29 days ago
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ብጹዕ አባታችን አቡነ መርቆሪዮስ ፣ የካናዳ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል
መንፈሳዊ ተልዕኮ ተቀብላችሁ ልዑል እግዚአብሔር በሰጣችሁ ጸጋ በተለያየ ስፍራ የምታገለግሉ ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን
ጥሪ የተደረገላችሁ ተጋባዥ እንግዳዎች ፣
የመንግስት እና የግል ሚዲያ ተቋማት ፣
ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለተገኛችሁ በልዑል እግዚአብሔር ስም ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን።
"ጾም የነፍስ ምግብ ነው፤ ለፈተናም መቋቋሚያ ጥንካሬን ይሰጣል።" እንዲል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ።" እኛ ኦርቶዶክሳዊያን የሐዋሪያት ጾም ላይ እንገኛለን፡፡
የሰኔ ጾም (ጾመ ሐዋርያት) ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰባቱ አዋጅ አጽዋማት አንዱ ሲሆን፣ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉና ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው።ይህ ጾም እንደ እምነቱ አስተምህሮ ለሁሉም ክርስቲያን የተሰጠ የበረከት ጾም ነው። ይህን ጾም እንድንካፈል ለፈቀደልን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው፤ለጾሙ ፍችም በሰላም ያድርሰን እያልኩ፣መግለጫው የተዘጋጀው በጽሁፍ ስለሆነ በተዘጋጀበት አግባብ ይቀርባል፡፡
በወልድ ውሉድ ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ ፣ አምላኩን በንጽሐ ነፍስ ፣ በንጽሐ ሥጋ የሚያገለግልበት እና ፣ ከራሱ ከፈጣሪው መድሐኒዓለም ክርስቶስ ዘንድ የተሰጠው የጸጋ አገልግሎት፣ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ የሚያገኙት ፤ መጨከንን ፣ ጥብዓትን ፣ ትሕርምትን እና ትዕግሥትን የሚጠይቅ ሕይወት ፣ የምንኩስና ሕይወት እና ሥርዓት ነው።የምንኩስና ሕይወት እና የገዳማዊ ሥርዓት በቅዱሳን አባቶች አባ እንጦንስ እና አባ መቃርስ የተጀመረ ሲሆን ፣ ሕይወቱም ሥርዓቱም በቀኖና ቤተክርስቲያን የተደነገገ እና የጸደቀ ሕግ ነው።
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ፣ ገዳም የእኔ የግሌ የሚሉት ንብረት የሌለበት፣ ሁሉ በማኅበር በአንድነት በጸሎት በስራ እየተጉ ፍጹም የዓለምን ኃላፊነት ተረድተው ፣ የማታልፍ የእግዚአብሔር መንግስት እንዳለች በመገንዘብ ዘወትር በቀኖና ተወስነው የሚኖሩበት የቅዱሳን መኖሪያና ጸጋ እግዚአብሔር የማይለይበት የዲያቢሎስ ፈተና የሚበዛበት ስፍራ ነው።
ገዳምና ገዳማዊ ሕይወት አስፈላጊ በመሆኑ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርአያ ሆኖን ፣ በገዳመ ቆሮንጦስ ከዲያቢሎስ ይፈተን ዘንድ ተቀመጠ (ማቴ. 4፡ 1-11) ፈታኝ ዲያቢሎስንም ድል አደረገው ፣ ገዳምና ገዳማዊ ሕይወት አስፈላጊ ሆኖ የመሰረተልን አምላካችን አርአያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዛሬም እርሱን በመከተል ገዳማዊ ሕይወት ለትሩፋት መስሪያ ፣ ለንስሃ ሕይወት ማቆያ ፣ ለበረከት ለረድኤት የአምላካችንን አርአያነት ተከትለው አባቶች እናቶች በገዳም ተወስነው ይገኛሉ።
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ “ገዳማዊ ህይወት” ራስን ለእግዚአብሔር በማስገዛት ትህትናን ገንዘብ አድርጎ እያንዳንዷን ሰዓት አንደበትን ፣ ጉልበትን እና ሃሳብን ለእግዚአብሔር በመስጠት የዓለም ዝና ሃብት ንብረት አላፊ የሆነውን ንግሥና ውበትን በመናቅ ቤተሰብ እና ዘመድን ተለይቶ በመውጣት በገዳም ውስጥ በስርዓተ አበው ተወስኖ መስቀሉን ተሸክሞ መኖር መሆኑን ትናገራለች።
ገዳማት የቤተ-ክርስቲያናችን ስውር ጓዳዎችና የሚስጢር መዝገቦች ፣ የመማጸኛ ቅዱስ ስፍራዎች ፣ የቤ-ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎት መሰረት ፣ የተግባራዊ ክርስትና ምሳሌዎች እና የታላላቅ የቤተ-ክርስቲያን ሊቃውንት መፍለቂያዎች ናቸው።
እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት እና ገዳማት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን እየሰጡ ፣ ትውልድንም በክርስቲያናዊ ስነ-ምግባር እያነጹ ይቀጥሉ ዘንድ ገቢ ያስፈልጋቸዋል። ይህንን ገቢያቸውን ከሚያገኙባቸው መንገዶች መካከል በራሳቸው አቅም ገቢ የሚያመነጩ ስራዎችን ማከናወን እንዲሁም ምዕመኑ በሚሰጡት መባ እና አስራት በኩራት ይጠቀሳሉ።
ይሁንና አንዳንዴ ተፈጥሮ ፊቷን ስታዞር እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ሲበረቱ ሰው ሰራሽ ችግሮችም ሲጨመሩ፣ገዳማት የገቢ ምንጫቸውና ህልውናቸው ሙሉ በሙሉ ህዝበ ክርስቲያኑ በሚያደርገው ድጋፍ ላይ የተንጠለጠለ የሚሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል ፤ ከ160 በላይ ገዳማዊያን የሚገኙበት ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የገጠመው ችግርም በዚህ ደረጃ የሚገለጽ ነው።
በዚህ ገዳም የሚገኙ ገዳማውያን ከፀሃይ ፣ ከብርድ ፣ ከዝናብ የሚከላከል መጠለያ አጥተው በከፍተኛ ችግር እየተፈተኑ የሚገኙ በመሆኑ ፣ ገዳማውያኑ ከነዚህ ችግሮች እንዲወጡ እና በቀጣይም ገዳሙ ራሱን እንዲችል ለማድረግ ፣ በጠቅላይ ቤተ-ክህነት እውቅና እና በሐገረ ስብከቱ ፍቃድ ገዳሙ ብቻ የሚጠቀመው በገዳሙ ስም የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ይፋ ተደርገው ፣ በሕዝበ ክርስቲያኑ በሚደረገው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ፣ ገዳሙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በወረዳ ቤተ-ክህነት ፣ በሐገረ ስብከት እና በጠቅላይ ቤተ-ክህነት ጸድቆ በሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬና የቅርብ ክትትል እየተደረገበት ከምዕመናን በሚገኘው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።
“ከእግዚአብሔር ዐይን የተሰወረ ምንም ፍጥረት የለም፤ ስለ ራሳችን መልስ መስጠት በሚገባን በርሱ ፊት ሁሉም ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው” (ዕብራውያን 4:13) እንዲል ቃሉ፣እኛም አጠቃላይ ፕሮጀክቱን በተመለከተ የተሰሩ ስራዎችን፣የተደረገውን ድጋፍ፣ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ስራዎች እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተለያዩ ጊዜያት ለምዕመኑ ይፋ እያደረግን፣እያሳወቅን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ዛሬ ስለ ፕሮጀክቱ እና የደረሰበትን ደረጃ በሚመለከት የምንሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለ4ኛ ጊዜ ሲሆን ይህም ምዕመኑ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ወቅታዊ የስራ ደረጃን እንዲገነዘብ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡
በገዳሙ የተያዙ የልማት ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ገቢ የማሰባሰብ ሂደት ዕቅዶችን በመንደፍ እና በመቅረጽ ተግባራዊ ለማድረግ ስንቀሳቀስ ቆይተናል፣አሁንም በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን። ለአብነትም ገዳሙ ያለበትን አሁናዊ እና ተጨባጭ ሁኔታ የሚገልፁ እና የሚያሳዩ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ ቀኖና እንዲሁም ትውፊት በጠበቀ መልኩ
በቴሌቪዥን ጥራታቸውን የጠበቁና ገላጭ የሆኑ ዶክመንተሪዎችን በማስተላለፍ ህብረተሰቡ መረጃው ኖሮት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥረት ተደርጓል።
ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ለታቀዱት የልማት ስራዎች የሚያስፈልገውን ገቢ ለማሰባሰብ ጥረት ተደርጓል፤እየተደረገም ይገኛል። በዚህም እስከ አሁን 52,640,000 ብር ( ሃምሳ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ሽህ ብር)የገንዘብ ድጋፍ እና 11,320,000 ብር ( አስራ አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ሽህ ብር) የሚገመት የአይነት ድጋፍ ማሰባሰብ ተችሏል።
በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የተጀመረው ፕሮጀክት 2 ዓመት ከ 6 ወር ያስቆጠረ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ምዕራፍ የፕሮጀክቱን 65 % በላይ ማሳካት ተችሏል። ከእነዚህም መካከል፦
የእናቶች በዓት እና የእንግዳ ማረፊያ በጥሩ ሁኔታ ተገንብቶ እናቶች እየተገለገሉበት ይገኛል።
ለገዳማውያኑ እንቅስቃሴ የማይመች እና አዳጋች የነበረው መንገድ 179 ሜትር ተራራ ተቦርቡሮ በአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
የእናቶች ቤተ እግዚአብሔር ግንባታ ተከናውኖ ሙሉ ቁሳቁስ ተሟልቶለት እየተገለገሉበት ይገኛል።
ገዳማት መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ኃላፊነት የሚወጡበት ፣ በተፈጥሮ እና ሰው - ሰራሽ አደጋዎች የተጎዱ ማኅበረሰቦችን የሚረዱበት እና ሕገ ወንጌልን የሚፈጽሙበት አቅምን ለማግኘት ፣ የኢኮኖሚ ነጻነት አስፈላጊ ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ “ገዳማዊ ሕይወት ጠንካራ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እንዲሁ ጠንካራ ትሆናለች ፤ ነገር ግን ገዳማዊ ሕይወት መዳከም ከጀመረ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ትደክማለች።” በማለት የገዳማት መጠንከርን አጽንዖት ሰጥቶ ይናገራል።
በዚህም መሰረት ገዳማዊያኑ በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸውን የምግብ አቅርቦት ችግር እና የአቅም ውስንነት በዘላቂነት ለመቅረፍ፣ ገዳማውያኑ እየሰሩ ቀጣይነት ያለው ገቢ እንዲያመነጩ ለማድረግ በማሰብ በሃሙሲት ከተማ የሸቀጣ ሸቀጥ እና የንዋያተ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ተከፍቶ እየሰሩበት ይገኛሉ እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ሱቅ ተከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
የእርሻ መሬት በመከራየት የእህል እና የጥጥ ምርቶችን በስፋ እያመረቱ ይገኛሉ፡፡
ገዳሙ በሃሙሲት ከተማ ላይ የእህል መጋዘን በመከራየት ያመረታቸው ምርቶች እንዲሁም ከገበሬ በመረከብ ለአከባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በስፋት እያቀረበ ይገኛል፡፡
ግሸን እና ላሊበላ እንዲሁም የተለያዩ አብያተክርስቲያናት እና ገዳማት ላይ ገዳሙ ያመረታቸው ምርቶች ለሽያጭ እያቀረበ ይገኛል፡፡
ምንኩስና በምድር ላይ እየኖሩ ከምድራውያን ተለይቶ ከሰማያውያን ቅዱሳን መላእክት ጋር ኅብረት የሚፈጥሩበት እና የሚገናኙበት መንገድ ነው።ሥራ ደግሞ የቅድስና መድረሻ የዲያብሎስ ውጊያን ማምለጫ መንገድ ነው። እንደ ሃገራችን አባባል “ሥራ የፈታ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል።” እንዲል ፣ ያለ ሥራ መቀመጥ በገዛ ፍቃድ አዕምሮን ለሰይጣን ቤተ ሙከራነት ማስረከብ ነውና ፣ ሁሌ ትጥቃቸውን ይዘው ከእግሩ በታች በመሆን የሚተጉ ንቁዓን ወታደሮች ፤ ሀብት ንብረታቸውን ትተው ለዓለሙ ሙት የሆኑ መነኮሳት በተሰበሰቡበት ገዳም፦ እርሻ ፣ የእጅ ሥራ እንዲሁም ሌሎች ተግባራትን የሚያከናውኑበት ቦታ ሊኖራቸው ግድ ነው። ነገር ግን በሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ያለው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ እና በረሃማነት ፣ ለእርሻ ሥራ ምቹ ባይሆንም ሴት መነኮሳዪያት የሚሠሩበት የተግባር ቤት ግንባታ ተጠናቆ ፣ የእደ ጥበብ ማምረቻ ማሽኖች ገብተው ገዳሙ ገቢ የሚያገኝበት እና ፣ መነኮሳዪታት የሰይጣንን ፈተና ድል የሚነሱበት ምቹ የሥራ ቦታ ተፈጥሯል። ከ20 ላላነሱ መነኮሳዪያት ሙያዊ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ቦታ ድረስ በማቅረብ ለረጅም ወራት ሥልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ስራ ገብተዋል።
የሻማ እና የጧፍ መስሪያ ማሽኖች ግዢ ተፈጽሞ ወደ ምርት ተገብቷል፣ በስፋት ለሽያጭ እየቀረበም ይገኛል፡፡
ገዳማት ከተፈጥሮ ጋር ባላቸው ትስስር ገዳማውያን ለሱባኤ የሚመርጡት ከከተማ የወጡ ፣ ዙርያቸውን በዕፀዋት የተሸፈኑ ገዳማትን ነው። ቤተክርስቲያን የነፍስን ቁስል ስታክም የተፈጥሮ መንፈስን ታድሳለች። ይህን ተመጋጋቢ ሂደት መነጠል የማይቻል ሲሆን ፣ በሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ምድረበዳነት ይህን ሂደት አስቀርቶ ለዓመታት ቢቆይም ፣ በተሰሩ የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ገዳሙ በእጽዋት እንዲሸፈን ከማድረጉም ባሻገር የአካባቢ የአየር ንብረት ጥበቃ ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ማለት ይቻላል።
ወደ ገዳሙ የሚያደርስ 8 (ስምንት) ኪሜ ደረጃ አንድ የጠጠር መንገድ ተሰርቶ ለአካባቢው ማህበረሰብ ጭምር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ለእናቶች መነኮሳይት ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ደረጃውን የጠበቀ ሻወር እና መጸዳጃ ቤት ተገንብቶ እናቶች እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የሲሚንቶ ማቡኪያ ማሽን፣የብረታ ብረትና የእንጨት መስሪያ ማሽን ፣ ዊንች ማሽን ፣ ኮንክሪት ቫይብሬተር፣ኮምፓክተር እንዲሁም ዘመናዊ የብሎኬት ማምረቻ ማሽን ግዥ ተፈጽሞ የፕሮጀክቱን ግንባታ ሙሉ ለሙሉ በራስ አቅም እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከመንግሥት ተቋማት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን በማድረግ የገዳሙ ህጋዊ ይዞታውን የመከለል፣የማስፋፋት እና ህጋዊ የማድረግ ሥራ ተከናውኗል።
ለአብነት ት/ቤት ፣ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት|ቤት ፣ ከፍተኛ ደረጃ ክሊኒክ እና ሌሎች አስፈላጊ የልማት ስራዎች የሚሰሩበት ህንጻ ግንባታ የሚገነባበት 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ካሬ ሜትር ቦታ በሀሙሲት ከተማ ላይ እንዲሁም 717 (ሰባት መቶ አስራ ሰባት) ካሬ ሜትር ለገበያ ማዕከል ግንባታ የሚውል ቦታ ከመንግስት በሊዝ ግዥ ተከናውኗል፡፡
ገዳሙን ከማስተዋወቅ እና ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ የሚገኙ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሚመለከታቸው የወረዳ ቤተ ክህነት፣ የሃገረ ስብከት እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት አመራሮች ፣መምህራነ ወንጌል እና ዘማሪዎች ቦታው ድረስ ተገኝተው ገዳሙ ያለበትን ሁኔታ እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እንዲመለከቱ ተደርጓል።
የቅዱስ ሚካኤልን በረከቱን ፣ ምልጃውን ፣ ተዓምሩን የሚገልጽ እና ገዳሙንም ለማስተዋወቅ በዘማሪ ዲያቆን አቤል መክበብ "ማር ሚካኤል" የተሰኘ ዝማሬ ተሰርቶ እና ቀረጻው በገዳሙ ላይ ተከናውኖ በማኅቶት ቲዩብ አማካኝነት ለህዝብ እንዲደርስ ተደርጓል፤ አሁንም በእይታ ላይ ይገኛል።
ከገዳሙ ወደ ጸበል ቦታ እና ከጸበልተኞች ማደሪያ ወደ ጸበል ቦታ የሚወስደው አስቸጋሪ የተራራ መንገድ የነበረ ሲሆን፣ተራራው እየተቆረጠ የአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት ፤ 260 ሜትር የሚሆን መንገድ ስራው ተጠናቆ ለአቅመ ደካሞች እና በህመም ላይ ሆነው ፈውስን ለሚጠብቁ ጭምር ለእንቅስቃሴ ምቹ ሆኖ እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
የአባቶች እና የሊቃውንት በዓት የግንባታ ሥራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
ለአባቶች መነኮሳት ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ደረጃውን የጠበቀ ሻወር እና መጸዳጃ ቤት ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
የአባቶች ቤተ እግዚአብሔር ግንባታ ሥራ ተጠናቆ አስፈላጊው ቁሳቁስ ተሟቶለት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
መነኮሳቱ ጉባኤዎችን፣ውይይቶችን ለማድረግ፣መንፈሳዊ ትምህርትን ለመስጠት የሚገለገሉበት ደረጃውን የጠበቀ የመሰብሰቢያ አዳራሽም ግንባታው ተጠናቆ እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
ዓይነ ስውራን እና የማየት እክል ያለባቸው ምዕመናን መጽሐፍ ቅዱስ፣ የጸሎት መጻሕፍት እና ሌሎች መንፈሳዊ መጻሕፍትን በራሳቸው እንዲያነቡ፣በአምልኮ ሕይወት በእኩልነት እንዲሳተፉ እና ሁሉም ምዕመናን የመንፈሳዊ ትምህርት ተደራሽነት እንዲያገኙ ለማስቻል የብሬል መጽሐፍ ቅዱስ ፣ውዳሴ ማርያም እና መዝሙረ ዳዊት ግዢ ተፈጽሟል፡፡
ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በሚኒሊየም አዳራሽ ተጋባዥ እንግዶች እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ገዳሙን ለማስተዋወቅ እንዲሁም ያለበትን ደረጃ ለማሳየት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ግንዛቤ ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡
“መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት፤ ተስፋን ሳንቆርጥ በጊዜው እናጭዳለንና፤ እንዲል (ገላትያ 6፥9) ።” ጅምራቸው መልካም፣ግንባታቸውም በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ የሚገኙ ስራዎችም ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ሰዓት “ገዳማዊ ልማት ለቤተክርስቲያን ትሩፋት” በሚል ንቅናቄ እየተሠሩ ካሉ ሥራዎች መካከል፡-
በገዳሙ ውስጥ የሚገኘው እና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የሚፈጸምበት በቅዱስ ሚካኤል ስም የተሰየመው ህንጻ ቤተ ክርስቲያን “ቤተ መቅደስ” ፣ እጅግ ጠባብ እና ከጥቂት ጊዜያት በኃላ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት መሆኑ ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት፣የጥንታዊውን የቤተ ክርስቲያን ቅርጽ ባልተወ መልኩ ፣ወደ ፊት የመነኮሳት እና ምዕመናን ቁጥር እንደሚጨምር በማሰብ ካለበት ስፋት በመጨመር እና ፣ መሰረታዊ የግንባታ ንድፍ በማውጣት፣ የሰርቬ ስራ በማከናወን ግንባታው ተጀምሮ የግንባታ ስራው ከ25 በመቶ በላይ ተከናውኗል፡፡
የግብጽ ቤተ ክርስቲያን በሁለት ታሪካዊ ክሥተቶች ተፈትና በነበረችበት ወቅት፣ ዳግም ሕዳሴዋን ያስገኙላት ሦስት ዐበይት ጉዳዮች ነበሩ። እነርሱም፦ የሥነ መለኮት ኮሌጅ መከፈት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴ እና የበጎ አድራጊ ምዕመናን መገኘት ናቸው።
ከዚህ የለውጥ ፋና ጀርባ የነበረውም ሊቀ ዲያቆናት ማር ሀቢብ ጊዮርጊስ ፣ ለትምህርት ሥርዓት ትኩረት በመስጠቱ ዛሬ ያሉ ግብጻውያን ከሀገራቸው አልፈው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ፣ ቤተ ክርስቲያንን በማስፋፋት ፣ የተማረ እና ለቤተ ክርስቲያን ፍቅር የጸናበት ትውልድ በማፍራት ጠንካራ ሥርዓትን መዘርጋት ችለዋል።
ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም መንፈሳዊ አገልጋዮችን ለማፍራት እና የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲሁም የዕውቀት ማዕከል ለመሆን፣ ከመንግሥት ግዥ በፈጸምነው የሊዝ መሬት ላይ G+3 የአብነት ትምህርት ቤት ስራን እያከናወነ ሲሆን የግንባታ ስራውንም ከ70 በመቶ በላይ ማሳካት ተችሏል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ያጋጠሟትን ችግሮች ያለፈችው በዓለማዊውም በመንፈሳዊውም ዕውቀት በበቁ ልጆቿ ነውና፣ በሁለት እንደተሳለ ሰይፍ ፍጹም በተሰማሩበት ሁሉ ስኬትን የሚጎናጸፉ አገልጋዮችን ለማፍራት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል የአስኳላ ትምህርት ቤት እየተሰራ ሲሆን ግንባታው የፊኒሽንግ ስራ ላይ የደረሰ እና ለትምህርት ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በማሟላት ላይ ይገኛል፡፡እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ካሪኩለም ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል
የጸበልተኞች እና የሱባኤ ማረፊያ ቤት ግንባታ ለማከናወን አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
የውሃ እና የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ፤ ማለትም የከርሰ ምድር ውሃ የማውጣት እና 8 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የመብራት ዝርጋታ ስራ የሚከናወን ይሆናል፡፡
