8 months ago
#እምዋ ሰላሌ
“ከየት ነህ ?” አልሽኝ ወይ …
ስሪት መሰረቴ ፣ ሁለት መልክ አለው ወይ ?
ግራ ገብቶሻል ወይ ?
.
ጠየቅሽኝ ጥያቄ ?
ባልገባው ዝም ብል
ናፍቆቴን አምቄ !
ዛሬስ ሆድ አስባሽኝ ፣ ለኩሰሽ በትናንት
በዛ ላይ ደመናው ፣ ነፍስያዬን ንጧት
ከፋኝና አነባው ፣ ውስጤ ሲበረበር
ትዝ አለችኝ ፍቼ ፣ የእትብቴ ማህደር
ሁለቴ ያስወጣችን ፣ ከፍታ አንዲቷን በር !
.
ተበረበርኩላት
ተቦረቦርኩላት
ያቺን ምድረ ገነት
የውበት ሰገነት…
ማሰንኩላት ባሳብ ወቃኝ ትዝታዋ
ሰላሌ እምዋ !
.
ከየት ነኝ መሰለሽ ?
ከዛ ከ … መዳሰ ፣ ከእነ ውቤ ሰፈር
የነ ፉትዬ ሱቅ ፣ ከበታቼ ነበር
አጸደ ህፃናት ፣
የጴጥሮስ ሀውልቱ ፣ ከበላዬ ነበር
(ያኔ ከቤቢ ጋር ፣ ያኔ ከፒና ጋር
ተያይዘን ስንበር )
እነርሱ መኅል ነው ፣ ታሪኬ ‘ሚጀመር ።
.
እዛ ነው መዳሰ !
የምቧርቅበት
አጥር ሳያግደኝ
የምጫወትበት
ህንፃ ሳይገድበኝ
መንጠራ እያሉ መስኩን በሚጠሩት
በሱ ደረት ነበር ትንፋሽ የተዋስኩት ።
ከየት ነው መሰለሽ ?
ከዛው ከመንጠራ ፣ ከሰፈረ ቄራ
(ከነ ፍሌ ፣ ድድሽ
ከቹቹሪ ጋራ
ዮርዲዬን ሳልጠራ !)
መስከረም ስትገልጥ ፣ በእሽት በሽንብራ
ከሚያቀማጥለን ፣ የበረከት ምድር
ያ ነው መነሾዬ የእስትንፋሴ ጅምር ።
.
ከዛ ቅፅ ተበጀሁ
ከዛ ገፅ ተዋጀሁ
በፍቼው ጊዮርጊስ ፣ እምነት ክሬን ባጀሁ
በአስራቴ አንባሻ ፣ ክርኔን አደረጀሁ።
ተሰራሁ በአርምሞ
ልቤ ተከርክሞ
ሼሂ እየሰማሁ ፣ ቁርዓን ሲቀራ …
እንደ ገዳም አጽድ ፣ ፀጥ ባለ ስፍራ
ቀዝቀዝ ባለ አየር ፣ ለሰስ ባለ ጮራ
በሰባቱ ምንጮች ፣ ፉፏቴ ሮጬ
የመቅደስ ዝማሬ ፣ በርቀት አድምጬ
የእነ ቡሬ ፣ ሀሮ “እንቧ … “ ቸው ሰምሮልኝ
የደብረ ሊባኖስ ንፍሮ ተሰፍሮልኝ
ቆለኛና ኦሮሞ ፣
ቅዳሜ ገበያ ፣ በሕብር ስቆልኝ
ቂሌ መጫወቻ ፣ ዱላ ተቆርጦልኝ
(አዲስ መጣኸብኝ !)
በቲቸር አስማማው ፣ በሚጣፍጥ መዝሙር
በየኔታ አርጩሜ ፣ ታርሜ ከነውር
እነ ዶርዜ በራፍ ፣
የአፍሪቃ ካርታ ፣ ቆሞልኝ ሀምሳያ
በደና ዘግኜ ፣ ቅዳሜ ገበያ
(እኔ አስር ፍሬ ፣ ሄርሞን ደግሞ ሀያ!)
ክገብርኤል ጀርባ ፣ ላዕከ ማርያም ቤት
ውዳሴ ማርያሟን ፣ ቀፅያት በስሌት
(አቤል ሲገፋበት ፣ እኔ ሸሸሁ ወጣሁ
ልደበቅ ግጥም ቤት )
ደግሞ ትምህርት ቤት …
በአብዲሳ … አጋ ፣ በእነ አብዮት … ፍሬ
አንድም የዓለሙን
አንድም የምናቡን
ቀለሞች ዘርፌ
ቃላትን ጠልፌ
ሁለት ሆኜ ወጣሁ
አንድ ብዕር ታቅፌ ።
.
“እና እንደው የምልሽ …
ተመለሰልሽ ወይ ?
መባቻ …
መነሻ …
መሰረት ፣ ታሪኬ ?
እንዲህ ነው ሲነገር
ይሄ ነው ሲዘከር
ሚካኤል የሚባል
ስሪት ሁለት መልኬ ፤
.
"መሃንዲስ ነው" አትበይ ፣ አይተሽ የቀኜን ገፅ
ገጣሚም ነኝ እና ከግራ ስመዘዝ !!”
