24 days ago
ዲጂታል መደመር፡ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት በብሪክስ መድረክ
******************
በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ባለው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በልማት፣ በዲፕሎማሲ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የነደፈችውን ግልጽ አቅጣጫ የሚያንፀባርቅ ነው።
"ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ የተንፀባረቀው ሀሳብ፣ በሀገር ውስጥ እየተተገበረ ካለው የመደመር እሳቤ እስከ ዓለም አቀፉ የብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ድረስ ያለውን ስትራቴጂያዊ ውህደት በሚገባ ያሳያል።
ሁለቱም አስተሳሰቦች አግላይ ከሆነው ነባር የዓለም ሥርዓት ወጥቶ የጋራ ተጠቃሚነትን፣ ፍትሐዊ የባለብዙ-ወገን ማዕቀፍን እና አዎንታዊ ትብብርን መገንባት ላይ ያተኩራሉ።
በኢትዮጵያ ምህዳር ውስጥ የዳበረው የመደመር እሳቤ ቀደምት ዕውቀቶችን በመጠበቅ፣ የወቅቱን አቅሞች በማጣመር እና ጉድለቶችን በመሙላት አዲስ አቅም መገንባትን መሠረት ያደረገ ነው።
ይህ አካታችነትን ያማከለ ፍልስፍና የብሪክስ ጥምረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ውሳኔዎች የተገለሉ አዳጊዎችን ከሚያሳትፈው ሰፊ ዓላማ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት፣ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እና የሰፊው አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕከል በመሆኗ፤ የብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ወደ አፍሪካ አህጉር በስፋት እንዲሰርፅ ትልቅ ድልድይ ሆና ታገለግላለች።
ካፒታልን፣ ቴክኖሎጂን እና ገበያን በማጣመር የጋራ ዕድገት ማምጣት የሚለው የብሪክስ መርህም፣ ሀብት እና አቅምን አቀናጅቶ የላቀ ውጤት ከማምጣቱ የመደመር እሳቤ ጋር ጥልቅ ውህደት ይፈጥራል።
ይህ የዲፕሎማሲ እና የልማት ትስስር ወደ ቴክኖሎጂው ዘርፍ ሲሰፋ ይበልጥ ጎልቶ ይታያል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ የኒው ዴልሂ የብሪክስ ጉባኤ ላይ፣ “የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና ይጫወታል” በማለት ያነሱት ሀሳብ፤ ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ አህጉራዊ መሪ ለመሆን ያላትን ጽኑ አቋም ያረጋግጣል።
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ይህ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት አልፋ ወደ ቴክኖሎጂ አመንጪነት እንድትሸጋገር የሚያስችል ታሪካዊ ተቋም ነው።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጥናት እንደሚያመለክተው፣ አፍሪካ ለዘርፉ ተገቢውን መሰረተ ልማት እና ዝግጅት ካደረገች የሰው ሠራሽ አስተውሎት የአህጉሪቱን ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በ4 በመቶ ሊያሳድገው ይችላል። የዩኒቨርሲቲው መቋቋም ይህን ግዙፍ የኢኮኖሚ አቅም እውን ለማድረግ የተወሰደ ትልቅ ርምጃ ነው።
የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ለሀገር በቀል ችግሮች መፍቻነት የማዋሉ ሥራ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት ተግባራት ጋር ተቀናጅቶ የላቀ ውጤት እያመጣ ይገኛል።
የሰብል በሽታዎች መቆጣጠሪያ ሥርዓት፣ ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ያቀፈው የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣ ከ130 በላይ የመንግሥት አገልግሎቶችን የሚሰጠው የመሶብ ፖርታል እንዲሁም የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ፕሮግራም የዚሁ ስትራቴጂያዊ ጉዞ አካላት ናቸው።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ መገኘቷ የዘርፉን ዕድገት ለማፋጠን ተጨማሪ ዕድል ይፈጥራል።
