5 months ago
በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ በአንድ ሳምንት ግማሽ ሚሊዮን ብር ተጨምሯል
#ethiopia | በመዲናዋ አዲስ አበባ በተሽከርካሪ ገበያ ላይ ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ መመዝገቡ ተሰማ። በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለብስራት ሬድዮ እንደገለጹት፣ በተለይም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ የታየው የዋጋ ንረት ገበያውን ያናወጠ ሆኗል።
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ በተወሰኑ የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎች ላይ እስከ 500,000 ብር የሚደርስ ጭማሪ የታየ ሲሆን፣ በገበያው በስፋት የሚታወቁ ሞዴሎች የዋጋ ለውጥ የሚከተለውን ይመስላል፦
* BYD Seagull: ባለፈው ሳምንት 3.4 ሚሊዮን ብር ይሸጥ የነበረ ሲሆን፣ አሁን በ500 ሺ ብር ጭማሪ 3.9 ሚሊዮን ብር ደርሷል።
* BYD E2: ዋጋው ከ3.9 ሚሊዮን ብር ተነስቶ በአሁኑ ወቅት 4.3 ሚሊዮን ብር እየተሸጠ ይገኛል።
* Yuan Up: ይህ ሞዴልም በተመሳሳይ የዋጋ ንረት ከ4.9 ሚሊዮን ብር ወደ 5.3 ሚሊዮን ብር አሻቅቧል።
ተግዳሮቱና የተጠቃሚው ስጋት
በአገሪቱ የነዳጅ መኪኖች ወደ አገር እንዳይገቡ የተጣለው እገዳ ተጠቃሚዎች ፊታቸውን ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች እንዲያዞሩ ቢያደርግም፣ እንዲህ ያለው ያልተጠበቀና ፈጣን የዋጋ ጭማሪ ግን መኪና ለመግዛት ለሚያስቡ ዜጎች ትልቅ መሰናክል እየሆነ መምጣቱን ነጋዴዎች ጠቁመዋል።
ይህ በታሪክ አጭር በሚባል ጊዜ ውስጥ የታየ ከፍተኛ የዋጋ መናር፣ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችንም ሆነ ፈላጊዎችን ግራ እያጋባ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የመኪና_ገበያ #አዲስ_አበባ #የኤሌክትሪክ_መኪና #የዋጋ_ንረት #ኢትዮጵያ #byd #ኢኮኖሚ

በአዲስ አበባ ከተማ የመኪና ገበያ ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጭማሪ ታየ
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ በተሽከርካሪዎች መሸጫ ዋጋ ላይ ገበያውን ያናወጠ እና እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ መመዝገቡን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
እንደ ነጋዴዎቹ ገለጻ፣ በተለይም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ እስከ 500 ሺ ብር የሚደርስ ጭማሪ የታየ ሲሆን፣ ይህም በመኪና ገበያው ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ የታየ ከፍተኛ የዋጋ መናር ሆኖ ተመዝግቧል።
