Logo
YenetaTube
መልካም ክርስቲያኖች የነበሩት ወላጆቹ ገና በልጅነቱ ሃይማኖትና ምግባርን ጠንቅቀው አስተምረውታል፡፡

ግብጻዊ ቅዱስ አባ ኅልያን ጾምንና ጸሎትን የሚያዘወትር በሥጋዊ ሞያውም የተመሰገነ አንጥረኛ በመሆኑ በወዙ በላቡ ሠርቶ ያገኘው ሃብት ነበረው፡፡ ከገቢውም ነዳያንን ያስብ ነበር፡፡ አንድ ቀን አንዲት ዐረባዊት ሴት መጥታ የወርቅ የጆሮ ጌጥ እንዲሠራላት ትጠይቀውና ይሠራላታል፡፡ የጀሮ ጌጡን ከሰጣት በሁዋላ ግን "ዋጋውን አልሠጥህም" ትለዋለች፡፡ እርሱም "ምነው እህቴ! የደከምኩበትን ለምን አትከፍይኝም?" ሲላት ገላዋን አጋልጣ "ሴትነቴን ልስጥህ" ብላ ለዝሙት ጠየቀችው፡፡ ድንግሉ ኅልያን ከአነጋገሯና ከድርጊቷ የተነሳ በጣም ደነገጠ፡፡ ከፊቷ ላይ አማትቦ፣ ገስጿት ወደ ቤቱ ሔደ፡፡ ሌሊትቱን ሙሉ ሲያዝን አድሮ ሊነጋጋ ሲል ይሕችን ዓለም ሊተዋት በልቡ ወሰነ፡፡

በወጣት ጉልበቱ ደክሞ ያፈራው ስጋዊ ሃብት ቢተርፈውም ናቀው፡፡ ነዳያንንም ሁሉ ወደ ቤቱ ጠርቶ ሙሉ ንብረቱን አከፋፈላቸው፡፡ የለበሳትን ልብስ ብቻ ስትተርፈውም ፈጽሞ ደስ እያለው ከተማውን ጥሎ ወደ በርሃ ተሰደደ፡፡ ልቡናን የሚመረምር ጌታ ሊመራው ወዷልና 3 ስውራን ቅዱሳንን ላከለት፡፡ እየመሩም ወስደው በግራና በቀኝ በውሃ የታጠረች፣ ደኗ የዐይን ደስታ የሆነ ስፍራ አደረሱት፡፡ አካባቢው እንኩዋን ሰው እንስሳትም አልነበሩበትም፡፡ ከቦታዋ እንደገቡ በላዩዋ ላይ ዕንቁ ያለባት የብርሃን ዘንግ ሰጥተውት "ወደ ፈጣሪ እንስገድ" አሉት፡፡ ሰግዶ ቀና ሲል ግን 3ቱም ተሠውረውታል፡፡ አባ ኅልያን ከቅዱሳኑ በመለየቱ ፈጽሞ አለቀሰ፡፡ ተጋድሎውን ግን በጾምና በጸሎት፣ በስግደትም አጠነከረ፡፡ የሚመገበውም፣ የሚለብሰውም ቅጠል ነበር፡፡ ቅዱሳኑ የሰጡት ዘንግ ሲመሽ ግሩም ብርሃን ታወጣ ነበርና በእርሱ ዘንድ ሌሊት የሚባል ነገር አልነበረም፡፡

በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋም ለበርካታ ዓመታት ከሰው ተለይቶ ኖረ፡፡ አጋንንትም ያመጡበትን ፈተኑት በእግዚአብሔር ኃይል አለፈው፡፡ ሊቋቋሙት ባልቻሉ ጊዜም ሰው ተመስለው ወደ ከተማ ሔደው ሽፍቶችን ላኩበት፡፡ በእግዚአብሔር ኃይልም አሸንፏቸው፣ አስተምሮም ሸኛቸው፡፡ የሚያርፍበት ዕለት ሲደርስ የተሠወሩበት 3ቱ ቅዱሳን ተገለጡለት፡፡ በደስታ ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አባ ኅልያን ሐምሌ 9 ቀን ወደ ምሥራቅ ሰግዶ ዐረፈ፡፡ 3ቱ ቅዱሳንም ሥጋውን ገንዘው በበዓቱ ቀብረውት፣ ዜና ሕይወቱንም ጽፈው አስቀምጠው ተሠወሩ፡፡ ገዳማውያን ዓለምን ትተው የመውጣታቸው ምክንያት የክርስቶስ ፍቅር እንጂ ሃብት ማጣት አይደለም፡፡ ያላቸውን ሁሉ ሰጥተው ወጥተዋልና ገዳማትን እንደግፍ በዓታቸውን እናጸና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.