የብሪክስ አባል ሀገራት በሴሚኮንዳክተር፣ በሱፐር ኮምፒዩቲንግ እና በዲጂታል መሰረተ ልማት ያላቸውን የበለፀገ አቅም ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና የመረጃ ማዕከላት ግንባታ መጠቀም ሰፊ አማራጭ ይከፍታል።
በጉባኤው ላይ እንደተብራራው የቀጣዩ ትውልድ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴሎች በምዕራባውያን ቋንቋዎች ላይ ብቻ ሳይገደቡ የአፍሪካን ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣ ባህሎች እና ቋንቋዎች ያካተቱ መሆን አለባቸው።
አዲሱ የልማት ባንክም ለዚህ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ የሆነውን አማራጭ ፋይናንስ ለማቅረብ ያስችላል።
ከቴክኖሎጂው መስፋፋት ጎን ለጎን የሚመጡትን የሳይበር ደኅንነት ሥጋቶች፣ የግል መረጃ መጣስ እና የአልጎሪዝም አድልዎን ለመከላከል ኢትዮጵያ ጠንካራ የሕግ እና ፖሊሲ ማዕቀፎችን ዘርግታለች።
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ብሔራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፖሊሲ የዘርፉ የአሠራር ሥርዓቶች ግልፅ፣ ተጠያቂነት ያለባቸው እና ከሰው ልጅ ቁጥጥር የማይወጡ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
በተጨማሪም የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ እና የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ የዜጎችን የመረጃ ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር ብሔራዊ የመረጃ ደኅንነትን ለመጠበቅ ጉልህ ድርሻ አላቸው።
የመደመር እሳቤ እና የብሪክስ ዓላማ በፅንሰ-ሀሳብ እና በስትራቴጂ ደረጃ የሚደጋገፉ፣ አካታችነትን እና የጋራ ብልፅግናን ማዕከል ያደረጉ የፖሊሲ አተያዮች ናቸው።
ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ መገኘቷ ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲጎለብት ከማድረጉም በላይ፣ የአፍሪካን ድምፅ እና የቴክኖሎጂ ፍላጎት በዓለም መድረክ ለማስተጋባት አቅም ሆኗታል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ የወጡት ብሔራዊ ፖሊሲዎች እና የሕግ ማዕቀፎች ደግሞ የቴክኖሎጂውን ሥጋቶች አስቀድሞ በመገደብ በራስ መተማመን እና በሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ የቴክኖሎጂ ዕድገትን ለማረጋገጥ አስችለዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #digitalethiopia #brics2026 #medemer #artificialintelligence #techtransfer #aiuniversity #globalsouth #innovation

27 days ago
የነገዋ ኢትዮጵያ - በሳይንስና ቴክኖሎጂ ምህዳር
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪካዊ የነጻነትና የሉዓላዊነት አርማ ባለቤት ነው።
የአድዋ ድል የዚህ እውነት አንዱ ማሳያ ነው። ዛሬ ላይ የሉዓላዊነት ትርጓሜ ከዚህም ተሻግሮ የሳይበር ምህዳርን እና የዲጂታል ደህንነትን መቆጣጠርን ጨምሯል።
ኢትዮጵያ ይህንን የዘመኑን ጥሪ በመቀበል ብሔራዊ የሳይበር ሉዓላዊነቷን አረጋግጣለች። መረጃዎቿን በሀገር ውስጥ ዘመናዊ ዳታ ማዕከላት በማከማቸት እውነተኛ የመረጃ ሉዓላዊነትን በተግባር እውን ማድረግ ችላለች።
ለዘላቂ ልማት የሰውን ልጅ አእምሮ ማበልጸግ ወሳኝ ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በ"5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ" ግዙፍ ፕሮጀክት ታላቅ የትውልድ ግንባታ በማካሄድ፣ ዘመኑን የዋጀ የተማረ የሰው ሀይል በማፍራት የጎላ ስራ መስራት ተችሏል።
ለዘመናት የቆየውን የተንዛዛ ቢሮክራሲያዊ ማነቆ ለመስበር ዲጂታል አገልግሎቶች በስፋት እየተተገበሩ ናቸው። በተለያዩ ቦታዎች በተበታተኖ መልኩ ሲሰጡ የነበሩ አገልግሎቶች ከ70 በላይ በሆኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች እየተሰጡ ይገኛሉ።