በገበያው ላይ በስፋት የሚታወቁ የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎችም ይህ የዋጋ ንረት ሰለባ የሆኑ ሲሆን፣ ቢዋይዲ ሴጉል (BYD Seagull) ባለፈው ሳምንት 3.4 ሚሊዮን ብር ይሸጥ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በ500,000 ብር ጭማሪ በማሳየት 3.9 ሚሊዮን ብር እየተሸጠ ይገኛል። በተመሳሳይ የቢዋይዲ ኢቱ (BYD E2) ዋጋ ከ3.9 ሚሊዮን ወደ 4.3 ሚሊዮን ብር ያሻቀበ ሲሆን፣ ዩዋን አፕ (Yuan Up) የተሰኘው ሞዴልም ከ4.9 ሚሊዮን ብር ተነስቶ 5.3 ሚሊዮን ብር እየተሸጠ መሆኑ ተረጋግጧል።
የነዳጅ መኪኖች ወደ ላይ የተጣለው እገዳ ተጠቃሚው ወደ ኤሌክትሪክ መኪና እንዲያዘነብል ቢያደርገውም፣ መሰል የዋጋ ጭማሬዎች ግን ተጠቃሚው በቀላሉ መኪና እንዳይገዛ ትልቅ መሰናክል እንደሆነበት በመዲናዋ በመኪና ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች ተናግረዋል።
በሰብል አበበ
seledadotio

6 months ago
ከሽመና መጋዝ ወደ ዓለም አቀፍ ዝና፡ሁላችንም የምንማርበት የሱዙኪ አስደናቂ ጉዞ
እስቲ በዕዕምሯቹ አንዲትን ደሀ ሴት አስቡ ።ያቺ ሴት ደግሞ በሃያኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በጃፓን በምትገኘው የሃማማትሱ የባህር ዳርቻ መንደር ውስጥ የነበረች ብላቹ አስቡ ።ያቺ እናት በእጅ በሚሰራ የሽመና መሣሪያ ጥጥ ስታደራጅ ቀኑ ይጨልምባታል። ልጇ የሚቺዮ ሱዙኪ የእናቱን መከራና የቆሰሉ እጆቿን እያየ ልቡ በሐዘን ይነካል።
ይህን የልጅነት ፍቅርና ርኅራኄ ነው እንግዲህ ዛሬ የምናውቀው የሱዙኪ ኩባንያ መሠረት የሆነው። የሚቺዮ የመጀመሪያው ህልም እናቱን ከድካም የሚያሳርፍ መሣሪያ መፍጠር እንጂ መኪና ማምረት አልነበረም፤ ይህ በንጹህ ልብ የተጀመረ ጥረት ግን የቴክኖሎጂ አብዮት ለመፍጠር በቂ ነበር።
ሚቺዮ በፈረንጆቹ 1909 ዓ.ም በ22 ዓመቱ የራሱን "ሱዙኪ የሽመና ፋብሪካ" ሲመሰርት ጃፓን ከእርሻ ወደ ኢንዱስትሪ የምትሸጋገርበት ወቅት ነበር።
እርሱ የሠራቸው የሽመና መሣሪያዎች ከሌሎቹ በበለጠ ፍጥነትና ጥራት ስለነበራቸው በሽመናው ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ዝናን አተረፉ፤ ስራውም እየሰፋ በመሄዱ በ1920ዎቹ ማሽኖቹ ወደ ውጭ ሀገራት መላክ ተጀመረ። የዚህ ሰው ስኬት ሚስጥር ግን ትርፍ ማግኘት ብቻ ሳይሆን የሰዎችን የዕለት ተዕለት ችግር መረዳትና መፍትሄ መስጠት መሆኑ ለቀጣዩ ትልቅ ለውጥ በር ከፋች ሆነ።
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ የጃፓን ኢኮኖሚና የጨርቃጨርቅ ገበያ ክፉኛ ተመታ፤ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ግለኛ አስተሳሰብ ያለው ሰው አልነበረምና ሚቺዮ ፋብሪካውን ለመዝጋት አልፈለገም ይልቁንም ህዝቡ ምን ይፈልጋል? የሚለውን አሰበ።
ጦርነቱ ያደቀቃት ጃፓን ውስጥ ሰዎች ለመንቀሳቀስ ብስክሌት ብቻ ነበር ያላቸው፤ እናም ሚቺዮ ለተራው ህዝብ ተመጣጣኝና ጉልበት የማይጠይቅ የትራንስፖርት አማራጭ ለማቅረብ ወሰነ። ይህ ውሳኔ የኩባንያውን አቅጣጫ ከሽመና ወደ ሞተር ዘርፍ የቀየረ የታሪክ ምዕራፍ ሆነ።
