2 months ago
የሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ኮሙኒኬሽን የሐምሌ 2018 ዓ/ም መረጃ እንደሚያመላክተው በወረዳው በተከሰተ ድርቅ ምክንያት
👉 14ሺህ 89 የቁም እንስሳቶች ሞተዋል።
👉 ከ3ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዋል።
👉 በወረዳው ከሚገኙ 24 ቀበሌዎች መካከል 10 ቀበሌዎች ማለትም እርን፣በተል፣በስቂያ፣መረው ብላ፣ መረው ገብርኤል፣ አገጣ፣ ደረባ፣ከረዋ፣ነጋዴ መሻገርያ እና አተባ ቀበሌዎች እስከ ሐምሌ መጨረሻ አካባቢ ምንም ዝናብ ያላገኙ ናቸው።
👉 6 ቀበሌዎች ማለትም አቁና፣ ግልቤና፣ ጣራ፣አዲ ምህረት፣ጭንፍራ እና ጤበላ ዝቅተኛ የዝናብ መጠን እያገኙ ሲሆን፣ቀሪዎቹ 8 ወረዳዎች ደግሞ ጥሩ ዝናብ እያገኙ እንደሆነ መረጃው ያሳያል።
👉 በወረዳው የተለያዩ ሰብሎችን መዝራት የሚቻለው ከባለፈው ሚያዚያ ወር ጀምሮ እንደነበር ቢነገርም ወቅቱን ጠብቆ በአርሶ አደሩ ሰብል የተሸፈነ 9ሺ 88 ሄክታር መሬት በድርቅ ሳቢያ ምንም አይነት ሰብል ማብቀል ሳይችል በመቅረቱ ለኪሳራ ዳርጓል።
👉 በድርቁ ምክንያት 592 አባውራዎችና 305 እማ ውራዎች በአጠቃላይ 3ሺህ 386 ሰዎች መኖሪያ ቀያቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ሆኗል።
👉 የ DW AMHARIC መረጃ እንደሚያመላክተው ደግሞ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በስቂያ ቀበሌ በምግብ እጥረትና በወረርሽኝ ምክንያት 35 ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሰደዳቸውን ፣ በወረዳው አገጣ ቀበሌ ደግሞ 8 ሰዎች መሞታቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጧል።
በዚህ ዘገባ የጠለምት ወረዳ አደጋ መከላከልና ቅድመ ማስጠንቀቂያ በወረዳው በድርቁ ምክንያት 14ሺ 88 እንስሳት መሞታቸውን ሲያረጋግጥ በድርቁ ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ አረጋግጧል።
👉 የአዲስ ማለዳ መረጃ እንደሚያመላክተው ደግሞ በጠለምት ወረዳ መረው ቀበሌ በድርቁ ምክንያት እስካሁን 16 ሰዎች መሞታቸውንና በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል።
👉 ዜጎችን ከድርቁ ለመታደግ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ። ከመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሰብዓዊ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ እየተነገረ ይገኛል። ይሁን እንጅ አሁንም ድረስ የድርቁ አሳሳቢነት እና እያደረሰ ያለው ጉዳት ትኩረት አልተሰጠውም።
በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ፣ በየዳ፣ አዲ አርቃይና ደባርቅ ወረዳዎች በድርቁ ከተጎዱ ወረዳዎች መካከል የሚገኙ ሲሆኑ በዋግኽምራ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተከሰተው ድርቅ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም መረጃዎች ያመላክታሉ።

በጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የመረው ቀበሌ አስተዳዳሪ ለአዲስ ማለዳ ገለጹ
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ መረው ቀበሌ በተከሰተው በረታች ድርቅ ሳቢያ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተሰብ አባላት ለስደት መዳረጋቸውን የመረው ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ጥላሁን ገብረሚካኤል ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ፣ በአካባቢው ከመጋቢት ወር ጀምሮ ምንም ዓይነት ዝናብ በመጥፋቱ አርሶ አደሩ የዘራው እህል ሳይበቅል ቀርቷል። በዚህም ምክንያት በአካባቢው የምግብ እጥረትና ረሃብ በመከሰቱ፣ የሰው ሕይወት ከማለፉ ባሻገር የቁም እንስሳትም በሙሉ ማለቃቸውን አክለዋል፡፡
በተጨማሪም ድርቁ ያስከተለው የረሃብን ሁኔታ መቋቋም የተሳናቸው 488 አባወራዎች ከአካባቢው ለቅቀው ወደ ምዕራብ ትግራይ መሰደዳቸውን ጥላሁን አስረድተዋል።