#via
ሚካኤል አስጨናቂ
“ከየት ነህ ?” አልሽኝ ወይ …
ስሪት መሰረቴ ፣ ሁለት መልክ አለው ወይ ?
ግራ ገብቶሻል ወይ ?
.
ጠየቅሽኝ ጥያቄ ?
ባልገባው ዝም ብል
ናፍቆቴን አምቄ !
ዛሬስ ሆድ አስባሽኝ ፣ ለኩሰሽ በትናንት
በዛ ላይ ደመናው ፣ ነፍስያዬን ንጧት
ከፋኝና አነባው ፣ ውስጤ ሲበረበር
ትዝ አለችኝ ፍቼ ፣ የእትብቴ ማህደር
ሁለቴ ያስወጣችን ፣ ከፍታ አንዲቷን በር !
.
ተበረበርኩላት
ተቦረቦርኩላት
ያቺን ምድረ ገነት
የውበት ሰገነት…
ማሰንኩላት ባሳብ ወቃኝ ትዝታዋ
ሰላሌ እምዋ !
.
ከየት ነኝ መሰለሽ ?
ከዛ ከ … መዳሰ ፣ ከእነ ውቤ ሰፈር
የነ ፉትዬ ሱቅ ፣ ከበታቼ ነበር
አጸደ ህፃናት ፣
የጴጥሮስ ሀውልቱ ፣ ከበላዬ ነበር
(ያኔ ከቤቢ ጋር ፣ ያኔ ከፒና ጋር
ተያይዘን ስንበር )
እነርሱ መኅል ነው ፣ ታሪኬ ‘ሚጀመር ።
.
እዛ ነው መዳሰ !
የምቧርቅበት
አጥር ሳያግደኝ
የምጫወትበት
ህንፃ ሳይገድበኝ
መንጠራ እያሉ መስኩን በሚጠሩት
በሱ ደረት ነበር ትንፋሽ የተዋስኩት ።
ከየት ነው መሰለሽ ?
ከዛው ከመንጠራ ፣ ከሰፈረ ቄራ
(ከነ ፍሌ ፣ ድድሽ
ከቹቹሪ ጋራ
ዮርዲዬን ሳልጠራ !)
መስከረም ስትገልጥ ፣ በእሽት በሽንብራ
ከሚያቀማጥለን ፣ የበረከት ምድር
ያ ነው መነሾዬ የእስትንፋሴ ጅምር ።
.
ከዛ ቅፅ ተበጀሁ
ከዛ ገፅ ተዋጀሁ
በፍቼው ጊዮርጊስ ፣ እምነት ክሬን ባጀሁ
በአስራቴ አንባሻ ፣ ክርኔን አደረጀሁ።
ተሰራሁ በአርምሞ
ልቤ ተከርክሞ
ሼሂ እየሰማሁ ፣ ቁርዓን ሲቀራ …
እንደ ገዳም አጽድ ፣ ፀጥ ባለ ስፍራ
ቀዝቀዝ ባለ አየር ፣ ለሰስ ባለ ጮራ
በሰባቱ ምንጮች ፣ ፉፏቴ ሮጬ
የመቅደስ ዝማሬ ፣ በርቀት አድምጬ
የእነ ቡሬ ፣ ሀሮ “እንቧ … “ ቸው ሰምሮልኝ
የደብረ ሊባኖስ ንፍሮ ተሰፍሮልኝ
ቆለኛና ኦሮሞ ፣
ቅዳሜ ገበያ ፣ በሕብር ስቆልኝ
ቂሌ መጫወቻ ፣ ዱላ ተቆርጦልኝ
(አዲስ መጣኸብኝ !)
በቲቸር አስማማው ፣ በሚጣፍጥ መዝሙር
በየኔታ አርጩሜ ፣ ታርሜ ከነውር
እነ ዶርዜ በራፍ ፣
የአፍሪቃ ካርታ ፣ ቆሞልኝ ሀምሳያ
በደና ዘግኜ ፣ ቅዳሜ ገበያ
(እኔ አስር ፍሬ ፣ ሄርሞን ደግሞ ሀያ!)
ክገብርኤል ጀርባ ፣ ላዕከ ማርያም ቤት
ውዳሴ ማርያሟን ፣ ቀፅያት በስሌት
(አቤል ሲገፋበት ፣ እኔ ሸሸሁ ወጣሁ
ልደበቅ ግጥም ቤት )
ደግሞ ትምህርት ቤት …
በአብዲሳ … አጋ ፣ በእነ አብዮት … ፍሬ
አንድም የዓለሙን
አንድም የምናቡን
ቀለሞች ዘርፌ
ቃላትን ጠልፌ
ሁለት ሆኜ ወጣሁ
አንድ ብዕር ታቅፌ ።
.
“እና እንደው የምልሽ …
ተመለሰልሽ ወይ ?
መባቻ …
መነሻ …
መሰረት ፣ ታሪኬ ?
እንዲህ ነው ሲነገር
ይሄ ነው ሲዘከር
ሚካኤል የሚባል
ስሪት ሁለት መልኬ ፤
.
"መሃንዲስ ነው" አትበይ ፣ አይተሽ የቀኜን ገፅ
ገጣሚም ነኝ እና ከግራ ስመዘዝ !!”
#via
ሚካኤል አስጨናቂ
Comments