በፈረንጆቹ 1952 "Power Free" የተሰኘችውን የመጀመሪያዋን 36cc አነስተኛ ሞተር ለገበያ አቀረበ፤ ይህች ሞተር በብስክሌት ላይ የምትገጠም ሆና በፔዳል ወይም በሞተር እንድትሰራ ተደርጋ የተነደፈች ብልህ ፈጠራ ነበረች። ይህ ስኬት ኩባንያው በ1954 "Diamond Free" የተባለችውን ጠንካራ ሞተር እንዲያመርትና ስሙን ወደ "ሱዙኪ ሞተር ኩባንያ" እንዲቀይር አደረገው፤ የሚቺዮ ህልም አሁን ከእጅ ስራ ወጥቶ በመንገዶች ላይ መፍሰስ ጀመረ።
የሱዙኪ ትልቁ ድፍረት የታየው በ1955 "Suzulight" የተባለችውን የመጀመሪያዋን አነስተኛ መኪና ሲያመርት ነው፤ መኪናዋ በወቅቱ በአውሮፓ እንኳን ብርቅ የነበሩ እንደ ፊት ለፊት ጎታችያሉ ቴክኖሎጂዎችን አካታ ነበር።
ይህች መኪና ለጃፓን ህዝብ የተስፋ ምልክት ሆና አገለገለች፤ ሱዙኪም በዓለም ዙሪያ "አነስተኛና ቀልጣፋ" መኪኖችን በማምረት ረገድ ተወዳዳሪ የሌለው መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመሰከረ።
እያደገ የመጣው ኩባንያ በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ ውስጥ ወደ ሞተር ሳይክሎች እና አነስተኛ የጭነት ተሽከርካሪዎች ዘርፍ ተስፋፋ፤ የሱዙኪ ሞተር ሳይክሎች በውድድር መድረኮች ላይ ድልን መቀዳጀት ሲጀምሩ፣ እንደ "Alto" ያሉ መኪኖች ደግሞ የቤት እመቤቶችና ተራ ሰራተኞች ተመራጭ ሆኑ። የኩባንያው ፍልስፍና "ቀላል፣ ብልህ እና ለሰው ልጅ ቅርብ" በሚሉ እሴቶች ላይ በመገንባቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱ በከፍተኛ ፍጥነት ጨመረ።
ሱዙኪ በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ትልቅ ስር የሰደደው በ1982 ዓ.ም ከህንድ "Maruti Udyog" ጋር ባደረገው አጋርነት ነው፤ ይህ ጥምረት የህንድን የመኪና ገበያ ከመቀየር ባለፈ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች የመኪና ባለቤት የመሆን ህልምን እውን አደረገ። በፓኪስታን እና በሌሎች ታዳጊ ሀገራትም ሱዙኪ የታማኝነትና የኢኮኖሚ ምልክት በመሆን በየቤቱ ስሙ የሚጠራ ተወዳጅ የምርት ስም መሆን ቻለ።
በ1990ዎቹ ኩባንያው ስሙን ወደ "ሱዙኪ ሞተር ኮርፖሬሽን" በመቀየር ዓለም አቀፋዊነቱን አጠናከረ፤ እንደ "Swift"፣ "Jimny" እና "Vitara" ያሉ ዝነኛ ሞዴሎችን በማፍራት የዘመኑን ወጣትና ቤተሰብ ፍላጎት ማርካት ቻለ።
እነዚህ መኪኖች በጠንካራነታቸውና በነዳጅ ቆጣቢነታቸው የታወቁ ሲሆኑ፣ ሱዙኪ በአነስተኛ መኪኖች ዘርፍ ያለውን የበላይነት ለዓለም በድጋሚ ያሳየባቸው ውጤቶች ነበሩ።
የኩባንያው መሪ መፈክር "By Your Side" (ከጎንዎ ነን) የሚል ሲሆን፣ ይህ ዝም ብሎ የንግድ ማስታወቂያ ሳይሆን የቆየው የሚቺዮ ሱዙኪ መንፈስ መገለጫ ነው፤ ይህም ማለት የደንበኞችን የዕለት ተዕለት ኑሮ መረዳትና ለኑሯቸው የሚመጥን መፍትሄ ማቅረብ ማለት ነው።
ዛሬ ሱዙኪ በከተማ መኪኖች፣ በሞተር ሳይክሎች ብቻ ሳይሆን በባህር ላይ ሞተሮችም ጭምር በዓለም ዙሪያ ካሉ ማህበረሰቦች ጋር በቅርበት የተቆራኘ ነው።
የሚቺዮ ሱዙኪ ታላቅነት ያለው ከመሬት ተነስቶ ቢሊዮን ዶላር የሚያንቀሳቅስ ኩባንያ በመገንባቱ ላይ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ለእናቱ ካለው ፍቅር ተነስቶ ለሰው ልጅ ሁሉ የሚጠቅም ስራ መስራቱ ላይ ነው። የእሱ ታሪክ እንደሚያስተምረን ትልቅ ለውጥ የሚመጣው ከትልቅ ካፒታል ሳይሆን የሰዎችን ችግር ለመቅረፍ ካለ ቅን ፍላጎትና ያላሰለሰ ጥረት ነው፤ ይህም ዛሬ ለደረሰበት ዓለም አቀፍ አቅኚነት ዋነኛው ነዳጅ ነበር።
