Logo
SeledaPost
በአዲስ አበባ ከተማ የመኪና ገበያ ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጭማሪ ታየ

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ በተሽከርካሪዎች መሸጫ ዋጋ ላይ ገበያውን ያናወጠ እና እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ መመዝገቡን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

እንደ ነጋዴዎቹ ገለጻ፣ በተለይም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ እስከ 500 ሺ ብር የሚደርስ ጭማሪ የታየ ሲሆን፣ ይህም በመኪና ገበያው ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ የታየ ከፍተኛ የዋጋ መናር ሆኖ ተመዝግቧል።

በገበያው ላይ በስፋት የሚታወቁ የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎችም ይህ የዋጋ ንረት ሰለባ የሆኑ ሲሆን፣ ቢዋይዲ ሴጉል (BYD Seagull) ባለፈው ሳምንት 3.4 ሚሊዮን ብር ይሸጥ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በ500,000 ብር ጭማሪ በማሳየት 3.9 ሚሊዮን ብር እየተሸጠ ይገኛል። በተመሳሳይ የቢዋይዲ ኢቱ (BYD E2) ዋጋ ከ3.9 ሚሊዮን ወደ 4.3 ሚሊዮን ብር ያሻቀበ ሲሆን፣ ዩዋን አፕ (Yuan Up) የተሰኘው ሞዴልም ከ4.9 ሚሊዮን ብር ተነስቶ 5.3 ሚሊዮን ብር እየተሸጠ መሆኑ ተረጋግጧል።

የነዳጅ መኪኖች ወደ ላይ የተጣለው እገዳ ተጠቃሚው ወደ ኤሌክትሪክ መኪና እንዲያዘነብል ቢያደርገውም፣ መሰል የዋጋ ጭማሬዎች ግን ተጠቃሚው በቀላሉ መኪና እንዳይገዛ ትልቅ መሰናክል እንደሆነበት በመዲናዋ በመኪና ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች ተናግረዋል።

በሰብል አበበ

seledadotio
seledadotio
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.