ከፍተኛ ደረጃ ክሊኒክ፣የንጽህና መጠበቂያ ውጤቶች ማምረቻ መጋዘን፣የምግብ ማቀነባበሪያ እየተሰሩ ካሉ እና በቀጣይ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል ናቸው፡፡
በገዳሙ የተከናወነው የልማት ስራ አበረታች የሚባል ቢሆንም በተሻለ ፍጥነት ሥራዎች እንዳይከናወኑ ያደረጉ ተግዳሮቶችም ማጋጠማቸው አልቀረም። ከነዚሀም መካከል ፦
በግንባታ ዕቃዎች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚስተዋል እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ።
በገበያ ላይ የእቃዎች አቅርቦት እጥረት።
ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ዛሬም ድረስ የራሳቸውን አሉታዊ ተጽዕኖ መፍጠራቸው።
የነዳጅ እና የትራንስፖርት ዋጋ በእጅጉ መጨመር።
በሶሻል ሚዲያ በተለይም ቲክቶክ ላይ ትክክለኛ ያልሆኑ፣ተጨባጭ ማስረጃ ሳይያዝ፣ የገዳሙ አባቶችንም ሆነ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ያሉ የሚመለከታቸውን አካላት ምንም አይነት መረጃ ሳይጠይቁ ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን ማሰራጨት ዛሬም እያጋጠመ ያለ ችግር ነው፡፡
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱት በገዳሙ ላይ ሊሰሩ የታስቡ ፕሮጀክቶች በሁለት ዓመት ሰርተን የምናጠናቅቅ ሲሆን በገዳሙ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ከፍፃሜ አድርሶ ገዳማውያኑም ካሉባቸው ተደራራቢ ችግሮች እራሳቸውን እንዲችሉ እና ከልመና እንዲወጡ ለማድረግ በቀጣይ ለሚስሩት የልማት ሥራዎች ማከናወኛ 210,000,000 ብር (ሁለት መቶ አስር ሚሊዮን ብር) የሚያስፈልግ ሲሆን ይህን የማሰባሰብ ሥራም የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተፈፃሚ እስኪሆኑ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
“እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ ፥ በጽድቄም ቀኝ እጅ እደግፍሃለሁ፤ (ኢሳይያስ 41:10)።” እንዲል ቃሉ፤ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች ሁሉ በሃያሉ በልዑል እግዚአብሄር ቸርነት ፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት እየታለፉ ገዳማዊያኑን ካለባቸው የዓለም ፈተና ለመታደግ አሁንም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ድንቅ ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞንም “ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሄር ያበድራል ፣ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል” ይላል፡፡ ቅዱሳን አባቶች ጀምረው ሳይፈጽሙት የተውት ስራ የለምና እኛም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት እና የቃል ኪዳን ልጆች በዚህ በእኛ ዘመን ፣ ለዓለሙ ሰላም፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ድኅነት ዘወትር የሚማጸኑት እነዚህ ገዳማዊያን፣ያሉባቸው ችግሮች ተፈተውላቸው፣ ዓለሙን ትተው የሄዱበትን የምንኩስና ህይወት ፈጣሪን መማጸን ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ፣ ሁሉም ምዕመን ባለው ጸጋ በዕውቀቱ፣ በጉልበቱ እና በገንዘቡ ድጋፍ እንዲያደርግ በልዑል እግዚአብሄር ስም ጥሪ እናቀርባለን።
የገዳማውያኑ ጸሎት እና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሰኔ ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል፣ አዲስ አበባ

ብጹዕ አባታችን አቡነ መቃሪዮስ ፣ የካናዳ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል

ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማግኘቱን አስታወቀ
#ethiopia |የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የገጠመውን መጠለያ የማጣት ችግር ለመቅረፍና ራሱን ለማስቻል በጀመረው የልማት ፕሮጀክት
ገዳሙ በሁለት ዓመት ከስድስት ወራት ጌዜ ውስጥ ባከናወናቸው የገቢ ማሰባሰብ ሥራዎች ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ማግኘት መቻሉን ገልጿል።
በመግለጫው ላይ የካናዳ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ መርቆሪዮስ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትና ጥሪ የተደረገላቸው የሚዲያ ተቋማት ተገኝተዋል።
የገዳሙ አስተዳደር እንዳመለከተው በተለያዩ የቴሌቪዥን ዶክመንተሪዎችና በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት በተደረገው ሰፊ የገቢ ማሰባሰብ ጥረት 52 ሚሊዮን 640 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቡን ገልጸዋል።
እንዲሁም 11 ሚሊዮን 320 ሺህ ብር የሚገመት የዓይነት (የቁሳቁስ) ድጋፍ መሰብሰቡ ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ የተገኘው ድጋፍ የልማት ፕሮጀክቱን የመጀመሪያና ሁለተኛ ምዕራፎች ከ65 በመቶ በላይ ለማሳካት ያስቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የእናቶች በዓት (የመኖሪያ ክፍል) እና የእንግዳ ማረፊያ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ እናቶች አገልግሎት ማግኘት መጀመራቸው ተጠቅሷል።
ከ160 በላይ ገዳማውያን የሚገኙበት ይህ አንድነት ገዳም ከተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ችግሮች ጋር ተያይዞ ገዳማውያኑ ከብርድና ከዝናብ የሚከላከል መጠለያ አጥተው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኙ እንደነበር በመግለጫው ላይ ተስቷል።
ይህንን የህልውና ፈተና በዘላቂነት ለመቅረፍ የተቀረጸው ይህ ፕሮጀክት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ዕውቅና በሐገረ ስብከቱ ፈቃድ እንዲሁም በሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ ክትትልና ቡራኬ ከወረዳ ቤተ-ክህነት ጀምሮ በቅንጅት እየተመራ ይገኛል ተብሏል።
የገዳሙ አስተዳደር "ጾም የነፍስ ምግብ ነው ለፈተናም መቋቋሚያ ጥንካሬን ይሰጣል" የሚለውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ኃይለ ቃል በመጥቀስ በአሁኑ ወቅት ምዕመናን የሚገኙበት የሐዋርያት ጾም (የሰኔ ጾም) የበረከት ወቅት በመሆኑ ድጋፋቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የተጀመረው የልማት ሥራ ሙሉ በሙሉ ፍጻሜ እንዲያገኝ ሕዝበ ክርስቲያኑ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ሙትአንሳማርቅዱስሚካኤልአንድነትገዳም

ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ለጀመረው የልማት ፕሮጀክት ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማግኘቱን አስታወቀ!
