12 days ago
ድንጋይ አቅልጣ ዶላር የምታድነው ኢትዮጵያ፤ የሴራሚክ ምርት ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሉዓላዊ አቅም
#የኢንዱስትሪ_ሽግግር #ኢትዮጵያ_ታምርት #ceramicindustry #madeinethiopia #importsubstitution
1 month ago
ኢትዮጵያን ወደ ኢንዱስትሪ ማዕከልነት የሚቀይረው አዲሱ የማዕድንና ኢንዱስትሪ ትስስር
********************
ኢትዮጵያ ከተፈጥሮ ያገኘችውን የማዕድን ሀብት በጥሬው ወደ ውጭ ከመላክ ባለፈ፣ እሴት ጨምሮ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት በማዋል ረገድ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየጻፈች ትገኛለች።
ከሪፎርሙ በፊት ዘርፉ ለሀገራዊ ምርት ያለው አስተዋጽኦ ከአንድ በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ማዕድንን የኢኮኖሚው ዋነኛ ምሰሶ በማድረግ የኢንዱስትሪ ሽግግር መሠረት እንዲሆን ተደርጓል።
ይህም በየዓመቱ ለነዳጅ፣ ለማዳበሪያና ለብረት ግብዓቶች ግዢ የሚወጣውን ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አለው።
በተለይም በብረት ማዕድን ዘርፍ ከ1.1 ቢሊዮን ቶን በላይ ክምችት ላይ በመመስረት በዓመት ሦስት ሚሊዮን ቶን ብረት በሀገር ውስጥ ለማምረት ሰፊ ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
በወርቅ ምርት ዘርፍም ቢሆን ከ2010 እስከ 2017 ባሉት ዓመታት ውስጥ የ1241.4 በመቶ ከፍተኛ የኤክስፖርት ዕድገት መመዝገቡ የሪፎርሙን ውጤታማነት በተጨባጭ ያሳያል። በተጨማሪም በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አማካኝነት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 4.85 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ተችሏል።
ይህ የማዕድንና ኢንዱስትሪ ትስስር ኢትዮጵያ ከውጭ ጥገኝነት እንድትላቀቅና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነቷን በጽኑ መሠረት ላይ እንድታቆም እያደረገው ያለውን ዘርፈ ብዙ ለውጥ በዝርዝር ለማንበብ ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።
#ethiopia #mining #industry #economicsovereignty #ethiopiatamirt #mineralreform #investment

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 በይፋ መርቀው ከፈቱ
****************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአምራች ዘርፍ ለማስፋፋት የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክረውን አራተኛውን 'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
ኤክስፖው እስካሁን ያሳያቸው እና የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች፦
- የአምራች ዘርፉ ግብዓት አቅርቦት በዓመት ከ9 ሚሊዮን ወደ 15 ሚሊዮን ቶን አድጓል፤
- ለአዳዲስ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች ከ3.4 ጊጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ቀርቧል፤
- ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው የፋይናንስ አቅርቦት ከ8.1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብር ያደገ ሲሆን፣ ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ከ262 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍ ብሏል፤
- ለዘርፉ ከ2.28 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተመድቧል፤
- የፋብሪካዎች የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ አድጓል፤
- የማምረት አቅም እና ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ በቀጣይም ተጨማሪ ዕድገት ይጠበቃል፤
- ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት እስከ 4.85 ቢሊዮን ዶላር ማዳን የተቻለ ሲሆን የወጪ ንግድም ከፍተኛ እድገት እያሳየ ይገኛል፤
- ከ2 ሺህ 800 በላይ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ ሲሆን፣ ለ1.4 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
ኤክስፖው ኢንዱስትሪዎችን የሚያስተሳስር፣ ኢንቨስትመንትን የሚስብ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ አምራቾችን እና በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን የሚያገናኝ ቁልፍ ሀገራዊ መድረክ ሆኗል።
በአጠቃላይ የኤክስፖው መከፈት የአምራች ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያለውን ፋይዳ በማጉላት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሽግግር እያፋጠነ መሆኑን ያሳያል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
#ebc #ethiopia #industry #madeinethiopia

የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ የሥራ ባህል እየገነባ ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ከቴክኒካዊ ብቃት ባሻገር አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ሰብዕና እና የሥራ ባህል እየገነባ ነው አለ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
አገልግሎቱ የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አስመልክቶ ባወጣው መረጃ፤ በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎች ዓለም አቀፍ የጥራት ቁጥጥር ስታንዳርዶችን፣ ጥብቅ የጊዜ አጠቃቀምንና ስልታዊ የአመራር ክህሎትን በመላበስ ላይ ናቸው ብሏል።
ከታችኛው የሥራ እርከን ተነስተው በዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ እስከ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪነት ደረጃ የደረሱ ወጣቶች፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው "ምርጥ ምርት" የሰው ሀብቷ መሆኑን እያስመሰከሩ ነው ሲልም ገልጿል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ‘በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምርትን ከማሳደግና የውጭ ምንዛሬን ከመታደግ ባሻገር ዕውቀትንና ክህሎትን ለዓለም የምናበረክትበት አዲስ የኢንዱስትሪ ምዕራፍ ተጀምሯል!’ በሚል ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፤ 830 ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ስራ በማስገባት፣ 4.85 ቢሊየን ዶላር ገቢ ምርትን በመተካት እና 433 ሚሊየን ዶላር ከኤክስፖርት በማስገኘት አስደናቂ የኢንዱስትሪ ሽግግር ውጤት አስመዝግቧል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ሀገራዊ ንቅናቄ ሲጀምር፣ ግቡ ምርትን ማሳደግና የውጭ ምንዛሬን መታደግ ብቻ አልነበረም።
ከእነዚህ ኢኮኖሚያዊ ስሌቶች ባሻገር፣ ትልቁና ስትራቴጂካዊው ስኬታችን የተመዘገበው ኢትዮጵያን የዕውቀትና የክህሎት ምንጭ በሚያደርገው የሰው ሀብት ልማት ላይ ነው። ዛሬ ላይ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የፋብሪካዎች ስብስብ መሆኑ ቀርቶ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚገነቡ ብቁ ባለሙያዎችና መሪዎች የሚፈሩበት ታላቅ የተግባር ትምህርት ቤት መሆን ችሏል። ይህ ሽግግር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተወዳዳሪነት ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ቴክኖሎጂ ላኪነትና ክህሎት አቅራቢነት ከፍ የሚያደርግ ለነገዋ ኢትዮጵያዊ መሠረት የሚጥል የታሪካችን እጥፋት ነው።
በታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በግዙፍ ፋብሪካዎች ውስጥ የታየው ተጨባጭ ለውጥ የመንግሥትን የፖሊሲ ጥንካሬ በተግባር የሚያረጋግጥ ነው። ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ክፍያ በሚመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች ብቻ ይተዳደሩ የነበሩ ውስብስብ የቴክኖሎጂ ሲስተሞች፣ ዘመናዊ የምርት መስመሮችና የሶፍትዌር መሠረተ-ልማቶች ዛሬ ላይ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ወጣት መሐንዲሶችና ቴክኒሻኖች እየተመሩ ይገኛሉ። ይህ ስኬታማ የዕውቀት ሽግግር፣ መንግሥት ጥራት ያለው ፖሊሲ የመቅረጽ ብቻ ሳይሆን ፖሊሲን በተጨባጭ ወደ ተግባር የመለወጥና የማስፈጸም አቅም እንዳለው ትልቅ ማሳያ ነው።
በዘረፉ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም የተፈጠረላቸውን ምቹ ዐውድ ተጠቀመው ቴክኖሎጂን የመቀበል ብቻ ሳይሆን፣ የመግራትና የማላመድ ብቃታቸውን በተግባር በማሳየት፣ ሀገራችን ለዘመናት የነበረባትን የቴክኖሎጂ ጥገኝነት በፈጠራ አቅማቸው እያስቀሩና አዳዲስ የሥራ ባሕልና የታሪክ ምዕራፍ እየጻፉ ይገኛሉ።
የ "ኢትዮጵያ ታምርት"ንቅናቄ ከቴክኒካዊ ብቃት ባሻገር፣ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ሰብዕና እና የሥራ ባህል እየገነባ ነው ። በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎች ዓለም አቀፍ የጥራት ቁጥጥር ስታንዳርዶችን፣ ጥብቅ የጊዜ አጠቃቀምንና ስልታዊ የአመራር ክህሎትን በመላበስ ላይ ናቸው። ከታችኛው የሥራ እርከን ተነስተው በዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ እስከ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪነት ደረጃ የደረሱ ወጣቶቻች፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው "ምርጥ ምርት" የሰው ሀብቷ መሆኑን እያስመሰከሩ ነው።
መንግሥት የኢንዱስትሪ ሽግግሩን ትክክለኛ ፍሬ የሚለካው በወጪ ንግድ ስሌቶች ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ የደረጀና በዕውቀት የበለጸገ አምራች ዜጋ መፈጠሩ ነው። በመሆኑም ይህን የክህሎት አብዮት ይበልጥ በማፋጠንና ዘርፉን የቴክኖሎጂ ምንጭ በማድረግ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች በቁርጠኝነት ይቀጥላሉ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኢንዱስትሪ ዘርፍ አቅምን የገለጠው ኢትዮጵያ ታምርት …
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ፖሊሲን በመከተል ሀገራዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ በአስደናቂ ጉዞ ላይ ትገኛለች፡፡
ከዚህ ቀደም በግብርና ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ የነበረውን የኢኮኖሚ ትኩረት በማስፋት በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በአይቲ ዘርፎች ያለውን ዕምቅ አቅም በመጠቀም የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ ውጤት ተመዝግቧል።
በዚህ ረገድ በተለይም ከውጭ የሚገባውን ምርት በመቀነስ እና ወደ ውጭ የሚላክ ምርትን በማሳደግ የተጀመረው የአምራች ኢንዱስትሪው ንቅናቄ በአብነት ይጠቀሳል።
በዚህም ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገቡ የኢንዱስትሪ ምርቶች ጥገኝነት ተላቅቃ ራስን በመቻል ብቻ ሳትገደብ ለውጭ ገበያ በማቅረብ በአስደናቂ የኢንዱስትሪ ሽግግር ሂደት ላይ ትገኛለች፡፡
ለዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ስር ነቀል ለውጥ በማምጣት ረገድ ገና ከጅምሩ ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡበት ሆኗል፡፡
በንቅናቄው አማካኝነት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተዘጉ ፋብሪካዎችን ዳግም ሥራ በማስጀመር፣ ምርታማነትን በማሳደግና በስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም ገቢ ምርቶችን በመተካት በቢሊየን ዶላር የሚገመት የውጭ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው በተለይም በተኪ ምርቶች ረገድ ባለፉት 9 ወራት ብቻ 4 ነጥብ 85 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርት በሀገር ውስጥ ተመርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች መተካት ብቻ ሳይሆን ምርታማነትን በማሳደግ ለውጭ ገበያ የማቅረብ ርዕይን ያነገበ ነው፡፡
ባለፉት 9 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የኢንዱስትሪ ምርቶች 433 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱ የኢንዱስትሪ ዘርፉ በፈጣን የሽግግር ሂደት ላይ እንደሚገኝ አመላካች ነው፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች ስራ አቁመው የነበሩ 830 ፋብሪካዎችን ዳግም ስራ ለማስጀመርና የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የማምረት አቅም እንዲያድግ ንቅናቄው ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡
በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እየተመዘገቡ የሚገኙ ውጤቶችን በማላቅ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ በተለይም የፋይናንስ እና የኃይል አቅርቦት ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ

Sponsored by
Surafel
4 months ago
የውጭ ምንዛሬን የሚታደገው ግዙፉ "አርጆ"፦ በዓመት 1.2 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም!
የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሽግግር የሚያፋጥነውና በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ ይገባ የነበረውን የድንጋይ ከሰል ፍላጎት በሀገር ውስጥ የሚተካው የአርጆ የድንጋይ ከሰል መፍጫና ማበልጸጊያ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመረቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃን ባገናዘበ መልኩ የኢንዱስትሪ ልማትን ለማሳደግ ለጀመረችው ቁርጠኝነት ትልቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
📌 የፋብሪካው ዋና ዋና የቴክኒክ መረጃዎች፦
የማምረት አቅም፦ ፋብሪካው በሰዓት 200 ቶን፣ በዓመት ደግሞ 1.2 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል የማጠብና የማበልጸግ ግዙፍ አቅም አለው።
ለታላላቅ ኢንዱስትሪዎች፦ ለሲሚንቶ፣ ለብረት እና ለሌሎች የኮንስትራክሽን ግብዓት አምራች ፋብሪካዎች ወሳኝ የሆነውን የኃይል ምንጭ (Fuel) በበቂ ሁኔታ ያቀርባል።
የኢኮኖሚ ፋይዳ፦ ቀደም ሲል ለድንጋይ ከሰል ግዥ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ (Hard Currency) በማስቀረት ለሀገር ውስጥ አምራቾች አስተማማኝ ግብዓት ይሆናል።
ይህ ፋብሪካ ስራ መጀመሩ በተለይ በሀገሪቱ ላለው የሲሚንቶ ምርት እጥረትና የዋጋ መናር እንደ አንድ መፍትሄ ይታያል። የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በኃይል እጥረት ምክንያት ምርታቸውን እንዳያስተጓጉሉ ጥራት ያለውና የደረጃውን የጠበቀ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል በቅርበት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። በተጨማሪም ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድም የጎላ ሚና ይኖረዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ የኢነርጂ ፕሮጀክት ተብሎ ተመረጠ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአፍሪካ የንግድ ምክር ቤት የ2026 የዓመቱ "የኢንዱስትሪ ኢነርጂ ፕሮጀክት" (Industrial Energy Project of the Year) ተብሎ ተመረጠ።
የዕውቅና ሥነ-ሥርዓቱ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ማታ በጋና አክራ ኬምፐንስኪ ጎልድ ኮስት ሆቴል ተካሂዷል።
ዕውቅናው የታላቁ ህዳሴ ግድብ አህጉራዊ ፋይዳ ያለው ታላቅ የኢንዱስትሪ ኢነርጂ ፕሮጀክት መሆኑን ለመመስከር ያለመ ነው።
የዕውቅና ሽልማቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን በመወከል በጋና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተጠባባቂ የሚሲዮን መሪ የሆኑት ክቡር አምባሳደር አሣየ ዓለማየሁ (ዶ/ር) ተቀብለዋል።
በእውቅና ሽልማቱ ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችና ተቋማት ኃላፊዎች፣ ኣምባሳደሮች እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡
በአፍሪካ የንግድ ምክር ቤት የአፍሪካ የንግድ ሽልማት ዳይሬክተር መሀሙዱ ሃያቱ እንደገለፁት ምክር ቤቱ ፕሮጀክቱን ለመሸለም የወሰነው ግድቡ ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሽግግር፣ ለቀጣናዊ የንግድና የኤሌክትሪክ ትስስር እያበረከተ ያለውን የጎላ አስተዋጽኦ እና የፕሮጀክት አመራር ሚና ዕውቅና ለመስጠት ነው።
ግድቡ በኃይል ማመንጨት አቅምና ዋስትና እንዲሁም በረጅም ጊዜ የኢንዱስትሪ ሽግግር ላይ የተደረገ ትልቅ ኢንቨስትመንት መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ግድቡ ለከፍተኛ ማኑፋክቸሪንግ፣ ለግብርና ማቀነባበሪያ እና ለኢንዱስትሪ የእሴት ሰንሰለቶች መሠረት የጣለ መሆኑን የጠቆሙት ሚስተር መሀሙዱ ለቀጣናዊ የኃይል ትስስር እና ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ዕውቅናው በአፍሪካ ንግድ ሽልማት ቋሚ ተቋማዊ መዝገብ ላይ የሚሰፍር ይሆናል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በኤምባሲው በኩል ዕውቅናውን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ሽልማቱ የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሀገራት በራሳችን ሀብትና ጥረት ለመገንባት ያለንን የጋራ ምኞት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ግድቡ ግዙፍ፣ ውስብስብ እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች በአፍሪካውያን ታስበው፣ ተገንብተው እና ተመርተው ለአፍሪካውያን የጋራ ብልፅግና ሊውሉ እንደሚችሉ ማረጋገጫ የሰጠ ነው።
ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ ኢነርጂ-መር የልማት ጎዳና የምታደርገውን ስልታዊ ሽግግር የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው ብለዋል ዋና ሥራ አስፈፃሚው በመልዕክታቸው።
ኢትዮጵያ ታዳሽ የውሃ ኃይልን በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና የአካባቢ ጥበቃ ተደጋግፈው የሚሄዱ ጉዳዮች መሆናቸውን እያስመሰከረች እንደምትገኝ አብራርተዋል።
ግድቡ በአሁኑ ወቅት ፋብሪካዎችን በማንቀሳቀስ፣ የዲጂታል ሽግግርን በማገዝ እና በምስራቅ አፍሪካ የኃይል ገንዳ (Eastern Africa Power Pool) በኩል ድንበር ተሻጋሪ የኃይል ትስስርን በማጠናከር እንደ አህጉራዊ የኃይል ማዕከል እያገለገለ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ዕውቅናው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ ስኬት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን በማንሳት ፕሮጀክቱ አፍሪካ በራሷ ኃይል ኢንዱስትሪዎቿን የማንቀሳቀስ አቅም እንዳላት ለዓለም ያበሰረ ክስተት ሆኖ መመዝገቡን በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

5 months ago
ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ጠንከር ያለ መልዕክት ለግብፅ ላኩ፤ ለኢትዮጵያም ግልባጭ ደርሷል
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ በላኩት ደብዳቤ፣ የዓባይ ውኃ ክፍፍልን በተመለከተ አሜሪካ ዳግም ወደ ሽምግልናው ለመመለስ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።
የመልዕክቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* "አንድ ሀገር ብቻውን መቆጣጠር የለበትም" — ትራምፕ ማንኛውም የቀጠናው ሀገር የዓባይን ሀብት በብቸኝነት በመቆጣጠር ጎረቤቶቹን መጉዳት የለበትም የሚል የአሜሪካን አቋም አንጸባርቀዋል።
* ለኢትዮጵያ የቀረበ ሐሳብ — ኢትዮጵያ በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል እንድታመነጭና ለጎረቤቶቿ እንድትሸጥ፣ ግብፅና ሱዳን ደግሞ በድርቅ ወቅት የሚለቀቅላቸው ውኃ እንዲረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት እንዲደረስ ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።
* የጦርነት ስጋት — በግድቡ ዙሪያ ያለው አለመግባባት ወደ ወታደራዊ ግጭት እንዳያመራ ያላቸውን ስጋት ገልጸው፤ ጉዳዩ በአጀንዳቸው አናት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።
* ግልባጭ — ደብዳቤው ለኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ ለሳውዲው አልጋ ወራሽ እና ለኤምሬትስ ፕሬዝዳንት በግልባጭ ተልኳል።
ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ትራምፕ ለአል ሲሲ የፃፉት ደብዳቤ; የውኃ ክፍፍል ወይስ የልማት እስራት?
በትራምፕ መግለጫ ጀርባ ያሉ ስትራቴጂካዊ ፍላጎቶችና የኢትዮጵያ ስጋቶች
በምስራቅ አፍሪካ ሰማይ ስር ለሺህ ዓመታት ሲፈስ የኖረው የዓባይ ወንዝ፣ ዛሬ የታሪክ፣ የሕግ እና የጂኦ-ፖለቲካ ፍላጎቶች ፍጭት የሚታይበት አውድማ ሆኗል።
ለአንዳንዶች ዓባይ የልማትና የተስፋ ቃል ነው፤ ለሌሎች ደግሞ የህልውና ስጋት።
ሰሞኑን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እና በሱዳን መካከል ያለውን ውጥረት ለመፍታት ዳግም ፍላጎት ማሳየቱ ለቀጠናው ሰላም ተስፋ የሚሰጥ ቢመስልም፣ የቀረበው ሃሳብ ግን በኢትዮጵያ በኩል መሠረታዊ የሆኑ የሉዓላዊነት እና የልማት ጥያቄዎችን አስነስቷል።
1. የ"ውኃ ክፍፍል" ጥያቄና የሕግ መርሆች ፍጭት
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመግለጫቸው "Water Sharing" (የውኃ ክፍፍል) የሚለውን ቃል ሆን ብለው ተጠቅመዋል።
ይህ ቃል በዲፕሎማሲያዊ መዝገበ-ቃላት ውስጥ ቀላል ቢመስልም፣ በውስጡ ግን ሁለት ተቃራኒ የሕግ ጽንሰ-ሃሳቦችን ያጋጫል።
ግብፅና ሱዳን "የታሪክ መብት" እና "ቀደምት ተጠቃሚነት" በሚሉ መርሆች ላይ በመመስረት የውኃ ኮታ (Quota) እንዲቀመጥ ይፈልጋሉ።
በአንጻሩ ኢትዮጵያ የምትከተለው ዓለም አቀፍ መርህ "ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም" (Equitable and Reasonable Utilization) የሚለውን ነው።
"ክፍፍል" የሚለው ቃል ወደ ኮታ ስለሚመራ፣ ኢትዮጵያ ወደፊት ለግብርና ወይም ለሌላ ልማት ከዓባይ ላይ ውኃ እንዳትቀዳ እጇን ሊያስር ይችላል የሚል ስጋት አለ።
ይህ ስጋት ደግሞ የኢትዮጵያን መጪው ትውልድ የልማት ዕድል የሚወስን በመሆኑ ጉዳዩን ልብ አንጠልጣይ ያደርገዋል።
2. የአሜሪካ ሚና፦ አደራዳሪነት ወይስ ወገንተኝነት?
