27 days ago
አገራዊ የንስሐ የይቅርታና የዕርቅ ሰላም ጥሪ ቀረበ።
የኢትዮጵያ የእምነት እናቶች ሀገራዊ ፈውስና ሰላም ለማምጣት የ3 ቀናት ብሔራዊ የጾምና የንስሐ ጸሎት ጠየቁ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የተለያዩ የእምነት እናቶች፣ ሀገሪቱ ከምትገኝበት ማህበራዊ፣ ሥነ-ምግባራዊና ሰብአዊ ቀውስ እንድትወጣ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በማለም፣ ለሁሉም የሃይማኖት መሪዎች የ3 ቀናት ብሔራዊ የንስሐና የጾም ጸሎት እንዲታወጅ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር ኤርጊጎ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብር እንግድነት በተገኙበት በዚህ መርሀ ግብር የሀይማኖት አባቶች በፀሎት ፕሮግራሙን እንደከፈቱት ለማወቅ ተችሏል።
እናቶቹ «ልዩ ቀን ለኢትዮጵያ» በሚል መሪ ቃል ባወጡት መግለጫ፣ በሀገሪቱ እየተስፋፉ ያሉ የጥላቻ ንግግሮች፣ ቂም፣ በቀልና የእርስ በርስ ግጭቶች የማህበረሰቡን አንድነት እየጎዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም መፈናቀል፣ ሙስና እና ግጭቶች በእናቶችና በቤተሰቦች ላይ ከባድ ስቃይ እያደረሱ መሆኑን በመጠቆም፣ «የሟችም የገዳይም እናት እኔው ነኝ» በሚል መንፈስ የግጭቱ ሰለባዎች ሁሉ ሊደገፉና ሊፅናኑ እንደሚገባ ወይዘሮ ትዕግሥት ታምራት ከአስተባባሪዎቹ አንዷ አሳስበዋል።
በመግለጫቸው የሃይማኖት አባቶች በሀገር ሰላምና እርቅ ሂደት ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
እናቶቹ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ ቀናት በጾም፣ በጸሎትና በንስሐ በመተባበር ለሀገራዊ ፈውስና ለዘላቂ ሰላም ወደ ፈጣሪ እንዲማፀኑ አሳስበዋል።
ወይዘሮ መአዛ በቀለ ከዕለቱ መርሀ ግብር አስተባባሪዎች አንዷ ባሰሙት ንግግር ሰላምን እና ፍቅርን ለማንገስ መፍትሔ በሐይማኖት አባቶች ዘንድ አለ ብለዋል።
በእውነተኛ ንስሐ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይሆናል በመሆኑም መንፈሳዊ አባቶች ትልቅ አደራ ተጥሎባችኃል ሲሉ ወይዘሮ መኣዛ ንስሀ መግባት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የሰላም፣ የእርቅና የመተማመን መንገድን ለመገንባት የጀመረቻቸው የሀገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትህ ሂደቶች ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ወሳኝ እርምጃዎች ተደርገው ይታያሉ።
እነዚህ ሂደቶች የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጡ ግን የህዝቡ ተሳትፎ፣ መተማመን፣ ይቅርታና የሞራል መታደስ ወሳኝ መሠረቶች ናቸው።
በዚህ አውድ የእምነት እናቶች ያቀረቡት የ3 ቀናት ብሔራዊ የንስሐና የጾም ጸሎት ጥሪ፣ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት፣ የቆዩ ቁስሎችን ለማከም እና የጋራ ሀገራዊ እሴቶችን ለማጠናከር ከሚደረጉ ጥረቶች ጋር የሚስማማ መንፈሳዊ አስተዋፅኦ ነው።
ዘላቂ ሰላም በሕግ ብቻ ወይም በፖለቲካ ስምምነት ብቻ አይገነባም፤ እውነትን በመቀበል፣ ፍትሕን በማክበር፣ ይቅርታን በማጎልበትና በጋራ የወደፊት ተስፋን በመገንባት እንጂ።
ስለዚህ ሀገራዊ ምክክር፣ የሽግግር ፍትህ ሂደት እና የእምነት ተቋማት የሚያበረታቱት የንስሐና የጸሎት መንፈስ ተደጋግፈው ሲጓዙ፣ በመተማመን፣ በእርቅና በአንድነት የተመሠረተች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጠንካራ መሠረት የሚፈጥር ነው።
በዕለቱ በተደረገው መርሀ ግብር መንፈሳዊ አባቶች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እና እንዲመካከሩ ዕድል የተሰጣቸው ሲሆን እነርሱም ተመካክረው መፍትሔ የሚሉትን ሀሣብ አቅርበዋል።
በዛሬው መርሀ ግብር ላይ የታደሙ እንግዶች ከሻይ ዕረፍት በኃላ የተሰማቸውን ሀሣብ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ የእምነት እናቶች ለሰላም በሚል መሪ ሀሣብ የተካሄደው ይህ ፕሮግራሙ ላለፉት 20 አመታት ቅድመ ዝግጅት ሲደረግበት እንደነበር አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
እናቶች ይህን መርሀ ግብር ዕውን ለማድረግ በትዕግሥት ተሞልተው ለዚህ ቀን በማድረሳቸው ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል ሲሉ በመድረኩ ላይ አስተያየት የሰጡ ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #የኢትዮጵያየእምነትእናቶች #የፆምናፀሎትፕሮጎራም

Comments