በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ብጹዕ አባታችን አቡነ መርቆሪዮስ ፣ የካናዳ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል
መንፈሳዊ ተልዕኮ ተቀብላችሁ ልዑል እግዚአብሔር በሰጣችሁ ጸጋ በተለያየ ስፍራ የምታገለግሉ ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን
ጥሪ የተደረገላችሁ ተጋባዥ እንግዳዎች ፣
የመንግስት እና የግል ሚዲያ ተቋማት ፣
ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለተገኛችሁ በልዑል እግዚአብሔር ስም ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን።
"ጾም የነፍስ ምግብ ነው፤ ለፈተናም መቋቋሚያ ጥንካሬን ይሰጣል።" እንዲል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ።" እኛ ኦርቶዶክሳዊያን የሐዋሪያት ጾም ላይ እንገኛለን፡፡
የሰኔ ጾም (ጾመ ሐዋርያት) ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰባቱ አዋጅ አጽዋማት አንዱ ሲሆን፣ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉና ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው።ይህ ጾም እንደ እምነቱ አስተምህሮ ለሁሉም ክርስቲያን የተሰጠ የበረከት ጾም ነው። ይህን ጾም እንድንካፈል ለፈቀደልን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው፤ለጾሙ ፍችም በሰላም ያድርሰን እያልኩ፣መግለጫው የተዘጋጀው በጽሁፍ ስለሆነ በተዘጋጀበት አግባብ ይቀርባል፡፡
በወልድ ውሉድ ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ ፣ አምላኩን በንጽሐ ነፍስ ፣ በንጽሐ ሥጋ የሚያገለግልበት እና ፣ ከራሱ ከፈጣሪው መድሐኒዓለም ክርስቶስ ዘንድ የተሰጠው የጸጋ አገልግሎት፣ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ የሚያገኙት ፤ መጨከንን ፣ ጥብዓትን ፣ ትሕርምትን እና ትዕግሥትን የሚጠይቅ ሕይወት ፣ የምንኩስና ሕይወት እና ሥርዓት ነው።የምንኩስና ሕይወት እና የገዳማዊ ሥርዓት በቅዱሳን አባቶች አባ እንጦንስ እና አባ መቃርስ የተጀመረ ሲሆን ፣ ሕይወቱም ሥርዓቱም በቀኖና ቤተክርስቲያን የተደነገገ እና የጸደቀ ሕግ ነው።
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ፣ ገዳም የእኔ የግሌ የሚሉት ንብረት የሌለበት፣ ሁሉ በማኅበር በአንድነት በጸሎት በስራ እየተጉ ፍጹም የዓለምን ኃላፊነት ተረድተው ፣ የማታልፍ የእግዚአብሔር መንግስት እንዳለች በመገንዘብ ዘወትር በቀኖና ተወስነው የሚኖሩበት የቅዱሳን መኖሪያና ጸጋ እግዚአብሔር የማይለይበት የዲያቢሎስ ፈተና የሚበዛበት ስፍራ ነው።
ገዳምና ገዳማዊ ሕይወት አስፈላጊ በመሆኑ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርአያ ሆኖን ፣ በገዳመ ቆሮንጦስ ከዲያቢሎስ ይፈተን ዘንድ ተቀመጠ (ማቴ. 4፡ 1-11) ፈታኝ ዲያቢሎስንም ድል አደረገው ፣ ገዳምና ገዳማዊ ሕይወት አስፈላጊ ሆኖ የመሰረተልን አምላካችን አርአያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዛሬም እርሱን በመከተል ገዳማዊ ሕይወት ለትሩፋት መስሪያ ፣ ለንስሃ ሕይወት ማቆያ ፣ ለበረከት ለረድኤት የአምላካችንን አርአያነት ተከትለው አባቶች እናቶች በገዳም ተወስነው ይገኛሉ።
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ “ገዳማዊ ህይወት” ራስን ለእግዚአብሔር በማስገዛት ትህትናን ገንዘብ አድርጎ እያንዳንዷን ሰዓት አንደበትን ፣ ጉልበትን እና ሃሳብን ለእግዚአብሔር በመስጠት የዓለም ዝና ሃብት ንብረት አላፊ የሆነውን ንግሥና ውበትን በመናቅ ቤተሰብ እና ዘመድን ተለይቶ በመውጣት በገዳም ውስጥ በስርዓተ አበው ተወስኖ መስቀሉን ተሸክሞ መኖር መሆኑን ትናገራለች።
ገዳማት የቤተ-ክርስቲያናችን ስውር ጓዳዎችና የሚስጢር መዝገቦች ፣ የመማጸኛ ቅዱስ ስፍራዎች ፣ የቤ-ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎት መሰረት ፣ የተግባራዊ ክርስትና ምሳሌዎች እና የታላላቅ የቤተ-ክርስቲያን ሊቃውንት መፍለቂያዎች ናቸው።
እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት እና ገዳማት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን እየሰጡ ፣ ትውልድንም በክርስቲያናዊ ስነ-ምግባር እያነጹ ይቀጥሉ ዘንድ ገቢ ያስፈልጋቸዋል። ይህንን ገቢያቸውን ከሚያገኙባቸው መንገዶች መካከል በራሳቸው አቅም ገቢ የሚያመነጩ ስራዎችን ማከናወን እንዲሁም ምዕመኑ በሚሰጡት መባ እና አስራት በኩራት ይጠቀሳሉ።
ይሁንና አንዳንዴ ተፈጥሮ ፊቷን ስታዞር እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ሲበረቱ ሰው ሰራሽ ችግሮችም ሲጨመሩ፣ገዳማት የገቢ ምንጫቸውና ህልውናቸው ሙሉ በሙሉ ህዝበ ክርስቲያኑ በሚያደርገው ድጋፍ ላይ የተንጠለጠለ የሚሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል ፤ ከ160 በላይ ገዳማዊያን የሚገኙበት ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የገጠመው ችግርም በዚህ ደረጃ የሚገለጽ ነው።
በዚህ ገዳም የሚገኙ ገዳማውያን ከፀሃይ ፣ ከብርድ ፣ ከዝናብ የሚከላከል መጠለያ አጥተው በከፍተኛ ችግር እየተፈተኑ የሚገኙ በመሆኑ ፣ ገዳማውያኑ ከነዚህ ችግሮች እንዲወጡ እና በቀጣይም ገዳሙ ራሱን እንዲችል ለማድረግ ፣ በጠቅላይ ቤተ-ክህነት እውቅና እና በሐገረ ስብከቱ ፍቃድ ገዳሙ ብቻ የሚጠቀመው በገዳሙ ስም የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ይፋ ተደርገው ፣ በሕዝበ ክርስቲያኑ በሚደረገው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ፣ ገዳሙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በወረዳ ቤተ-ክህነት ፣ በሐገረ ስብከት እና በጠቅላይ ቤተ-ክህነት ጸድቆ በሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬና የቅርብ ክትትል እየተደረገበት ከምዕመናን በሚገኘው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።
“ከእግዚአብሔር ዐይን የተሰወረ ምንም ፍጥረት የለም፤ ስለ ራሳችን መልስ መስጠት በሚገባን በርሱ ፊት ሁሉም ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው” (ዕብራውያን 4:13) እንዲል ቃሉ፣እኛም አጠቃላይ ፕሮጀክቱን በተመለከተ የተሰሩ ስራዎችን፣የተደረገውን ድጋፍ፣ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ስራዎች እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተለያዩ ጊዜያት ለምዕመኑ ይፋ እያደረግን፣እያሳወቅን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ዛሬ ስለ ፕሮጀክቱ እና የደረሰበትን ደረጃ በሚመለከት የምንሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለ4ኛ ጊዜ ሲሆን ይህም ምዕመኑ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ወቅታዊ የስራ ደረጃን እንዲገነዘብ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡
በገዳሙ የተያዙ የልማት ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ገቢ የማሰባሰብ ሂደት ዕቅዶችን በመንደፍ እና በመቅረጽ ተግባራዊ ለማድረግ ስንቀሳቀስ ቆይተናል፣አሁንም በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን። ለአብነትም ገዳሙ ያለበትን አሁናዊ እና ተጨባጭ ሁኔታ የሚገልፁ እና የሚያሳዩ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ ቀኖና እንዲሁም ትውፊት በጠበቀ መልኩ
በቴሌቪዥን ጥራታቸውን የጠበቁና ገላጭ የሆኑ ዶክመንተሪዎችን በማስተላለፍ ህብረተሰቡ መረጃው ኖሮት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥረት ተደርጓል።
ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ለታቀዱት የልማት ስራዎች የሚያስፈልገውን ገቢ ለማሰባሰብ ጥረት ተደርጓል፤እየተደረገም ይገኛል። በዚህም እስከ አሁን 52,640,000 ብር ( ሃምሳ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ሽህ ብር)የገንዘብ ድጋፍ እና 11,320,000 ብር ( አስራ አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ሽህ ብር) የሚገመት የአይነት ድጋፍ ማሰባሰብ ተችሏል።
በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የተጀመረው ፕሮጀክት 2 ዓመት ከ 6 ወር ያስቆጠረ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ምዕራፍ የፕሮጀክቱን 65 % በላይ ማሳካት ተችሏል። ከእነዚህም መካከል፦
የእናቶች በዓት እና የእንግዳ ማረፊያ በጥሩ ሁኔታ ተገንብቶ እናቶች እየተገለገሉበት ይገኛል።
ለገዳማውያኑ እንቅስቃሴ የማይመች እና አዳጋች የነበረው መንገድ 179 ሜትር ተራራ ተቦርቡሮ በአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
የእናቶች ቤተ እግዚአብሔር ግንባታ ተከናውኖ ሙሉ ቁሳቁስ ተሟልቶለት እየተገለገሉበት ይገኛል።
ገዳማት መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ኃላፊነት የሚወጡበት ፣ በተፈጥሮ እና ሰው - ሰራሽ አደጋዎች የተጎዱ ማኅበረሰቦችን የሚረዱበት እና ሕገ ወንጌልን የሚፈጽሙበት አቅምን ለማግኘት ፣ የኢኮኖሚ ነጻነት አስፈላጊ ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ “ገዳማዊ ሕይወት ጠንካራ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እንዲሁ ጠንካራ ትሆናለች ፤ ነገር ግን ገዳማዊ ሕይወት መዳከም ከጀመረ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ትደክማለች።” በማለት የገዳማት መጠንከርን አጽንዖት ሰጥቶ ይናገራል።
በዚህም መሰረት ገዳማዊያኑ በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸውን የምግብ አቅርቦት ችግር እና የአቅም ውስንነት በዘላቂነት ለመቅረፍ፣ ገዳማውያኑ እየሰሩ ቀጣይነት ያለው ገቢ እንዲያመነጩ ለማድረግ በማሰብ በሃሙሲት ከተማ የሸቀጣ ሸቀጥ እና የንዋያተ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ተከፍቶ እየሰሩበት ይገኛሉ እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ሱቅ ተከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
የእርሻ መሬት በመከራየት የእህል እና የጥጥ ምርቶችን በስፋ እያመረቱ ይገኛሉ፡፡
ገዳሙ በሃሙሲት ከተማ ላይ የእህል መጋዘን በመከራየት ያመረታቸው ምርቶች እንዲሁም ከገበሬ በመረከብ ለአከባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በስፋት እያቀረበ ይገኛል፡፡
ግሸን እና ላሊበላ እንዲሁም የተለያዩ አብያተክርስቲያናት እና ገዳማት ላይ ገዳሙ ያመረታቸው ምርቶች ለሽያጭ እያቀረበ ይገኛል፡፡
ምንኩስና በምድር ላይ እየኖሩ ከምድራውያን ተለይቶ ከሰማያውያን ቅዱሳን መላእክት ጋር ኅብረት የሚፈጥሩበት እና የሚገናኙበት መንገድ ነው።ሥራ ደግሞ የቅድስና መድረሻ የዲያብሎስ ውጊያን ማምለጫ መንገድ ነው። እንደ ሃገራችን አባባል “ሥራ የፈታ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል።” እንዲል ፣ ያለ ሥራ መቀመጥ በገዛ ፍቃድ አዕምሮን ለሰይጣን ቤተ ሙከራነት ማስረከብ ነውና ፣ ሁሌ ትጥቃቸውን ይዘው ከእግሩ በታች በመሆን የሚተጉ ንቁዓን ወታደሮች ፤ ሀብት ንብረታቸውን ትተው ለዓለሙ ሙት የሆኑ መነኮሳት በተሰበሰቡበት ገዳም፦ እርሻ ፣ የእጅ ሥራ እንዲሁም ሌሎች ተግባራትን የሚያከናውኑበት ቦታ ሊኖራቸው ግድ ነው። ነገር ግን በሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ያለው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ እና በረሃማነት ፣ ለእርሻ ሥራ ምቹ ባይሆንም ሴት መነኮሳዪያት የሚሠሩበት የተግባር ቤት ግንባታ ተጠናቆ ፣ የእደ ጥበብ ማምረቻ ማሽኖች ገብተው ገዳሙ ገቢ የሚያገኝበት እና ፣ መነኮሳዪታት የሰይጣንን ፈተና ድል የሚነሱበት ምቹ የሥራ ቦታ ተፈጥሯል። ከ20 ላላነሱ መነኮሳዪያት ሙያዊ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ቦታ ድረስ በማቅረብ ለረጅም ወራት ሥልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ስራ ገብተዋል።
የሻማ እና የጧፍ መስሪያ ማሽኖች ግዢ ተፈጽሞ ወደ ምርት ተገብቷል፣ በስፋት ለሽያጭ እየቀረበም ይገኛል፡፡
