26 days ago
ዲጂታል መደመር፡ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት በብሪክስ መድረክ
******************
በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ባለው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በልማት፣ በዲፕሎማሲ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የነደፈችውን ግልጽ አቅጣጫ የሚያንፀባርቅ ነው።
"ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ የተንፀባረቀው ሀሳብ፣ በሀገር ውስጥ እየተተገበረ ካለው የመደመር እሳቤ እስከ ዓለም አቀፉ የብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ድረስ ያለውን ስትራቴጂያዊ ውህደት በሚገባ ያሳያል።
ሁለቱም አስተሳሰቦች አግላይ ከሆነው ነባር የዓለም ሥርዓት ወጥቶ የጋራ ተጠቃሚነትን፣ ፍትሐዊ የባለብዙ-ወገን ማዕቀፍን እና አዎንታዊ ትብብርን መገንባት ላይ ያተኩራሉ።
በኢትዮጵያ ምህዳር ውስጥ የዳበረው የመደመር እሳቤ ቀደምት ዕውቀቶችን በመጠበቅ፣ የወቅቱን አቅሞች በማጣመር እና ጉድለቶችን በመሙላት አዲስ አቅም መገንባትን መሠረት ያደረገ ነው።
ይህ አካታችነትን ያማከለ ፍልስፍና የብሪክስ ጥምረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ውሳኔዎች የተገለሉ አዳጊዎችን ከሚያሳትፈው ሰፊ ዓላማ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት፣ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እና የሰፊው አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕከል በመሆኗ፤ የብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ወደ አፍሪካ አህጉር በስፋት እንዲሰርፅ ትልቅ ድልድይ ሆና ታገለግላለች።
ካፒታልን፣ ቴክኖሎጂን እና ገበያን በማጣመር የጋራ ዕድገት ማምጣት የሚለው የብሪክስ መርህም፣ ሀብት እና አቅምን አቀናጅቶ የላቀ ውጤት ከማምጣቱ የመደመር እሳቤ ጋር ጥልቅ ውህደት ይፈጥራል።
ይህ የዲፕሎማሲ እና የልማት ትስስር ወደ ቴክኖሎጂው ዘርፍ ሲሰፋ ይበልጥ ጎልቶ ይታያል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ የኒው ዴልሂ የብሪክስ ጉባኤ ላይ፣ “የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና ይጫወታል” በማለት ያነሱት ሀሳብ፤ ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ አህጉራዊ መሪ ለመሆን ያላትን ጽኑ አቋም ያረጋግጣል።
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ይህ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት አልፋ ወደ ቴክኖሎጂ አመንጪነት እንድትሸጋገር የሚያስችል ታሪካዊ ተቋም ነው።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጥናት እንደሚያመለክተው፣ አፍሪካ ለዘርፉ ተገቢውን መሰረተ ልማት እና ዝግጅት ካደረገች የሰው ሠራሽ አስተውሎት የአህጉሪቱን ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በ4 በመቶ ሊያሳድገው ይችላል። የዩኒቨርሲቲው መቋቋም ይህን ግዙፍ የኢኮኖሚ አቅም እውን ለማድረግ የተወሰደ ትልቅ ርምጃ ነው።
የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ለሀገር በቀል ችግሮች መፍቻነት የማዋሉ ሥራ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት ተግባራት ጋር ተቀናጅቶ የላቀ ውጤት እያመጣ ይገኛል።
የሰብል በሽታዎች መቆጣጠሪያ ሥርዓት፣ ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ያቀፈው የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣ ከ130 በላይ የመንግሥት አገልግሎቶችን የሚሰጠው የመሶብ ፖርታል እንዲሁም የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ፕሮግራም የዚሁ ስትራቴጂያዊ ጉዞ አካላት ናቸው።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ መገኘቷ የዘርፉን ዕድገት ለማፋጠን ተጨማሪ ዕድል ይፈጥራል።
የብሪክስ አባል ሀገራት በሴሚኮንዳክተር፣ በሱፐር ኮምፒዩቲንግ እና በዲጂታል መሰረተ ልማት ያላቸውን የበለፀገ አቅም ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና የመረጃ ማዕከላት ግንባታ መጠቀም ሰፊ አማራጭ ይከፍታል።
በጉባኤው ላይ እንደተብራራው የቀጣዩ ትውልድ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴሎች በምዕራባውያን ቋንቋዎች ላይ ብቻ ሳይገደቡ የአፍሪካን ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣ ባህሎች እና ቋንቋዎች ያካተቱ መሆን አለባቸው።
አዲሱ የልማት ባንክም ለዚህ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ የሆነውን አማራጭ ፋይናንስ ለማቅረብ ያስችላል።
ከቴክኖሎጂው መስፋፋት ጎን ለጎን የሚመጡትን የሳይበር ደኅንነት ሥጋቶች፣ የግል መረጃ መጣስ እና የአልጎሪዝም አድልዎን ለመከላከል ኢትዮጵያ ጠንካራ የሕግ እና ፖሊሲ ማዕቀፎችን ዘርግታለች።
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ብሔራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፖሊሲ የዘርፉ የአሠራር ሥርዓቶች ግልፅ፣ ተጠያቂነት ያለባቸው እና ከሰው ልጅ ቁጥጥር የማይወጡ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
በተጨማሪም የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ እና የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ የዜጎችን የመረጃ ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር ብሔራዊ የመረጃ ደኅንነትን ለመጠበቅ ጉልህ ድርሻ አላቸው።
የመደመር እሳቤ እና የብሪክስ ዓላማ በፅንሰ-ሀሳብ እና በስትራቴጂ ደረጃ የሚደጋገፉ፣ አካታችነትን እና የጋራ ብልፅግናን ማዕከል ያደረጉ የፖሊሲ አተያዮች ናቸው።
ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ መገኘቷ ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲጎለብት ከማድረጉም በላይ፣ የአፍሪካን ድምፅ እና የቴክኖሎጂ ፍላጎት በዓለም መድረክ ለማስተጋባት አቅም ሆኗታል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ የወጡት ብሔራዊ ፖሊሲዎች እና የሕግ ማዕቀፎች ደግሞ የቴክኖሎጂውን ሥጋቶች አስቀድሞ በመገደብ በራስ መተማመን እና በሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ የቴክኖሎጂ ዕድገትን ለማረጋገጥ አስችለዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #digitalethiopia #brics2026 #medemer #artificialintelligence #techtransfer #aiuniversity #globalsouth #innovation

Comments