10 months ago
ፎቶ ተከስተብርሃን
አቶ ተከስተብርሃን ያዘው ይባላሉ። የጉርሱም ከተማ የመጀመሪያው ፎቶግራፈር ናቸው። "ፎቶ ተከስተ ብርሃን" በሚል መጠሪያ በመላው ጉርሱም ይታወቃሉ።ፎቶ ተከስተን የማያቅ የጉርሱም ሰው የለም ማለት ይቻላል ። ስማቸው ከጉርሱም ከተማ ጋር በተደጋጋሚ ይነሳል።
አቶ ተከሰተብርሃን ትውልዳቸው ግራዋ ከተማ ነው። በልጅነታቸው ጉርሱም አክስታቸው ጋር ይመላለሱ እንደነበር ይናገራሉ።ጉጋዴን እና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ላይ ሰርተዋል ።
ከ1967 ዓም ጀምሮ ፎቶግራፍ ማንሳት የጀመሩ ሲሆን ለረጅም አመታት በዚህ ሞያ አገልግለዋል። በ1969 ዓም ጉርሱም ከተማ ጠቅልለው እንደገቡ የሚናገሩት አቶ ተከሰተ እስከ 1983 ማለትም ለአስራ አራት አመታት ያህል በዚህ ሞያ ጉርሱም ከተማ ላይ ሰርተዋል ።
ስለ ካሜራቸው ጠይቀናቸው ... እንዲህ አሉን ...
" ጉርሱም ከተማ ባዶ እጄን ነው የመጣሁት ካሜራ አልነበረኝም, በግዜ ውድ የነበረ ሰአት ነበረኝ እርሱ ሸጬ ካሜራ ገዛው ፎቶ ማንሳት ጀመርኩ “ አሉን
ከፎቶግራፍ ስራ ቀጥሎ ሌሎች ስራዎችን ይሰሩ እንደነበር አጫውተውናል።
አቶ ተከስተ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው። ዛሬም ኑራቸው ጉርሱም ከተማ ነው። እንደዚህ ቀደሙ ተሯሩጠው መስራት የሚችሉ አይመስሉም። የመጨረሻ ልጃቸው ማየት የተሳናት ነች።
ወደ ቤታቸው ጓራ ብለን ባለቤታቸውን እና ሴት ልጃቸውን ጠየቅ አደረግን ከመንገድም የመጨረሻ ወንድ ልጃቸውን አስተዋወቁን።
ድጋፍ እንደሚፈልጉ ለመረዳት ጊዜ አልወሰደብንም እርሷቸውም ትንሽ ጠቋም አደረጉን። እኛም እንደተስፈኛ ፎቶግራፈርነታችን በግሩፕችን ስም ( Bored Cellphone ) የተወሰነ ብር ሰብሰብ አድርገን በሞያቸው ለሰጡት አገልግሎት አመስግነን ቀበል አደረግናቸው።
መረቁን...
"ለካስ ሰው አለኝ ... ሀገራችሁን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ። ለወግ ለማዕረግ ያብቃችሁ። ተባረኩ"
እንቧ ባይናቸው ግጥም ብሎ ነበር። ተመሰጋግን ስልክ ተቀብለን እንደምደውል ቃል ገብተን ተለያየን።
የጉርሱም ናፍቆት ይቀጥላል ...
Via: Mastewal Eyasu
.#kundudo #diredawa #bcaatour #tecno #camon40 #tecnoai #7yearsofboredcellphone

Comments