ገዳማት ከተፈጥሮ ጋር ባላቸው ትስስር ገዳማውያን ለሱባኤ የሚመርጡት ከከተማ የወጡ ፣ ዙርያቸውን በዕፀዋት የተሸፈኑ ገዳማትን ነው። ቤተክርስቲያን የነፍስን ቁስል ስታክም የተፈጥሮ መንፈስን ታድሳለች። ይህን ተመጋጋቢ ሂደት መነጠል የማይቻል ሲሆን ፣ በሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ምድረበዳነት ይህን ሂደት አስቀርቶ ለዓመታት ቢቆይም ፣ በተሰሩ የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ገዳሙ በእጽዋት እንዲሸፈን ከማድረጉም ባሻገር የአካባቢ የአየር ንብረት ጥበቃ ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ማለት ይቻላል።
ወደ ገዳሙ የሚያደርስ 8 (ስምንት) ኪሜ ደረጃ አንድ የጠጠር መንገድ ተሰርቶ ለአካባቢው ማህበረሰብ ጭምር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ለእናቶች መነኮሳይት ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ደረጃውን የጠበቀ ሻወር እና መጸዳጃ ቤት ተገንብቶ እናቶች እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የሲሚንቶ ማቡኪያ ማሽን፣የብረታ ብረትና የእንጨት መስሪያ ማሽን ፣ ዊንች ማሽን ፣ ኮንክሪት ቫይብሬተር፣ኮምፓክተር እንዲሁም ዘመናዊ የብሎኬት ማምረቻ ማሽን ግዥ ተፈጽሞ የፕሮጀክቱን ግንባታ ሙሉ ለሙሉ በራስ አቅም እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከመንግሥት ተቋማት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን በማድረግ የገዳሙ ህጋዊ ይዞታውን የመከለል፣የማስፋፋት እና ህጋዊ የማድረግ ሥራ ተከናውኗል።
ለአብነት ት/ቤት ፣ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት|ቤት ፣ ከፍተኛ ደረጃ ክሊኒክ እና ሌሎች አስፈላጊ የልማት ስራዎች የሚሰሩበት ህንጻ ግንባታ የሚገነባበት 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ካሬ ሜትር ቦታ በሀሙሲት ከተማ ላይ እንዲሁም 717 (ሰባት መቶ አስራ ሰባት) ካሬ ሜትር ለገበያ ማዕከል ግንባታ የሚውል ቦታ ከመንግስት በሊዝ ግዥ ተከናውኗል፡፡
ገዳሙን ከማስተዋወቅ እና ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ የሚገኙ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሚመለከታቸው የወረዳ ቤተ ክህነት፣ የሃገረ ስብከት እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት አመራሮች ፣መምህራነ ወንጌል እና ዘማሪዎች ቦታው ድረስ ተገኝተው ገዳሙ ያለበትን ሁኔታ እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እንዲመለከቱ ተደርጓል።
የቅዱስ ሚካኤልን በረከቱን ፣ ምልጃውን ፣ ተዓምሩን የሚገልጽ እና ገዳሙንም ለማስተዋወቅ በዘማሪ ዲያቆን አቤል መክበብ "ማር ሚካኤል" የተሰኘ ዝማሬ ተሰርቶ እና ቀረጻው በገዳሙ ላይ ተከናውኖ በማኅቶት ቲዩብ አማካኝነት ለህዝብ እንዲደርስ ተደርጓል፤ አሁንም በእይታ ላይ ይገኛል።
ከገዳሙ ወደ ጸበል ቦታ እና ከጸበልተኞች ማደሪያ ወደ ጸበል ቦታ የሚወስደው አስቸጋሪ የተራራ መንገድ የነበረ ሲሆን፣ተራራው እየተቆረጠ የአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት ፤ 260 ሜትር የሚሆን መንገድ ስራው ተጠናቆ ለአቅመ ደካሞች እና በህመም ላይ ሆነው ፈውስን ለሚጠብቁ ጭምር ለእንቅስቃሴ ምቹ ሆኖ እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
የአባቶች እና የሊቃውንት በዓት የግንባታ ሥራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
ለአባቶች መነኮሳት ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ደረጃውን የጠበቀ ሻወር እና መጸዳጃ ቤት ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
የአባቶች ቤተ እግዚአብሔር ግንባታ ሥራ ተጠናቆ አስፈላጊው ቁሳቁስ ተሟቶለት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
