27 days ago
ሁለት የአሜሪካ የጦር ጄቶች በአየር ላይ ተጋጭተው ተከሰከሱ
በአሜሪካ አይዳሆ ግዛት በሚገኘው የነፋስ ተራራ የባህር ኃይል ጣቢያ በተካሄደው የ"Gunfighter Skies" የአየር ትዕይንት ላይ፣ ሁለት የአሜሪካ ባህር ኃይል EA-18G Growler የጦር ጄቶች በአየር ላይ ተጋጭተው መከስከሳቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት እና የዐይን እማኞች ገልጸዋል።
ሁለቱ የኤሌክትሮኒክስ ውጊያ አውሮፕላኖች የአየር ላይ ትዕይንት እያሳዩ ባሉበት ወቅት የተጋጩ ሲሆን፣ ከጣቢያው በስተሰሜን ምዕራብ 2 ማይል ርቀት ላይ መከስከሳቸው ተረጋግጧል።ከአደጋው በኋላ በቪዲዮ ምስሎች ላይ 4 አብራሪዎች በአየር ላይ በፓራሹት አማካኝነት ከአውሮፕላኖቹ እራሳቸውን አውጥተው ሲወርዱ ታይተዋል።
አደጋውን ተከትሎ የጦር ሰፈሩ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታው ላይ የማዳን ስራ እያከናወኑ ይገኛል። ስለ አብራሪዎቹ ወቅታዊ የጤና ሁኔታ ዝርዝር መረጃ አልወጣም።
seledadotio

1 month ago
በምሥራቅ ጉራጌ ዞን አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ አምስት ሰዎች በታጣቂች ተገደሉ።ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ትናንት ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ በተኙበት ገብተው መሣሪያ በመተኮስ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሟች ዘመዶች ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡
ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳ ኢንሴኖ በተባለ ከተማ ውስጥ መሆኑን ለዶቼ ቬለ የተናገሩ አንድ የሟች የቅርብ ዘመድ «ታጣቂዎቹ በተለምዶ አየር ጤና ተብሎ በሚጠራው መንደር እየተኮሱ ነው የገቡት፡፡ወደ መኖሪያ ቤት በመግባት አምስት ሰዎችን ተኩሰው ከገደሉ በኋላ ተመልሰው ሄደዋል፡፡ከሟቾቹ መካከል አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ እናት ከሦስት ልጆቿ ጋር ነው» ብለዋል ፡፡
በከተማው ነዋሪ የሆኑ ሌላ የዐይን አማኝ በበኩላቸው ግድያው መፈጸሙን አረጋግጠው ጥቃት አድራሾቹ በአካባቢው በሽፍትነት የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ሳይሆኑ እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡ዶቼ ቬለ ጥቃቱን በተመለከተ ለማነጋገር በስልክ ያገኛቸው የምሥራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ሰረላ መረጃውን አሰባስበው እንደሚገልጹ ቀጠሮ ይዘው ነበር፡፡ነገር ግን በቀጠሮው ሰዓት ሥልካቸው ዝግ በመሆኑ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡
Via DW

2 months ago
የዓይን መቅላት መንስኤዎችና ምልክቶቻቸዉ
⏩ #የአይን መቅላት የተለመደና የብዙ ሰው ችግር ነው የአይን መቅላት አይን ውስጥ ያሉ የደም ስሮች ወደ ላይኛው የአይን ክፍል በተለያዩ ምክንያቶች ተለጥጠው (dilated) በሚወጡበት ወቅት ይፈጠራል፡፡
የዓይን መቅላት ገጽታ ሊለያይ ይችላል።
በነጩ የዓይን ክፍላችን ላይ ሮዝ ወይም ቀይ መስመሮች ያሉ ይመስላሉ ወይም ሙሉውን ሮዝ ወይም ቀይ ሆኖ ሊታይ ይችላል።
👉 #ምልክቶች
🔹 የአይን መቅላት
🔹 ማሳከክ
🔹 አይን ማዝ መያዝ
🔹 ዉሃ የመሰለ የአይን ፈሳሽ( እንባ መብዛት)
🔹 ማቃጠል
🔹 ድርቀት
🔹 ህመም
🔹 ብርሃን አለመቻል
🔹የዓይን ብዥታ
👉 #መንስኤዎቹ
🔹 ለፀሐይ ብርሃን ከመጠን በላይ መጋለጥ
🔹 የዓይን መድረቅ
🔹 የዓይን አለርጂዎች
🔹 የዓይን ብግነቶች (conjunctivitis)
🔹 የአየር ብክለት
🔹 ጭስ (ከእሳት ጋር የተዛመደ ፣ የሲጋራ ጭስ ፣ ወዘተ)
🔹 ደረቅ አየር
🔹 አቧራ
🔹 የኬሚካል ተጋላጭነት (በመዋኛ ገንዳዎች ውስጥ ክሎሪን ፣ ወዘተ)
🔹 ለእረጅም ሰዓት ስክሪኖችን መጠቀም
🔹 በሃኪም ያልታዘዙ የዕይታ መነፅሮችን መጠቀም
👉 #የዐይን መቅላት ካለብዎት የሚከተሉትን ይጠንቀቁ
🔹 ዓይን አለማሸት
🔹 ችግር ያለበት ዓይን ነክቶ ሌላኛዉን ዓይን አለመንካት
🔹 አለርጂ ካለብዎ የአይን መዋቢያዎችን አለመጠቀም
🔹 በሃኪም ያልታዘዘ ምንም አይነት የዓይን ጠብታ አለመጠቀም
🔹 አለርጂ ከሚሆኑቦት ነገሮች መራቅ

3 months ago
Conjunctivitis/ በብዛት እንደሚታወቀው "የአይን መቅላት/ብግነት"
ይህ በሽታ conjunctiva ተብሎ የሚጠራው የአይን ክፍል ሲቆጣ ወይም ሲበከል የሚከሰት ነው።
ኮንጃንክቲቫ ማለት የአይን ሽፋኖቻችንን የውስጥ ክፍል እና የአይናችንን ነጭ ክፍል (ስክሌራ) የሚሸፍን ስስ እና ግልፅ የሆነ የቆዳ ሽፋን ነው።
ዋና ዋና አይነቶች እና መንስኤዎች:
የተለያዩ የኮንጃንክቲቫይተስ አይነቶች አሉ፣ እያንዳንዳቸውም የተለያየ መንስኤ አላቸው፦
በቫይረስ የሚመጣ (Viral Conjunctivitis):
ምልክቶች: ውሀማ ፈሳሽ፣ መቅላት፣ የማቃጠል ስሜት፣ አንዳንዴ አይን ውስጥ እንደቆሻሻ ያለ ስሜት። ብዙውን ጊዜ በአንድ አይን ይጀምርና ወደ ሌላኛው ሊዛመት ይችላል። ከጉንፋን መሰል ምልክቶች ጋር አብሮ ሊታይ ይችላል።
በባክቴሪያ የሚመጣ (Bacterial Conjunctivitis):
ምልክቶች: ወፍራም፣ መግል የመሰለ ፈሳሽ (ብዙውን ጊዜ ቢጫ ወይም አረንጓዴማ) በተለይ ከእንቅልፍ ሲነቁ የዐይን ሽፋኖችን ሊያጣብቅ ይችላል። መቅላት፣ የማቃጠል ስሜት እና አንዳንዴም የዐይን ሽፋኖች ማበጥ።
በአለርጂ የሚመጣ (Allergic Conjunctivitis):
ምልክቶች: ከፍተኛ የማሳከክ ስሜት፣ መቅላት፣ የእንባ መብዛት እና አንዳንዴም የዐይን ሽፋኖች ማበጥ። ብዙውን ጊዜ በሁለቱም አይኖች ላይ ይከሰታል። እንደ ማስነጠስ እና ንፍጥ ካሉ ሌሎች የአለርጂ ምልክቶች ጋር አብሮ ይከሰታል።
Irritant or Chemical Conjunctivitis:
መንስኤ: እንደ ጭስ፣ በመዋኛ ገንዳ ውስጥ ያለ ክሎሪን፣ ትነት፣ አይን ውስጥ የገባ ባዕድ ነገር ወይም ጠንካራ ኬሚካሎች ባሉ irritant ነገሮች ይከሰታል።
የተለመዱ ምልክቶች (እንደ አይነቱ ሊለያዩ ይችላሉ):
በአይን(ቹ) ነጭ ክፍል ላይ መቅላት ወይም ሮዝማ መሆን።
የኮንጃንክቲቫ እና/ወይም የዐይን ሽፋኖች ማበጥ።
የእንባ መብዛት ወይም ውሀማ አይኖች።
ፈሳሽ (ውሀማ፣ ንፍጥ መሰል ወይም መግል መሰል)።
የማሳከክ፣ የማቃጠል ወይም የመለብለብ ስሜት።
አይን ውስጥ እንደ አሸዋ ያለ ስሜት።
በተለይ ጠዋት ላይ የዐይን ሽፋኖች ወይም የዐይን ሽፋሽፍቶች ላይ ቅርፊት መፈጠር።
አንዳንዴ ብርሃን የመፍራት ስሜት (ፎቶፎቢያ) ሊከሰት ይችላል።
ህክምና:
ህክምናው እንደ መንስኤው ይለያያል፦
መከላከያ መንገዶች:
እጅዎን በተደጋጋሚ እና በደንብ ይታጠቡ
አይንዎን ከመንካት ወይም ከማሸት ይቆጠቡ።
ፎጣ፣ የእጅ መታጠቢያ ጨርቅ፣ ትራስ ልብስ፣ የአይን መዋቢያዎች ወይም የአይን ጠብታዎችን በጋራ አይጠቀሙ።
የአይን መነፅር (contact lenses) የሚጠቀሙ ከሆነ በአይን ሐኪምዎ እንደታዘዘው ያፅዱ እና ይተኩ።

መልካም ክርስቲያኖች የነበሩት ወላጆቹ ገና በልጅነቱ ሃይማኖትና ምግባርን ጠንቅቀው አስተምረውታል፡፡
ግብጻዊ ቅዱስ አባ ኅልያን ጾምንና ጸሎትን የሚያዘወትር በሥጋዊ ሞያውም የተመሰገነ አንጥረኛ በመሆኑ በወዙ በላቡ ሠርቶ ያገኘው ሃብት ነበረው፡፡ ከገቢውም ነዳያንን ያስብ ነበር፡፡ አንድ ቀን አንዲት ዐረባዊት ሴት መጥታ የወርቅ የጆሮ ጌጥ እንዲሠራላት ትጠይቀውና ይሠራላታል፡፡ የጀሮ ጌጡን ከሰጣት በሁዋላ ግን "ዋጋውን አልሠጥህም" ትለዋለች፡፡ እርሱም "ምነው እህቴ! የደከምኩበትን ለምን አትከፍይኝም?" ሲላት ገላዋን አጋልጣ "ሴትነቴን ልስጥህ" ብላ ለዝሙት ጠየቀችው፡፡ ድንግሉ ኅልያን ከአነጋገሯና ከድርጊቷ የተነሳ በጣም ደነገጠ፡፡ ከፊቷ ላይ አማትቦ፣ ገስጿት ወደ ቤቱ ሔደ፡፡ ሌሊትቱን ሙሉ ሲያዝን አድሮ ሊነጋጋ ሲል ይሕችን ዓለም ሊተዋት በልቡ ወሰነ፡፡
በወጣት ጉልበቱ ደክሞ ያፈራው ስጋዊ ሃብት ቢተርፈውም ናቀው፡፡ ነዳያንንም ሁሉ ወደ ቤቱ ጠርቶ ሙሉ ንብረቱን አከፋፈላቸው፡፡ የለበሳትን ልብስ ብቻ ስትተርፈውም ፈጽሞ ደስ እያለው ከተማውን ጥሎ ወደ በርሃ ተሰደደ፡፡ ልቡናን የሚመረምር ጌታ ሊመራው ወዷልና 3 ስውራን ቅዱሳንን ላከለት፡፡ እየመሩም ወስደው በግራና በቀኝ በውሃ የታጠረች፣ ደኗ የዐይን ደስታ የሆነ ስፍራ አደረሱት፡፡ አካባቢው እንኩዋን ሰው እንስሳትም አልነበሩበትም፡፡ ከቦታዋ እንደገቡ በላዩዋ ላይ ዕንቁ ያለባት የብርሃን ዘንግ ሰጥተውት "ወደ ፈጣሪ እንስገድ" አሉት፡፡ ሰግዶ ቀና ሲል ግን 3ቱም ተሠውረውታል፡፡ አባ ኅልያን ከቅዱሳኑ በመለየቱ ፈጽሞ አለቀሰ፡፡ ተጋድሎውን ግን በጾምና በጸሎት፣ በስግደትም አጠነከረ፡፡ የሚመገበውም፣ የሚለብሰውም ቅጠል ነበር፡፡ ቅዱሳኑ የሰጡት ዘንግ ሲመሽ ግሩም ብርሃን ታወጣ ነበርና በእርሱ ዘንድ ሌሊት የሚባል ነገር አልነበረም፡፡
በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋም ለበርካታ ዓመታት ከሰው ተለይቶ ኖረ፡፡ አጋንንትም ያመጡበትን ፈተኑት በእግዚአብሔር ኃይል አለፈው፡፡ ሊቋቋሙት ባልቻሉ ጊዜም ሰው ተመስለው ወደ ከተማ ሔደው ሽፍቶችን ላኩበት፡፡ በእግዚአብሔር ኃይልም አሸንፏቸው፣ አስተምሮም ሸኛቸው፡፡ የሚያርፍበት ዕለት ሲደርስ የተሠወሩበት 3ቱ ቅዱሳን ተገለጡለት፡፡ በደስታ ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አባ ኅልያን ሐምሌ 9 ቀን ወደ ምሥራቅ ሰግዶ ዐረፈ፡፡ 3ቱ ቅዱሳንም ሥጋውን ገንዘው በበዓቱ ቀብረውት፣ ዜና ሕይወቱንም ጽፈው አስቀምጠው ተሠወሩ፡፡ ገዳማውያን ዓለምን ትተው የመውጣታቸው ምክንያት የክርስቶስ ፍቅር እንጂ ሃብት ማጣት አይደለም፡፡ ያላቸውን ሁሉ ሰጥተው ወጥተዋልና ገዳማትን እንደግፍ በዓታቸውን እናጸና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

Sponsored by
Surafel
3 months ago
🙏 ለወንድማችን ለዶ/ር ያዕቆብ ጨመረ የህይወት አድን ጥሪ!
#ethiopia | በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የዐይን ህክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር በመሆን ወገኖቹን በታማኝነት እያገለገለ የሚገኘው ወጣት ሀኪም ዶ/ር ያዕቆብ ጨመረ፣ በአሁኑ ወቅት አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ይሻል።
የሁኔታው ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የጤና ሁኔታው
ህመሙ፦
ከሦስት ዓመት በፊት በጭንቅላት ካንሰር (Brain Cancer) ታሞ በህንድ ሀገር በደረገው ቀዶ ጥገና፣ ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ ተሽሎት ነበረ።
ወቅታዊ ሁኔታ፦
ካንሰሩ በአሁኑ ወቅት ዳግም ስላገረሸበት (Cancer Recurrence)، የሃኪሞች ቦርድ በአስቸኳይ ወደ ህንድ ሀገር ሄዶ እንዲታከም ወስነዋል።
የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ
የህክምናው ወጪ ከዶ/ር ያዕቆብ እና ከቤተሰቦቹ አቅም በላይ በመሆኑ፣ እኛ ወገኖቹ የቻልነውን በማድረግ ይህንን ውድ ሀኪም እንድንታደገው ጥሪ ቀርቧል።
የባንክ አካውንት መረጃ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000272436014
የአካውንት ስም፦ ያዕቆብ ጨመረ (Yaqob Chemere)
📞 ለተጨማሪ መረጃ፦
ስልክ፦ 0910144989
ሀኪም ማለት የሀገር ተስፋ ነው። ዶ/ር ያዕቆብ ነገ የብዙዎችን ዐይን እንዲያበራና ወገኖቹን ማገልገሉን እንዲቀጥል ዛሬ እኛ እጃችንን እንዘርጋለት።
"ቸርነት ለራስ ነው!"
ስለምታደርጉት ትብብር ሁሉ ከወዲሁ ከልብ እናመሰግናለን።
#ዶ/ርያዕቆብጨመረ #የህይወትአድንጥሪ #ድሬዳዋዩኒቨርሲቲ #ኢትዮጵያ #ደግነት #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

እስራኤል በቴህራን የሚገኘውን የፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት ደበደበች
የሟቾች ቁጥር 787 ደርሷል
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በተሸጋገረበት በዚህ ወቅት፥እስራኤል በኢራን መዲና ቴህራን በሚገኘው "የመሪዎች ቅጥር ግቢ" እና በፕሬዝዳንቱ ፅሕፈት ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች።
ከቅዳሜ ጀምሮ በቴህራን "እያንዳንዱ የከተማዋ ክፍል" ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን የዐይን እማኞች እየገለጹ ነው።
አዳዲስ የወጡ ምስሎችም በከተማዋ ምስራቃዊ አቅጣጫ ግዙፍ ፍንዳታዎች መከሰታቸውን ያሳያሉ።
የቀይ ጨረቃ ባወጣው መረጃ መሠረት፥ የአሜሪካና የእስራኤል ጥቃት ከተጀመረ ወዲህ በኢራን የሟቾች ቁጥር 787 ደርሷል።
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከኢራን በተነሱ ሁለት ድሮኖች መመታቱ ተረጋግጧል።
በሌላ ግንባር እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምድር ወረራዋን እንደምታሰፋና "ተጨማሪ ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ለመቆጣጠር" ወታደሮቿ ወደፊት እንደሚገሰግሱ አስታውቃለች።
ግጭቱን ተከትሎ የዓለም አቀፍ የጋዝ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየናረ ይገኛል።
ሰኞ ዕለት የ50 በመቶ ጭማሪ የታየ ሲሆን፥ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ ተጨማሪ የ30 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
Ethio Fm

5 months ago
የዐይን መድረቅ
ዐይን መድረቅ በህክምና አጠራሩ "ኬራቶ ኮንጀክቲቫይተስ ሲካ" ሲባል ዐይን በተገቢው እንባ ማምረት ባለመቻሉ ወይም እንባ ቶሎ መትነን ምክንያት ይፈጠራል ።
⏩ #ምልክቶች
🔺 የአይን መቆጥቆጥ፣ ማቃጠል
🔺 ብርሃን መጥላት( ምቾት መንሳት)
🔺 የአይን መቅላት
🔺 አይናችን ላይ ባእድ ነገር እንዳለ መሰማት
🔺 የአይን መድከም
🔺 የአይን ብዥታ
⏩ #መንስኤ
🔺 የአይን ሌንስ መጠቀም
🔺 የእንባ አመንጪ እጢ በተገቢው አለመስራት
🔺 የአይን አለርጂ
🔺 እርግዝና የቫይታሚን ኤ እጥረት
🔺 ለአንዳንድ ህመሞች የሚታዘዙ መድሃኒቶች
🔺 የሆርሞን ህክምናዎች
🔺 የስኳር ህመም
🔺 ተደጋጋሚ የአይን ኢንፌክሽን
⏩ #መፍትሄ
🔺 የኮምፒውተር አጠቃቀማችንን ማስተካከል( ከዐይናችን ማራቅ)
🔺 ቤታችን እርጥበታማ አየር እንዲኖር ማድረግ ( ስቲም ማድረግ)
🔺 ኦሜጋ 3 የበለጸጉ ምግቦችን መጠቀም
🔺 ቫይታሚን ኤ መውሰድ
🔺 የአይን ማለስለሻ ጠብታዎችን መጠቀም
🔺 ከጭስ መራቅ
🔺 ለረጅም ሰአት አንድ ነገር ላይ አተኩሮ አለመቆየት
🔺 ባስ ካለ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ
ህክምና ማድረግ ተገቢ ነው

በሐዋሳ ዛሬ ንጋት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሙሽሮችን ጨምሮ የ4 ሰዎች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አለፈ
🕯️ ስለ ሟቾች፦
2ቱ ሙሽሮች፦ ገና ትዳር መስርተው በጫጉላ ጊዜያቸው ላይ የነበሩ ሲሆን፣ በመኝታ ክፍላቸው ውስጥ ተኝተው ሳለ ህይወታቸው አልፏል።
2ቱ በመኪናው ውስጥ የነበሩ፦ የጭነት መኪናው አሽከርካሪ እና ረዳቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።
📍 አደጋው እንዴት ደረሰ?
ከሐዋሳ ወደ ሰደ ቦረ ዕቃ ጭኖ ይጓዝ የነበረ "አይሱዝ" የጭነት መኪና፣ ከመንገዱ ወጥቶ አጥር በመጣስ የሙሽሮቹን መኝታ ቤት ሰብሮ በመግባት አደጋውን አድርሷል።
💔 ያልታሰበው የሞት ግብዣ
ጥንዶቹ አደጋው የደስታ ቤታቸውን ወደ ሀዘን ቀይሮታል። አደጋው የደረሰው መኪናው በከፍተኛ ፍጥነት ይጓዝ ስለነበር አሽከርካሪው መቆጣጠር በማቃቱ እንደሆነ የዐይን እማኞች ተናግረዋል።
ነዋሪዎች መንገዱ ለቤቶች ቅርብ በመሆኑ የፍጥነት ገደብ እንዲደረግ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ እንደነበርም ተመላክቷል።

🐎 " ሰካራሙ ሰውዬ እና አስተዋዩ ፈረስ''
#ethiopia | በሉዊዚያና ግዛት የተከሰተ አስገራሚ ድራማ በዩናይትድ ስቴትስ ሉዊዚያና ግዛት ውስጥ አንድ ግለሰብ በከፍተኛ ሁኔታ ሰክሮ መኪና ከመንዳት ይልቅ "አስተማማኝ" ያለውን አማራጭ በመምረጥ በፈረስ ተጭኖ ወደ ቤቱ ለመሄድ ሲሞክር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
🥃 ከመጠጥ ቤት ወደ ፈረስ ጀርባ
ግለሰቡ በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ አመሽቶ ከወጣ በኋላ፣ የመኪናውን ቁልፍ ከመያዝ ይልቅ የፈረሱን ልጓም መያዝን መርጧል። በከተማዋ መንገዶች ላይ በፈረስ ሲጓዝ ያስቆሙት የፖሊስ አባላት በሁኔታው ግራ ተጋብተው ጥያቄ ሲያቀርቡለት፤ ግለሰቡ በልበ ሙሉነት “እኔ ባላውቅም ፈረሱ መንገዱን ያውቃል” የሚል አስቂኝ ምላሽ ሰጥቷቸዋል።
🐴 ታማኙ እና ረጋው ፈረስ
የዐይን እማኞችና ፖሊሶች እንደገለጹት፣ ጋላቢው ራሱን መቆጣጠር በማይችልበት የክፉኛ ስካር ውስጥ ቢሆንም ፈረሱ ግን እጅግ የሚደነቅ ስነ-ምግባር አሳይቷል። ከኋላው የሚከተሉት የፖሊስ መኪና መብራቶችና ሳይረኖች ሳይረብሹት፣ መስመሩን ጠብቆና ረግቶ ጌታውን ወደ ቤት ለማድረስ ሲጓዝ ታይቷል። "ሰውየው አስተዋይነቱን ባጣበት ሰዓት እንስሳው ግን ኃላፊነት የሚሰማው ሆኖ ተገኝቷል" በሚል በነዋሪዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።
⚖️ የሕግ ተጠያቂነት
ምንም እንኳን በሉዊዚያና ሕግ ሰክሮ ፈረስ መጋለብ እንደ መኪና ማሽከርከር በከባድ ወንጀል ባያስቀጣውም፣ ግለሰቡ ግን ከሕግ አላመለጠም። ፖሊስ ግለሰቡን "የሕዝብን ሰላም በማወክ" ወንጀል የከሰሰው ሲሆን፣ ለፈጠረው ሁከትም ቅጣቱን እንደሚቀበል ታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ሉዊዚያና #አስቂኝዜና #ፈረስ #ታማኝነት #አሜሪካ #መንገድይችላል #እንስሳት #strangenews #louisiana #horserider

የአርቲስት ያየህይራድ አላምረው (1957-2017)÷ መዘክር እና የስብስቦቹ ቤተመጻሕፍት፤
(ሠርጸ ፍሬስብሐት)
አጭር ማስታወሻ
#ethiopia | ኹላችን በምናውቀው ታሪኩ፤ ያየህይራድ አላምረው፤ የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ፕሮዲውሰር እንዲያም ሲል የታላላቅ ሙዚቃዊ ፕሮጀክቶች ነዳፊ ኢንተርፕረነር ነበር፡፡ ለብዙዎቻችን በሚያስገርም እና በሚያስደንቅ፣ ብዙም ባልተነገረለት፣ ጥቂት የቅርቦቹ በኾኑ ወዳጆቹ እና በቤተሰቦቹ ዘንድ ብቻ በሚታወቅ ልምዱ ደግሞ፤ የንባብ ፍቅሩን ብዙ እጥፍ የሚያስከነዳ መጽሐፍ ሰብሳቢነቱ አስደናቂ ነበር፡፡
ከኅልፈቱ በኋላ የተገለጸው ምሥጢሩ ይህ መጻሕፍትን እጅግ አድርጎ የመውደዱ ነገር ነው ቢባል ማጋነን አይኾንም፡፡ “ምን ሲያደርግ ሰበሰባቸው?” የሚያስብሉ መጻሕፍትን እና ያልታተሙ መዛግብትን ሰብስቧል፡፡ የኅልፈቱ ዜና ከተሰማበት ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ቀደም ባሉ ቀናት የወጡ ዐዳዲስ መጻሕፍትን ሳይቀር ገዝቶ እያነበበ ነበር፡፡ እነዚህን መጻሕፍት በወጉ አደራጅቶ የሚያስቀምጥበት ቤት እንደሚያስፈልገው ለቤቶች ኮርፖሬሽን ማመልከቻ እስከመጻፍ ባደረሰ ፍቅር፣ መጻሕፍቱን የሚያስቀምጥበት ክፍል ቢጠበውም እንኳ፣ መጻሕፍትን ከመሰብሰብ ግን አልቦዘነም፡፡
ምናልባት የግጥም ድርሰቶቹ ጠለቅ ማለት፣ የሀገር ፍቅርን፣ ታሪክን፣ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን፣ ለየት ያሉ የሕይወት ፍልስፍናዎችን እንዲያነሳ ሰበቡ ከንባብ ልምዱ የተነሳ ነበርን? ብለን እንድናስብ የሚያደርጉ፣ በሕይወት ዘመኑ ሙሉ የሰበሰባቸውን መጻሕፍት አግኝተን ተደንቀናል፡፡
በአንድ መልኩ በክዋኔ ጥበባት ባለሙያዎች (በከያንያን) ልማድ ውስጥ “እምብዛም አይስተዋልም” የሚባለውን የንባብን ጉዳይ፣ “ለካ እንዲህ በጥልቀት የሚያነበም አለ፤” እንድንል የ“ቆምታ” ዕድል ፈጥሮልናል፡፡
እንዲህ ለመኾን መቼም መሠረት ያስፈልጋል፡፡ መሠረቱ ከወላጆቹ፣ በተለይም ከወታደር አባቱ ከሻለቃ አላምረው መንገሻ የተነሳ ይመስላል፡፡ የእናቱ የወ/ሮ አዳም ከበደ አስተዋጽዖም ለያየህይራድ አላምረው በሀገር ፍቅር የነደደ ማንነት የራሱ ድርሻ ነበረው፡፡
የወታደሮች ካምፕ (ሚሊተሪ ካምፕ) የነበረው፣ የጦር ሠራዊት የሙዚቃ ክፍልን ዕያየ ለማደግ ዕድል የሠጠው የልደታ አቅራቢያው የቶሎሣ ሠፈር ልጅ መኾን በራሱ፣ የሙዚቃንም የሀገር ፍቅርንም አዛንቆ ለማደጉ ሰበብ ሳይኾን ይቀራል? የተማረባቸው ተማሪ ቤቶች÷ ተስፋ ኮከብ እና ልዑል መኮንን ከስማቸው በሚነሣ ማንነት፣ ያየህይራድን በሀገር እና በጥበብ ፍቅር አንጾ፣ በንባብ ልምድ ቀርጾ ለማሳደግ የሚበቃ የተማሪ ቤት ባህል የዘረጉ ነበሩ፡፡
እንዲያውም፤ ያየህይራድ ራሱ እንደገለጸው፤ ከዘፈን ግጥም የመጻፍ ዝንባሌው አስቀድሞ የጻፋት አንዲት የሬዲዮ ድራማ፣ በእሑድ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ሬዲዮ ላይ የመተላለፍ ዕድል ማግኘቷ፣ በተማሪ ቤቱ መምህራን እና በተማሪ ጓደኞቹ ዘንድ ዝነኛ እና የወደፊት በጥበብ ሕይወት የመዝለቅ ተስፋውን በሩቅ እንዲያይ ዕድል የሠጠ የልጅነት አጋጣሚም ነበር ማለት ይቻላል፡፡
የጥበብ ሥራ ከክዋኔው በላይ፣ ከማጊያጊያጥ ከማሠማመሩ በላይ ፈጠራው እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ መንገድ እና ሥልቱ የማይታወቅ፣ በቀመር የማይሠላ፣ ዛሬ የሔዱበት መንገድ ለነገው የማይሠራ፣ በየቀኑ ተአምር የመጠበቅ ያህል ከባድ ጉዳይ ነው፡፡
በተለይ እንደ ሥነ ግጥም ያለው፣ ከግጥምም፤ ለዜማ ወይም ለሙዚቃ የሚኾን ግጥምን መጻፍ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ለዜማ የሚኾን ግጥምን የመድረስን ሥራ ከባድ የሚያደርገው፣ ግጥም ራሱ ዜማዊ መኾኑ ሲኾን፣ ይሄው ራሱ ሙዚቃዊ የኾነው ግጥም፣ ዜማዊ ሥልጣኑ ከፍ ባለው ሙዚቃ ውስጥ “ና ግባ” ሲባል፣ የራሱ መግደርደር እና እምቢ ባይነት ስላለው ነው፡፡ ግጥሙ ለዜማ ሥልጣን ለመሸነፍ ግዴታ አለበት፡፡
ዜማ ባወጣለት ሐዲድ ለመጓዝ ይገደዳል፡፡ ለዜማው ምጣኔ ሲባል ቃል ይቆረጣል፡፡ ቅርፁ እንዲያጥር ወይም እንዲረዝም ይደረጋል፡፡ የራሱን ምት ትቶ፣ የሙዚቃውን ሥልተ ምት፣ ባር እና ሪዝም እንዲከተል ይገደዳል፡፡
በብዙ የሚያከራክር ቢኾንም፤(ከዜማ ወደ ግጥም ድርሰት መምጣት ይሻላል? ወይስ ግጥሙን ወደ ዜማ መተርጎም ይሻላል? የሚለውን የማይቋጭ ክርክር ለጊዜው እናቆየውና፤) የዜማ ግጥም ጸሐፊ የኾነ ሰው፣ የዜማን ልሣን ወደ ቃል የመተርጎም ችሎታ የታደለ ቢኾን ይበልጥ ይሳካለታል፡፡
እንዲህ ያለው ተሠጥዖ ለገጣሚዎች ኹሉ የተሠጠ አይመስልም፡፡ የራሳቸውን የቃል እና የቤት ነጻነት ለሚፈልጉ ባለቅኔዎች፣ ይህ ዓይነቱ የሙዚቃዊ ዜማ ሥልጣን አይዋጥላቸውም፡፡ በቅኔያዊ መራቀቃቸው እጅግ የሚያስደንቁን ጠቢባን፣ ወደ ሙዚቃዊው የዜማ ግጥም ሲመጡ ግር የሚላቸው ለዚህ ነው፡፡
ያየህ ይራድ አላመረው፤ የዚህ ምሥጢር የተገለጠለት ድንቅ የዘፈን ግጥም ደራሲ ነው፡፡ በጻፋቸው የዘፈን ዜማ ግጥሞች ላይ ኹሉ የምናየው ጸጋው፣ የዜማን ልሳን በቃል የመተርጎም ችሎታውን ነው፡፡ ይህንንም በሕይወት ታሪኩ ላይ ለተጠቀሱት ድምጻውያን በሠጣቸው ሥራዎች ላይ ኹሉ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ሙዚቃዊ ባህል ውስጥ ኾኖ የዘፈን ግጥም ጸሐፊ መኾን ሌላም ከባድ ነገር አለው፡፡ የጥንታዊ ሕዝብ ጠንካራ የገጣሚነት ጣጣ፡፡ በተለምዶ “ጥንታዊ ሕዝቦች ቀልድ እና ግጥም ዐዋቂዎች ናቸው፤” ይባላል፡፡
ለዚህም የመካከለኛው ምሥራቅ ጥንታውያን ሀገራትን፣ እና ኢትዮጵያንን ምሣሌ የሚያደርጉ ብዙዎች ናቸው፡፡ የኹሉንም እንተወውና የሀገራችን የገጣሚነት ባህል ጠንካራነቱ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ጋሽ ጸጋዬ ገብረ መድኅን እንዳሉት “ኢትዮጵያዊ፤ ከአንቀልባው እስከ መቃብሩ በግጥም የተከበበ ነው፤” ጭራሽ፣ አዝማሪው የሚያዜመው ግጥም አልበቃ ብሎት፣ “ተቀበል” ብሎ ግጥም የሚሠጥ ሕዝብ ነው፡፡ እዚህ ገጣሚ ሕዝብ መሐል፣ አንጀት አርስ የዘፈን ግጥም ጸሐፊ ኾኖ መገኘት እጅግ ከባዱ ፈተና ነው፡፡
የያየህይራድ አላምረውን የጥበብ ሕይወት እጅግ እንድናደንቅ የሚያደርጉን ጉዳዮች ይሄንን መሠረትም ሊሰቱት አይገባም፡፡ ኹሉም የፈጠራ ጉዞዎች የየራሳቸው ፈተና ያለባቸው ቢኾንም፣ የዘፈን ግጥም ደራሲነት የሚጨምራቸው፣ ከሌላኛው የሙዚቃ ጥበብ ጓዝ እና ቅንጣቶች የሚነሱ ፈተናዎች አሉበት፡፡
እንደ ያየህ ይራድ አላመረው ያሉትን የዘፈን ግጥም ደራሲዎች እጅግ እንድናደንቃቸው የምንገደደው በዚህ እና ከራሱ ከገጣሚነት ችሎታቸው በሚመነጭ ጠቢብነታቸው ምክንያት ነው፡፡ የሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ፣ የተዘራ ኃይለ ሚካኤል፣ የተስፋዬ አበበ፣ የሸዋ ሉል መንግሥቱ፣ የዓለምፀሐይ ወዳጆ፣ የይልማ ገብረ አብ፣ የሙሉጌታ ተስፋዬ፣ የተመስገን ተካ እና የሌሎችም ታላላቅ የዘፈን ግጥም ደራስያን፤ የዜማ ግጥም ደራሲነት ጉዞ መንግድ፣ ሥልቱ እና ዐቅዱ ይሄንኑ ይመስላል፡፡
ያየህ ይራድ፤ ዜማን ወደ ግጥም የመተርጎም ሥራን ብቻ ሳይኾን፤ ዜማን እና ግጥምን በአንድ ላይ የመፍጠር ሥራ የሠራባቸው የሙዚቃ ሥራዎችም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ዜማ እና ግጥም መንታ ኾነው ከአንድ የፈጠራ ሰው ሲወለዱ የሚታይ ሌላ ውበትም አለ፡፡
ታላቁ የዜማ እና ግጥም ደራሲ፣ ፕሮዲውሰር እና የትላልቅ ሙዚቃዊ ፕሮጀክቶች አዘጋጅ የነበረው፤ ያያየህ ይራድ አላምረው፤ ከበርካታ የድርሰት ሥራዎቹ መካከል፤
ለኩኩ ስብስቤ (“ይቺ ነች ሀገሬ” ያለበትን አልበም፤ በርካታ ሥራዎች ግጥም፤ በኋላ ደግሞ “የአፍሪካ ገናና” አልበም ውስጥ ያሉ ድርሰቶችን)፣
ለአስቴር ዐወቀ(የ“ሰበቡ” አልበም ሙሉ ድርሰት)፣
ለዳምጠው አየለ፣
ለኤልያስ ተባባል (“ቅሪብኝ”)፣
ለፀሐይ ዮሐንስ፣
ለቴዎድሮስ ታደሰ፣
ለተሾመ አሰግድ፣
ለተሾመ ወልዴ፣
ለኃይልዬ ታደሰ (ይሞታል ወይ አልበም ፕሮዲውሰሩ ራሱ ያየህ ይራድ ሲኾን፣ የኢትዮጵያ አምላክ እና ይሞታል ወይ የራሱ የያየህ ይራድ ድርሰቶች ናቸው፡፡
ለጽጌሮማን አስናቀ (ባቲ)፣
ለጸጋቸው ኃይለ ኢየሱስ (ለመለም)፣
ለታደለ ሮባ እና ለብርሃኑ ተዘራ፣
ለደረጀ ደገፋው፣
ለጌራወርቅ ነቅዓ ጥበብ፣ እና
በመጨረሻ ደግሞ፤ “ቆሜ ልመርቅሽ” የጥላሁን ገሠሠ አልበም ላይ ራሱን “ቆሜ ልመርቅሽ”ን ጨምሮ የአልበሙን ድርሰት የሠራው ያየህ ይራድ አላምረው ነበር፡፡
ያየህይራድ፤ በተምሣሌት እና በፈሊጥ የበለጸጉ ግጥማዊ ይዘቶችን እጅግ ይወዳል፡፡ በተለይም የአዝማሪዎችን የግጥም ሥልት አጅግ አድናቂ ሙዚቀኛ ነው፡፡ በአገጣጠም ሥልቶቹ ውስጥ የአዝማሪዎችን የግጥም መንገድ የተከተለባቸው ሥራዎች በርካታ ናቸው፡፡
ለማርታ አሻጋሪ፣ ለተሾመ አሰግድ፣ ለበዛወርቅ አስፋው እና ለኤልያስ ተባባል የሠጣቸው ድርሰቶች፤ ይህንን ፍላጎቱን በይበልጥ ጎልተው እንዲወጡ ያደረገባቸው ሥራዎቹ ናቸው፡፡ በአስቴር ዐወቀ ሰበቡ አልበም ውስጥ የፎክ ግጥሞችን መቀላቀሉ የዚህ አዝማሚያው ማሣያ ነው፡፡ ምናልባት፤ ታላቁን የባህል ጥበበኛ እና አዝማሪ ባሕሩ ቀኜን የማድነቁ እና ሥራዎቻችው ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና እንዲያገኙ እና እንዲሸለሙ የማድረጉ ፍላጎትም ከዚህ የረዥም ጊዜ ጥረቱ የመነጨ ሊኾን ይችላል፡፡
በማኅበራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ በርካታ ሥራዎችንም ሠርቷል፡፡ በተለይ “እንኖራለን ገና” አልበም፤ ፕሮጀክቱን ከመምራት እስከ ድርሰት ትልቅ ሥራ የሠራበት አልበም ነው፡፡ ይህ አልበም፤ አንድን ማኅበረሰባዊ መልእክት በጥበብ ለማቅረብ ዘወትር የምንጠቀማቸውን የተሰለቹ መንገዶች እንደገና እንድንመረምር፣ በፖፕ ሙዚቃ ቅርጽ እና ደረጃ መልእክቱ ቀጥተኛ ትምህርት ሳይኾን፣ በጥበብ የተዋዛ መኾን እንደሚችል ያሣየበት ሥራው ነው፡፡
ለዚህ አልበም ስኬት፣ የሙዚቃ ባለሙያዎቹ እና የድምጻውያኑ አስተዋጽዖ ምንም ምትክ የማይገኝለት ቢኾንም፤ የፕሮዳክሽን አቅጣጫውን እና ፍልስፍናውን የመወሰን ሥራው አልበሙን እጅግ የተዋጣለት ያደርገዋል፡፡ ዛሬ ፍቅረዐዲስ ነቅዓ ጥበብ የተጫወተቺውን በዚያ አልበም ውስጥ የተካተተውን የዶ/ር ተሸገር ሺፈራው ድርሰት የኾነውን ሙዚቃ፣ ለኤች.አይ.ቪ. የተሠራ ሥራ ነው ብለን ብንናገር ብዙ ሰው እውነት አይመስለውም፡፡
ለአብነት ያህል እሱን አነሳን እንጂ፣ በዚህ አልበም ላይ የተካተቱት፤ የንዋይ ደበበ፣ የአስቴር ዐወቀ፣ የበዛወርቅ እና የኤልያስ፣ የቴዎድሮስ ታደሰ፣ የኄኖክ መሐሪ፣ የጼዴንያ ገብረ ማርቆስ፣ የዳዊት መለሰ… ሥራዎች ይሄንኑ እውነት የሚያረጋግጡልን ሥራዎች ናቸው፡፡
የዚሁ አልበም ማስተዋወቂያ ሌላ ሥራ ኾኖ የወጣው፤ ዘሪቱ ከበደ፣ አብነት አጎናፍር፣ ጆኒ ራጋ የተጫወቱት “መኖርህን ሌሎች ይሻሉ ይፈልጋሉ” የሚለው መዝሙር የግጥም ድርሰት ያየህ ይራድ አላምረው ከኤልያስ መልካ ጋር የጻፈው ነው፡፡ የመልእክት ጥልቀቱ ከኤልያስ ኅልፈት ጋር ተያይዞ በሰፊው የተተርኳል፡፡ ነገር ግን፤ የኤልያስ መልካ እና የያየህ ይራድ አላምረው ስሜት እና ሐሳብ ምን ያህል ውሕደት እንደነበረው ለማየት በአብነት የሚጠቀስ ድንቅ ሥራ ነው፡፤ የዚህ ሙዚቃ በእነዚህ ማኅበራዊ ጉዳይ ላይ በሚያተኩሩ ሥራዎቹ ውስጥ የሚታየው የጥበብ ልቀት፤ ማኅበራዊ ጉዳይን ርእሳቸው አድረገው የሚነሱ ሥራዎች፣ መዝሙር መሳይ ብቻ ሳይኾን፣ የዘመኑን የፖፕ ሙዚቃ ቅርጽ ተሸክመው፣ በጥበብ ልቀው መሠራት እንደሚችሉ መረጋገጫ እና ማስተማሪያ ጭምር ነው፡፡
ኢትዮጵያ በያየህ ይራድ ድርሰት ውስጥ የትልቅ ብዕሩ መገለጫ ነች፡፡ ከሀገር ውጪ በነበረው ሕይወት ናፍቆት ብቻ የተፈጠረች ጉዳይ አይደለቺም “ኢትዮጵያ” ለያየህ ይራድ አላምረው፡፡ እንዲያውም፤ በወታደር ልጅነቱ፣ በወታደር ሠፈር በማደጉ የተፈጠረች “ከ-ይቺ ነች ሀገሬ” እስከ “ቆሜ ልመርቅሽ የዘለቀች፣ የዕድሜ ልክ ጉዳዩ ነበረች ማለት ይቻላል፡፡ ትንቢትም ተናግሮላል፡፡
“የሺ ዓመታት የአፍሪቃ ገናና፣
ተከብራ የኖረች በዓለም ዙሪያ ገና፤
ኢትዮጵያ ዳግም እንደገና፣
ይታየኛል ያገር አውራ ኾና፤” (ኩኩ ሰብስቤ)
“የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል ሳይውል ሳያድር፣
ይጥልላታል ጠላቷን እባንዲራው ሥር፤
አይቀር አንድ ቀን መድረሱ ወቅቱን ጠብቆ፣
ማሪኝ ይላታል ጠላቷ እግሯ ላይ ወድቆ፤” (ኃይልዬ ታደሠ)
“አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና፣
ማግስቱን ይውሰደኝ ዐሥር ሞት ይምጣና፤”
(ቆሜ ልመርቅሽ-ጥላሁን ገሠሠ)
እነ “አንድ ብር ለአንድ” ወገን፣ “ሀገር ፍቅር ክብር፤ ኢትዮጵያ በፊትም ወደፊትም” የተሰኙ ትላልቅ ሀገራዊ መድረኮችን እና ፕሮጀክቶችን በመምራት፣ ከዩ.ኤስ.አይ.ዲ.፣ ከአሜሪካን ኤምባሲ፣ ከዚ.ዲ.ሲ.፣ ከወርልድ ባንክ፣ ከናይክ ፋውንዴሽን ጋር ሠርቷል፡፡
1957 ዓ.ም. ወደዚህች ዓለም መጥቶ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በድንገት ከዚህች ዓለም በሞት የተለየው ያየህይራድ አላምረው፣ በዚህች አጭር ማስታወሻ ተዘርዝረው የማያልቁ በጥበብ ሰውነቱ በግዝፈት ምንጊዜም የሚያስጠሩትን በርካታ ሥራዎች ሠርቶ አፏል፡፡
በሥራዎቹ ምንጊዜም የመታወሱ ነገር አንድና ኹሉት ባይኖረውም፣ በቤተሰቦቹ አማካኝነት፣ ለኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) የሚሠጡት(የሚበረከቱት) የዕድሜ ልክ ስብስብ መጻሕፍቱ እና እነዚህን መጻሕፍት ተረክቦ የሚያስነብብበት የማንበቢያ ክፍል ደግሞ፤ በልዩ ኹኔታ እንዲታወስ እንደሚያደርገው አይጠረጠርም፡፡
አንባብያን፤ በዚህ በያየህይራድ አላምረው ስም በተሰየመ የንባብ ክፍል ውስጥ የሚያሳልፉት ጊዜ ከንባብም በላይ ነው፡፡ የዚህን ታላቅ ደራሲ ቀልብ መግዛት የቻሉ፣ የእርሱ መዳፍ ይዟቸው፣ የዐይን ትኩረቱ ያረፈባቸውን መጻሕፍት ማንበብ ትርጉሙ “እንዲህ እና እንዲያ ነው” የሚባል አይደለም፡፡
ይህ ታኅሣሥ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. መርቀን የምንከፍተው “የአርቲስት ያየህይራድ አላምረው÷መዘክር እና የስብስቦቹ ቤተመጻሕፍት”፤ ሌሎች ጠቢባንም እንዲሁ ሥራዎቻቸውን እና የመጻሕፍት ስብስቦቻቸውን ለዚህ ታላቅ ተቋም እንዲሠጡም ያነሣሣል የሚል ተስፋ አለን፡፡ በመጨረሻም፤ ይህ እንዲኾን ትልቁን ድርሻ የተወጡትን፣ የያየህይራድ አላምረውን ቤተሰቦች፣ በተለይም እኅቱን ወ/ሮ ኂሩት አላምረውን፣ መጻሕፍቱ በዚህ ተቋም እንዲህ ያለ ሥፍራ አግኝተው ለትውልድ የሚተርፍ ቁም ነገር እንዲሠራባቸው ላደረጉት ጥረት እና ልግስና፤ ተቋማችን እጅግ አድርጎ ያመሰግናል፡፡

6 months ago
በሆሮ ጉዱሩ በታጣቂዎች የተገደሉት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት አስከሬን አለመገኘቱ ተነገረ
በኦሮሚያ ክልል፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሁለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች በታጣቂዎች ከተገደሉ ቀናት ቢቆጠርም አስከሬናቸው እንዳልተገኘ ተገለጸ።
ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ. ም. ቀሳውስቱ በሀራቶ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓል ታድመው ወደ ሻምቡ ከተማ እየተመለሱ ሳለ ነበር መኪናቸው በታጣቂዎች እንዲቆም ከተደረገ በኋላ ወደ ጫካ ተወስደው የተገደሉት።
በጉዞው ላይ አብረዋቸው ከነበሩት ቀሳውስት አንደኛው "በጅማ ገነቲ አካባቢ የቅድስት ማርያም ክብረ በዓል ነበር። ከሥነ ሥርዓቱ ስንመለስ 9 ሰዓት አካባቢ ታጣቂዎች አስቆሙን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
እኝህ የዐይን እማኝ በመኪናው ተሳፍረው የነበሩት "20 ሰዎች" እንደሆኑ ገልጸው፤ "ከ20ዎቹ መካከል አስሩን አስወርደው ወደ ጫካ ወሰዷቸው። የተቀሩት በበቆሎ ማሳ ውስጥ ተበታትነው በመሮጥ አመለጡ" ብለዋል።
ቄሱ እንደገለጹት፤ ታጣቂዎቹ በሻምቡ ከተማ መግቢያ ላይ መንገድ ዘግተው እና ስናይፐር መሣሪያ ይዘው ነበር።
ወደ ጫካ አካባቢ ከተወሰዱት ቀሳውስት መካከል የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፣ ሕጻናት እና መዘምራን እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።
"ጫካው ውስጥ ወስደው በስም ጠሯቸው። አንድ በአንድ በስም ከጠሯቸው በኋላ ልጆቹ ታጣቂዎቹ ከያዙት የስም ዝርዝር ውስጥ ስላልነበሩ ለቀቋቸው" ብለዋል።
"አራቱ ሰዎች የሆሮ ጉዱሩ አገረ ስብከት ዋና ኃላፊ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ዱፋ፣ ቄስ ቀናሳ ጊዲሳ፣ ቄስ ደሳለኝ ነሞምሳ እና ቄስ ባቡሽን ጠሩ ናቸው" ሲሉም በስም ጠቅሰዋል።
መንግሥት 'ሸኔ' የሚለው እና በሽብር ቡድንነት የፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከእገታዎች እና ከግድያዎች ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ተጠያቂ ቢደረግም ክሶቹን ያስተባብላል።
አሁን ከተፈጸመው ግድያ ጋር በተያያዘ በቀረበበት ክስ ላይም ምላሽ አልሰጠም።
ከቀሳውስቱ መካከል ሁለቱ ታግተው መለቀቃቸውን የዐይን እማኙ ገልጸዋል። ቄስ ዱጉማ ዱፋ እና ቄስ ደሳለኝ ነሞምሳ ደግሞ መገደላቸው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክት አክለዋል።
ታጣቂዎቹ "ሁለቱን ቀሳውስት ከገደሉ በኋላ ሁለቱን አርብ ዕለት ለቅቀዋቸዋል" ብለዋል።
ለቀሳውስቱ የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት በቤተ ክርስቲያኗ የተደረገ ሲሆን፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው እንዳይፈጸም ግን አስከሬናቸው እንዳልተሰጣቸው ገልጸዋል።
ሌላ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ የሚያገልግሉ እና ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ቀሲስ ግድያው "የታቀደ" እንደነበረ ተናግረዋል።
"ከታገቱ በኋላ እንዲለቀቁ ለመጠየቅ ቤተሰቦቻቸው ስልክ ደውለዋል። እንደማይለቋቸው እና አስከሬናቸውንም እንደማይሰጡ ታጣቂዎቹ ገልጸዋል" ብለዋል።
በአካባቢው ባለው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መከፋፈል እንደነበር እና የተለያዩ ቡድኖች ደጋፊዎች እና ነቃፊዎች እንዳሉ ገልጸዋል።
ግድያው ከክፍፍሉ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ቢያስቀምጡም ቢቢሲ ጉዳዩን ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም።
"እነዚህ ሰዎች ፖለቲከኞች አይደሉም። ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት የላቸውም።ሰላም ለማምጣት ነው የሚጥሩት። ታጣቂዎቹ ማን እንደሆኑ እንኳን ስላላወቁ ስማቸውን እየጠሩ ነበር ማንነታቸውን የለዩት " ሲሉ ተናግረዋል።
ቀሳውስቱ ስማቸው ተመዝግቦ ሲጠራ እንደነበር በመጥቀስ ጥቃቱ "የተቀነባበረ እና ቀሳውስቱን ዒላማ ያደረገ" እንደሆነ ገልጸዋል።
ታጣቂዎቹ ቀሳውስቱ "በኦሮምኛ እንጂ በአማርኛ መስበክ የለባቸውም" ማለታቸውን የቢቢሲ ምንጭ ጠቁመዋል። ሆኖም ግን የተገደሉት ሁለቱም ቀሳውስት የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው።
የሆሮ ጉዱሩ አገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ዱጉማ ዱፋ ማኅበረሰባቸውን በቀናነት ሲያገለግሉ እንደነበር የዐይን እማኞቹ አክለዋል።
ከግድያው ጋር በተያያዘ በከተማው ውስጥ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት ቀሳውስት መንግሥት ስለ ግድያው ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የሻምቡ ከተማ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይ የሟቾቹን ስም ጠቅሶ በታጣቂዎች ተወስደው መገደላቸውን አስታውቋል።
የምሥራቅ ሐረርጌ፣ የምሥራቅ ወለጋ እና የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ የአገረ ስብከት መሪ ሐዘናቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ገልጸዋል።
ቢቢሲ ስለ ግድያው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
BBC

መፈንቅለ መንግስት በትግራይ? ወይስ ሌላ የፖለቲካ ጨዋታ ?
የህወሓት ታጣቂዎች የድምፂ ወያነ ቢሮ እና ፕረዝዳንት ፅሕፈት ቤት (ደጀን ቢሮ) ተቆጣጥረዋል።
ሰራተኞችን ከቢሮ አስወጥተዋል። ሁለቱን ቢሮዎች መቆጣጠራቸውን ካረጋገጡ በኋላ በሐውልት (የህወሓት ፅሕፈት ቤት) የደስታ ቶክስ ወደ ሰማይ ተተኩሷል።
የትግራይ ኃይል ታጣቂዎች የክልሉ አስተዳደር
ሕንጻ ላይ ከበባ መፈጸማቸው ተነገረ
በመቀለ ነዋሪዎች ዘንድ ስጋት ተፈጥሯል
የታጠቁ የትግራይ ኃይል አባላት "ደመወዝ ዘገየብን" በሚል ቅሬታ መቀለ የሚገኘው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሕንጻ ላይ ከበባ መፈጸማቸውን ተነገረ።
የትግራይ ኃይል አርሚ 31 የተባለው ክፍል ከ70 በላይ የሚሆኑ አባላት ረቡዕ ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምሽት አራጉር (እንደርታ) ከተባለ ቦታ ተነስተው ነው ዛሬ ሐሙስ በአስተዳደሩ ሕንጻ ላይ ከበባ የፈጸሙት። የሠራዊት አባላቱ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ የሆነውን ክላሽንኮቭ ጨምሮ ዲሽቃ የተባለውን የቡድን መሣሪያ የታጠቁ መሆናቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአርሚ 31 የቅርብ አዛዦች ክስተቱን ለማርገብ ሊያናግሯቸው ቢሞክሩም "ከፍተኛ ባለሥልጣናት መጥተው ያናግሩን" በሚል ሳይቀበሏቸው መቅረታቸው ተገልጿል።
የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ ከትናንት ጀምሮ የታየ መሆኑን ነዋሪዎች ያመለከቱ ሲሆን በዚህም ሳቢያ በመቀለ ነዋሪዎች ዘንድ ስጋት ተፈጥሯል። የክልሉ ባለሥልጣናት ውጥረቱን ለማርገብ ጥረት እያደረጉ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ከዕኩለ ቀን በኋላ ታጣቂዎቹ ከጊዜያዊ አስተዳሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት መጀመራቸውን አሁን የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