አሜሪካ "የበላይ ተመልካች፣ አስተባባሪ እና ተቆጣጣሪ" ሆና ለመግባት ያሳየችው ፍላጎት በሁለት መንገድ ሊታይ ይችላል።
በአዎንታዊ ጎኑ፣ የአሜሪካ ተጽዕኖ ሀገራቱ ወደ ግጭት እንዳይገቡ እና የቴክኒክ ድጋፎች እንዲመቻቹ ሊረዳ ይችላል።
ይሁን እንጂ፣ ፕሬዝዳንቱ "ለግብፅ ሕዝብ ደህንነት ካለን ቁርጠኝነት" በማለት መነሳታቸው፣ በኢትዮጵያ በኩል ገለልተኛ ዳኛ የመሆን ብቃቷን ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል።
ኢትዮጵያ በዓድዋና በሌሎች የታሪክ አጋጣሚዎች ያስጠበቀችው ነፃነቷ፣ አሁን "በዲፕሎማሲያዊ ሞግዚትነት" ሊሸረሸር አይገባም የሚል ጽኑ አቋም አላት።
ሽምግልናው ከአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር ወጥቶ ወደ ዋሽንግተን መሄዱ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጫና ስር እንድትወድቅና ሉዓላዊ ውሳኔዎቿን አሳልፋ እንድትሰጥ ሊያደርጋት ይችላል የሚለው ስጋት በትንታኔው ውስጥ ጎልቶ ይታያል።
3. የቴክኒክ አጣብቂኝ፦ የድርቅ ወቅት አስተዳደር
በትራምፕ መግለጫ ውስጥ "በድርቅ ወቅት የውኃ ልቀትን ማረጋገጥ" (Predictable releases during drought) የሚለው ነጥብ ትልቁ የቴክኒክ ልዩነት ያለበት ቦታ ነው።
ይህ ነጥብ ለግብፅ የህልውና ዋስትና ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ ደግሞ የኢነርጂ ዋስትና ስጋት ነው።
ተፈጥሮአዊ ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት በግድቡ ውስጥ ያለው የውኃ መጠን ይቀንሳል።
በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ "ለግብፅ ውኃ ልቀቂ" ተብላ ከተገደደች፣ ግድቡ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ሊያቆም ይችላል።
ይህ ማለት ኢትዮጵያ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥታ የገነባችው ግድብ፣ በድርቅ ወቅት ለራሷ ሳይሆን ለታችኞቹ ሀገራት ብቻ አገልግሎት ይሰጣል ማለት ነው።
ኤሌክትሪክን በነፃ ወይም በዝቅተኛ ዋጋ ለግብፅ መስጠት የሚለው ሃሳብም የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ሽግግር እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል "ኢኮኖሚያዊ አጣብቂኝ" ነው።
4. የቀጠናው ሰላም እና "የጦርነት ስጋት" ትርክት
ደብዳቤው በማጠቃለያው ላይ ስለ "ወታደራዊ ግጭት" ማንሳቱ ጉዳዩ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለማሳየት ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ግን በሀገራቱ መካከል ያለውን የመተማመን መንፈስ ሊሸረሽር ይችላል።
አሜሪካ ጦርነትን እንደ አማራጭ ማንሳቷ አንዱ ወገን ሌላውን እንዲያስፈራራ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት አለ።
በተለይም ጉዳዩን ለሳዑዲ ዓረቢያ እና ለኤምሬትስ መሪዎች ግልባጭ ማድረጉ የዓባይን ጉዳይ ከአፍሪካ ቀንድ አውጥቶ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካዊ ተጽዕኖ የመውሰድ ፍላጎት መኖሩን ያሳያል።
ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ከአፍሪካዊ ወንድሞቿ የመነጠል እና በብቸኝነት እንድትደራደር የማድረግ ስልታዊ ጫና ሊሆን ይችላል።