#fastmereja I የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የገጠመውን መጠለያ የማጣት ችግር ለመቅረፍና ራሱን ለማስቻል በጀመረው የልማት ፕሮጀክት ገዳሙ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከስድስት ወራት ውስጥ ባከናወናቸው የገቢ ማሰባሰብ ሥራዎች፣ ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ማግኘት መቻሉን በዛሬዉ እለት የአስተዳደሩ ተወካዮች ገልጸዋል።
በመግለጫው ላይ የካናዳ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ መርቆሪዮስ፣ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትና ጥሪ የተደረገላቸው የሚዲያ ተቋማት ተገኝተዋል።
የገዳሙ አስተዳደር እንዳመለከተው፣ በተለያዩ የቴሌቪዥን ዶክመንተሪዎችና በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት በተደረገው ሰፊ የገቢ ማሰባሰብ ጥረት፦52 ሚሊዮን 640 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ፣11 ሚሊዮን 320 ሺህ ብር የሚገመት የዓይነት (የቁሳቁስ) ድጋፍ መሰብሰቡ ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ የተገኘው ድጋፍ የልማት ፕሮጀክቱን የመጀመሪያና ሁለተኛ ምዕራፎች ከ65 በመቶ በላይ ለማሳካት ያስቻለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የእናቶች በዓት (የመኖሪያ ክፍል) እና የእንግዳ ማረፊያ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ እናቶች አገልግሎት ማግኘት መጀመራቸው ተጠቅሷል።
ከ160 በላይ ገዳማውያን የሚገኙበት ይህ አንድነት ገዳም፣ ከተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ችግሮች ጋር ተያይዞ ገዳማውያኑ ከብርድና ከዝናብ የሚከላከል መጠለያ አጥተው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኙ እንደነበር በመግለጫው ላይ ተስቷል።
ይህንን የህልውና ፈተና በዘላቂነት ለመቅረፍ የተቀረጸው ይህ ፕሮጀክት፤ በጠቅላይ ቤተ-ክህነት ዕውቅና፣ በሐገረ ስብከቱ ፈቃድ እንዲሁም በሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ ክትትልና ቡራኬ ከወረዳ ቤተ-ክህነት ጀምሮ በቅንጅት እየተመራ ይገኛል።
የገዳሙ አስተዳደር "ጾም የነፍስ ምግብ ነው፤ ለፈተናም መቋቋሚያ ጥንካሬን ይሰጣል" የሚለውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ኃይለ ቃል በመጥቀስ፣ በአሁኑ ወቅት ምዕመናን የሚገኙበት የሐዋርያት ጾም (የሰኔ ጾም) የበረከት ወቅት በመሆኑ፣ የተጀመረው የልማት ሥራ ሙሉ በሙሉ ፍጻሜ እንዲያገኝ ሕዝበ ክርስቲያኑ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

Sponsored by
Surafel
3 months ago
ሚያዝያ 24/25 በድምቀት ይመረቃል
ማረፊያና ማለፊያው ደብር
በጉራጌ ምድር ጠርዙን ይዞ የቆመው የምሁር ኢየሱስ ገዳም፣ ከምድራዊው ዓለም ይልቅ ወደ ሰማያዊው መንግሥት የቀረበ ይመስላል።
ወደ ቅጽረ ግቢው ሲዘልቁ ነፍስን የሚያረሰርሱ፣ ሥጋን የሚያሳርፉ ድንቅ ትዕይንቶች በፊቱ ይዘረጋሉ።
ጥንታውያንና ግርማ ሞገስ የተላበሱት የገዳሙ ዛፎች፣ እንደ ዘበኛ ቆመው ጥላን ይግታሉ። ነፋሱ በቅጠሎቻቸው መካከል ሲያልፍ የሚፈጥረው "ሹክሹክታ" ለፀሎት የሚጋብዝ ረቂቅ ድምፅ አለው።
በቅርንጫፎቹ ላይ የሚረግጡት አእዋፍ፣ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡ ይመስል በልዩ ዜማቸው የገዳሙን ሰላም ያደምቁታል። ዝማሬያቸው ከገዳሙ መንፈሳዊነት ጋር ተዋህዶ የነፍስ ምግብ ይሆናል።
የገዳሙ አቀማመጥና የሕንፃው ጥበብ የአባቶቻችንን የታሪክ አሻራ በጉልህ ያሳያል። ከሩቅ ሲታይ የማማው ግርማ፣ በውስጥ ሲታይ ደግሞ የቅድስናው ድባብ የሰው ልጅን ልብ በአድናቆት ይሞላል።
በዚያ የተቀደሰ ስፍራ የካህናቱ ዝማሬ ሲሰማ፣ ምድራዊው ድምፅ ጠፍቶ ሰማያዊ ዜማ የተጀመረ ይመስላል። በጥበብና በትሕትና የተሞላው አስተምሯቸው ደግሞ የጠፋውን የሚመልስ፣ የደከመውን የሚያጸና የመንፈስ ብርሃን ነው።
ምሁር ኢየሱስ ገዳም ተፈጥሮ ከፈጣሪዋ ጋር የተገናኘችበት፣ ሰው ከራሱ ጋር የታረቀበት፣ በቅድስናና በውበት የተከበበ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የከበረ ዕንቁ ነው።
ለዚህ ምረቃ በዓል መብቃት እንደ ፀሃይ ብርሃን ነው። አንድም ጠዋት ሁለትም ቀትር ሆኖ ፍንትው ብሎ መታየት።
ምንጭ 👉እንዳልካቸው ደሳለኝ
ያለን ቦታ ጥቂት ነው ፈጥነው ይመዝገቡ
አዘጋጅ ምሁር ኢየሱስ ገዳም
ቅዱስ ዳዊት የበገና ቤተሰብ ጋር ይጓዙ
0911358560/0911083713
0921327074 /0913383033

4 months ago
#ዲያብሎስን_ቤት_አሳጣው
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
#ዲያብሎስን_ቤት_አሳጣው
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ።
አዲሱን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ገበያ ላይ መዋል ምክንያት በማድረግ እነሆ ከመጽሐፉ ጀርባ ለቅምሻ ጋብዘናል።
#ዲያብሎስን_ቤት_አሳጣው
ዲያብሎስ በወንድማችን፣ በጓደኛችን፣ በሚስታችን ወይም በጣም በምንቀርበው ሰው ውስጥ አድሮ ተገቢ ያልሆነ ምክር ቢሰጠን፣ ምክሩን አንቀበል። ይልቁንም ያ ገዳይ ምክር የመጣው ከጠላት እንደሆነ አውቀን ከሰሚው እንራቅ። ዛሬም ቢሆን ሰይጣን የርኅራኄ ጭንብል ለብሶ፣ ወዳጅ መስሎ፣ ከመርዝ የከፋ ጥፋትን በሰዎች ውስጥ ያሰርጋል።
☦️☦️☦️
አንተ የንጉሥ ልጅ ብትሆንና በአባትህ ማዕድ የመቀመጥ ክብር ቢኖርህ፣ ያን ትተህ በወህኒ ቤት ካሉ እስረኞችና ከተፈረደባቸው ሰዎች ጋር በማዕዳቸው ለመካፈል ብትመርጥ፣ አባትህ ይህን ይፈቅድልሃልን? ይልቁንም በታላቅ ኃይል ከዚያ ያስወጣሃል እንጂ። ይህን የሚያደርገው ማዕዱ ስለሚጎዳህ ሳይሆን፣ ያንተን ክብርና የንጉሡን ማዕድ ስለሚያቃልል ነው።
☦️☦️☦️
በዓለም ምን ትሠራለህ? በተሰበረ ማሰሮ ውስጥ ውኃ ለማከማቸት ነውን? አሁን ላለችው ሕይወት በብላሽ ለመድከም ነውን? መቃጠሉ የማይቀርን ድር ለምን ታዳውራለህ? ለምንስ በምድረ በዳ ነፋሳትን ትከተላለህ? ለምንስ በሸለቆ ውስጥ ዓይንህን ጨፍነህ ትቅበዘበዛለህ? እያንዳንዱ ጥበብ ነገር አይደለምን? ይህ ለሁላችንም ግልጽ ነው። እንግዲህ አንተም በሕይወትህ ውስጥ ለምትሠራው ሥራ ዓላማ አሳየኝ። በእውነት አንዳች የለህም።
☦️☦️☦️
ሌቦች ጭቃ፣ ገለባ ወይም እንጨት ባለበት ቤት አይሰርቁም። ይልቁንም ወርቅና ብር ወዳለበት ቤት ዓይናቸውን ይጥላሉ። ሰይጣንም ልክ እንደዚሁ ነው፤ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ለመንፈሳዊ ነገር ቦታ በሚሰጡ ሰዎች ላይ ነው። በጎነት ባለበት ቦታ ወጥመድ ይበዛል፤ ምጽዋትና ዕርዳታ ባለበትም ምቀኝነት አይጠፋም። ነገር ግን ይሄንን ሁሉ የጠላት ተንኮል የምናሸንፍበት አንድ ትልቅ መሣሪያ አለን፤ ይሄ ድንቅ መሳሪያ ምን ይሆን?
