Logo
SeledaPost
ነስርን ለማስቆም የሚረዱ ቀላል ምክሮች | Stopping a Nosebleed: A Quick Guide

ነስር ወይም የአፍንጫ መድማት (ኤፒስታክስ) (Epistaxis) ሲያጋጥም ሊያስደነግጥ ይችላል፤ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ከባድ የጤና ችግርን አያመለክትም።

ነስር ወይም የአፍንጫ መድማት ሲያጋጥምዎ ምን ማድረግ እንዳለብዎ እና በምን ጊዜ መጨነቅ እንዳለብዎ እንጠቁምዎ።

ምን ማድረግ አለብን? | What to Do

1️⃣ መረጋጋት (Stay Calm):- ቀጥ ብለው ይቀመጡ፣ እና በትንሹ ወደፊት ያዘንብሉ። ይህ ደም ወደ ጉሮሮዎ እንዳይወርድ ይረዳል።

2️⃣ አፍንጫን መያዝ (Pinch):- አውራ ጣት እና አመልካች ጣትዎን ተጠቅመው ከአፍንጫዎ አጥንት በታች ያለውን ለስላሳ የአፍንጫ ክፍል አጥብቀው (ቆንጥጠው) ይያዙ።

3️⃣ ይዞ መቆየት (Hold):- መድማቱ መቆሙን ለማየት (ለማረጋገጥ) የያዙትን ሳይለቁ ከ 10 እስከ 15 ደቂቃዎች ያህል ይቆዩ።

4️⃣ መተንፈስ (Breathe):- በአፍዎ ይተንፍሱ።

ማድረግ የሌለብን ነገሮች | What to Avoid

ወደ ኋላ አይተኙ ወይም ራስዎን (ጭንቅላትዎን) ወደ ኋላ አያድርጉ። አፍንጫዎን በሶፍት አይሙሉት ወይም አይጠቅጥቁት።

መቼ ወደ ሐኪም መሄድ አለብን? | When to See a Doctor

የሚከተሉት ከተከሰቱ በአፋጣኝ የሕክምና ዕርዳታ ያግኙ፤

🔹 ደም መፍሰሱ ከ20 ደቂቃ በላይ ከቀጠለ።
🔹 የማዞር፣ የድካም ስሜት ከተሰማዎ።
🔹 የአፍንጫ መድማቱ በደረሰብዎ ጉዳት ለምሳሌ በጭንቅላትዎ ላይ በደረሰ ምት የተከሰተ ከሆነ።

የመከላከያ ምክሮች | Prevention Tips

🔹 ቤትዎ ደረቅ ከሆነ አየርን እርጥበት አዘል የሚያደርግ መሳሪያ (humidifier) ይጠቀሙ።
🔹 የአፍንጫዎን መድረቅ ለመከላከል ቀለል ያለ ቫዝሊን በአፍንጫዎ ቀዳዳ ውስጥ ይቀቡ።
🔹 አፍንጫዎን ከመጎርጎር ይቆጠቡ።

seledadotio
seledadotio
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.