3 months ago
የአፍሪካው ቁንጮ አሊኮ ዳንጎቴ አልተቻሉም
#ethiopia | የአህጉራችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ፣ በፈረንጆቹ 2026 ዓመት አስገራሚ የሀብት እድገት በማስመዝገብ ግስጋሴያቸውን ቀጥለዋል።
እንደ ብሉምበርግ የቢሊየነሮች መረጃ መሠረት፣ የባለሀብቱ ጠቅላላ የሀብት መጠን 34.0 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም በዓለም የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ ወደ 69ኛ ደረጃ ከፍ እንዲሉ አድርጓቸዋል።
ዳንጎቴ በዚህ ዓመት ብቻ 3.99 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ማግኘት የቻሉ ሲሆን፣ ይህም በአህጉሪቱ ያላቸውን የበላይነት ይበልጥ አጠናክሮታል።
የዚህ የሀብት ዝላይ አንዱ ተጠቃሽ ምክንያት በሌጎስ የሚገኘው ግዙፉ የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ስራውን በሙሉ አቅሙ መጀመሩ ነው። ማጣሪያው በቀን 650,000 በርሜል የማምረት አቅሙን መጠቀም የጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጥታ የጄት ነዳጅ አቅርቦት መጀመሩ ተረጋግጧል።
ይህ ስምምነት ለአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድ የኢነርጂ ዋስትናን የሚሰጥ ሲሆን፣ በተለይም በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ በሚታየው የአቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ለነዳጅ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ለመሙላት እንደ ትልቅ ዕድል ተቆጥሯል። ማጣሪያው የጄት ነዳጅ ኤክስፖርቱን በቀን ወደ 158,000 በርሜል አሳድጓል።
በአፍሪካ የኢንዱስትሪ ባለቤትነት እና በንግድ ትስስር ረገድ ይህ የዳንጎቴ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋርነት አዲስ ምዕራፍ እንደሆነ ይታመናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #capitalnews #alikodangote #ethiopianairlines #africaeconomy #businessnews #dangoterefinery #aviation #ethiopia #nigeria #wealthreport

5 months ago
አሊኮ ዳንጎቴ ነዳጅ ቀነሱ
#ethiopia | በናይጄሪያው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ ባለቤትነት የሚመራው ግዙፉ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ በተጣሩ የነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን ይፋ አደረገ።
ኩባንያው ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ በቤንዚንና በናፍታ ምርቶች ላይ ይህ የዋጋ ማስተካከያ የተደረገው በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የታየውን የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ መቀነስ ተከትሎ ነው። ባለፈው ሰኞ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በአንድ በርሜል 119 ዶላር በመንካት ከሰኔ 2022 ወዲህ ከፍተኛውን የዋጋ ጭማሪ አሳይቶ ነበር።
ሆኖም የቡድን ሰባት (G7) አባል አገራት ያላቸውን የነዳጅ ክምችት ወደ ገበያ ሊለቁ እንደሚችሉ ማስታወቃቸውን ተከትሎ፣ የነዳጅ ዋጋ በአንድ በርሜል ከ90 ዶላር በታች ዝቅ ብሏል። የዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካም ይህንን የዓለም አቀፍ ገበያ መረጋጋት መሠረት በማድረግ ለተጠቃሚዎች የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቀደም ሲል በመካከለኛው ምስራቅ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የኃይል እጥረት ለመከላከልና የናይጄሪያን የነዳጅ ዋስትና ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸው ነበር።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nigeria #dangoterefinery #fuelprice #energynews #globalmarket #oilandgas #africaeconomy

Comments