5. ሚዛናዊ መውጫ መንገዶች እና የኢትዮጵያ አቋም
የአሜሪካ ተሳትፎ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው የኢትዮጵያን የልማት ፍላጎት እና የግብፅን የህልውና ስጋት በእኩል ሚዛን ማየት ሲችል ብቻ ነው።
* ለዚህም የሚከተሉት ነጥቦች እንደ መፍትሔ ይነሳሉ
የአፍሪካዊ መፍትሔ የበላይነት ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ቀጥሎ አሜሪካ እና ሌሎች አካላት በታዛቢነት እና በቴክኒክ ድጋፍ ቢሳተፉ ይበልጥ ተቀባይነት ይኖረዋል።
ሁለገብ ስምምነት (CFA) ስለ ውኃ ክፍፍል የሚደረግ ውይይት በሦስቱ ሀገራት ላይ ብቻ ሳይሆንሁሉንም የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን ባካተተ መልኩ መካሄድ አለበት።
የጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win) ትኩረቱ ከፖለቲካዊ ጫና ወጥቶ ድርቅን በጋራ ለመቋቋም በሚያስችል ሳይንሳዊ እና ቴክኒካዊ ስምምነት ላይ ማተኮር ይኖርበታል።
* ማጠቃለያ የኢትዮጵያ ቀይ መስመር
ይህ የአሜሪካ መግለጫ ለኢትዮጵያ የሰላም ጥሪ ቢመስልም፣ በጥንቃቄ ካልተያዘ ግን የልማት ዕድሏን የሚገደብ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ሊሆን ይችላል።
ኢትዮጵያ 86% የሚሆነውን ውኃ እያመነጨች፣ በገዛ ሀብቷ የመጠቀም መብቷን አሳልፋ መስጠት የለባትም።
የዓባይ ጉዳይ የዛሬ ብቻ ሳይሆን፣ የመጪው ትውልድ የህልውና መሰረት ነው።
በመሆኑም ኢትዮጵያ በሕዝባዊ አንድነት፣ በዲፕሎማሲያዊ ብልሃት ይህንን ጫና መቋቋም ይኖርባታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

👉በትራምፕ መግለጫ ጀርባ ያሉ ስትራቴጂካዊ ፍላጎቶችና የኢትዮጵያ ስጋቶች
በምስራቅ አፍሪካ ሰማይ ስር ለሺህ ዓመታት ሲፈስ የኖረው የዓባይ ወንዝ፣ ዛሬ የታሪክ፣ የሕግ እና የጂኦ-ፖለቲካ ፍላጎቶች ፍጭት የሚታይበት አውድማ ሆኗል። ለአንዳንዶች ዓባይ የልማትና የተስፋ ቃል ነው፤ ለሌሎች ደግሞ የህልውና ስጋት። ሰሞኑን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እና በሱዳን መካከል ያለውን ውጥረት ለመፍታት ዳግም ፍላጎት ማሳየቱ ለቀጠናው ሰላም ተስፋ የሚሰጥ ቢመስልም፣ የቀረበው ሃሳብ ግን በኢትዮጵያ በኩል መሠረታዊ የሆኑ የሉዓላዊነት እና የልማት ጥያቄዎችን አስነስቷል።
1. የ"ውኃ ክፍፍል" ጥያቄና የሕግ መርሆች ፍጭት
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመግለጫቸው "Water Sharing" (የውኃ ክፍፍል) የሚለውን ቃል ሆን ብለው ተጠቅመዋል። ይህ ቃል በዲፕሎማሲያዊ መዝገበ-ቃላት ውስጥ ቀላል ቢመስልም፣ በውስጡ ግን ሁለት ተቃራኒ የሕግ ጽንሰ-ሃሳቦችን ያጋጫል።
ግብፅና ሱዳን "የታሪክ መብት" እና "ቀደምት ተጠቃሚነት" በሚሉ መርሆች ላይ በመመስረት የውኃ ኮታ (Quota) እንዲቀመጥ ይፈልጋሉ። በአንጻሩ ኢትዮጵያ የምትከተለው ዓለም አቀፍ መርህ "ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም" (Equitable and Reasonable Utilization) የሚለውን ነው። "ክፍፍል" የሚለው ቃል ወደ ኮታ ስለሚመራ፣ ኢትዮጵያ ወደፊት ለግብርና ወይም ለሌላ ልማት ከዓባይ ላይ ውኃ እንዳትቀዳ እጇን ሊያስር ይችላል የሚል ስጋት አለ። ይህ ስጋት ደግሞ የኢትዮጵያን መጪው ትውልድ የልማት ዕድል የሚወስን በመሆኑ ጉዳዩን ልብ አንጠልጣይ ያደርገዋል።
2. የአሜሪካ ሚና፦ አደራዳሪነት ወይስ ወገንተኝነት?