ችግሩን በተመለከተ እስከ ክልል ድረስ አቤቱታ መቅረቡን የጠቆሙት አስተዳዳሪው፣ ከየቀበሌው የተመደቡ አካላት የሞቱ ሰዎችን፣ የተሰደዱ አባወራዎችን እና ያለቁ እንስሳትን ቁጥር መዝግበው ለሚመለከተው አካል ቢያሳውቁም እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አለመገኘቱን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም ከመንግሥት የተደረገው ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች ብቻ የተሰጠ የሴፍቲኔት እርዳታ እንደነበርም አክለው ጠቁመዋል።
እየከፋ የመጣውን የረሃብ አደጋ ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች የድንገተኛ እርዳታ ጥያቄ በማንሳት ሰልፍ መውጣታቸውን የገለጹት ጥላሁን፤ አሁንም አስቸኳይ ድጋፍ ካልቀረበ የአካባቢው ሕዝብ በረሃብ የሚያልቅበት አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት እንዲደርሱላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።(አዲስ ማለዳ )
Seledadotio

3 months ago
በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ‼️
ለሐምሌ 11 የተጠራው ሰልፍ ፈቃድ አገኘ‼️
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ አፈሳ ለማውገዝ በአዲስ አበባ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ የተፈናቀሉትን እንደሚያሳትፍ ተሰምቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ ለመጪው ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም የተጠራውና በሕገ-ወጥ ወታደራዊ ምልመላ እንዲሁም በሰላማዊ ዜጎች እስር ላይ ያተኮረው የተቃውሞ ሰልፍ የመንግስትን ፈቃድ ማግኘቱንና በከተማዋ የሚገኙ በርካታ የትግራይ ተፈናቃዮችም በሰልፉ ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል።።
የስምረት ፓርቲን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎችን ያካተተው የትግራይ ሰላምና የለውጥ ምክር ቤት የጠራው ይህ ሰልፍ፤ በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ነው ያሉትን ወታደራዊ አፈሳ ለማውገዝ፣ የታሰሩ እናቶችንና ገበሬዎችን ድምጽ ለማሰማት እንዲሁም ለአዲስ አበባ ተፈናቃዮች ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግ ለመጠየቅ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የስምረት ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሃለፎም ምርአ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፤ የሰልፉ ዋና ዓላማ በትግራይ ክልል ሕጋዊ ያልሆነ አዋጅን መነሻ በማድረግ በወጣቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላና ያለአግባብ የታሰሩ እናቶችንና ገበሬዎችን በደል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ ማድረግ ነው።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የነፈገውን የህወሃት ቡድን “የፕሪቶሪያው ስምምነት ፈርሷል” በሚል እያከናወነ ያለውን ተግባር ለማውገዝ፣ የፌደራል መንግሥት የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ለመጠየቅና በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው አዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች አስፈላጊውን ሰብአዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻል እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል።

4 months ago
በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፍራንስ 24 ምርጫውን አስመልክቶ በሰራው ዘገባ ላይ የአዲስ አበባን ልማት “አስከፊ” ብሎ በመፈረጅ ያሰራጨው ዘገባ የያዛቸው መረጃዎች “ከእውነት የራቁ ናቸው” አለ
#ethiopia | በፈረንሳይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ፍራንስ 24 ባለፈው ሰኞ የተካሄደውን 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ በሰራው ዘገባ “ምርጫውን የይስሙላ” እንዲሁም የአዲስ አበባን ልማት “አስከፊ” ሲል መግለጹ፣ ኢትዮጵያ ያለችበንት ሁኔታ እና እውነታ ያላገናዘበ ነው ሲል የተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል።
ኤምባሲው ፍራንስ 24 የቴሌቪዥን ጣቢያ ከሳቢን ፕላኔል ከተባሉ “እንግዳ” ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ፤ የቀረቡትን ሀሳቦች፣ አሳሳችና ወገንተኝነት የተሞላባቸው ትችቶች ናቸው በማለት በጽኑ እንደሚቃወም አስታውቋል፡፡ ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ የጣቢያው ዘገባ የሀገሪቱን ነባራዊ እውነታም ሆነ የመንግሥትን ሰፊ ጥረቶች የማያንጸባርቅ አሳሳች ትርክት ነው ሲል ፈርጆታል።
አክሎም ባለፉት ዓመታት ተመዝግበዋል ያላቸው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስኬቶችን ወደ ጎን በመተው አስተዳደሩን በ“እርስ በርስ ጦርነት” ብቻ ከፋፍሎ ለመግለጽ የተደረገው ሙከራ ማጋነንና ከተጨባጭ እውነታ የራቀ መሆኑን ጠቅሷል። ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ቀጣናዊ ሁኔታዎች ውስጥም ሆና በዋና ዋና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የተመሰከረለትን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግባለች ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና የመሠረተ ልማት ማዘመን ሥራዎችን “አስከፊ” ሲል የገለጸበትን አግባብ፣ ኤምባሲው ውድቅ እንደሚያደርገው በመግለጽ ይህ የልማት ፕሮጀክት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት እየቀየረ ያለና በዋና ከተማዋም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በከፍተኛ ደረጃ አድናቆት የተቸረው ስኬት ነው በማለት አወድሷል።
ኤምባሲው አክሎም በምርጫው ላይ ስለአሳታፊነትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን አስመልክቶ የሰራውና የተቸበት መንገድ በስህተት የተሞሉ ናቸው ሲል በጽኑ ነቅፏል። የፈረንሳዩ የዜና አውታር በሰራው ዘገባ “በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ግማሽ ያህሉ የምርጫ ክልሎች አልመረጡም” ማለቱን በተመለከተ ደግሞ ይህ መረጃ ሙሉ በሙሉ ሐሰት መሆኑን ኤምባሲው በአሐዛዊ መረጃዎች አስደግፎ ተከላክሏል።
ለአብነትም “በአማራ ክልል ከ138 የምርጫ ክልል በስምንቱ ብቻ አለመካሄዱን በመጥቀስ፣ ይህም ከክልሉ አጠቃላይ ቁጥር 6 በመቶ ብቻ መሆኑን” አመልክቷል።
እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና አጠቃላይ ሂደቱ ዲሞክራሲን የተከተለ መሆኑን በመግለጽ መገናኛ ብዙኃኑ የሰራቸው እና ያሰራጫቸው መረጃዎች እውነታን ያላገናዘቡ ናቸው ሲል አጣጥሏል፡፡
ምርጫው በተለይም በዴሞክራሲ ምህዳር መስፋትና መገናኛ ብዙኃን ተሳትፎ ዙሪያ የይስሙላ እንደነበር በዘገባው መጠቀሱን ያወሳው መግለጫው፤ የተመራጮችን፣ የሲቪል ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ ታዛቢዎችን፣ የሚዲያ ብዛት እና የሚዘግቡ ጋዜጠኞችን ቁጥር እንዲሁም በአጠቃላይ ምርጫው ላይ ያሉ ቁጥሮችን በመጥቀስ ውድቅ አድርጎታል።
ኤምባሲው አክሎም ሚዲያው የውጭ ወገኖችን ማለትም የአፍሪካ ሕብረት እና የኢጋድን ታዛቢዎችን ሚና ለማሳነስ “ትላልቅ ግድፈቶችን ሪፖርት አያደርጉም” ማለቱ የተቋማቱን ስራ ማሳነስ ነው ብሎታል ። የሁለቱንም ተቋማት ልዑካን የሚመሩትን ኃላፊዎች ማንነት በመግለጽ አንጋፋ ተቋማትና መሪዎችን ማጣጣል የአስተሳሰብ አድሏዊነት ማሳያ ነው በማለት ኮንኖታል።
በመጨረሻም የዚህ ምርጫ ውጤት የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በራሱ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንጂ ከውጭ በሚሰጡ መግለጫዎችና አስተያየቶች አይደለም ሲል አስታውቋል።