ስማርት ፖሊስ ጣቢያ ማቋቋምን ጨምሮ በፍትህ ተቋማት ዲጂታላይዝድ አሰራር መዘርጋቱ የወንጀል መከላከልና የፍትህ አሰጣጡን አዘምኗል። ከ41 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበው ዘመናዊ አሰራር ውስጥ ገብተዋል፡፡ የዲጂታል ግብር አሰባሰብም የሀገር ውስጥ ገቢን በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጓል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ አዳዲስ እመርታዎች ታይተዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ መቋቋሙ ለምርምር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። በምጥን ግብርና ቴክኖሎጂ አርሶ አደሩ የአፈርና የዝናብ ሁኔታን አስቀድሞ በማወቅ ምርታማነቱን ማሳደግ ችሏል።
ስታርት አፕ ኢትዮጵያ ወጣቶች ሀሳባቸውን ወደ ንግድ እንዲቀይሩ ምቹ ምህዳር ፈጥሯል። ስማርት ስልኮችን በሀገር ውስጥ የመገጣጠም ስራ መጀመሩ ሀገሪቱን ከሸማችነት ወደ ፈጣሪነትና አምራችነት እያሸጋገራት ይገኛል። የ4ጂ እና 5ጂ ኔትወርክ ተደራሽነት እየሰፋ ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ግቦች በመሳካት ላይ ናቸው።
እነዚህ ሁለንተናዊ የቴክኖሎጂ ስኬቶች የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን እያደረጓት ይገኛሉ። ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የነገ ህልም ብቻ ሳይሆን ዛሬ በገሀድ የምንኖረው እውነት መሆኑን በተጨባጭ መረጃዎች አይተናል።
አዲሷ ኢትዮጵያ በማይናወጥ ጠንካራ መሰረት ላይ ቆማለች። የነገዋ ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ የበለጸገች፣ በራሷ ልጆች አቅም የምትተዳደር እና ለዜጎቿ ሁሉ የምትመች ታላቅ ሀገር እንደምትሆን የጀመርናቸው ስራዎች ይመሰክራሉ።
በቴዎድሮስ ኮሬ

3 months ago
ኢትዮጵያ ወደ ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት የምታደርገው ጉዞ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዘመናዊው ዓለም የሀገራት ፉክክር በወታደራዊ ኃይል ወይም በተፈጥሮ ሀብት ብቻ አይወሰንም፡፡
የቴክኖሎጂ አቅም፣ የዲጂታል መሠረተ ልማትና የመረጃ ሉዓላዊነት የሀገራትን የወደፊት እድገት የሚወስኑ ቁልፍ መለኪያዎች ሆነዋል።
ኢትዮጵያም ባለፉት 5 ዓመታት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ያከናወነቻቸው ሥራዎች የዲጂታል ሽግግር መሠረት ጥለዋል፡፡ በ2ኛው ምዕራፍ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ወደ ቀጣዩ የቴክኖሎጂ ዘመን ለማሸጋገር በትኩረት እየሰራች ነው።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ዋና ግብ የመንግሥት አሰራርን ማዘመን፣ የቢሮክራሲ ጫናን መቀነስ፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን ማፋጠንና የዜጎችን የኑሮ ጥራት ማሻሻል ነበር።
በዚህም የቴሌኮም ዘርፉ ለውድድር ተከፍቶ፣ የ4ኛና 5ኛ ትውልድ ኔትወርክ አገልግሎቶች ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲስፋፉ በማድረግ የኢንተርኔት ተደራሽነትን እንዲጠናከር አድርጓል፡፡ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ የሚፈጠሩ አዳዲስ ዕድሎችንም አስፍቷል።
የዲጂታል ፋይናንስ ሽግግሩም በሀገሪቱ ውስጥ አዲስ ምዕራፍን የከፈተ ሲሆን÷ የሠራተኞች ደመወዝ፣ የነዳጅ ግብይትና የትራፊክ ቅጣት ክፍያዎች በዲጂታል ስርዓት መፈጸማቸው ግብይቶችን ፈጣን፣ ግልጽና ቀልጣፋ አድርጓል።
በተመሳሳይ ሚሊየኖች በፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ተመዝግበው አገልግሎት እያገኙ ሲሆን÷ የፓስፖርት፣ የንግድ ፈቃድና የታክስ አገልግሎቶችን ወደ ኦንላይን ማሸጋገር ጊዜን ከመቆጠብ ባሻገር የሙስና እድሎችንም ለመቀነስ አስችሏል።
የቴክኖሎጂ ሽግግሩ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን ብቻ አልተወሰነም፤ የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ የወጣቶችን የቴክኖሎጂ ክህሎት በማሳደግ ለወደፊቱ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጠንካራ የሰው ኃይል ለመገንባት አግዟል፡፡ይህም ቴክኖሎጂን ከመጠቀም ወደ መፍጠርና ማልማት የሚደረግ ስልታዊ ሽግግር መሆኑን ያሳያል።
