዜ የማይገለፅ ውጤት ላይኖራቸው ይችላል።ስለዚህ በዲፕሎማሲ ረዥሙን ጨዋታ መጫወት የሚችል ስትራቴጂክ ትዕግስት እንዲኖረው ከአንድ ዲፕሎማት ይጠበቃል።በዚህ ሂደት መቼ የወደፊት ርምጃ ማድረግ ያስፈልገኛል።
መቼስ ወደኋላ ልመለስ ያስፈልጋል።እርምጃ ማድረግ አለብኝ የለብኝም የሚለውን ማወቅ አስፈላጊ ነው ።
ሁለተኛ የታሪክና የባህል ጥልቅ ግንዛቤ ሊኖረውም ይገባል። ይህ ሲሆን አንድ ዲፕሎማት ውጤታማ ዲፕሎማሲ ይሰራል ተብሎ ይታመናል።
ሶስተኛው ከቋንቋ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ያሉ ክህሎቶችን መረዳት ነው።ዶ/ር ምናሴም ባየነው የድርድር መድረክ ላይ በአጭር አገላለፅ በተመጠነ ቋንቋ የሀገራቸውን ጥቅም ያስጠበቁበትን ሁኔታ ማየት ይችላሉ።
በመሠል የድርድር እና ምክክር መድረኮች የሀገርን ጥቅም ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ።ችግሮች ሲከሰቱ መደናገጥና ስሜታው መሆን ሳይሆን በተረጋጋ ሁኔታ ለተነሣ ጉዳይ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል።አስፈላጊ ሲሆን ተግሳጽ መስጠት ጭምር እንደሚያስፈልግ መማር ይቻላል።ይህን ከቀደሙ በሳል ዲፕሎማቶች መማር የምንችለው ነው።"ብለዋል
አምባሳደር ብዙነሽ መሠረት "ስለ ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ ብዙ የምናነሳውቸው ነገሮች አሉ።በእርሳቸው ዘመን በነበረው ዲፕሎማሲ እና የውጭ ጉዳይ ሥራ አመራርነት ሁሉንም አንስቶ መጨረስ አይቻልም።የ10ኛውን የአፍሪካ አንድነት ክስተት መነሻ አድርገን ትውልድ ሊማር የሚችለው ከምንም ነገር በፊት የሀገርን ጥቅም ማስቀደም፣ ሀገርን ሊጎዳ የሚችል ነገር ሲገጥም ለሀገር ቆፍጠን ብሎ መቆምን አስተምረዋል።
በአሁኑ ጊዜ የሚነገር ነገር አለ። በሀገር ጉዳይ የሀገር ጥቅምን ቆፍጠን ብሎ መናገር እና ማስከበርን ብዙ እንማራለን ።ሌላው የሚፈጥረው ስሜት አለ መለስ ብሎ እንዲህ አይነት ጉዳይ ሲታይና ሲነበብ የሚፈጥረው ስሜትና የሀገር ፍቅር የበለጠ ይቀሰቅሳል።ትውልድም ከዶ/ር ምናሴ ይህን ይማራል ብዬ አምናለሁ።" ብለዋል አምባሳደር ብዙነሽ መሠረት።

