ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ የኢነርጂ ፕሮጀክት ተብሎ ተመረጠ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአፍሪካ የንግድ ምክር ቤት የ2026 የዓመቱ "የኢንዱስትሪ ኢነርጂ ፕሮጀክት" (Industrial Energy Project of the Year) ተብሎ ተመረጠ።
የዕውቅና ሥነ-ሥርዓቱ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ማታ በጋና አክራ ኬምፐንስኪ ጎልድ ኮስት ሆቴል ተካሂዷል።
ዕውቅናው የታላቁ ህዳሴ ግድብ አህጉራዊ ፋይዳ ያለው ታላቅ የኢንዱስትሪ ኢነርጂ ፕሮጀክት መሆኑን ለመመስከር ያለመ ነው።
የዕውቅና ሽልማቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን በመወከል በጋና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተጠባባቂ የሚሲዮን መሪ የሆኑት ክቡር አምባሳደር አሣየ ዓለማየሁ (ዶ/ር) ተቀብለዋል።
በእውቅና ሽልማቱ ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችና ተቋማት ኃላፊዎች፣ ኣምባሳደሮች እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡
በአፍሪካ የንግድ ምክር ቤት የአፍሪካ የንግድ ሽልማት ዳይሬክተር መሀሙዱ ሃያቱ እንደገለፁት ምክር ቤቱ ፕሮጀክቱን ለመሸለም የወሰነው ግድቡ ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሽግግር፣ ለቀጣናዊ የንግድና የኤሌክትሪክ ትስስር እያበረከተ ያለውን የጎላ አስተዋጽኦ እና የፕሮጀክት አመራር ሚና ዕውቅና ለመስጠት ነው።
ግድቡ በኃይል ማመንጨት አቅምና ዋስትና እንዲሁም በረጅም ጊዜ የኢንዱስትሪ ሽግግር ላይ የተደረገ ትልቅ ኢንቨስትመንት መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ግድቡ ለከፍተኛ ማኑፋክቸሪንግ፣ ለግብርና ማቀነባበሪያ እና ለኢንዱስትሪ የእሴት ሰንሰለቶች መሠረት የጣለ መሆኑን የጠቆሙት ሚስተር መሀሙዱ ለቀጣናዊ የኃይል ትስስር እና ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ዕውቅናው በአፍሪካ ንግድ ሽልማት ቋሚ ተቋማዊ መዝገብ ላይ የሚሰፍር ይሆናል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በኤምባሲው በኩል ዕውቅናውን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ሽልማቱ የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሀገራት በራሳችን ሀብትና ጥረት ለመገንባት ያለንን የጋራ ምኞት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ግድቡ ግዙፍ፣ ውስብስብ እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች በአፍሪካውያን ታስበው፣ ተገንብተው እና ተመርተው ለአፍሪካውያን የጋራ ብልፅግና ሊውሉ እንደሚችሉ ማረጋገጫ የሰጠ ነው።
ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ ኢነርጂ-መር የልማት ጎዳና የምታደርገውን ስልታዊ ሽግግር የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው ብለዋል ዋና ሥራ አስፈፃሚው በመልዕክታቸው።
ኢትዮጵያ ታዳሽ የውሃ ኃይልን በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና የአካባቢ ጥበቃ ተደጋግፈው የሚሄዱ ጉዳዮች መሆናቸውን እያስመሰከረች እንደምትገኝ አብራርተዋል።
ግድቡ በአሁኑ ወቅት ፋብሪካዎችን በማንቀሳቀስ፣ የዲጂታል ሽግግርን በማገዝ እና በምስራቅ አፍሪካ የኃይል ገንዳ (Eastern Africa Power Pool) በኩል ድንበር ተሻጋሪ የኃይል ትስስርን በማጠናከር እንደ አህጉራዊ የኃይል ማዕከል እያገለገለ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ዕውቅናው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ ስኬት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን በማንሳት ፕሮጀክቱ አፍሪካ በራሷ ኃይል ኢንዱስትሪዎቿን የማንቀሳቀስ አቅም እንዳላት ለዓለም ያበሰረ ክስተት ሆኖ መመዝገቡን በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

4 months ago