የዲጂታል ሉዓላዊነቷን ለማጠናከር ከሶፍትዌር ልማት ባለፈ በሃርድዌር ምርት ላይም ትኩረት የሰጠችው ኢትዮጵያ የላፕቶፕ፣ የታብሌትና ሌሎች ዲጂታል መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የፋብሪካ ግንባታ እያከናወነች ትገኛለች።
ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ሩቅ ይመስል የነበረው የድሮን ቴክኖሎጂ ዛሬ በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉ በቴክኖሎጂ ራስን የመቻል አቅም እየጠነከረ መምጣቱን ያመለክታል።
ዲጂታላይዜሽን ያለ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ሊሳካ እንደማይችል በመገንዘብም ኢትዮጵያ የሕግ፣ የተቋምና የቴክኖሎጂ አቅሟን በማጠናከር የዲጂታል ሥነ ምህዳሯን እየገነባች ትገኛለች።
የተሻሻለው ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ የግል መረጃ ጥበቃና የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ሕጎች ለዲጂታል ኢኮኖሚው አስተማማኝ ሕጋዊ መሠረት ፈጥረዋል።
በተመሳሳይ የመከላከያ ሳይበር ማዕከል የሰለጠኑ የሳይበር ኃይሎችን በማፍራት የአገሪቱን ዲጂታል ሀብቶችና ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን ለመጠበቅ አቅሙን እያጠናከረ ይገኛል።
በዚህ መሠረት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የ2025 ስትራቴጂ ቀጣይ ምዕራፍ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ፣ ወደ ቴክኖሎጂ ፈጠራና ወደ ሉዓላዊ የመረጃ ሥርዓት የሚያሸጋግር ብሔራዊ ራዕይ ነው።
ስትራቴጂው የሰው ሰራሽ አስተውሎትን እና ሌሎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በኢኮኖሚ፣ በመንግሥታዊ አገልግሎትና በማኅበራዊ ዘርፎች ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ያለመ ነው።
በመሆኑም ኢትዮጵያ የጀመረችው የዲጂታል ጉዞ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ከማስፋት ባለፈ የራሷን ቴክኖሎጂ የምትፈጥር፣ የምታመርትና የምትጠብቅ ሀገር ለመሆን የተጀመረ ስልታዊ ጉዞ መሆኑን በግልጽ አሳይቷል።
የዲጂታል 2030 ራዕይ ጥንካሬ ያላት፣ በቴክኖሎጂ ራሷን የቻለች እና ለወደፊቱ ፉክክር ዝግጁ የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጠንካራ መሠረት ይጥላል።
በዮናስ ጌትነት

5 months ago
የሕብረተሰቡን የመረጃ እውቀት ያሳደገው “የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት” ጉባኤ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) “የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት” ጉባኤ እንደ ሀገር በመረጃ ልማት የተሰሩ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች በአውደ ርዕይ የቀረቡበት ነበር አሉ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር)።
“የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት” በሚል መሪ ሐሳብ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ ጉባኤ ተጠናቅቋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በጉባኤው ከ30 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ገልጸው÷ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በአራት ዘርፎች የመረጃ አሰባሰብና ልማት ሥራዎችን ሲከውን መቆየቱን ተናግረዋል።
በዋናነት በሕብረተሰብ ጤና፣ በግብርና ጥናት፣ በቤተሰብ ወጪ ጥናት እና በድርጅት ቆጠራ ሰፊ የመረጃ ልማት ሥራዎች መሰራታቸውን አመልክተዋል።
የመረጃ ልማት ሥራው የሀገር አቀፍ የምርት እድገት ክለሳ ለማድረግ በእጅጉ እንደሚያግዝም ጠቁመዋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሃጽዮን በበኩላቸው÷ ጉባኤው ሕብረተሰቡ ስለ መረጃ ያለውን እውቀት ከፍ ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
በሔብሮን ዋልታው

የሰው ልጅ ታሪክ የኃይል ሽግግር ታሪክ ነው፤ የኢትዮጵያ ‘የዲጂታል ድንበር’ የት ላይ ነው?
