6 months ago
አማን ፍስሐፂዮን በአብሮ አደጎች ዕይታ
( ከዕዝራ እጅጉ)
#አማን በዳንኤል አሰፋ ዕይታ
#ethiopia | እኔ አማንን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ በSandford English School አውቀዋለሁ። በዚያን ጊዜ ቅርብ ጓደኞች ነበርን፤ “Fantastic 5” ተብሎ የሚጠራ የልጅነት ቡድን ነበረን፣ እናም ቃሉን በብር ቀለም በእጆቻችን ላይ በኩራት እንፅፍ ነበር። እርሱ ቀድሞ ወደ አሜሪካ ሄደ፣ ነገር ግን ከሃይስኩል በኋላ በፔንሲልቬኒያ እንደገና ተገናኘን።
ኮሌጅ ሳለ ክብደት ያነሳ ስለነበር በጣም ጡንቻማ ሆኖ ያገኘሁትን ጊዜ አልረሳውም።
እርሱና ወንድሞቹ የኬብል ሥራ ንግድ ጀምረው ነበረ። ይህም ጥሩ ሁኖላቸው ነበር።። ነገር ግን ልቡ ሁልጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደሚፈልግ ይነግረኝ ነበር።
በእርግጥም ያንን አደረገ፤ ተመልሶም EBS የቲቪ ጣቢያን ጀመረ። ሁሉንም ችግሮች ተጋፍጦ ኢቢኤስ ለቁምነገር አበቃው። ሲያጋጥመው የነበረውን ጽናቱን እጅግ አደንቃለሁ።
ለእኔ ደስ የሚል ነገር ሁልጊዜ ከወደቀ በኃላ ዳግመኛ ተነስቶ ከቀድሞው ይልቅ ይበልጥ ስኬታማ መሆኑ ነበር።
በህመሙ ጊዜ ጥቂት ጊዜያት ጎበኘሁት፤ ሁልጊዜ አዎንታዊ፣ ተስፋ ያለው እና ጽኑ ፍላጎት ያለው ነበር — እውነተኛ ድንቅ ሰው! መጨረሻ ያየሁት በአዲስ አበባ በተካሄደው “Celebration of Life” ፓርቲው ላይ ነበር።
መጨረሻ በስልክ ያነጋገርኩት በጥቅምት ወር ነበር፣ በታኅሣሥም ልናገኘው ተዘጋጅተን ነበር፤ ነገር ግን ሞት ቀደመው።
#አማን በሔኖክ አስመሮም ዕይታ
እኔ ሁልጊዜ የአማንን ፈገግታና የልቡን ቸርነት አስታውሰዋለሁ። እርሱ ቁርጠኛና ትልቅ ራዕይ ያለው ሰው ነበር፤ በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ደስ ለማሰኘት የተፈጠረ የልዩ ስጦታ ባለቤት ነበር።
ትውውቃችን በሳንፎርድ ከስድስተኛ ክፍል ጀመረ። እስካሁንም ያ ትዝታ በአእምሮዬ አለ። ወደ ፓርቲ ለመሄድ ወይም በቦሌ ሚኒ በርገር ለመብላት እንድንሄድ የቤተሰቡን ፒክአፕ መኪና ከቤቱ በጸጥታ እየገፋን ስንወጣ የነበረውን ሳስብ እስቃለሁ። አማን ደፋርና እና እጅግ ታማኝ ነበር።
ለአገሩ ያለው ፍቅር የማይካድ ነበር፤ በፔን ስቴት በርቀት ሲኖርም ኢትዮጵያ ሁልጊዜ በሐሳቡ ውስጥ ነበረች። ወደ አገሩ ለመመለስ በጣም ይመኝ ነበር—እናም ተመለሰ።
አማን ታላቅ ሰው፣ እውነተኛ ጓደኛና ወንድም ነበር። እጅግ ይናፍቃል። ነፍሱን ይማር!!!!
#አማንም በሰፈር አብሮ አደጎቹም የተወደደ ነበር
ፋሲል አለማየሁ ከአማን በ4 አመት ቢያንስም እነ አማን ቤት እየሄደ እንደ እኩያ ጓደኛ ይጫወት እንደነበር ያስታውሳል። አማን ታናናሾቹን በመንከባከብ እና ደስ ብሏቸው እንዲጫወቱ በማድረግ ትልቅ ሚና ነበረው። " በጣም የምወደው ልጅ ነበር። በጣም የሚያማምሩ ኮርስ ሳይክሎች ነበሩት። ቤታቸው 1,000 ካሬ ሜትርና ባለ አራት መኝታ ቤት ነው። ግቢው ሙሉ አስፋልት ሲሆን ለእኛ ለመጫወት ምቹም ነበር። ታዲያ አማን በጊዜው በዲኤክስ መኪና ይዞን ያንሸራሽረን እንደነበር ትዝ ይለኛል።" በማለት ፋሲል ትዝታውን አውግቶናል።
ፋሲል የልጅነት አብሮ አደጉ አማን ያደረገለትን ውለታ እንዲህ በማለት ያስታውሳል፦" አንድ ጊዜ የአባቴን መኪና በልጅነቴ ሰፈር ውስጥ ስነዳ ድንገት መኪናዋ ከፊት አካባቢ ተጋጨች። ይህን የሰማው አማን አባቴ ሳይሰማ መኪናውን ጋራዥ ወስዶ ከአባቴ ቁጣ እንድድን አድርጎኛል።" በማለት የአማንን ለችግር ደራሽነት ነግሮናል ።
አሁን ላሊበላ ሆቴል ያለበት ጋር ከእነ አማን ጋር ኳስ ይጫወት እንደነበር ፋሲል ያስታውሳል። አማን በ1980 ግድም የሀይስኩል ተማሪ ሳለ ወደ አሜሪካ ማቅናቱን ፋሲል ይናገራል። አማን ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ከአሜሪካ ሲመጣ ከፋሲል ጋር ተገናኝተው ነበር። ፋሲል በአማን እረፍት ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማው ነግሮናል። "ከረጅም ጊዜ በኃላ ሳላየው ፣ ነገ ዛሬ አገኘዋለሁ እያልኹ በማረፉ አዝኛለሁ " ብሎናል።
#ቀፀላወርቅ ሰይፉ ስለ አማን
ቀፀላወርቅ ሰይፉ የአንጋፋዋ ጋዜጠኛ የወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ልጅ ስትሆን የተማረችው ሳንፎርድ ነው። አማንን በትንሽ ክፍል ብትበልጠውም ( ሲኒየሩ ብትሆንም- እርሱ ግን ከረጅም ጊዜ በኃላ ሳንፎርድ ተምረናል ብሎ አስታውሶ ሰላምታ እንዳቀረበላት ታስታውሳለች።
ቀፀላወርቅ ሰይፉ አማን ከቅርቦቹ ጋር ሆኖ ኢቢኤስን የጀመረ ሰሞን አግኝታው እንደነበር ትናገራለች። በአፍሪካ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አየር ላይ ለማዋሀል አጭር የተነደፈ ዕቅድ አዘጋጂ ብሏት እንደነበር ትዝ ይላታል። ቀፀላ በራሷ ምክንያት የዛን ጊዜውን እቅድ ተግባራዊ ባታደርገውም የዛሬ አመት 2017 ግድም ድጋሚ ሥራውን ለመጀመር ከአማን ጋር ጭውውት አድርጋ ነበር።
"...ከአማን ጋር በፕሮግራሙ ዙሪያ ከ 2 ሰዓት በላይ ተነጋግረናል። በሚድያ ላይ ያለው እውቀት ምን ያህል የዳበረ እንደሆነ ግንዛቤ አግኝቻለሁ።የህመም ስሜት እንዳለው ያጫውተኝ ነበር። በዕውነቱ የአማን ህልፈት ለኢትዮጵያ ትልቅ እጦት ነው" በማለት ቀፀላ ምስክርነት ሰጥታለች ።
#ዮናስ ማህረነ ስለ አማን
ዮናስ ማህረነ ከአማን ጋር ሳንፎርድ ከተማሩ ጓደኞቹ አንዱ ነው። ምስክርቱን እንደሚከተለው ሰጥቶናል፦
"........አማን ጨዋታ የሚችል እና ደግ ነበር። ኳስ እንጫወት ነበር። እኔ በረኛ ነበርኩ። አማን መሀል ነው። 1992 በፈረንጆች አቆጣጠር ላይ ከብዙ ጊዜ በኃላ አገኘሁት። 'ሞንክ 'ብሎ በትምህርት ቤት የቅፅል ስሜ ጮሆ ጠራኝ። በጊዜው ክብደት ያነሳ ስለነበር ወፍሮ ጠበቀኝ። 2004 እ.ኤ.አ አሜሪካ አብረን የተማርን አብሮ አደጎቹ ቤቱ ሄደን ጠየቅነው። አማን ከእኛ ቡድን የሚለየው ቢዝነስ ላይ ጥሩ ነበር። የሥራ የመፍጠር ክህሎት ነበረው።አሜሪካ ሳለ calling card ቢዝነስ ነበረው። የማስደወል ቢዝነስ ይሠራ ነበር። ወንድማችን አማን ከድሮም ደግነትን የተላበሰ ወንድማችን ነበር። መሞቱን ግሩም ነው የነገረኝ። ህዳር ላይ ሆስፒታል ሄደን ልንጠይቀው ነበር። ነገር ግን ማለፉ ሲሰማ ጥልቅ ሀዘን ነው የተሰማኝ።" በማለት ዮናስ ማህረነ ከአሜሪካ ሆኖ ምስክርነት ሰጥቷል።
የእነ አማን ሰፈር
አማን ከአንደኛ ክፍል እስከ 7ኛ ማለትም ከ1970-1977 የተማረው ሳንፎርድ ትምህርት ቤት ሲሆን ለቤቱም የመጨረሻ ልጅ ነው። ከ8ኛ ክፍል በኃላ የሁለተኛ ደረጃ እና የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን በአሜሪካን አገር ነበር የተከታተለው።የዛን ጊዜ ቤታቸው ቀበሌ 20 አሁን ስካይላይት ጀርባ የቻይና ኤምባሲ ያለበት የእነ አማን ቤት ነበር። የአማን አባት አቶ ፍስሐፂዮን ገብረህይወት 'ባድራግ' የተሰኘ ጎማ አስመጪ ነበሩ። ደርግም ለተወሰኑ ዓመታት ለእስር ዳርጓቸው ነበር። የቤቱ የመጨረሻ ልጅ አማን ሰፈር ኳስ በመጫወት ያሳልፍ እንደነበር አብረውት ያደጉ ልጆችን በማነጋገር ማረጋገጥ ችለናል።
#አማን በሳንፎርድ
በአንድ ክፍል ውስጥ 20 ልጆች ብቻ የሚማሩበት ሳንፎርድ በዚያን ጊዜ በዓመት 4,000 ብር ለአንድ ልጅ የሚከፈልበት ተማሪ ቤት ሲሆን የትምህርት ሥርዓቱም ዓለምአቀፍ ደረጃ በመሆኑ ተማሪዎች በጥራት እንዲማሩ ይደረጋል። ግሩም ፋንቱ ሳንፎርድ ከአማን ጋር አብሮ ተምሯል።ግሩም ለዚህ የሕይወት ታሪክ አዘጋጅ እንዳጫወተው አማን ከልጅነት ጀምሮ ቀናነት የተላበሰ እና በወጉ በጥሩ ሁኔታ ያደገ ልጅ ባህሪይ ያሳይ እንደነበር ተናግሯል።
"...አማን ጋር ኤለመንተሪ ስንማር ይህን ቀናነቱን እና ከሰው ጋር ያለውን ተግባቢነት አስተውል ነበር። በኃላ ካደግን በኃላ ኒዮርክ ፊላደልፊያ አግኝቼው የድሮ ተግባቢነቱ ሳይቀየር አነኘሁ" ብሎናል።
"አማን ሳንፎርድ ሳለን የቅርጫት ኳስም ይጫወት ነበር። ተግባቢነቱ እዚህም ላይ ነበር። አብረውን ከተማሩት መካከል የእኛ ሁለት ዓመት ሲኒየር ብትሆንም ቀፀላወርቅ ሰይፉ፣ ያሲር ባገርሽ የሚጠቀሱ ናቸው። ያኔ አብረን ጓደኛሞች የነበርነው እኔ( ግሩም ፋንቱ)፣ ሔኖክ አስመሮም፣ኢክረም ሰኢድ፣ ዳንኤል አሰፋ፣ዮሐንስ ማህረነ፣ነበርን።ኢክረም ሰኢድ (አርፏል) እና አማን በሁላችንም የሚወደድ ልጅ ነበር። አለባበሱም ምርጥ ነበር። ካደገም በኃላ አለባበስ ላይ ጥሩ ነው። አማን የቤቱ መጨረሻ ሲሆን እህት ወንድሞቹ ቀድመው ነበር ውጭ የሄዱት። "በማለት ግሩም ምስክርነቱን ሰጥቶናል።
#ከአማን ጋር ሳንፎርድ አብራ የተማረችው ሀናን አብደላ ስለ አማን ስትናገር ገና 4ኛ ክፍል ሳለ ያለውን የአእምሮ ብስለት ወይሞ imotional intelligence ታደንቃለች። በልጅነቱ አማን ምንም ነገር ቢያጋጥመው ስሜት የመቆጣጠር ችሎታው ትልቅ እንደነበር አስታውሳለሁ ስትልም ወደ ኃላ መለስ ብላ ታስታውሳለች።
"....አማን በጣም የምናከብረው ወንድማችን ነው። ከብዙ ጊዜ በኃላ ሲያገኘኝ ሀናን ረሳሽኝ እንዴ ብሎ እንደ ልጅነታችን ሰላምታ የሚሰጠኝ አብሮ አደጌ ነው። አንዳንድ ሰው አብረኸው ተምረህ እያየህ ዝም ሊልህ ይችላል አማን ግን እንደዚያ አይደለም። እሱን በማጣታችን እጅግ አዝነናል።" በማለት ሀናን ምስክርነት ሰጥታለች።

የራዕይ ሰው ስንብት፡ አማን ፍስሃጽዮን እና ያልተጨረሰው የዲጂታል ድልድይ
በአንድ ወቅት ታዋቂው ደራሲ ጋብርኤል ጋርሲያ ማርኬዝ "ሰው መሞት በሚገባው ጊዜ ሳይሆን መሞት በሚችልበት ጊዜ ነው የሚሞተው" ብሎ ነበር። ይህ አባባል ለአማን ፍስሃጽዮን እጅግ ይቀርባል። አማን መሞት የሚገባው ሰው አልነበረም፤ ገና ብዙ የሚያልማቸው ህልሞች፣ ሊገነባቸው ያሰባቸው የሚዲያ መንደሮችና ሊያሻግራቸው ያቀዳቸው ወጣቶች ነበሩ።
ነገር ግን በ 54 አመቱ፣ የካንሰር ህመም በደካማው ስጋው ላይ በርትቶበት፣ በስተመጨረሻ በሄደበት አሜሪካ በዝምታ አሸለበ። ይህ ፅሁፍ የአንድን ሰው ሞት ብቻ ሳይሆን፣ የአንድን ትልቅ ራዕይ ጊዜያዊ መቆም የሚተርክ ልብ አንጠልጣይ ስንብት ነው።
አማን ለሦስት ዓመታት ያህል ከካንሰር ጋር ሲታገል ቆይቷል። ህመሙ አንዴ ሻል እያለው ተስፋ ሲሰጠው፣ መልሶ ደግሞ ክፉኛ እያመመው ሲያሰቃየው ነበር። ህመም እንደ ውቅያኖስ ማዕበል ነው፤ ሲመጣ ሁሉንም ይዞ ይሄዳል፣ ሲመለስ ግን ባዶነትን ጥሎ ይከንፋል። አማን የመጨረሻው ሰዓት መቃረቡን በተረዳ ጊዜ፣ ለአንድ የቅርብ የሥራ ባልደረባው እንዲህ ብሎ ነበር፡- "የምድን አይመስለኝም... ኢትዮጵያ ውስጥ መሞት እፈልጋለሁ።" ይህ ቃል በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ያለውን የትውልድ ሀገር ፍቅርና ናፍቆት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። "ባለፈው ሰኞ እመጣለሁ" ብሎ የገባው ቃል ግን፣ በአካላዊ ጉዞ ሳይሆን በነፍስ ሽኝት ተተካ።
የኢቢኤስ (EBS) ሰራተኞች አለቃቸው እንደማይመጣ አላሰቡም ነበር። ለእነሱ አማን ማለት የማይበገር ተራራ፣ በማንኛውም ማዕበል ውስጥ የማይናወጥ መሪ ነበር። አሜሪካ ለህክምና በተመላለሰ ቁጥር "ይመለሳል" የሚለው ተስፋቸው ፀንቶ ነበር። ቪክቶር ሁጎ "ሞት ማለት መጥፋት ሳይሆን ወደ ሌላ ክፍል መሸጋገር ነው" እንደሚለው ሁሉ፣ አማንም ወደ ሌላው ዓለም ሲሸጋገር በቢሮዎቹ ውስጥ የቀረው ባዶነት ግን የሚሞላ አልነበረም። ሰራተኞቹ ሰኞን የጠበቁት በአካል ሊቀበሉት እንጂ በሀዘን መግለጫ ሊሸኙት አልነበረም።
የአማን ታሪክ ሲነሳ የግዴታ ሌላውን የዓለም ክፍል ማስታወስ ይገባል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካዊው የሚዲያ ንጉስ ጆሴፍ ፑሊትዘር ጋዜጠኝነትን ለህዝብ ቅርብ ለማድረግ የታገለው ትግል ከአማን ጋር ይመሳሰላል።
አማንም በ2008 በሜሪላንድ ሲልቨር ስፕሪንግ EBSን ሲመሰርት፣ ዓላማው ዳያስፖራውን ከሀገር ቤት ጋር ማገናኘት ብቻ አልነበረም፤ የኢትዮጵያን ሚዲያ ዘመናዊ ማድረግም እንጂ። ልክ እንደ ፑሊትዘር ሁሉ አማንም በስራው ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን (መዝናኛ ብቻ ነው፣ ከውጭ የተቀዳ ነው የሚሉትን) በዝምታና በስራ ነበር የሚመልሰው። እሱ የሚያየው ከትችቱ ባሻገር ያለውን ትልቅ ምስል ነበር።
አማን ፍስሃጽዮን ሚዲያን እንደ ተራ መዝናኛ ሳይሆን እንደ "ኢንዱስትሪ" የተመለከተ ቀዳሚ ሰው ነው። በኢትዮጵያ አንድ ለእናቱ በነበረው ኢቲቪ (ETV) ዘመን፣ አማን የሳተላይት ቴሌቪዥን ባህልን ቀይሯል። ሰይፉ በኢቢኤስ፣ አስፋው፣ ነፃነት እና የጠፉ ቤተሰቦችን ፍለጋ ያሉ ፕሮግራሞች በኢትዮጵያውያን ሳሎን ውስጥ አዲስ ንፋስ ነፈሱ። እሱ በHD ጥራት ማሰራጨት ሲጀምር፣ ብዙዎች "ይህ ለኢትዮጵያ ገና ነው" ይሉ ነበር። እሱ ግን "ኢትዮጵያ ለጥራት ዝግጁ ነች" ብሎ ያምን ነበር። ጆርጅ በርናርድ ሾው "አንዳንዶች ነገሮችን ባሉበት ያዩና 'ለምን?' ይላሉ፤ እኔ ግን የሌሉ ነገሮችን አልምና 'ለምን አይሆንም?' እላለሁ" እንዳለው፣ አማንም "ለምን አይሆንም" ባይ ነበር።
በህይወቱ የመጨረሻ ቀናት አማን ስለ ሀገሩ ያለው ጭንቀት ከህመሙ በላይ ነበር። የኢትዮጵያ ቢዝነስ ሪቪው (EBR) እንደገለጸው፣ አማን የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር ሰብሳቢ ሆኖ ሲያገለግል ለግል ሚዲያዎች ነፃነትና ዕድገት ተሟግቷል። የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የሳተላይት ክፍያና የህግ ማዕቀፎች እንቅፋት ቢሆኑበትም፣ እሱ ግን ሁልጊዜም መፍትሄ አፈላላጊ ነበር። "ትዕግስት እና ጥራት" ለወጣቶች የሚሰጠው ትልቁ ምክሩ ነበር። ዛሬ ያ ምክሩ በኢቢኤስ ስቱዲዮዎች ውስጥ እንደ ማሚቶ ያስተጋባል።
አማን ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችም አልጠፉም ነበር። ፕሮግራሞቹ "ዐደንዛዥ" ናቸው፣ ወጣቱን አያነቁም የሚሉ ወገኖች ነበሩ። ነገር ግን አንድ የጥበብ ሰው "ትችት የማይሰነዘርበት ስራ፣ ስራ አይደለም" ይላል። አማን የሰዎችን ቤት በሳቅና በደስታ መሙላቱ፣ የጠፉ ቤተሰቦችን ማገናኘቱና ለብዙ ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩ የሚካድ ሀቅ አይደለም። የእሱ ህልም ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ታሪክ በራሳቸው አንደበት እንዲነግሩ ማስቻል ነበር። ይህ ራዕይ ደግሞ ከትችቶች ሁሉ በላይ ግዙፍ ነው።
የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. የኢቢኤስ ማኔጅመንት የአማንን ህልፈት ሲያበስር መላው የሚዲያ ቤተሰብ ደንግጧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሰጡት መግለጫ "አማን ለኢትዮጵያ የግል ሚዲያ ዕድገት ወሳኝ ሚና ከነበራቸው አንዱ ነው" ብለዋል። ይህ ምስክርነት አማን በህይወት ዘመኑ የዘራው ፍሬ ምን ያህል ጥልቅ እንደነበረ ያሳያል። እርግጥ ነው፣ አካሉ በአሜሪካ ቢረግፍም፣ አሻራው ግን በአዲስ አበባ ጎዳናዎችና በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ለዘላለም ይኖራል።
በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት የሽኝት መርሃ ግብሮች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ዛሬ ሐሙስ እና ነገ ዓርብ በታኮማ ፓርክ ወዳጅ ዘመዶቹ ይሰበሰባሉ። ቅዳሜ ደግሞ በጸሎት ይሸኛል። ሁሉም ሰው የሚያወራው ስለ አማን ደግነት፣ ስለ ራዕዩና ስለ ብርቱነቱ ነው። አንቶን ቼኮቭ "ሰው ህያው የሚሆነው በሌሎች ትውስታ ውስጥ እስከኖረ ድረስ ነው" ይላል። አማን በፈጠረው የቴሌቪዥን ጣቢያና በለወጠው የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ለዘላለም ህያው ሆኖ ይኖራል።
የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴው አስከሬኑ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣበትን ቀን እያመቻቸ ነው። አማን የተመኘው በሀገሩ አፈር ውስጥ ለማረፍ ነበር። ያ ምኞቱ ሊፈጸም ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። የኢቢኤስ ስቱዲዮዎች ዛሬ ባዶ ቢመስሉም፣ የአማን መንፈስ ግን እዚያው አለ። "ራዕዩ ይቀጥላል" ያለው የጣቢያው መግለጫ፣ የአማን ሞት ፍፃሜ ሳይሆን የአዲስ ምዕራፍ ጅምር መሆኑን ያመለክታል።
በመጨረሻም፣ አማን ፍስሃጽዮን 54 ዓመታትን ብቻ አይደለም የኖረው፤ በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ የሚቀመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዓታትን የሚዲያ ታሪክ ነው የሰራው። ከካንሰር ጋር ያደረገው ትግል በአካል ቢሸነፍም፣ በስራውና በታሪኩ ግን አሸናፊ ሆኖ አልፏል። "ኢትዮጵያ መሞት እፈልጋለሁ" ያለው ቃሉ፣ ለሀገሩ ያለውን የከበረ ፍቅር የመጨረሻ መግለጫ ሆኖ ይኖራል። ነፍስ ይማር አማን፤ ስራህ ግን ለዘላለም አይሞትም።

1 year ago
ዮርዳኖስ ለፍልስጤማውያን አለሁ አለች !
ዮርዳኖስ በጋዛ የረሃብ አደጋ እየጨመረ ወደመጣበት የጋዛ ሰርጥ አካባቢ የነብስ አድን እርዳታ በመላክና ለፍልስጤማዉያን ፈጥኖ በመድረስ ቀዳሚዋ ሀገር መሆኗ ተሰማ ።
በጆርዳን ሃሽሚት በጎ አድራጎት ድርጅት (JHCO) ከአለም ሴንትራል ኩሽና እና ከአለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የተላከው የእርዳታ ኮንቮይ ሃሙስ እለት ከአማን ተነስቶ ወደስፍራው መላኩን የመንግስት ቃል አቀባይ መሀመድ ሞማኒ ተናግረዋል።
ሞማኒ ለዮርዳኖስ ሮያ የዜና ጣቢያ በሰጠው መግለጫ ምንም እንኳን መሰናክሎች እና ተግዳሮቶች ቢኖሩም ዮርዳኖስ "እርዳታን በማስጀመር እና በመላክ ከመጀመሪያዎቹ መካከል በመሆኗ ኩራት ይሰማታል" ብሏል።
ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ 147 የጭነት መኪናዎች የተውጣጡ አምስት ኮንቮይዎች ወደ ጋዛ መላካቸውን የገለፁት ሚኒስተሩ በዚህ ዙር 50 የጭነት መኪና ኮንቮይ ዱቄት፣ እህል፣ ዘይት እና የህጻናት ፎርሙላዎችን ጨምሮ አስፈላጊ የምግብ ምርቶችን መያዙን ገልፀዋል ።
የዮርዳኖስ የዜና ወኪል እንደገለጸው እርዳታን ለማድረስ የሚደረገው ጥረት በእስራኤል ድንበር ላይ ረጅም መጓተት እንደገጠመው እና እርዳታውን ለመቀበል ወደ መሻገሪያ በሚመጡት ተስፋ የቆረጡ ሲቪሎች ላይ የእስራኤል ወታደሮች በቀጥታ ጥይቶች ይተኩሳሉ ብሏል።
የዮርዳኖስ መንግሥቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ የእርዳታ መኪናዎችን ወደ ጋዛ ለመላክ ዝግጁ ብትሆንም ነገር ግን እስራኤል ፍቃደኛ አለመሆኗን የገለፁ ሲሆን “የእስራኤል መሰናክሎች ጋዛ ላይ ለመድረስ ቀዳሚ እንቅፋት ሆነው ቀጥለዋል” በማለት የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ለተጨማሪ እርዳታ ግፊት ለማድረግ “ሁሉንም እድሎች ” እንደሚጠቀም ተናግሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጋዛ ያለው ሰብአዊ ቀዉስ መቀጠሉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል ደ
እንደ ተቋሙ ገለፃ ከሆነ በግንቦት ወር በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል የሚደገፈው የጋዛ ሰብአዊ ፋውንዴሽን ኦፕሬሽንን ከተቆጣጠረ በኋላ የእስራኤል ወታደሮች ምግብ ለማግኘት ሲሉ ከ1,000 በላይ ፍልስጤማውያንን መግደላቸውን በዚህ ሳምንት ተናግሯል። ሲል የዘገበው ዘሚዲሊስት የዜና ወኪል ነዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

Comments