#ዲያብሎስን_ቤት_አሳጣው መጽሐፍ መጽሐፍ በገበያ ላይ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ።
ሌሎች #የቅዱስ_ዮሐንስ እና #የአቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ አዳዲስ መንፈሳዊ መጽሐፍት በገበያ ላይ
👇🎀👇
👉#መንፈሳዊ_ተጋድሎ መጽሐፍ
👉#ለነፍስ_የሚበጅ_መንገድ መጽሐፍ
👉#የነፍስን_ነገር_ማሰብ መጽሐፍ
👉#ለደከመች_ነፍስ_መመሪያ መጽሐፍ
👉#መንፈሳዊ_ሰው_መሆን መጽሐፍ
👉#ኦርቶዶክሳዊ_ሕይወትን_መኖር መጽሐፍ
👉#ጠይቁ_ይመለስላችኋል መጽሐፍ
👉 #ሰይጣንን_አስርቡት መጽሐፍ
👉 #ሕይወት_እና_ክርስትና መጽሐፍ
👉 #የጽድቅ_መንገድ መጽሐፍ
👉 #የነፍስ_ምግብ መጽሐፍ
👉 #ለነፍስህ_ቤት_ስራላት መጽሐፍ
👉 #እስከማዕዜኑ መጽሐፍ
👉 #ትምህርተ_ሺኖዳ መጽሐፍ
👉 #አቡነሺኖዳ_መልስ_አላቸው መጽሐፍ
👉 #ኦርቶጵያ መጽሐፍ
👉#የተሰቀለው_ንጉሥ መጽሐፍ
👉#the_crucifixion_of_the_king_of_glory (በእንግሊዝኛ)
ሁሉም መጽሐፍት በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ።
📕📕📕
ፌስቡክ ገጽ
👉 https://web.facebook.com/p...
ቲክቶክ-
👉https://www.tiktok.com/@ha...

#ያበቃልህ_ሲመስልህ_እነዚህን_5ቱን_አስብ፦
1. አብርሃም የመቶ ዓመት ሽማግሌ ነበር
👉ግን የብዙ ሕዝብ አባት ሆነ።
2. ሳራ ማሕፀኗ ደርቆ ነበር
👉 ግን በስተርጅናዋ ይስሐቅን ወለደች
3. አላዛር ሞቶ አራት ቀን ሆኖት ነበር
👉 ግን በመቃብር ውስጥ ሕይወት አገኘ
4. ሐና ለብዙ ዓመታት መካን ነበረች
👉ግን ታላቁን ነቢይ ሳሙኤልን አቀፈች
5. ያ መጻጉዕ ለ38 ዓመታት በአልጋ ላይ ነበር
👉 ግን በቃሉ ተፈውሶ ተነሳ።
የአንተ "ዘግይቷል" የእግዚአብሔር "ትክክለኛው ሰዓት" ነው።
#መንፈሳዊ_ተጋድሎ መጽሐፍ
እና #ለነፍስ_የሚበጅ_መንገድ መጽሐፍ
ሁለት አዳዲስ የአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ መጽሐፍት በገበያ ላይ
የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ፣ የቅዱስ ዮሐንስ አዲስ ምርጥ ምርጥ መንፈሳዊ መጽሐፍት በገበያ ላይ
👇🎀👇
👉#በቤት_ውስጥ_ያለች_ቤተክርስቲያን
👉#ኃጢአትን_ማሸነፍ
👉#ለደከመች_ነፍስ_መመሪያ
👉#መንፈሳዊ_ሰው_መሆን
👉#ኦርቶዶክሳዊ_ሕይወትን_መኖር
👉#ጠይቁ_ይመለስላችኋል
👉 #ሰይጣንን_አስርቡት
👉 #ሕይወት_እና_ክርስትና
👉 #የጽድቅ_መንገድ
👉 #የነፍስ_ምግብ
👉 #ለነፍስህ_ቤት_ስራላት
👉 #እስከማዕዜኑ
👉 #ትምህርተ_ሺኖዳ
👉 #አቡነሺኖዳ_መልስ_አላቸው
👉 #ኦርቶጵያ
👉#የተሰቀለው_ንጉሥ

#ሰይጣን_እንዳይገዛህ_ራስህን_ግዛ_5_ዘዴዎች፦
1. ርሐብን ናቀው
ስጋህ ሲራብ መንፈስህ ይበረታል፤ ጾም የነፍስ ጅራፍ ነው።
2. ዝምታን ጌጥ አድርገው
በወሬ ብዛት ጸጋህ ይፈሳል፤ ከንፈርህን ለጉመህ ልብህን ክፈት።
3. ምቾትን አትላመድ
ተድላና ቅንጦት ለነፍስ እንቅልፍ ናቸው፤ ራስህን አስጨንቀው።
4. በትዕግስት እረፍ
መከራ ሲመጣ አትማረር፤ ፈጣሪ አልማዝ እያደረገህ ነው።
5. እንደ ወታደር ሁን
መንፈሳዊ ጉዞ ዘና ማለት የለውም፤ ዘወትር በንቃት ጠብቅ።

#የሥጋህን_ብቻ_ሳይሆን_የነፍስህንም_ነገር_አስብ !!!
#የነፍስን_ነገር_ማሰብ መጽሐፍ #ለነፍስ_የሚበጅ_መንገድ መጽሐፍ #መንፈሳዊ_ተጋድሎ መጽሐፍ
የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ሶስት አዳዲስ መጽሐፍት በገበያ ላይ
#የነፍስን_ነገር_ማሰብ መጽሐፍ
ለሥጋችን ጤንነትና ደህንነት እጅግ ጥንቁቆች ነን። "ይህ ምግብ ያጠነክረኛል፣ ያኛው በሽታ ይከላከልልኛል" እያልን እንመርጣለን። ለምንለብሰው ልብስና ለምንጫማው ጫማ ጥራት የምንጨነቀው፣ ከውጫዊ ጉዳት እንዲጠብቀን ነው። ለጊዜያዊው ሥጋችን እንዲህ ከተጨነቅን፣ በየዕለቱ ከባድ ፈተና ለሚገጥማት ዘላለማዊ ነፍሳችን ምን ያህል አብልጠን መጠንቀቅ ይኖርብን ይሆን?