#ኢትዮጵያ #የዲጂታል_ድንበር #የመረጃ_ሉዓላዊነት #ቴክኖሎጂ #ሳይበር_ደህንነት
5 months ago
የመደመር አንቀጽ
የመደመር መንግሥት የውስጥ የኢኮኖሚ ሽግግርን በታቀደ መልኩ የሚመራ ብቻ ሳይሆን ከባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታን ይተነትናል። ራሱን ለመለወጥና ከእነዚህ ሁኔታዎች ጋር ራሱን ለማላመድ አስቀድሞ ይዘጋጃል። ዓለም ከአንዱ የኢኮኖሚ አብዮት ወለ ሌው እየዘለለ ከተለምዷዊው አሰራር ወጥቶ ወደ ዲጂታል ተሸጋግሯል። ከዚያም አልፎ አልፎ እንደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዓይነት ጨዋታ ቀያሪ ዐቅም ያላቸው ቴክኖሎጂዎችን እየታጠቀ ነው።
ከዚያም አልፎ እንደ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ዓይነት ጨዋታ ቀያሪ ዐቅም ያላቸው ይሄንን ለውጥ በቶሎ የተላመዱ ሀገራትን ዛሬ የበለጸጉ ብለን እንጠራቸዋለን። ምክንያቱም ለውጥ የሚላመዱትን ያከብራል፤ የማይላመዱትን ደግሞ ይሰብራል። የነገው የበለጸጉ ሀገራት ዝርዝር ማለት፣ የሚቀጥሉትን አብዮቶች መላመድ የቻሉና ራሳቸውን በለውጡ ውስጥ ያሸጋገሩ ሀገራት ዝርዝር ነው።
የመደመር መንግስት
ገፅ 133
Ethiopian Broadcasting Corporation #digitalethiopia #የመረጃ_ሉዓላዊነት #data #ኢትዮጵያ

የመረጃ ሉዐላዊነትን ማረጋገጥ
*****
በዲጂታሉ ዓለም የሀገርን ሉዐላዊነት እንዴት እናስጠብቅ?
መልሱን በተከታዩ ሊንክ ያገኙታል - https://youtu.be/ocGZX5Vv-...
#ኢትዮጵያ #የዲጂታል_ድንበር #የመረጃ_ሉዓላዊነት #ቴክኖሎጂ #ሳይበር_ደህንነት #ኃይል_ሽግግር #datasovereignty #digitalfrontier #cybersecurity #digitalethiopia #techrevolution #ebcworld
5 months ago
የልማት አስተዳደር ሪፎርሙ ፖሊሲዎች በተናበበ መንገድ እንዲዘጋጁ አስችሏል - የፕላንና ልማት ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገችው የተቀናጀ የልማት አስተዳደር ሪፎርም የተለያዩ ፖሊሲዎች በተናበበ መንገድ እንዲዘጋጁ አስችሏል አለ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፡፡
“የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በሚል መሪ ሐሳብ ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ባስመዘገበችው ስኬት ላይ ያተኮረ ሀገራዊ ጉባኤ ተካሂዷል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በረከት ፍስሃጽዮን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በሀገር ደረጃ የሚታቀዱ እቅዶች እስከታችኛው የአስተዳደር እርከን ድረስ የሚወርዱበት አሰራርና ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል፡፡
ባለፉት ጊዜያት ለእቅድ፣ ክትትልና ግምገማ የሚሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ እንደነበር አስታውሰው፥ በዚህም የሀብትና የሰው ኃይል አመዳደብ ችግር እንደነበረበት ጠቅሰዋል፡፡
የአካባቢ አስተዳደሮች ሚናቸው በግልጽ ያልተለየ በመሆኑ በየደረጃው ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ አሰራር አልነበረም ነው ያሉት፡፡
ከይፋዊ ስታቲስቲክስ ባለፈ የእቅድና ግምገማ ሂደቱ እንዲሁም መረጃዎች በአግባቡ የሚያልፉ ባለመሆናቸው ሀሰተኛና የተጋነኑ ሪፖርቶች ለመንግስት ሲቀርቡ ነበር ብለዋል፡፡
እቅድ እና ፋይናንስ ያልተሳሰረበት አሰራርና በዘፈቀደ የሚከናወን የፕሮጀክት አተገባበር ሀገሪቱን ለማክሮ ኢኮኖሚ መናጋት ዳርገው እንደነበር አንስተዋል፡፡
ባለፉት የለውጥ አመታት በፖሊሲ ሪፎርም እንዲሁም በእቅድና ክትትል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው፥ በዚህም ችግሮቹን በተቀናጀ የልማት አስተዳደር መፍታት መቻሉን አስረድተዋል፡፡
የመንግስትን የውሳኔ አሰጣጥ በተጨባጭ መረጃ መደገፍና ዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር በቀጣይ በትኩረት የሚሰራባቸው መስኮች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በአቤል ነዋይ

Sponsored by
Surafel
5 months ago
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብዱልአዚዝ ሸፋ፤ ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በተሰኘው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ የሰጡት ማብራሪያ
5 months ago
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በተሰኘው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ለሚመዘገበው ዕድገት መሠረት የሚሆን የሉዓላዊ ዲጂታል መሠረተ ልማት እየገነባች መሆኗን ገልጸዋል።
#artificialintelligence #digitalethiopia2030 #ethiopiantechnology #datasovereignty
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

የዳታ አያያዝን ለማዘመን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚና ከፍተኛ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዳታ አያያዝን ለማዘመን የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ሚና ከፍተኛ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በሚል መሪ ሀሳብ ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ባስመዘገበችው ስኬት ላይ ያተኮረ ሀገራዊ ጉባኤ ተካሂዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ እንዳሉት፤ የዳታ አያያዝን ለማዘመንና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደትን ለማሳለጥ ቴክኖሎጂ በተለይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚናው ከፍተኛ ነው።
በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂዎች እርስ በርስ እየተቀናጁ በመምጣታቸው ነጣጥሎ ማየት የማይቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን ተናግረዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ከ60 እስከ 80 በመቶ የሚሆነውን ስራ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ታግዞ ማከናወኑን ጠቁመዋል።