በአሁኑ ሰዓት ሱዙኪ ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖችና ወደ ተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እየተሸጋገረ ቢሆንም፣ አሁንም መሠረታዊ ማንነቱን ግን አልለቀቀም። የአካባቢ ጥበቃን ያገናዘቡ እና አነስተኛ የካርቦን ልቀት ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በማምረት የወደፊቱን የትራንስፖርት ዓለም እየመራ ይገኛል፤ ይህ ደግሞ የሚቺዮን የፈጠራ መንፈስ ከአዲሱ ዘመን ጋር የማስማማት ጥበብ ውጤት ነው።
የሱዙኪ ጉዞ ከጃፓን የባህር ዳርቻ መንደር ተነስቶ በዓለም አውራ ጎዳናዎች ላይ የነገሰ ታሪክ ነው፤ ይህ ታሪክ ትጋት፣ ርኅራኄና ጽናት ካለ የማይታለፍ መሰናክል እንደሌለ ያረጋግጣል። የዚያ ታናሽ የገበሬ ልጅ ህልም ዛሬም በቢሊዮኖች ልብ ውስጥና በየመንገዱ በሚሽከረከሩት የሱዙኪ መኪኖች ውስጥ ህያው ሆኖ ይቀጥላል።
ሱዙኪ ከቴክኖሎጂ በላይ የሰው ልጅ የጽናት ውጤት ነው።

10 months ago
ኢትዮፒካር በቅርቡ እጅግ ቅንጡና አዳዲስ መኪናዎችን ሊያቀርብ ነው
#ethiopia | በአሁኑ ወቅት የዓለም የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ በብዙ መልኩ እየተለወጠ ይገኛል።የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች ኩባንያዎች ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ ወደኤሌክትሪክ እያዞሩ ነው።
በርካታ ሀገራትም የተሽከርካሪ ፖሊሲያቸውን እየከለሱ ሲሆን ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እያበረታቱ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያም ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራች ትገኛለች።
እንደሚታወቀው መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መመሪያ ያወጣ ሲሆን የተለያዩ የማበረታቻ አሰራሮችንም ዘርግቷል።በዚህም በዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃት እየተስተዋለ ይገኛል።
ይንን ቀድሞ የተረዳው ኩባንያችን ኢትዮፒካር የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና ፍላጎትን ለመመለስ ቀድሞ ዘርፉን ተቀላቅሏል።
በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪና አስመጪዎች መካከል ግንባር ቀደሙና ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው የኔታ ብራንድ ወኪል የሆነው ኢትዮፒካር የተለያየ ሞዴል ያላቸው የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለኢትዮጵያውያን ፈላጊዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በስፋት እያቀረበ ይገኛል።
ተቋማችን ከአስር ዓመታት በላይ በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ከተለያዩ ሃገራት በማስመጣትና ለደንበኞቹ በማቅረብ በተጠቃሚዎች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነትና ታማኝነት ማትረፍ ችሏል።
ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰራ ሲሆን የብድርቦትን በማመቻቸን ደንበኞች በቀላሉ የመኪና ባለቤት አድርጓል።
ኢትዮፒካር የረጅም ጊዜ ልምዱንና በደንበኞቹ ያተረፈውን መልካም ስሙን የበለጠ ለማሳደግም በአሁኑ ወቅት ስትራቴጂ ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ኩባንያችን ኢትዮፒካር በኢትዮጵያ የመኪና ገበያ ላይ በተለይም በኤሌክትሪ የሚሰሩ ተሽከርካሪ ዘርፍ ያለውን ግንባር ቀደምነት ሚና ለማስቀጠልም በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡
በቀጣይም አዳዲስና እጅግ ቅንጡ መኪኖችን በቅርቡ ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን ሲገልጽ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል፡፡
ኢትዮፒካር ለገበያ የሚቀርባቸው የመኪና ዓይነቶች
1 2BYD
2 NETA
3 Icar
4 Dongfeng
5 NETA
አብረውት የሚሰሩ የፋይናንስ ተቋማት
1 አሚጎስ ገንዘብ ቁጠባና ብድር ሕብረት ስራ ማህበር
2 ኦሜጋ ገንዘብ ቁጠባና ብድር ሕብረት ስራ
3 ግሎባል ገንዘብ ቁጠባና ብድር ሕብረት ስራ

1 year ago
ቴስላ "ዋይ" የተሰኘች አዲስ ሞዴል መኪና አስተዋወቀ
#ethiopia | የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ኩባንያ ከፍተኛ ዋጋ የተቆረጠላትን ዋይ ሞዴል መኪና በህንድ ሙምባይ አስተዋውቋል፡፡
አዲሷ ዋይ ሞደል መኪና በ70 ሺህ ዶላር ለገበያ መቅረቧ ማክሰኞ እለት ይፋ ተደርጓል፡፡
በህንድ ከውጭ በሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለውን ከፍተኛ ታሪፍ ተከትሎ የመሸጫ ዋጋዋ ከሌሎች ገበያዎች አንፃር ከፍተኛ ሊሆን ችሏል፡፡
በርግጥ የቴስላ ሥራ አስፈፃሚና እና የዓለማችን ቁጥር አንድ ቱጃሩ ኤለን መስክ ከዋጋው መወደድ ጋር ተያይዞ ብዙ ትችት አስተናግዷል፡፡
አራት በመቶ ያህሉን የአሜሪካን የመኪና ገበያ ሽያጭ በመሸፈን 3ኛው የዓለማችን ትልቁ የመኪና ግብይት ማዕከል የሆነችው ህንድ በበርካታ የአሜሪካ መኪና አምራች ኩባንያዎች ዐይን ውስጥ ገብታለች፡፡
በህንድ ሰፊ ግብይት ያላቸው ታታ ሞተርስ እና ማሂንድራን በብዙ እጥፍ ይበልጣል የተባለለት አዲሱ የቴስላ ምርት ዋይ ሞዴል መኪና ከቅንጡዎቹ የጀርመን ቢ ኤም ደብሊው ፣ መርሴዲስ ቤንዝ እና ከደቡብ ኮሪያው ኪያ ከተሰኙ መኪናዎች ጋር የሚወዳደር ነው ተብሏል፡፡
በህንድ ገበያ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ዘመናዊው ዋይ ሞዴል ማክሰኞ እለት በሙምባይ የማሳያ ማዕከሉ የተዋወቀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም ትዕዛዞችን እየተቀበለ እንደሚገኝ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ #amn

Sponsored by
Surafel
Comments