#አዲስ_ማለዳ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen

Sponsored by
Surafel
4 months ago
በኢትዮጵያ የመንግስት ስልጣን የሚያዝበት መንገድ “በጦር መሳሪያ ነበር” ሲሉ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደ ገለጹ
በኢትዮጵያ የመንግስት ታሪክ ውስጥ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ በአብዛኛው ከጦር መሳሪያ እና በጉልበት የሚመጣ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት በባህርዳር ከተማ በህዳሴ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ተናግረዋል።
ሀገሪቱን ዴሞክራሲን ጀማሪ ብለው የጠሯት ፕሪዝዳንቱ “በእኛ አገር ዴሞክራሲ አለመዳበሩ ብቻ ሳይሆን የመንግስት ስልጣን የሚያዝበት መንገድ ሁላችሁም እንደምታውቁት፣ በታሪካችንም እንደምናውቀው በአብዛኛው በብረት ነው የሚመነጨው፣ ከጦር መሳሪያ ነው የሚመነጨው፣ ከኃይል የሚመነጭ እንጂ ከህዝብ ድምፅ አይመንጭም” በማለት ይህንን የሚያስቀር መንግስታት በህዝብ ድምፅ ብቻ እንዲወጡ የሚያደርግ ነው ሲሉ የምርጫውን አስፈላጊነት አንስተዋል።
በህዝብ እና በዴሞክራሲ የተመረጠ መንግስት መመስረት መልመድ አለብን ሲሉም አክለዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚደረግ ምርጫ ሁለት ነገሮችን ያሳካል ብለዋል፡፡ አንዱ መንግስትነት በምርጫ እንጂ በጦርነት እና በአፈሙዝ እንደ ማይገኝ ሲሆን ሌላው ደግሞ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ አሁን ላይ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት የሚፈልጉ አካላት አሉ በማለት በዚህ ሂደት ውስጥ የምታልፍ ከሆነ “ ኢትዮጵያን የጸና መንግስት እና ሥርዓት አይኖራትም” በማለት ተናግረዋል።
በአማራ ክልል በጸጥታ ስጋት ምክንያት በስምንት የምርጫ ክልሎች ምርጫ የማይደረግ ሲሆን በክልሉ የሚካሄዱት በትጥቅ የታገዙ ግጭቶች መቀጠላቸው በሚዘገብበት ወቅት ነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡(አዲስ ማለዳ)

5 months ago
100 ቢሊዮን ብር መዘረፉ ከተጋለጠ በኋላ ሚዲያዎች በፓርላማ እንዳይዘግቡ ተከለከለ!
ሪፖርተር ጋዜጣ በትናንት እትሙ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች 98 ቢሊዮን ብር መመዝበራቸውን መዘገቡ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል፡፡
98 ቢሊዮን ብር ማለት የኢትዮጵያ አመታዊ በጀት አምስት በመቶ እንደማለት ነው፡፡
ይህ መረጃ መጋለጡን ተከትሎ ሚዲያዎች ላይ ክልከላ ተጥሏል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያቀርበው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ላይ መንግስታዊ ያልሆኑ የግል መገናኛ ብዙኃን ተገኝተው እንዳይዘግቡ ከልክሏል፡፡
የግል መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች የመግቢያ በር ላይ መግባት አትችሉም ተብለው ሲከለከሉ እንደ ብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ እና ኦ.ቤ.ኤን ያሉት ግን ተፈቅዶላቸው መግባታቸውን የአዲስ ማለዳ ሪፖርተር ተመልክቷል፡፡
ይህ ውሳኔ የቋሚ ኮሚቴው ውሳኔ ስለመሆኑም ለጋዜጠኞቹ ተነግሯቸዋል፡፡
በተመሳሳይ ዛሬ ከሰዓት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የጤና ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገም ለግል ሚዲያዎች ክፍት ይደረጋል ወይስ እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር ክልከላ ይጣልበታል በሚል በስፍራው ከነበሩ ዘጋቢዎች በኩል ለምክር ቤቱ ጥያቄ ቢቀርብም እናሳውቃለን የሚል ምላሽ ከማግኘት ባለፈ ይሁንታ አልተገኘም፡፡
seledadotio

6 months ago
መረጃ‼️
