5 months ago
ሩጫ ለጤና
የክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የካንሰር ህሙማን ማዕከል ጉብኝት
#ethiopia | ነገ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ አስመልክቶ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘውን የካንሰር ህሙማን ማዕከል ጎብኝተዋል።
ዓላማ፦ "AKTIVE AGAINST CANCER" የተሰኘው ንቅናቄ በሩጫ ውድድሩ አማካኝነት ሴቶች የካንሰር ህመምን ቀድሞ ለመከላከልና ጤናቸውን ለመጠበቅ እንዲተጉ ግንዛቤ መፍጠር ነው።
ዶክተር ኤርጎጌ እንዲህ ያሉ ትብብሮች ለኢትዮጵያ ሴቶች ትልቅ ትርጉም እንዳላቸው ገልጸው፣ ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ሴቶችን የሚያበረታታ መድረክ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ካንሰርን ለመከላከልና ለማገገም ያለውን ጠቀሜታ ለማስተዋወቅ ከአክቲቭ አጌንስት ካንሰር ጋር ለአራት ዓመታት የሚቆይ ስምምነት መፈራረሙ ተገልጿል።
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ለካንሰር ማዕከሉ ላደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል።
ለ23ኛ ጊዜ የሚከናወነው የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ፣ ነገ መነሻና መድረሻውን ቦሌ አትላስ በማድረግ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
ሩጫው ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባለፈ ለጤናና ለግንዛቤ ያለውን ፋይዳ ለመጋራት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
#getu #ethiopia #womenempowerment #cancerawareness #safaricom #greatethiopianrun #health #addisababa #ቅድሚያለሴቶች #ካንሰርንእንከላከል #ታላቁሩጫ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments