ሲራመዱ ቢውሉም ሊደርሱበት አልቻሉም
ጻድቁ ተወልዶ ያደገው የስሟ ትርጓሜ “ዐይነ ፀሐይ” በሆነ የቀድሞ የግብፅ ክፍለ ሃገር ሲሆን ወላጆቹ ዲስጣና ካልሞና ይባላሉ:: እነርሱ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩና ገና በልጅነት ሃይማኖትና ምግባርን ጠንቅቀው አስተምረውታል:: ቅዱሱ ኅልያን ጾምን፣ ጸሎትን ብቻ ያይደለ በሥጋዊ ሞያውም የተመሰገነ አንጥረኛ ነበር፡፡ በወዙ በላቡ ሠርቶ ያገኘው ሃብት ነበረው፡፡ በተለይ ወርቅና ብር እየሠራ ይተዳደር፣ ከገቢውም ነዳያንን ያስብ ነበር፡፡ እንዲህ ባለ ግብር ሳለ አንድ ቀን ፈተና መጣበት፡፡ አንዲት ዐረባዊት ሴት መጥታ የጆሮ ጌጥ እንዲሠራላት ትጠይቀውና እርሱም ከወርቅ ይሠራላታል፡፡ የጀሮ ጌጡን ከሰጣት በሁዋላ ግን "ዋጋውን አልሠጥህም" ትለዋለች፡፡ እርሱም "ምነው እህቴ! የደከምኩበትን ለምን አትከፍይኝም?" ሲላት ገላዋን አጋልጣ "ሴትነቴን ልስጥህ" ብላ ለዝሙት ጠየቀችው፡፡
ድንግሉ ኅልያን ከአነጋገሯና ከድርጊቷ የተነሳ በጣም ደነገጠ፡፡ ከፊቷ ላይ አማትቦ፣ ገስጿት ወደ ቤቱ ሔደ፡፡ ሌሊትቱን ሙሉ ሲያዝን አድሮ ሊነጋጋ ሲል ይሕችን ዓለም ሊተዋት በልቡ ወሰነ፡፡ በወጣት ጉልበቱ ደክሞ ያፈራው ሃብቱ፣ ንብረቱ፣ ቤቱ፣ መሬቱ፣ ወርቁ፣ ብሩ አላሳሳውም፡፡ ስጋዊ ሃብት ቢተርፈውም ናቀው፡፡ ነዳያንንም ሁሉ ወደ ቤቱ ጠርቶ ሙሉ ንብረቱን አከፋፈላቸው፡፡ የለበሳት ልብስ ብቻ ስትተርፈውም ፈጽሞ ደስ እያለው ከተማውን ጥሎ ወደ በርሃ ተሰደደ፡፡ ልቡናን የሚመረምር ጌታ ሊመራው ወዷልና 3 ስውራን ቅዱሳንን ላከለት፡፡ ሦስቱም የብርሃን አክሊል ደፍተው፣ የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሰው፣ የብርሃን ዘንግ ይዘው ተገለጡለት፡፡ እየመሩም ወስደው በግራና በቀኝ በውሃ የታጠረች፣ ደኗ የዐይን ደስታ የሆነ ስፍራ አደረሱት:: አካባቢው እንኩዋን ሰው እንስሳትም አልነበሩበትም፡፡
3ቱ ቅዱሳን ከቦታዋ እንደ ገቡ በላዩዋ ላይ ዕንቁ ያለባት የብርሃን ዘንግ ሰጥተውት "ወደ ፈጣሪ እንስገድ" አሉት፡፡ ሰግዶ ቀና ሲል ግን 3ቱም ተሠውረውታል፡፡ አባ ኅልያን ከቅዱሳኑ በመለየቱ ፈጽሞ አለቀሰ፡፡ ተጋድሎውን ግን በጾምና በጸሎት፣ በስግደትም አጠነከረ፡፡ ቅዱሱ የሚመገበውም፣ የሚለብሰውም ቅጠል ነበር:: ቅዱሳኑ የሰጡት ዘንግ ሲመሽ ግሩም ብርሃን ታወጣ ነበርና በእርሱ ዘንድ ሌሊት የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ መንገድ መሔድ ሲፈልግም ትመራውና ጐዳናውንም ታሳጥርለት ነበር፡፡ በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋም ለበርካታ ዓመታት ከሰው ተለይቶ ኖረ፡፡ በተለያየ መንገድ አጋንንት ያመጡበትን ፈተኑት በእግዚአብሔር ኃይል አለፈው፡፡ ሊቋቋሙት ባልቻሉ ጊዜም ሰው ተመስለው ወደ ከተማ ሔደው ሽፍቶችን አነጋግረው ሊያስገድሉት ሞከሩ፡፡
ሽፍቶቹ ከፊት ለፊታቸው እያዩት ሲራመዱ ቢውሉም ሊደርሱበት አልቻሉም፡፡ እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ መንገዱን ያረዝምባቸው ነበር፡፡ በሁዋላ ግን ሽፍቶቹ በድካምና በውሃ ጥም ሊያልቁ ሆነ፡፡ ጻድቁ ምንም እርሱን ለመግደል ቢመጡም አዘነላቸው፡፡ ባሕሩን ያለ ታንኩዋ እየረገጠ ደረሰላቸው፡፡ ከዱር ፍሬ አብልቶ፣ ንጹሕ ውሃም አጠጥቶ ሸኛቸው፡፡ የሚያርፍበት ዕለት ሲደርስ እነዚያ በፊት የተሠወሩበትና ወደዚህች ስፍራ ያመጡት 3 ቅዱሳን እንደ ገና ተገለጡለት፡፡ በደስታ ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አባ ኅልያን ሐምሌ 9 ቀን ወደ ምሥራቅ ሰግዶ ዐረፈ፡፡ 3ቱ ቅዱሳንም ሥጋውን ገንዘው በበዓቱ ቀብረውት፣ ዜና ሕይወቱንም ጽፈው አስቀምጠው ተሠወሩ፡፡ ገዳማውያን ዓለምን ትተው የመውጣታቸው ምክንያት የክርስቶስ ፍቅር እንጂ ሃብት ማጣት አይደለም፡፡ ያላቸውን ሁሉ ሰጥተው ወጥተዋልና፡፡ ለዚህ ነው ገዳማትን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና በረከት የምናገኘው፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

11 months ago