ፌደራል ፖሊስ ከቴዲ አፍሮ ጋር በተያያዘ የተሰራጨው “የስቱዲዮ ዘረፋ” መረጃ መሠረተ ቢስ ነው ሲል ገለጸ
በከያኒ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የቅርብ ሰዎች ላይ ተደርጓል የተባለውን እስርና ክልከላ እንዲሁም የስቱዲዮ ዝርፊያ በተመለከተ ምላሽ የሰጡት የፌዴራል ፖሊስ ሃላፊው መረጃው መሠረተ ቢስና ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባበሉ።
የታዋቂው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ኢትዮሪካ የተሰኘ አልበሙን ለህዝብ ይፋ ካደረገ በኃላ በዙሪያው ያሉት ሰዎች ላይ እስር መፈጸሙ እንዲሁም “የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ አካላት የድምፃዊውን ስቲድዮ እቃዎች እና ለህዝብ ጀሮ ያልደረሱ ስራዎቹን ተዘርፈዋል" መባሉን ተከትሎ አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ከፌደራል ፖሊስ ምላሽ ጠይቃለች።
ፖሊስም “የፌዴራል ፖሊስ እንዲህ ዓይነት ወንጀል አይሰራም። ሰብዕናውም አይደለም” በማለት ለአዲስ ማለዳ ምላሹን ሰጥቷል።

ዳንኤል ክብረት የብልጽግና ፓርቲ እጩ ሆነው ለምርጫ ቀረቡ
#ethiopia | በስደስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በግላቸው ተወዳድረው ፓርላማ የገቡት ዳንኤል ክብረት፣ ዘንድሮ በሚካሄደው ሰባተኛው ምርጫ ግን ብልጽግናን ተቀላቅለዋል፤ እጩ ሆነውም ቀርበዋል።
በእርግጥ በ2013ቱ ምርጫም ብልጽግና በአዲስ አበባ ዕጩ ያላቀረበበት የምርጫ ክልል ዳንኤል የተወዳደሩበት ብቻ ነበር።
ምንም እንኳን የእንደራሴዎች መቀመጫን አሸንፈው በግላቸው ፓርላማውን ቢቀላቀሉም ቢያንስ አዲስ ማለዳ ተገኝታ በተከታተለቻቸው እና በቀጥታ ሥርጭት በተላለፉ መደበኛም ይሁን አስቸኳይ ስብሰባዎች ላይ ዳንኤል ጥያቄ ሲያቀርቡ አልያም አስተያየት ሲሰጡ አልተስተዋለም።
ዳንኤል የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ መሆናቸውም ይታወቃል ስትል የዘገበችው አዲስ ማለዳ ናት።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

9 months ago
ፍርድ ቤቱ፣ በእነ ዮሐንስ ቧያሌው መዝገብ የአቃቤ ሕግን አስተያየት ለመጠባበቅ ለጥር 28 ቀን ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃቸው ገለጹ
አቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ ባቀረበው የፎረንሲክና ቴክኒካዊ ማስረጃዎች ላይ የቀረበውን የሰነድ አስተያየት መነሻ በማድረግ፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ፀረ-ሽብር ችሎት ለጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠቱን የተከሳሾች ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።
የዮሐንስ ቧያሌው፣ የክርስቲያን ታደለ እና የአማረ መለስን የችሎት ውሎ በተመለከተ ጠበቃቸው እንደገለጹት፤ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት አቃቤ ሕግ ካቀረባቸው የፎረንሲክ ማስረጃዎች ጋር በተያያዘ የተከሳሾች የሰነድ አስተያየት የቀረበ ሲሆን፣ ችሎቱም በዚህ ላይ የአቃቤ ሕግን ምላሽ ለመጠባበቅ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ያለመከሰስ መብት ክርክር በችሎቱ ላይ በተከሳሾች በኩል "ያለመከሰስ መብታችን ስለመነሳቱ የቀረበ ማስረጃ የለም" የሚል ጠንካራ መከራከሪያ መቅረቡን ጠበቃው አስረድተዋል። ዮሐንስ ቧያሌው የአማራ ክልል ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል መሆናቸውን የጠቀሱት ጠበቃው፤ ከሁለቱም ምክር ቤቶች መብታቸው መነሳቱን የሚያረጋግጥ ቃለ-ጉባኤ እንዲቀርብ መጠየቃቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ክርስቲያን ታደለ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆናቸው፣ መብታቸው የተነሳበት መንገድ ሕጋዊ አካሄዱን የተከተለ ባለመሆኑ የምክር ቤቱ ቃለ-ጉባኤ እንዲመጣ እንዲሁም የዶ/ር ካሳ ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች ተዛማጅ የጽሑፍ ክርክሮች ለችሎቱ መቅረባቸው ታውቋል።