7 months ago
የአይን አስገራሚ እውነታዎች
🔹 የሰው ዓይን ሌንስ በካሜራ ሌንስ ውስጥ እንዳለ የማስተካከያ (zoom) ተግባር አለው። ነገር ግን፣ ሌንሱ ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ ያድጋል እና በጊዜ ሂደት ጥንካሬው እየጨመረ ይሄዳል። ለዚህም ነው በእድሜ እየገፋን ስንሄድ ቅርብ ያሉ ነገሮችን ማየት የሚቸግረን (ይህም ፕሬስባዮፒያ ይባላል)።
🔹"20/20" ወይም በአዲስ መለኪያ 6/6 እይታ ማለት ፍፁም እይታ ማለት አይደለም። ይህ ማለት አንድ ሰው በ20 ጫማ ርቀት (ወይም 6 ሜትር) ሆኖ፣ መደበኛ እይታ ያለው ሰው በ20 ጫማ ርቀት ላይ ቆሞ ማየት የሚችለውን ነገር ማየት ይችላል ማለት ነው።
🔹 አይን ለመንቀሳቀስ የሚጠቀመው ጡንቻ (Extraocular muscles) የሰውንነት በጣም ጠንካራ ጡንቻዎች ናቸው—ከሰሩት ስራ አንፃር ሲታይ። በሌላ አገላለጽ፣ የሚያደርጉትን ትንሽ ስራ ለመስራት ከሌሎች ጡንቻዎች የበለጠ ብዙ ጥንካሬ አላቸው።
🔹የአይሪስ ቀለም (ለምሳሌ ሰማያዊ ወይም አረንጓዴ አይኖች) የሚመጣው በቀለም (ፒግመንት) እጥረት ምክንያት ነው። አብዛኛው የቀለም ልዩነት የሚፈጠረው ብርሃን በዓይኑ ፊት ባለው ንብርብር ላይ በሚፈነዳበት መንገድ ነው።
🔹የዐይን ሽፋሽፍቶች ዋና ተግባር እንደ አቧራ እና ትናንሽ ቅንጣቶች ያሉ ነገሮች ወደ አይን እንዳይገቡ መከላከል ነው። እንደ አውቶማቲክ ዳሳሽ ሆነው ያገለግላሉ።
🔹እኛ በአይናችን ሳይሆን በአእምሮአችን ነው የምናየው። አይኖች የሚሰበስቡት መረጃን ብቻ ነው። መረጃውን የሚተረጉመው እና ወደ ምስል የሚቀይረው ግን የአንጎል የኋላ ክፍል ነው።

8 months ago
በአሜሪካ ውስጥ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስፔሻሊስቶች ከ35 ዓመት በላይ ሲሆኑ በሥራ ቦታ "ያረጁ" እና "ጊዜ ያለፈባቸው" እንዳይመስሉ በብዛት የፊት፣ የዐይን ሽፋሽፍት እና የአንገት ማንሳት ቀዶ ሕክምና እያደረጉ ነው ሲል Wall Street Journal ።
ምክንያቱ ደግሞ በኩባንያዎች ውስጥ ያለው በእድሜ መድልዎ ሲሆን፣ የሰው ሃብት ሥራ አስኪያጆች "ከ30 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን አይቀጥሩም" የሚል አመለካከት በመኖሩ ነው። የቴክኖሎጂ ስፔሻሊስቶች "በገበያው ውስጥ ለመቆየት" ለውበት ለውጦች ከ$100,000 እስከ $200,000 እየከፈሉ ነው።

11 months ago
በባንግላዲሽ ጄት ተከስክሶ ህጻናትን ጨምሮ የ27 ሰዎች ህይወት አለፈ
የባንግላዲሽ አየር ኃይል ጄት በትምህርት ቤት ላይ ተከስክሶ 25 ህጻናትን ጨምሮ የ27 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
በዋና ከተማዋ ዳካ በደረሰው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ 170 ሰዎች ጉዳት እንደደረሳበቸው የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
የሀገሪቱ ጦር እንዳስታወቀው የጦር ጄቱ የተከሰከሰው በልምምድ ላይ በነበረበት ወቅት ሲሆን፥ የቴክኒክ እክል እንደገጠመው ነው የተገለጸው፡፡
ጄቱ በትምህርት ቤቱ ህንጻ ላይ ሲወድቅ በእሳት ተያይዞ እንደነበር የዐይን እማኞችን ጠቅሶ የዘገበው ሮይተርስ ነው፡፡
Via FBC

ሲራመዱ ቢውሉም ሊደርሱበት አልቻሉም
ጻድቁ ተወልዶ ያደገው የስሟ ትርጓሜ “ዐይነ ፀሐይ” በሆነ የቀድሞ የግብፅ ክፍለ ሃገር ሲሆን ወላጆቹ ዲስጣና ካልሞና ይባላሉ:: እነርሱ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩና ገና በልጅነት ሃይማኖትና ምግባርን ጠንቅቀው አስተምረውታል:: ቅዱሱ ኅልያን ጾምን፣ ጸሎትን ብቻ ያይደለ በሥጋዊ ሞያውም የተመሰገነ አንጥረኛ ነበር፡፡ በወዙ በላቡ ሠርቶ ያገኘው ሃብት ነበረው፡፡ በተለይ ወርቅና ብር እየሠራ ይተዳደር፣ ከገቢውም ነዳያንን ያስብ ነበር፡፡ እንዲህ ባለ ግብር ሳለ አንድ ቀን ፈተና መጣበት፡፡ አንዲት ዐረባዊት ሴት መጥታ የጆሮ ጌጥ እንዲሠራላት ትጠይቀውና እርሱም ከወርቅ ይሠራላታል፡፡ የጀሮ ጌጡን ከሰጣት በሁዋላ ግን "ዋጋውን አልሠጥህም" ትለዋለች፡፡ እርሱም "ምነው እህቴ! የደከምኩበትን ለምን አትከፍይኝም?" ሲላት ገላዋን አጋልጣ "ሴትነቴን ልስጥህ" ብላ ለዝሙት ጠየቀችው፡፡
ድንግሉ ኅልያን ከአነጋገሯና ከድርጊቷ የተነሳ በጣም ደነገጠ፡፡ ከፊቷ ላይ አማትቦ፣ ገስጿት ወደ ቤቱ ሔደ፡፡ ሌሊትቱን ሙሉ ሲያዝን አድሮ ሊነጋጋ ሲል ይሕችን ዓለም ሊተዋት በልቡ ወሰነ፡፡ በወጣት ጉልበቱ ደክሞ ያፈራው ሃብቱ፣ ንብረቱ፣ ቤቱ፣ መሬቱ፣ ወርቁ፣ ብሩ አላሳሳውም፡፡ ስጋዊ ሃብት ቢተርፈውም ናቀው፡፡ ነዳያንንም ሁሉ ወደ ቤቱ ጠርቶ ሙሉ ንብረቱን አከፋፈላቸው፡፡ የለበሳት ልብስ ብቻ ስትተርፈውም ፈጽሞ ደስ እያለው ከተማውን ጥሎ ወደ በርሃ ተሰደደ፡፡ ልቡናን የሚመረምር ጌታ ሊመራው ወዷልና 3 ስውራን ቅዱሳንን ላከለት፡፡ ሦስቱም የብርሃን አክሊል ደፍተው፣ የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሰው፣ የብርሃን ዘንግ ይዘው ተገለጡለት፡፡ እየመሩም ወስደው በግራና በቀኝ በውሃ የታጠረች፣ ደኗ የዐይን ደስታ የሆነ ስፍራ አደረሱት:: አካባቢው እንኩዋን ሰው እንስሳትም አልነበሩበትም፡፡
3ቱ ቅዱሳን ከቦታዋ እንደ ገቡ በላዩዋ ላይ ዕንቁ ያለባት የብርሃን ዘንግ ሰጥተውት "ወደ ፈጣሪ እንስገድ" አሉት፡፡ ሰግዶ ቀና ሲል ግን 3ቱም ተሠውረውታል፡፡ አባ ኅልያን ከቅዱሳኑ በመለየቱ ፈጽሞ አለቀሰ፡፡ ተጋድሎውን ግን በጾምና በጸሎት፣ በስግደትም አጠነከረ፡፡ ቅዱሱ የሚመገበውም፣ የሚለብሰውም ቅጠል ነበር:: ቅዱሳኑ የሰጡት ዘንግ ሲመሽ ግሩም ብርሃን ታወጣ ነበርና በእርሱ ዘንድ ሌሊት የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ መንገድ መሔድ ሲፈልግም ትመራውና ጐዳናውንም ታሳጥርለት ነበር፡፡ በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋም ለበርካታ ዓመታት ከሰው ተለይቶ ኖረ፡፡ በተለያየ መንገድ አጋንንት ያመጡበትን ፈተኑት በእግዚአብሔር ኃይል አለፈው፡፡ ሊቋቋሙት ባልቻሉ ጊዜም ሰው ተመስለው ወደ ከተማ ሔደው ሽፍቶችን አነጋግረው ሊያስገድሉት ሞከሩ፡፡
ሽፍቶቹ ከፊት ለፊታቸው እያዩት ሲራመዱ ቢውሉም ሊደርሱበት አልቻሉም፡፡ እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ መንገዱን ያረዝምባቸው ነበር፡፡ በሁዋላ ግን ሽፍቶቹ በድካምና በውሃ ጥም ሊያልቁ ሆነ፡፡ ጻድቁ ምንም እርሱን ለመግደል ቢመጡም አዘነላቸው፡፡ ባሕሩን ያለ ታንኩዋ እየረገጠ ደረሰላቸው፡፡ ከዱር ፍሬ አብልቶ፣ ንጹሕ ውሃም አጠጥቶ ሸኛቸው፡፡ የሚያርፍበት ዕለት ሲደርስ እነዚያ በፊት የተሠወሩበትና ወደዚህች ስፍራ ያመጡት 3 ቅዱሳን እንደ ገና ተገለጡለት፡፡ በደስታ ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አባ ኅልያን ሐምሌ 9 ቀን ወደ ምሥራቅ ሰግዶ ዐረፈ፡፡ 3ቱ ቅዱሳንም ሥጋውን ገንዘው በበዓቱ ቀብረውት፣ ዜና ሕይወቱንም ጽፈው አስቀምጠው ተሠወሩ፡፡ ገዳማውያን ዓለምን ትተው የመውጣታቸው ምክንያት የክርስቶስ ፍቅር እንጂ ሃብት ማጣት አይደለም፡፡ ያላቸውን ሁሉ ሰጥተው ወጥተዋልና፡፡ ለዚህ ነው ገዳማትን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና በረከት የምናገኘው፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Comments