10 months ago
በግሬስ ፕላስ
ጤናማ እናት ፣ ጤናማ ልጅ ፣ ጤናማ ቤተሰብ
#ethiopia | ግሬስ የእናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል የህይወትዎ ትልቁን እና እጅግ በጣም አስደናቂ የሆነውን ጉዞ ይጀምሩ።
አዲሱ የቤተሰብዎን ምዕራፍ በአዲሱ ግሬስ ፕላስ ሆስፒታል በታዋቂ ፣ ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች እርስዎ እና ለልጆት ምርጡን እንክብካቤ ለመስጠት ሁሌም ዝግጁ የሆኑ ሥመጥር ሐኪሞች በክብር ይጠብቋችኋል።
ዶ/ር አብዱ ኢብራሂም
ታዋቂ የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም ሲሆኑ በሙያቸዉ ረጅም አመት ልምድ ያካበቱ እና በማህበረሰቡም ዘንድ መልካም ስምን ያተረፉ ተወዳጅ ሐኪም ናቸዉ።
በማህፀን እና ፅንስ ዙሪያ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሲሆን የቅድመ ወሊድ እና ድህረ ወሊድ ክትትል ፣ በቀዶ ህክምና የማዋለድ አገልግሎቶች የተወሰኑት ናቸዉ።
ዶ/ር ታከለ ጸጋዬ
ታዋቂ የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም
በሙያቸዉ ከ30 አመት በላይ ልምድ ያካበቱ የብዙ እናቶች ጤና ላይ የሰሩ እዉቅ ሐኪም ናቸዉ። የማህፀን በር ላይ ሊኖሩ የሚችሉ ያልተገቡ ለዉጦችን ቀድሞ ለማግኘት እና ለማከም ኮልፖስኮፒን በመጠቀም ይሰራሉ።
ዶ/ር ደነቃቸዉ አሰግደዉ
የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት
በሙያቸዉ ከ20 አመት በላይ ልምድ ያካበቱ የብዙ እናቶች ጤና ላይ የሰሩ እዉቅ ሐኪም ናቸዉ። በተጨማሪም የማህፀን በር ላይ ሊኖሩ የሚችሉ ያልተገቡ ለዉጦችን ቀድሞ ለማግኘት እና ለማከም ኮልፖስኮፒን በመጠቀም ይሰራሉ።
ዶ/ር ሳምራዊት ርዕሶም
የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት
ዶ/ር ልንገርህ ተፈራ
የማህፀን እና ፅንስ ሐኪም
ጤናማ እናት ፣ ጤናማ ልጅ ፣ ጤናማ ቤተሰብ
***
አድራሻችን
📍ቁጥር 1
ቦሌ ቀለበት መንገድ ሞይንኮ ፊት ለፊት
0118612707
0922750491 ይደውሉ
📍ቁጥር 2
ብሪቲሽ ኤምባሲ ከእስኩል ኦፍ ቱሞሮው (School Of Tomorrow) አጠገብ
በ0977555599
Telegram - GraceMCH
#የህፃናት ህክምና #የህፃናት ጤና #የህጻናት ሃኪም #ዶክተር #ጤና #ህክምና #ሃኪምቤት #gracemch #pediatriccare #childhealth #gracedoctors #excellenceincare s #maternalandchildhealth #pediatricspecialist #ethiopiahealthcare #childrenswellbeing #healthforall #compassionatecare #kidshealthmatters #healthcareprofessionals #medicalexcellence #meetourdoctor #expertcare #maternalhealthexpert #obstetricianandgynecologist #bestdoctor , #bestobstetrician , #womenhealthspecialist , #doctor #womanhealth #gynecologist #gracemchcenter #gracemch #maternalhealth #childhealth #pregnancycare #deliveryethiopia #addisababahealth #womenshealthethiopia #pediatricsethiopia #ethiopiahealth

ዶኒኮ ሥነ-መለኮት ኮሌጅ (DONIKO THEOLOGICAL COLLEGE) ተማሪዎችን አስመረቀ!
ዶኒኮ ሥነ-መለኮት ኮሌጅ በ2017 የትምህርት ዘመን ከ515 በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል። ኮሌጁ እውቅና ባገኘባቸው በዲፕሎማ፣ በዲግሪና በማስተርስ መረለ-ግብር በ9ኛ ዙር ነው ተማሪዎችን ያስመረቀው።
ከተመሰረተ ከ11 አመት በላይ ያስቆጠረዉ ኮሌጁ፤ አዲስ አበባ፣ ሀዋሳ አዳማ፣ ሀረ ር፣ ሆለታ ወሊሶ ሻሸመኔ እና በሌሎች ክልል ከተሞች የሚገኙ ተማሪዎችን በአመራርና አስተዳደር፣ ሥነ-መማክርት እና ሥነ-መለኮት ማለትም
1. Doctor of Christian Leadership
2. Leadership and Management
3. Business Administration
4. Peace Building and Community Development
5. Christian Counseling
6. Counseling Psychology
7. Systematic Theology
8. Practical Theology
9. Public Theology
10. Philosophy and Religious Studies
ነው ተማሪዎችን ያስመረቀው።
በዛሬው እለት 515 ተማሪዎችን
በማስተርስ 125፡ በዲግሪ 270
በዲፕሎማ 120 ተማሪዎችን በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ማስመረቁን ዶክተር ወርቁ ወዬሳ የኮሌጁ መስራችና ፕረዘዳንት ገልፀዋል።
ከተመሰረተ 11 አመት የሆነው ኮሌጁ በዲፕሎማ 9 ዙር፣ በዲግሪ 8 እና በማስተርስ ደግሞ 4ኛ ዙር እስካሁን ያስመረቀ ሲሆን በአጠቃላይ በእነኚህ ዓመታት ከ4ሺ በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀው ዶኒኮ ሥነ-መለኮት ኮሌጅ በዚህ አመት ከአሜሪካ እና ከተለያዩ አገራት ከሚገኙ ዪኒቨርስቲዎች ጋር በመሆን የፒኤች ዲ ትምህርት እንደጀመረ የገለፀ ሲሆን በተለያዪ ቋንቋ ዘርፎችም ማለትም እንግሊዘኛ፣ ቻይንኛ፣ ግሪክ፣ እብራይሰጥ እና ፈረንሳይኛ በአገር ውስጥ አማርኛ፣ ኦሮምኛ ሲዳምኛ የትርት አይነቶችን ይሰጣል።

Max Planck Internships in Germany 2026 | Fully Funded
Duration: 12-14 weeks
Link: https://scholarshipscorner...
Open to Bachelors, Masters, and Doctoral students worldwide
Benefits: These internships are fully funded, covering living expenses, housing, and round-trip travel.

Comments