የጤና ሁኔታና የሕክምና ትዕዛዝ በተመለከተ ደግሞ ተከሳሾች ካቀረቧቸው የሕክምና አቤቱታዎች መካከል፣ ዮሐንስ ቧያሌው በግል ሆስፒታል የመታከም መብታቸው እንዲከበር በጠየቁት መሠረት፤ ፍርድ ቤቱ በዳኑ ሆስፒታል ሄደው እንዲታከሙ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በሌላ በኩል ተከሳሽ አማረ መለስ "በአዕምሮ ሕመም ምክንያት ችሎቱን መከታተል የማይችሉ በመሆናቸው ሕክምና እንዲያገኙ" የቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ፤ ማረሚያ ቤቱ ሕክምና እየሰጠ መሆኑን ገልጿል። ፍርድ ቤቱም ማረሚያ ቤቱ የታካሚውን የሕክምና ውጤት ለችሎቱ እንዲያሳውቅ ትዕዛዝ በማስተላለፍ የዛሬውን ውሎ አጠናቅቋል።
በዛሬው የችሎት ውሎ ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አያያዝ ጋር የተያያዘ አዲስ አቤቱታ እንዳልቀረበ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ አረጋግጠዋል።Via_addismaleda

አቶ ታዬ ደንደአ “በካቴና አልታሰርም” በማለታቸው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት “ታዩ ደንደአ በካቴና አልታሰርም በማለት አለመቅረባቸውን ” ተከትሎ፣ ለነገ ታህሳስ 23 ቀጠሮ መስጠቱን አዲስ ማለዳ ጠበቃቸውን ጠቅሳ ዘግባለች፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳይ ወንጀል ችሎት፣ በታዬ ደንደአ ላይ የተመሰረቱትን ሦስት አዳዲስ ክሶች በሚመለከት በቀረበው የክስ መቃወሚያና የዋስትና ክርክር ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ታህሳስ 22 መቅጠሩን ጠበቃ አበራ ንጉስ አስታውሰዋል፡፡
ይሁንና ማረሚያ ቤቱ አቶ ታዬን ስላላቀረባቸው፣ ፍርድ ቤቱ ለነገ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን አክለዋል፡፡
ማረሚያ ቤቱ ተከሳሹን ያላቀረበው “በካቴና አልታሰርም ስላሉ ነው" የሚል ምክንያት መቅረቡንና ይህንንም ለማረጋገጥ ወደ ማረሚያ ቤቱ እያቀኑ መሆኑን ጠበቃው ተናግረዋል ተብሏል፡፡
“ታዬ ደንደአ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በነበሩበት ወቅት የካቴና አለርጂክ ስለነበረባቸው ለፍርድ ቤቱ በማሳወቃቸው፣ ፍርድ ቤቱ ካቴና ሳያደርጉ እንዲመጡ ትዕዛዝ መስጠቱን ” በማስታወስ፣ አሁን ላይ ያሉበት ማረሚያ ቤት ሌላ በመሆኑ ትዕዛዙ ስላልደረሰ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ሀሰተኛ መረጃ‼️
ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በእስር ያሉ ሰዎች “ በይቅርታ ሊፈቱ ነው ” በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ “ ሐሰተኛ ነው ” ሲሉ ጠበቃቸው ተናግሯል‼️
ፖለቲከኞችና የማህበረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌሎች በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው በትጥቅ የታገዘ ግጭት ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙት ግለሰቦች ከእስር ሊፈቱ ነው መባሉን የእነ ክርስቲያን ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ “ ሐሰተኛ ነው ” ሲሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡
እየተሰራጨ በሚገኘው መረጃ ይፈታሉ ከተባሉት መካከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርስቲያን ታደለ የሚገኙበት ሲሆን ከመጪው ገና በዓል በፊት ከእስር እንደሚፈቱ እንደሚጠበቅም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እየተሳጩ የሚገኙት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በእርግጥ መንግስት ከዚህ ቀደም በ2014 የገና በዓል እንደ እስክንድር ነጋ፣ ጀዋር መሐመድ፣ ስብሃት ነጋን ያሉትን ጨምሮ ሌሎችንም ፖለቲከኞች በተመሳሳይ በበዓሉ ዕለት እንደለቀቃቸው ይታወሳል፡፡
