2 months ago
የመምህር ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የ፵ ቀን መታሰቢያ ጥሪ 🕯️
"የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው!" (ምሳሌ ፲፥፯)
በሕይወትና በቃል ትምህርታቸው ብዙዎችን ወደ ብርሃን የመለሱት የተወደዱት መምህራችን መምህር ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) ካረፉ ፵ ቀናት ተቆጠሩ።
የመታሰቢያው ቀን፦ ረቡዕ ሚያዝያ ፯ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም.
ለመጨረሻ ጊዜ የስብከት አገልግሎት በሰጡበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
የሥነ-ሥርዓቱ ዝርዝር፦
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ እንዲሁም በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በጸሎተ ፍትሐት ይታሰባል።
ከጸሎተ ፍትሐቱ በኋላ መምህሩን በዝማሬ እንደሸኘናቸው ሁሉ፣ በአንድነት እየዘመርን በካቴድራሉ አዳራሽና በተዘጋጀው ድንኳን ለመታሰቢያቸው የተዘጋጀውን ጸበል ጸዲቅ እንድንቀምስ ቤተሰቦቻቸው በአክብሮት ጥሪ አቅርበዋል።
የመምህራችን የወልደ ሰማዕት የአገልግሎት ጸጋና በረከት ይደርብን። ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።
#getu #memherzelalem #woldesemaet #orthodoxtewahedo #memorial #addisababa #ethiopia #spirituallife #trinitycathedral #መምህርዘላለምወንድሙ #ወልደሰማዕት #መታሰቢያ #ኦርቶዶክስ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

3 months ago
🕯️ የመምህር ዘለዓለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የሽኝት መርሐ-ግብር
በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የሚከናወነው የታዋቂው መምህር ዘለዓለም ወንድሙ የአስክሬን ሽኝት መርሐ-ግብር ዝርዝር ይፋ ሆኗል። መርሐ-ግብሩ ከዛሬ እሑድ ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ድረስ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ይከናወናል።
የጊዜ ሰሌዳ (ዋሽንግተን ዲሲ)
፩. እሑድ የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም (March 8, 2026)
ጸሎተ ፍትሐት፦ በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ይከናወናል።
የሀዘን መግለጫ፦
ከቅዳሴ በኋላ በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የላይኛው መኪና ማቆሚያ ላይ አገልጋዮችና ምእመናን ተሰብስበው ሀዘናቸውን ይገልጻሉ።
፪. ሰኞ የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም (March 9, 2026)
ለቅሶ መድረሻ፦ ከቀኑ 6:00 (12pm) - 10:00 (4pm) ሰዓት በላይኛው ትራቨለር ለቅሶ መድረስ ለሚፈልጉ ክፍት ይሆናል።
የሠርክ ጸሎት፦ ከቀኑ 10:30 (4:30pm) - 1:30 (7:30pm) በትምህርተ ወንጌልና በውዳሴ ማርያም መዝከር ይከናወናል።
ወደ ቤተክርስቲያን መግባት፦ ከምሽቱ 1:00 (7pm) ክቡር አስከሬኑ ወደ ቤተክርስቲያን ይገባል።
የሌሊት ማህሌት፦ ከሌሊቱ 7:00 (1am) ጀምሮ አገልጋዮችና ምእመናን ሰዓታት ቆመው ያድራሉ።
፫. ማክሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም (March 10, 2026)
ጸሎተ ፍትሐት፦ ከጠዋቱ 3:00 (9am) - 6:00 (12pm) ይከናወናል።
ምስክርነት፦ ከቀኑ 6:00 (12pm) ጀምሮ የሕይወት ታሪክና የወዳጅ ዘመድ ምስክርነት ይሰጣል።
ትምህርተ ወንጌልና ቡራኬ፦ በፓትርያርኩ አጭር ትምህርተ ወንጌል እንዲሁም በብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ይሰጣል።
ሽኝት፦ ከሥነ-ሥርዓቱ በኋላ ክቡር አስከሬኑ ወደ ትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ሽኝት ይደረግለታል።
⚠️ ጠቃሚ ማሳሰቢያዎች
የአለባበስ ሥርዓት፦
በፍትሐቱና በሽኝቱ ላይ የሚገኙ አገልጋዮችና ምእመናን በሙሉ ነጭ ልብስ ለብሰው እንዲገኙ በአክብሮት ተጠይቀዋል።
አድራሻ፦
1350 Buchanan St. NW, Washington, D.C 20011
"ኦ እግዚኦ አእርፍ ለነፍሰ ገብረከ ወልደ ሰማዕት!"
(አቤቱ የባሪያህን የወልደ ሰማዕትን ነፍስ አሳርፍ!)
የመምህራችንን ነፍስ ከቅዱሳን ጋር ይደምርልን፤ ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹም መፅናናትን ይስጥልን።
#መምህርዘለዓለምወንድሙ #ወልደሰማዕት #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ #ዋሽንግተንዲሲ #ሽኝት #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን