4 months ago
ጋሽ አንተነህ በትንሳዔ ዋዜማ 2 ሚሊዮን ብር ተበረከተላቸው
#ethiopia | አዋሽ ባንክ 1 ሚሊዮን ብር የሸለመ ሲሆን፣ ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን እና ከሊያን ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመተባበር ተጨማሪ 1 ሚሊዮን ብር አበርክተዋል። በአጠቃላይ ደራሲ አንተነህ የ2 ሚሊዮን ብር ስጦታ ተረክበዋል።
ደራሲ አንተነህ ከጤና እክላቸው ጋር እየታገሉ ላሳዩት ከፍተኛ የሥራ ተነሳሽነትና ውጤታማነት የተሰጠ እውቅና ነው። ደራሲው ያዘጋጇቸውን የሥራ ውጤቶችም ሙሉ በሙሉ ሽጠው ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።
የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ባንኩ በየዓመቱ ለማህበራዊ ኃላፊነት አገልግሎት ከ500 እስከ 700 ሚሊዮን ብር እንደሚመድብ ጠቁመው፣ እንደ ደራሲ አንተነህ ያሉ ጠንካራና ለሀገር ባለውለታ የሆኑ ዜጎችን መደገፍ የኩራት ምንጭ እንደሆነ ገልጸዋል።
ይህ እውቅና ለታታሪ ዜጎች የሚሰጥ ማበረታቻና የባለሙያዎችን ድካም የሚመጥን ተግባር መሆኑ በዕለቱ ተመላክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #sputnik #ደራሲ_አንተነህ #አዋሽ_ባንክ #ታሜሶል #ታታሪነት #ኢትዮጵያ #awashbank #tamesol #ethiopia #kidame_gebeya #etbusinessview

አዋሽ ባንክና ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ለሀገር ባለውለታዎች የገንዘብ ሽልማት አበረከቱ
#ethiopia | አዋሽ ባንክ ከታሜሶል ኮሙኒኬሽን ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሲያካሂድ የቆየው የአዋሽ ግራንድ ፕሮሞ ፋሲካ ኤክስፖ 2018 የማጠቃለያ መርሃ ግብር ደማቅ በሆነ የሽልማት እና የምስጋና ስነ-ስርዓት ተከናወነ።
በመርሐግብሩ ላይ በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲዘዋወር በነበረው ምስል በባሌ ሮቤ ከተማ ጥቃት ደርሶባቸው የነበሩት የ35 ዓመታት የጤና ባለሙያው አቶ ዋቆ ከድር ቱጌ በአዋሽ ባንክ የ500 ሺህ ብር የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
አቶ ዋቆ ሀገራቸውን በህክምና ሙያ ሲያገለግሉ የቆዩና በግጭት ወቅት ልጃቸውን ያጡ የሀገር ባለውለታ ቢሆኑም፣ በጡረታ ጉዳያቸው ላይ በነበሩበት ወቅት በማስተዋል በጎደላቸው ወጣቶች ድብደባና እንግልት ደርሶባቸው የነበረ ሲሆን፣ ባንኩ ይህንን የሀገር ባለውለታ ክብር ለመመለስና መቋቋሚያ እንዲሆናቸው ይህንን ድጋፍ አድርጓል።
በሌላ በኩል በነርቭ ህመም እየተሰቃዩም ቢሆን ተስፋ ሳይቆርጡ በመስቀል አደባባይ መግቢያ ላይ መጽሐፍ በመሸጥ የሚተዳደሩት ታታሪው ደራሲ አንተነህ ወንድሙ የተለየ እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
ደራሲ አንተነህ ላሳዩት አስደናቂ የስራ ትጋት አዋሽ ባንክ የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሰጠ ሲሆን፣ ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን እና ሊያን ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመተባበር ተጨማሪ 1 ሚሊዮን ብር በመጨመር በአጠቃላይ የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተረክበዋል።
የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በመርሐግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ባንኩ በየዓመቱ ለማህበራዊ ኃላፊነት አገልግሎት ከ500 እስከ 700 ሚሊዮን ብር እንደሚመድብ ጠቁመው፣ ዛሬም የሀገር ባለውለታዎችንና ጠንካራ ዜጎችን በማገዙ ኩራት እንደሚሰማቸው ገልጸዋል።
በዚህ ታላቅ መርሃ ግብር ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የባለ እጣዎች ሽልማት ይፋ ሲደረግ፣ ወጣት ሳሮን ሸዋንግዛው የዕለቱ ደማቅ ተሸላሚ ሆናለች።
ከአዲስ አበባ ጎፋ አካባቢ የመጣችው ወጣት ሳሮን፣ በኤክስፖው ማጠቃለያ ላይ በወጣው እጣ የቢዋይዲ ሴጉል 2025 (BYD Seagull 2025) ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን ማሸነፍ ችላለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

Comments