#ለነፍስ_የሚበጅ_መንገድ መጽሐፍ
በዚህች ዓለም የሕይወት ጉዞ ላይ ብዙ መንገዶች ከፊታችን ተዘርግተዋል። አንዳንዱ ለዐይን የሚያምር ግን ወደ ጥፋት የሚወስድ ነው፤ ሌላው ደግሞ ጠባብና አስቸጋሪ ቢመስልም ወደ ሕይወት የሚያደርስ ነው። ታዲያ በዚህ የመንገድ መጥፋት ዘመን፣ ለዘላለማዊት ነፍሳችን በእርግጥ የሚበጀው የትኛው ነው?
#መንፈሳዊ_ተጋድሎ መጽሐፍ
የሰው ልጅ አእምሮ የእግዚአብሔር ጥበብ ማደሪያ፣ እጹብና ድንቅ የሆነ ስጦታ ነው። በየዕለቱ በአእምሯችን ጓዳ ውስጥ የሚመላለሱት እልፍ አዕላፍ ሀሳቦች የዚህን ተፈጥሮ ልዕልና ይመሰክራሉ። ነገር ግን፣ በዚህ ግራ በተጋባ የቴክኖሎጂ ዘመን፣ ወደ አእምሯችን የሚጎርፉት አብዛኛዎቹ ሀሳቦች እንደ መርዝ የሚናደፉና ነፍስን የሚያቆስሉ ሆነዋል።
ከሕጻናት እስከ አረጋውያን ድረስ፣ በስልክና በኮምፒውተር መስኮት በኩል የሚረጨው የዓለም መንፈስ ግን ፊቱን ቀይሮና ተሽሞንሙኖ ይቀርብላቸዋል።
እነዚህ የጠላት ጦሮች፦
👉ዘመናዊነት እና ሥልጣኔ፣
👉አራዳነት እና ምሁራዊነት፣
👉 ጠያቂነት እና ዓለም አቀፋዊነት...
የሚሉ "የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች" ናቸው። ውጫቸው ሲታይ ያማረ፣ ውስጣቸው ግን መንፈሳዊ ማንነትን የሚቦርብር ነው።
ታዲያ በፈተና ማዕበል የሚናወጠው ክርስቲያን፣ ይህንን የመንፈስ ውጊያ እንዴት ድል ይነሳል? እንዴትስ ነው መርዙን ከማር ለይቶ የሚጥለው?
ሶስቱም የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ አዳዲስ መጽሐፍት በገበያ ላይ ውለዋል።

5 months ago
የደም ትስስርና የነፍስ ጩኸት፡ ከዐድዋ ተራሮች እስከ ጋርቬይ
ዐድዋ አንድ ሺ ጊዜ ቢነገር አንድ ሺ መልዕክት ያለው ድል ነው።ዓለም በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ለጥቁር ሕዝቦች አስከፊ ነበረች። አፍሪካ በበርሊን የካርታ ጠረጴዛ ላይ እንደ ታረደ በሬ በቅርጫ ተከፋፍላ፣ ልጆቿ በገዛ ምድራቸው ባዕድ ሆነው ነበር።
በባሕር ማዶ፣ በአሜሪካና በካሪቢያን ደሴቶች፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቁሮች ከማንነታቸው ተላቀው፣ ስማቸው ተፍቆ፣ እንደ ቁስ ተቆጥረው በነጮች እርሻ ውስጥ በባርነት አለንጋ ይገረፉ ነበር። ጥቁር መሆን የውርደት፣ የዝቅተኝነትና የሽንፈት ምልክት ተደርጎ የታተመበት ያ ዘመን፣ ለብዙዎች ተስፋ የሞተበት ድቅድቅ ጨለማ ነበር።
ነገር ግን፣ በዚህ ሁሉ ስቃይና እንባ መካከል፣ ከአፍሪካ ቀንድ አንዲት ብርሃን ብልጭ አለች። ያቺ ብርሃን ከኢትዮጵያ ምድር የተገኘች "አድዋ" ትባላለች።
በዛ ዘመን የኢትዮጵያ ተራሮች በጭስና በደም ተሸፍነዋል። ንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ፣ ገበሬውን፣ ቄሱን፣ ሸማኔውንና አርሶ አደሩን አስተባብረው ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀውን የጣሊያን ጦር ፊት ለፊት ተጋጠሙት። ያ ዛረም ድረስ ምናከብረው የድል ቀን ለነጭ ገዢዎች የውርደት፣ ለጥቁር ሕዝቦች ግን የትንሳኤ ቀን ነበር።
ድሉ ሲበሰር "ጥቁር ሰው ነጭን ማሸነፍ ይችላል!" የሚለው ዜና በባርነት ቀንበር ስር ላሉት ወንድሞቻችን የነፃነት ወንጌል ሆነ። ይህ ዜና ጃማይካ ደሴት ላይ ወደሚገኘውና ገና በልጅነቱ የዘሩን መገፋት እያየ ወደሚያለቅሰው ወጣቱ ማርከስ ጋርቬይ ደረሰ።
ማርከስ ጋርቬይ በጃማይካ ሲያድግ፣ በዙሪያው የሚያየው ድህነትን፣ ንቀትንና የጥቁርነትን ስብራት ነበር። ነገር ግን ስለ አድዋ ሲሰማ፣ በውስጡ አንድ ታላቅ እሳት ነደደ። ጋርቬይ ኢትዮጵያን በአካል አይቷት አያውቅም፤ ነገር ግን በልቡ ውስጥ ኢትዮጵያ "የእናት ምድር" ምልክት፣ የክብር ተራራ፣ የነፃነት መቅደስ ሆና ተቀረጸች።
ጋርቬይ "Universal Negro Improvement Association" (UNIA) የተባለውን ማኅበር ሲመሠርት፣ በቢሊዮን ለሚቆጠሩ ጥቁር ሕዝቦች የነገራቸው አንድ ትልቅ እውነት ነበር፦ "እናንተ አገር የሌላችሁ ተቅበዝባዦች አይደላችሁም፤ እናንተ አድዋ ላይ ታሪክ የሠሩ የጀግኖች ወንድሞች ናችሁ!" እያለ ይጮኽ ነበር። ጋርቬይ ለጥቁር ሕዝቦች የሰጠው ሰንደቅ ዓላማ መነሻው የአድዋው የኢትዮጵያ ባንዲራ ነበር። ቀዩ—ስለ ነፃነት የፈሰሰውን ደም፣ ጥቁሩ—የሕዝቡን ክብር፣ አረንጓዴው ደግሞ የአፍሪካን ተስፋ ይወክሉ ነበር።
የጋርቬይ ሕይወት በመከራ የተሞላ ነበር። በዘረኞች እየታደነ፣ በገዛ ወንድሞቹ እየተከዳ፣ በእስር ቤት እየማቀቀ እንኳን፣ ከአንደበቱ የማይጠፋው ቃል "ኢትዮጵያ" የሚል ነበር። ጋርቬይ በሃርለም ጎዳናዎች ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቁሮችን ሰብስቦ ሲያሰልፍ "ወደ አፍሪካ ተመልከቱ" እያለ ሲቀሰቅስ፣ በዓይነ ሕሊናው የሚታየው የምኒልክ ጎራዴና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ነበር።
ጋርቬይ እንዲህ ይል ነበር፦ "እግዚአብሔር ሆይ! ጥቁር ሕዝቦች በራሳቸው መርከብ ወደ እናት ምድራቸው ተመልሰው፣ እንደ አድዋ ጀግኖች በነፃነት የሚኖሩበትን ቀን አሳየኝ!" እርሱ ለዚህ ራዕይ ሲል ክብሩን፣ ገንዘቡንና ጤናውን መሥዋዕት አደረገ።
በወቅቱ የነበሩት ኃያላን መንግሥታት "ይህ ሰው ጥቁሮችን እያነቃ ነው" ብለው ፈሩት። በሐሰት ወንጀል ከሰሱት፣ አሰሩት፣ መጨረሻም ከአሜሪካ አባረሩት።
በ1930 ዓ.ም ንጉሥ ተፈሪ መኮንን "ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ" ተብለው ሲነግሡ፣ በካሪቢያን የሚገኙ የጋርቬይ ተከታዮች በደስታ አበዱ ። ጋርቬይ ቀድሞ "ጥቁር ንጉሥ በአፍሪካ ይነግሣል" ብሎ ተንብዮ ስለነበር፣ የንጉሡ መክሊት ለጋርቬይ ተከታዮች መሲሐዊ ትርጉም ነበረው።
ነገር ግን ታሪኩ እዚህ ላይ አሳዛኝ መልክ ይይዛል። በ1935 ዓ.ም ፋሺስት ጣሊያን በአድዋ የተሸነፈችውን ሽንፈት ለመበቀል በድጋሚ ኢትዮጵያን ስትወርር፣ ጋርቬይ በለንደን ስደት ላይ ነበር። ኢትዮጵያ ስትወረርና ንጉሡ ወደ ስደት ሲመጡ፣ ጋርቬይ ልቡ በሐዘን ተሰበረ። "እንዴት አባቶቻችን አድዋ ላይ ያስከበሩትን ክብር እናጣለን?" ብሎ ምርር ብሎ አለቀሰ። በወቅቱ ከንጉሡ ጋር የነበረው መጠነኛ የሐሳብ ልዩነትና የኢትዮጵያ በጣሊያን እጅ መውደቅ፣ ጋርቬይን ለከፍተኛ ሕመም ዳረገው።
ማርከስ ጋርቬይ በ1940 ዓ.ም በለንደን በብቸኝነት ሲያልፍ፣ የመጨረሻ ቃላቱ ስለ ጥቁር ሕዝብ አንድነትና ስለ አፍሪካ ነፃነት ነበሩ። የሚገርመውና ልብን የሚሰብረው፣ ጋርቬይ ሕይወቱን ሙሉ የዘመረላት፣ ስለ ክብሯ የታገለላትና መላ ሕይወቱን የሰጠላትን ኢትዮጵያን አንድም ቀን በአካል ሳይረግጣት መሞቱ ነው።
እርሱ ለጥቁር ሕዝቦች "ሥር" የሰጠ፣ ከአድዋ ተራሮች የተነሳውን የነፃነት እሳት ወደ ዓለም ያሰራጨ ታላቅ ነፍስ ነበር። እርሱ ሲሞት የነበረው ብቸኝነትና ድህነት፣ ለጥቁር ሕዝብ የከፈለው መሥዋዕትነት ትልቅነት ማረጋገጫ ነው።
ዛሬ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባ ላይ ሲቆም፣ አድዋ የፓን አፍሪካኒዝም ማዕከል ስትሆን፣ የማርከስ ጋርቬይ መንፈስ በዚያ ደጃፍ ላይ ቆሞ ይታያል።
ጋርቬይ በአካል ባይመጣም፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጃማይካና የዲያስፖራ ጥቁሮች ዛሬም "ኢትዮጵያ" እያሉ ይዘምራሉ።
አድዋ ላይ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም፣ በካሪቢያንና በአሜሪካ ለነበሩት ባሮች የነፍስ ምግብ ሆኗቸዋል። ጋርቬይ ደግሞ ያንን ደም ወደ ርዕዮተ ዓለም ቀይሮ፣ ጥቁር ሕዝብ በራሱ እንዲተማመን አድርጓል።
አድዋ እና ጋርቬይ የአንድ ታሪክ ሁለት አካላት ናቸው። አድዋ—ሥጋዊና ሞራላዊ ነፃነትን ሲሰጠን፣ ጋርቬይ—መንፈሳዊና አእምሯዊ ነፃነትን ሰጥቶናል። ዛሬም ድረስ በጃማይካ የሚገኙ ራስተፋሪያውያን ወደ ኢትዮጵያ (ሻሸመኔ) ሲመጡ፣ "ወደ አገራችን ተመለስን" የሚሉት ለዚህ ነው።
የአድዋ ድል ባይኖር ጋርቬይ የሚሰብከው ክብር አይኖርም ነበር። ጋርቬይ ባይኖር ደግሞ የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ተራሮች መካከል ብቻ ተቀብሮ በቀረ ነበር።
ዛሬ ላይ ሆነን ስናስበው፣ ጋርቬይ ማለት በአድዋ የተነሳው የነፃነት ብርሃን በዓለም ዙሪያ እንዲበራ ያደረገ ታላቅ የመብራት ማማ ነው።
ይህ ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ የአፍሪካውያንና የጥቁር ሕዝቦች ትስስር በውቅያኖስ የማይገደብ፣ በባርነት የማይበጠስና በጊዜ የማይደበዝዝ የደም ትስስር መሆኑን ነው። ጋርቬይ በለንደን ስደት ላይ ሆኖ የፈሰሰው እንባ፣ ዛሬ በአፍሪካ አንድነት ውስጥ ፍሬ አፍርቷል።
እኛ የአድዋ ልጆች፣ የማርከስ ጋርቬይ ራዕይ አደራዎች ነን። እርሱ ያላያትን ኢትዮጵያ እኛ ይዘናታል፤ እርሱ የናፈቃትን ነፃነት እኛ እየኖርንባት ነው። ይህን ታላቅ ክብር መጠበቅና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የታሪክ ግዴታችን ነው።
ክብር ለአድዋ ጀግኖች! ዝንተዓለም መታሰቢያነት ለአፍሪካ ኩራት ለማርከስ ጋርቬይ!

6 months ago
🕊️✨ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! ✨🕊️
🙏 "ኑ በአንድነት የጥምቀትን በዓል በጋራ እናክብር!" 🙏
⛪ በሼፊልድ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት፤ በዩኬ 🇬🇧 ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በአንድነት የሚያከብሩት ታላቅ የጥምቀት በዓል ሊከናወን ⏳ አንድ ቀን ብቻ ቀረው!
📅 ነገ አርብ ከሰዓት ጀምሮ
👑 ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን
✝️ ጥሪ የተደረገላቸው ካህናት
📚 መምህራን
🎶 ዘማሪያን
👨👩👧👦 እና ምዕመናን
ከየአጥቢያው እና ከየደብሩ በሼፊልድ ይከተማሉ።
🌟 በዚህ ታላቅ በዓል ላይ፦ 🌟
✅ 🎼 ልዩ የሊቃውንት ያሬዳዊ ዝማሬና ወረብ
✅ 📖 የነፍስ ምግብ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል
✅ 🍲🥖 የተትረፈረፈ የምስጋና ማዕድ
⚠️ በዚህ በዓል ላይ መቅረት አይደለም፤ ማርፈድ ያስቆጫል!
⏰ ቀድመው ይገኙ – ለበረከት ይሽቀዳደሙ! 🙌
📍 ቦታ: Magna Science Adventure Centre
🏢 Address: Magna Way, Templeborough, Rotherham S60 1FD
💧✨ እንግዲኛ በደስታ፣ በአንድነት፣ በበረከት እንገናኝ! ✨💧

Comments