ስታቲስቲክስን፣ ግብርናንና ጤናን ከቴክኖሎጂ ውጭ ማሰብ ወደማይቻልበት ደረጃ መደረሱን ጠቅሰው፤ እያንዳንዱ ተቋም ቴክኖሎጂን በብቃት መጠቀም ሲችል የመረጃ ጥራት፣ ስፋትና ተደራሽነት እንደሚያድግ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ጠንካራ ስራ ሲሰሩ ከቆዩ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አንዱ መሆኑን አንስተው፤ ተቋሙ አሁን የደረሰበት የዲጂታላይዜሽን ደረጃ ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት የመረጃ ሰብሳቢዎችን የመገኛ ቦታ በአይፓድ በመከታተል፣ መረጃው በተቀመጠለት ጊዜ በመሰብሰብ እና ማንኛውንም እንከን በራሱ በሲስተሙ በመታገዝ ማረም የሚያስችል የዳታ ማረጋገጫ ስርዓት በመዘርጋት መሰራቱ በእጅጉ አጋዥ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ዳታና ወርቅ እኩል ዋጋ እንዳላቸው በማመን በፖሊሲ፣ በሕግ እና በእውቀት የሚመራ ማንኛውም ሀገርና መንግሥት ብልፅግናን ማረጋገጡ የማይቀር መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
እያንዳንዱ ህግ፣ ፖሊሲና የስራ መዘርዝር በዳታና በእውቀት ላይ ተንተርሶ እንዲሰራ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በዳታ ሉዓላዊነት ዙሪያ የተከናወኑ ስራዎች የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ሊያገለግሉ ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዳታ ሉዓላዊነት ዙሪያ የተከናወኑ ስራዎች የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለመለወጥ ሊያገለግሉ ይገባል አሉ።
''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በሚል መሪ ሀሳብ ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ባስመዘገበችው ስኬት ላይ ያተኮረ ሀገራዊ ጉባኤ ተካሂዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመድረኩ ላይ፤ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በሳተላይት፣ በድሮንና በጂኦስፓሻል መረጃ የታገዘ ዘመናዊ አሰራርን መዘርጋቱ ለመላው ኢትዮጵያውያን ታላቅ ድል ነው ብለዋል።
በርካታ ሺህ ሰዎችን በማሰማራት የተሰበሰቡ መረጃዎችና ጥቅም ላይ የዋሉ ሳይንሳዊ ዘዴዎች ለሀገሪቱ ቀጣይ እድገትና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል።
በጥቂት ሀገራት ብቻ የሚታየውን የመረጃ አሰባሰብ፣ የትንተና እና የአቀራረብ ዘዴ በሀገር በቀል ባለሙያዎች ማየት መቻሉ ትልቅ የኩራት ምንጭ መሆኑንም ነው የገልጹት።
በመረጃ አሰባሰብ ሂደት ውስጥ በመስክ ላይ የሚሰበሰብ ተጨባጭ መረጃ የላቀ ዋጋ እንዳለው በማንሳት፤ የተሰበሰበው ዳታ በፖሊሲ ተደግፎና አመራር ተሰጥቶት ወደ ተጨባጭ ውጤት መሸጋገር ይገባዋል ነው ያሉት።
የተሰበሰበው ዳታ የመጨረሻ ግብ የእያንዳንዱን ሰው ህይወት መንካት፣ ማሻሻል እና ውጤት ማምጣት እንደሆነ ጠቅሰው፤ የሰው ህይወት መለወጡን ማረጋገጥ እንደሚገባ አመልክተዋል።
አርሶ አደሩ ከማምረት ባለፈ ልጆቹን ሲያስተምር፣ ህጻናት በምግብ እጥረት እንዳይጎዱ ሲደረግ እንዲሁም ይህንኑ እንደ ሀገራዊ ኢንቨስትመንት የሚገነዘቡ ዜጎች ሲበራከቱ መረጃው እውነተኛ ፋይዳውን አገኘ ማለት እንደሆነም አብራርተዋል።

መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ በመገኘት፣ ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል እና በዘርፉ የታየውን እመርታ ተመልክተው አድንቀዋል፡።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላፉት መልዕክት፤መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻትን ማሳካት ስለማያስችል የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት እንደሆነ አስገንዝበዋል።
አክለውም የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራው በሀገር ልጆች እውቀትና ክህሎት ሲከወን ማየት ታላቅ ሀገራዊ ኩራት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ወደፊትም የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦች ላይ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
#datasovereignty #policyindependence #ethiopia #pmabiyahmed #ethiopianbroadcastingcorporation

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት "የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት" በሚል መሪ ሀሳብ ሀገራዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
******************
"የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ከፍተኛ ሀገራዊ ጉባኤ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።
ኢትዮጵያ የልማት ትልሞቿን እንዲሁም ያመዘገበቻቸውን ስኬቶች በመረጃ እና በአሃዛዊ ማስረጃዎች አስደግፋ መሰነድ ከጀመረች መሰነባበቷን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ይህ የተወሰደው ስልታዊ እርምጃ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በሌሎች አካላት በሚደገፉና በተበታተኑ የመረጃ ቋቶች ላይ የነበራትን ሙሉ ጥገኝነት ለመቅረፍ ያሳየችውን ከፍተኛ ቁርጠኝነት ማረጋገጫ መሆኑም ነው የተገለጸው።
ይህ አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ የሀገራችንን የመረጃ ሉዓላዊነት በተግባር በማረጋገጥ ረገድ የላቀ ሚና ያለው ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በራሷ ተዓማኒ መረጃ ላይ ብቻ ተመስርታ ውሳኔዎችን እንድታሳልፍና የራሷን የልማት መስመር በነፃነት እንድትተልም አስችሏታል።
በዚህም መሠረት በዛሬው ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ልማትና የመረጃ ሉዓላዊነት ጉዞ ያመጣቸው አበይት ስኬቶች እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫዎች በጥልቀት እንደሚዳሰሱ ተጠቁሟል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #pmabiyahmed #datasovereignty #policyindependence #ethiopiastatics

1 year ago
"አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የራሷን የመረጃ ሉዓላዊነት ሊኖራት ይገባል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የራሷን የመረጃ ሉዓላዊነት ሊኖራት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት፤ ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤን በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በከፈቱበት ወቅት ነው።
በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የቀጣናውና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ "የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናን ለመቋቋም ከጎደለን ሳይሆን ካለን መጀመር አለብን" ብለዋል።
ከዚህ አኳያ አፍሪካ በርካታ የወጣቶች ቁጥር፣ መልማት የሚችል መሬት እንዲሁም ለታዳሽ ሃይል የሚሆን በርካታ አቅም እንዳላት ተናግረዋል።
"በመሆኑም እዚህ የተገኘነው የዓለምን የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ ለመቀየስ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አፍሪካ ሥነ ምህዳሯን ሳትጎዳ ማደግ እንደምትችል አብራርተዋል።
አፍሪካ የአየር ንብረት ተጠቂ ብቻ ሳትሆን የመፍትሄውም አህጉር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተውበታል፡፡
"አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ የምትሻው እርዳታ ሳይሆን የጋራ ኢንቨስትመንት ነው" ያሉም ሲሆን፤ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ፋይዳው ጉልህ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም ከአየር ንብረት ርዳታ ወደ አየር ንብረት ኢንቨስትመንት ለውጥ ሊደረግ እንደሚገባ በመግለጽ፤ Climate Innovation Compact የተሠኘ በ2030 1000 አፍሪካ መር መፍትሔዎች የሚገኙበትን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።
አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ዋነኛዋ መፍትሄ አመንጪ መሆን እንዳለባት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የራሷን የመረጃ ሉዓላዊነት ሊኖራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአህጉሪቷ ዩኒቨርሲቲዎችና ተመራማሪዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈና ለአየር ንብረት ለውጥ የተደራጀ መፍትሄ የሚያቀርብ ማዕቀፍ እንዲቋቋም ሃሳብ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ ከ7 ዓመት በፊት በጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከሏን ጠቁመዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከባቢን ከመጠበቅ ባሻገር የተጎዱ ከባቢዎች እንዲያገግሙ፣ ለምግብ ዋስትና እና ለስራ እድል ፈጠራ ትልቅ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ችግር መፍትሄ ጋር የተጣጣመ የመስኖ ልማት በማካሄድም በስንዴ ምርት ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቷን አብራርተዋል።
በቅርቡ የሚመረቀው ታላቁ የሕዳሴ ግድብም ከ5 ሺሕ ዋት በላይ ታዳሽ ሃይል በማመንጨት ኢትዮጵያንና ቀጠናውን በሃይል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በተጨማሪም አፍሪካ በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ዋስትና እና የሥነ ምኅዳር ጥበቃ የመምራት አቅሟንም በማጽናት አንስተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የCOP32 ጉባኤን ለማስተናገድ ያላትን ጥያቄም አቅርበዋል።
ENA

Comments