ጠበቃ ሰለሞን ሐሰተኛ ናቸው ያሏቸው መረጃዎች ግን በመጀመሪያ ዙር ከእስር ይፈታሉ ተብሎ ከሚጠበቁት መካከል ዮሐንስ ቧያለው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ክርስቲያን ታደለ፣ ሲሳይ አውግቼው፣ ቴዎድሮስ ኃይለማርያም፣ ወንድወሰን አሰፋ፣ መስከረም አበራ፣ ጫኔ ከበደ እና ካሳ ተሻገር እንደሚገኙበት ተመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ በክርስቲያን ታደለ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ የቀረበውን ምስክር ተከትሎ በዐቃቤ ህግ ባቀረበው ሰነድ ላይ አስተያየት ለመስጠት ለጥር 8 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
Via : አዲስ ማለዳ

10 months ago
ለማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
የማርበርግ ቫይረስ ምላሽን ለማሳደግ የሚረዳ የሙከራ ክትባት ለተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ሊሰጥ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ክትባቱ ከሕዳር 29 ቀን ጀምሮ መስጠት የሚጀመር ሲሆን የጤና ባለሙያዎችን እና ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑ ቡድኖች ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።
ለዚህም የማርበርግ ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ 2 ሺ 500 የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት ከአሜሪካ መንግስት በድጋፍ የተገኘ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ክትባቱ በአርማወር ሃንሰን የምርምር ተቋም በሚመራ ፈጣን የደረጃ 2 ክሊኒካዊ ሙከራ ተደርጎለት ጥቅም ላይ እንደሚውልም ነው የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ የገለጹት።
ጤና ሚኒስቴር ወርሽኙን ለመግታት ከሚመለከታችዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የምላሽ አሰጣጡን አጠናክሮ የቀጠሉ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ፤ ለዚህም የቅኝትና ቁጥጥር ስራዉን ማጠናከር፣ የጤና ባለሙያዉንና ጤና ሰራተኞች ጨምሮ ተጋላጭ የሆኑትን በመጠበቅ ላይ ትኩረት በማድረግ የመከላከል ስራው አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አመልከተዋል።
ክትባቶቹን ለጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ያስረከቡት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው አሜሪካ ክትባቶቹን በባርዳ እና ሳቢን የክትባት ተቋም በኩል ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓን ተናግረዋል።
አሜሪካ የማርበርግ ቫይረስን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት የበለጠ ሊያግዝ የሚያስችል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጓን አዲስ ማለዳ ትናንትና መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን ከድጋፎቹ መካከል አንደኛው ክትባት መሆኑን ዛሬ የቴና ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህም ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስን ለመቆጣጠር እያደረገችው ያለውን ጥረት የበለጠ ሊያግዝና ወደፊት ሊያራምድ የሚያስችል መሆኑን አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት መግለጻቸው ይታወሳል።

11 months ago
አቶ ታዬ ደንደአ “ ሦስት አዳዲስ ተደራራቢ የወንጀል ክሶች እንደተከፈተባቸው ” ጠበቃቸው ተናገሩ
ዛሬ ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት የቀድሞው ምክትል የሰላም ሚኒስትር ታዬ ደንደአ ሦስት አዳዲስ ተደራራቢ ክሶች በዐቃቤ ህግ እንደተከፈተባቸው ጠበቃቸው አበራ ንጉስ ለአዲስ ማለዳ ነግረዋታል፡፡