መነኮሳቱ ጉባኤዎችን፣ውይይቶችን ለማድረግ፣መንፈሳዊ ትምህርትን ለመስጠት የሚገለገሉበት ደረጃውን የጠበቀ የመሰብሰቢያ አዳራሽም ግንባታው ተጠናቆ እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
ዓይነ ስውራን እና የማየት እክል ያለባቸው ምዕመናን መጽሐፍ ቅዱስ፣ የጸሎት መጻሕፍት እና ሌሎች መንፈሳዊ መጻሕፍትን በራሳቸው እንዲያነቡ፣በአምልኮ ሕይወት በእኩልነት እንዲሳተፉ እና ሁሉም ምዕመናን የመንፈሳዊ ትምህርት ተደራሽነት እንዲያገኙ ለማስቻል የብሬል መጽሐፍ ቅዱስ ፣ውዳሴ ማርያም እና መዝሙረ ዳዊት ግዢ ተፈጽሟል፡፡
ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በሚኒሊየም አዳራሽ ተጋባዥ እንግዶች እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ገዳሙን ለማስተዋወቅ እንዲሁም ያለበትን ደረጃ ለማሳየት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ግንዛቤ ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡
“መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት፤ ተስፋን ሳንቆርጥ በጊዜው እናጭዳለንና፤ እንዲል (ገላትያ 6፥9) ።” ጅምራቸው መልካም፣ግንባታቸውም በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ የሚገኙ ስራዎችም ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ሰዓት “ገዳማዊ ልማት ለቤተክርስቲያን ትሩፋት” በሚል ንቅናቄ እየተሠሩ ካሉ ሥራዎች መካከል፡-
በገዳሙ ውስጥ የሚገኘው እና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የሚፈጸምበት በቅዱስ ሚካኤል ስም የተሰየመው ህንጻ ቤተ ክርስቲያን “ቤተ መቅደስ” ፣ እጅግ ጠባብ እና ከጥቂት ጊዜያት በኃላ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት መሆኑ ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት፣የጥንታዊውን የቤተ ክርስቲያን ቅርጽ ባልተወ መልኩ ፣ወደ ፊት የመነኮሳት እና ምዕመናን ቁጥር እንደሚጨምር በማሰብ ካለበት ስፋት በመጨመር እና ፣ መሰረታዊ የግንባታ ንድፍ በማውጣት፣ የሰርቬ ስራ በማከናወን ግንባታው ተጀምሮ የግንባታ ስራው ከ25 በመቶ በላይ ተከናውኗል፡፡
የግብጽ ቤተ ክርስቲያን በሁለት ታሪካዊ ክሥተቶች ተፈትና በነበረችበት ወቅት፣ ዳግም ሕዳሴዋን ያስገኙላት ሦስት ዐበይት ጉዳዮች ነበሩ። እነርሱም፦ የሥነ መለኮት ኮሌጅ መከፈት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴ እና የበጎ አድራጊ ምዕመናን መገኘት ናቸው።
ከዚህ የለውጥ ፋና ጀርባ የነበረውም ሊቀ ዲያቆናት ማር ሀቢብ ጊዮርጊስ ፣ ለትምህርት ሥርዓት ትኩረት በመስጠቱ ዛሬ ያሉ ግብጻውያን ከሀገራቸው አልፈው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ፣ ቤተ ክርስቲያንን በማስፋፋት ፣ የተማረ እና ለቤተ ክርስቲያን ፍቅር የጸናበት ትውልድ በማፍራት ጠንካራ ሥርዓትን መዘርጋት ችለዋል።
ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም መንፈሳዊ አገልጋዮችን ለማፍራት እና የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲሁም የዕውቀት ማዕከል ለመሆን፣ ከመንግሥት ግዥ በፈጸምነው የሊዝ መሬት ላይ G+3 የአብነት ትምህርት ቤት ስራን እያከናወነ ሲሆን የግንባታ ስራውንም ከ70 በመቶ በላይ ማሳካት ተችሏል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ያጋጠሟትን ችግሮች ያለፈችው በዓለማዊውም በመንፈሳዊውም ዕውቀት በበቁ ልጆቿ ነውና፣ በሁለት እንደተሳለ ሰይፍ ፍጹም በተሰማሩበት ሁሉ ስኬትን የሚጎናጸፉ አገልጋዮችን ለማፍራት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል የአስኳላ ትምህርት ቤት እየተሰራ ሲሆን ግንባታው የፊኒሽንግ ስራ ላይ የደረሰ እና ለትምህርት ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በማሟላት ላይ ይገኛል፡፡እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ካሪኩለም ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል
የጸበልተኞች እና የሱባኤ ማረፊያ ቤት ግንባታ ለማከናወን አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
የውሃ እና የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ፤ ማለትም የከርሰ ምድር ውሃ የማውጣት እና 8 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የመብራት ዝርጋታ ስራ የሚከናወን ይሆናል፡፡
ከፍተኛ ደረጃ ክሊኒክ፣የንጽህና መጠበቂያ ውጤቶች ማምረቻ መጋዘን፣የምግብ ማቀነባበሪያ እየተሰሩ ካሉ እና በቀጣይ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል ናቸው፡፡
በገዳሙ የተከናወነው የልማት ስራ አበረታች የሚባል ቢሆንም በተሻለ ፍጥነት ሥራዎች እንዳይከናወኑ ያደረጉ ተግዳሮቶችም ማጋጠማቸው አልቀረም። ከነዚሀም መካከል ፦
በግንባታ ዕቃዎች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚስተዋል እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ።
በገበያ ላይ የእቃዎች አቅርቦት እጥረት።
ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ዛሬም ድረስ የራሳቸውን አሉታዊ ተጽዕኖ መፍጠራቸው።
የነዳጅ እና የትራንስፖርት ዋጋ በእጅጉ መጨመር።
በሶሻል ሚዲያ በተለይም ቲክቶክ ላይ ትክክለኛ ያልሆኑ፣ተጨባጭ ማስረጃ ሳይያዝ፣ የገዳሙ አባቶችንም ሆነ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ያሉ የሚመለከታቸውን አካላት ምንም አይነት መረጃ ሳይጠይቁ ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን ማሰራጨት ዛሬም እያጋጠመ ያለ ችግር ነው፡፡
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱት በገዳሙ ላይ ሊሰሩ የታስቡ ፕሮጀክቶች በሁለት ዓመት ሰርተን የምናጠናቅቅ ሲሆን በገዳሙ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ከፍፃሜ አድርሶ ገዳማውያኑም ካሉባቸው ተደራራቢ ችግሮች እራሳቸውን እንዲችሉ እና ከልመና እንዲወጡ ለማድረግ በቀጣይ ለሚስሩት የልማት ሥራዎች ማከናወኛ 210,000,000 ብር (ሁለት መቶ አስር ሚሊዮን ብር) የሚያስፈልግ ሲሆን ይህን የማሰባሰብ ሥራም የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተፈፃሚ እስኪሆኑ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
“እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ ፥ በጽድቄም ቀኝ እጅ እደግፍሃለሁ፤ (ኢሳይያስ 41:10)።” እንዲል ቃሉ፤ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች ሁሉ በሃያሉ በልዑል እግዚአብሄር ቸርነት ፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት እየታለፉ ገዳማዊያኑን ካለባቸው የዓለም ፈተና ለመታደግ አሁንም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ድንቅ ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞንም “ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሄር ያበድራል ፣ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል” ይላል፡፡ ቅዱሳን አባቶች ጀምረው ሳይፈጽሙት የተውት ስራ የለምና እኛም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት እና የቃል ኪዳን ልጆች በዚህ በእኛ ዘመን ፣ ለዓለሙ ሰላም፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ድኅነት ዘወትር የሚማጸኑት እነዚህ ገዳማዊያን፣ያሉባቸው ችግሮች ተፈተውላቸው፣ ዓለሙን ትተው የሄዱበትን የምንኩስና ህይወት ፈጣሪን መማጸን ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ፣ ሁሉም ምዕመን ባለው ጸጋ በዕውቀቱ፣ በጉልበቱ እና በገንዘቡ ድጋፍ እንዲያደርግ በልዑል እግዚአብሄር ስም ጥሪ እናቀርባለን።
የገዳማውያኑ ጸሎት እና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሰኔ ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል፣ አዲስ አበባ

29 days ago