አሜሪካ "የበላይ ተመልካች፣ አስተባባሪ እና ተቆጣጣሪ" ሆና ለመግባት ያሳየችው ፍላጎት በሁለት መንገድ ሊታይ ይችላል። በአዎንታዊ ጎኑ፣ የአሜሪካ ተጽዕኖ ሀገራቱ ወደ ግጭት እንዳይገቡ እና የቴክኒክ ድጋፎች እንዲመቻቹ ሊረዳ ይችላል። ይሁን እንጂ፣ ፕሬዝዳንቱ "ለግብፅ ሕዝብ ደህንነት ካለን ቁርጠኝነት" በማለት መነሳታቸው፣ በኢትዮጵያ በኩል ገለልተኛ ዳኛ የመሆን ብቃቷን ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል።
ኢትዮጵያ በዓድዋና በሌሎች የታሪክ አጋጣሚዎች ያስጠበቀችው ነፃነቷ፣ አሁን "በዲፕሎማሲያዊ ሞግዚትነት" ሊሸረሸር አይገባም የሚል ጽኑ አቋም አላት። ሽምግልናው ከአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር ወጥቶ ወደ ዋሽንግተን መሄዱ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጫና ስር እንድትወድቅና ሉዓላዊ ውሳኔዎቿን አሳልፋ እንድትሰጥ ሊያደርጋት ይችላል የሚለው ስጋት በትንታኔው ውስጥ ጎልቶ ይታያል።
3. የቴክኒክ አጣብቂኝ፦ የድርቅ ወቅት አስተዳደር
በትራምፕ መግለጫ ውስጥ "በድርቅ ወቅት የውኃ ልቀትን ማረጋገጥ" (Predictable releases during drought) የሚለው ነጥብ ትልቁ የቴክኒክ ልዩነት ያለበት ቦታ ነው። ይህ ነጥብ ለግብፅ የህልውና ዋስትና ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ ደግሞ የኢነርጂ ዋስትና ስጋት ነው።
ተፈጥሮአዊ ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት በግድቡ ውስጥ ያለው የውኃ መጠን ይቀንሳል። በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ "ለግብፅ ውኃ ልቀቂ" ተብላ ከተገደደች፣ ግድቡ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ሊያቆም ይችላል። ይህ ማለት ኢትዮጵያ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥታ የገነባችው ግድብ፣ በድርቅ ወቅት ለራሷ ሳይሆን ለታችኞቹ ሀገራት ብቻ አገልግሎት ይሰጣል ማለት ነው። ኤሌክትሪክን በነፃ ወይም በዝቅተኛ ዋጋ ለግብፅ መስጠት የሚለው ሃሳብም የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ሽግግር እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል "ኢኮኖሚያዊ አጣብቂኝ" ነው።
4. የቀጠናው ሰላም እና "የጦርነት ስጋት" ትርክት
ደብዳቤው በማጠቃለያው ላይ ስለ "ወታደራዊ ግጭት" ማንሳቱ ጉዳዩ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለማሳየት ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ግን በሀገራቱ መካከል ያለውን የመተማመን መንፈስ ሊሸረሽር ይችላል። አሜሪካ ጦርነትን እንደ አማራጭ ማንሳቷ፣ አንዱ ወገን ሌላውን እንዲያስፈራራ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት አለ።
በተለይም ጉዳዩን ለሳዑዲ ዓረቢያ እና ለኤምሬትስ መሪዎች ግልባጭ ማድረጉ፣ የዓባይን ጉዳይ ከአፍሪካ ቀንድ አውጥቶ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካዊ ተጽዕኖ የመውሰድ ፍላጎት መኖሩን ያሳያል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ከአፍሪካዊ ወንድሞቿ የመነጠል እና በብቸኝነት እንድትደራደር የማድረግ ስልታዊ ጫና ሊሆን ይችላል።
5. ሚዛናዊ መውጫ መንገዶች እና የኢትዮጵያ አቋም
የአሜሪካ ተሳትፎ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው የኢትዮጵያን የልማት ፍላጎት እና የግብፅን የህልውና ስጋት በእኩል ሚዛን ማየት ሲችል ብቻ ነው። ለዚህም የሚከተሉት ነጥቦች እንደ መፍትሔ ይነሳሉ፦
የአፍሪካዊ መፍትሔ የበላይነት፦ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ቀጥሎ፣ አሜሪካ እና ሌሎች አካላት በታዛቢነት እና በቴክኒክ ድጋፍ ቢሳተፉ ይበልጥ ተቀባይነት ይኖረዋል።
ሁለገብ ስምምነት (CFA)፦ ስለ ውኃ ክፍፍል የሚደረግ ውይይት በሦስቱ ሀገራት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉንም የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን ባካተተ መልኩ መካሄድ አለበት።
የጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win)፦ ትኩረቱ ከፖለቲካዊ ጫና ወጥቶ፣ ድርቅን በጋራ ለመቋቋም በሚያስችል ሳይንሳዊ እና ቴክኒካዊ ስምምነት ላይ ማተኮር ይኖርበታል።
❗️ማጠቃለያ፦ የኢትዮጵያ ቀይ መስመር
ይህ የአሜሪካ መግለጫ ለኢትዮጵያ የሰላም ጥሪ ቢመስልም፣ በጥንቃቄ ካልተያዘ ግን የልማት ዕድሏን የሚገደብ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ሊሆን ይችላል። ኢትዮጵያ 86% የሚሆነውን ውኃ እያመነጨች፣ በገዛ ሀብቷ የመጠቀም መብቷን አሳልፋ መስጠት የለባትም።
የዓባይ ጉዳይ የዛሬ ብቻ ሳይሆን፣ የመጪው ትውልድ የህልውና መሰረት ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያ በሕዝባዊ አንድነት፣ በዲፕሎማሲያዊ ብልሃት ይህንን ጫና መቋቋም ይኖርባታል።
የኢትዮጵያን መብት ጥሶ በጋራ ተጠቃሚነትን ስም ያሚመጣ ስምምነት ለቀጠናው ሰላም የሚያመጣ ቢመስልም ፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የልማት መብት መጣስ ግን መፍትሔ ሊሆን አይችልም።

6 months ago
የኢትዮጵያ"የሀይል ማስፋት" (Power Projection)፡በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዲፕሎማሲ ጥረት...!
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ )
#ethiopia | በቅርቡ የተከናወነው በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት የG-20 የኢትዮጵያ ተሳትፎ እንዲሁም የማሌዥያና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት፣የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት እየተከተለው ያለውን የዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ "የሀይል ማስፋት"ስትራቴጂ ቁልፍ ማሳያዎች ናቸው።ይህ ስትራቴጂ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ በማስፋት፣ለሀገር ውስጥ ዕድገት የሚያስፈልገውን ሀብትና ዕውቀት ለመሳብ ያለመ መሆኑን ያሳያል።
🔴 የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዲፕሎማሲያዊ ራዕይ፦
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በዋናነት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ (Economic Diplomacy) እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በማስፋት ላይ ያተኮረ ነው።ከዓለም ደቡብ (Global South) አገሮች በተለይም ከእስያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር አዲስና ጠንካራ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መገንባት፤ በሁሉም ወገን የሀገርን መሰረታዊ ብሄራዊ ጥቅም ማስከበር እና ማረጋገጥ አጋርነትን ማስፋትን ያካትታል።
የ"ብልጽግና" ጽንሰ-ሀሳብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በሙሉ ከብልጽግና ራዕይ ጋር የተሳሰሩ ሲሆን፣ የውጭ ግንኙነት በዋናነት ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ዕድገት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲያገለግል ለማድረግ ያለመ ነው።
🔴የቡድን ሀያ አባለ ሀገራት (G-20) ተሳትፎ፦የብዙ-ዋልታ ዓለምን (Multipolar World) መቀበል ኢትዮጵያ በG-20 ስብሰባ ላይ እንደ ልዩ እንግዳ መሳተፏ፣በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀንድ ባሻገር ዓለም አቀፋዊ ተዋናይ አድርጎ ለማስቀመጥ ያለውን ጥረት ያሳያል።በዓለም የፋይናንስ እና የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ ማዕከላት ላይ ድምጽ እንዲኖራት ማድረግ።ክቡር ዶ/ር ዐቢይ በተደጋጋሚ እንደሚገልጹት፣ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኀብረት ዋና መስሪያቤት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን የአፍሪካን አጠቃላይ ጥቅም በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በማንሳት፣ የሀይል ማስፋት ጥረቷን ከአህጉራዊ ሚናዋ ጋር አጣምራለች።
🔴 የእስያ መሪዎች ጉብኝት፦የቴክኖሎጂና የኢንቨስትመንት ድልድይ የማሌዥያ እና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት የዶ/ር ዐቢይ የዲፕሎማሲ ጥረት ዋነኛ መገለጫ ነው።ከእነዚህ ፈጣን ዕድገት ካላቸው የእስያ "ነብሮች" (Asian Tigers) ጋር ግንኙነት መፍጠር የኢትዮጵያን የመበልፀግ የማደግ ስትራቴጂ ለመደገፍ ወሳኝ ነው።
🖊እንደ መውጫ ስልታዊ ትኩረት የሀይል ማስፋት ትርጉም⁉️
ሲንጋፖር የላቀ የሎጅስቲክስ አስተዳደር፣ ዘመናዊ የከተማ ልማት (Smart City)፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልምድ ሽግግር፤ የኢትዮጵያን የባህር በር ፈተና ለመቅረፍ ዘመናዊ የንግድ መስመሮችን መገንባት እንደ አስረጅነት ይጠቀሳል ።( በሀገራችን በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልል ከተሞች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይጠቀሳል ።
ማሌዥያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) በኤሌክትሮኒክስና በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሳብ፣ የዘይትና ዘይት ነክ ምርቶች ንግድ በማጠናከር የኢኮኖሚ አጋርነትን እና የንግድ አጋሮች ማጎልበትን ያሳያል ።( Industrial Park Development cooperation ስር የሚከናወኑ የእውቀት እና የኢንዱስትሪ ሽግግር መጥቀስ ይቻላል ።)
🔴የማጣቀሻዎች (Reference )
1️⃣Abiy Ahmed (PhD). Medemer: A Collective Journey. (የዶ/ር ዐቢይ የፍልስፍና መሰረት ለዲፕሎማሲያዊ ስትራቴጂያቸው።)
2️⃣ Minister's Office. Official Press Releases on G20 and Bilateral Visits. (የጉብኝቶቹን ዓላማ እና የተደረጉትን ስምምነቶች ለመረዳት።)
3️⃣Think Tank Analysis. ISS, Chatham House or Brookings papers focused on Ethiopia's shift in foreign policy towards Asia and Global South engagement.
ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ የሀይል ማስፋት እቅድ በዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት ኢኮኖሚን ማዕከል ባደረገ እና በብዙ-ዋልታ ትብብር ላይ በተመሰረተ ዘመናዊ ዲፕሎማሲ እየተመራ መሆኑን ያሳያል ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia 🇪🇹
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-tps://x.com/HDebasu?t=WkEcsELrZrHGV1UGX3oSMg&s=09
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

Comments