አንደኛው “ መንግስትን በኃይል ለመጣል በሚደረግ ዝግጅት ላይ ጫካ ካሉት ኃይሎች ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ ፕሮፓጋንዳ ፈጽመዋል፤ የፕሮፓጋዳ ድጋፍ አድርገዋል ” የሚል ሲሆን ይህንን ድጋፍ ያደረጉት ደግሞ ሆርን ኮንቨርሴሽን በሚባል የዩቱብ ቻናል ላይ ቀርበው በሰጡት በሦስት ተከታታይ ክፍሎች በተሰራጨው ዝግጅት ላይ ነው፡፡
ሁለተኛው ክስ ደግሞ በተመሳሳይ በተጠቀሰው የዩቱብ ቻናል ላይ መከላከያ ሠራዊት በተለይም ስለሰሜን ዕዝ ጥቃትና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ “ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሉኝ ብለው የተናገሩት በመከላከያ ላይ የተነዛ ሀሰተኛ መረጃ ነው ” በሚል ሲሆን ሦስተኛው ክስም በዚሁ ቻናል በሰጡት አስተያየት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ታዬ “ ብልጽግና የአንድን ሰው ስልጣን ለማቆየት የተደራጀ ፓርቲ ነው፤ ፓርቲው በአመዛኙ የማፊያ ባህሪ ያለው መንግስት እንዲመሰረት አስተዋጽዖ ያደረገ እንጂ የህዝብን ፍላጎት ለማስፈጸም የተደራጀ ፓርቲ አይደለም፣ በማለት በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት የተመረጠውን መንግስት ስም በማጉደፍ” በሚል ተከስሰዋል፡፡
በእነዚህ ተደራራቢ ክሶች ላይ መቃወሚያ ላይ ለማቅረብና ውሳኔ ለመስጠት ለህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠጡንም ተናግረዋል፡፡
አዲስ ማለዳ

በትግራይ ክልል መዲና መቀሌ ከተማ ዳግም ጦርነት ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ፍጆታዎች ዋና መናሩን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገለጹ
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የአፋር ክልል ወሰንን አልፎ በክልሉ የተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች ፈፅሞታል ሲል ክልሉ ከገለጸው ጥቃት ወዲህ “ በመቀሌ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ መደበኛ እንቅስቃሴ መቀዛቀዙን ” አዲስ ማለዳ ያነገጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
ስማቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡ አንድ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት “ ጥቃቱ ተፈጽሟል ከተባለበት ጊዜ ወዲህ የቀደመው ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ስጋት ነዋሪዎች ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል ” ፤ “ አተርፍ ባይ” ሲሉ የገለጧቸው ነጋዴዎችም ሁኔታውን ተጠቅመው ለማትረፍ በምግብ እና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ለአብነትም የአምስት ሊትር ዘይት ዋጋ ይሸጥበት ከነበረው አንድ ሺህ አምስት መቶ (1,500) ብር አንድ ሺህ ስምንት መቶ (1,800) ብር ማሻቀቡን አመልክተዋል፡፡
በክልሉ ከሚመረቱ እና በቅርብ ከሚገኙ የአትክልት ምግቦች ባሻገር በሌሎች እንደ ማኮሮኒ፣ ሩዝና የመሳሰሉ ምግቦች ላይም ከ20 እስከ 30 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንደተደረገባቸው ተናግረዋል፡፡
“ ይህ በወንድማማች ህዝቦች መካከል በየጊዜው የሚነሳ ግጭትና ጦርነት ለምን ያስፈልጋል ” የሚል ጥያቄ በህብረተሰቡ ዘንድ እንዳለ የተናገሩት አስተያየት ሰጪው በሸቀጦች ላይ ዋጋ ከመጨመር ባለፈ ምርቶቹ እየተደበቁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ስማቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ለአዲስ ማለዳ ሲናገሩ “ ከዚህ ቀደም የነበረውን ጦርነት ያውቀዋል፤ በቀደመው ጦርነት ያጣው አብሮ አደግ ወንድሙን ነውና በጭራሽ ወደ ጦርነት የመግባት ሀሳብ የለውም ”
የመቀሌ ከተማ ከሁለት ዓመቱ አውዳሚ ጦርነት ለማገገም እንቅስቃሴ ላይ ባለችበት ሁኔታ የተከሰተው የባለፈው ሳምንት ጥቃት ዛሬ ላይ ከተማዋን ወደ መቀዛቀዝ እንደከተታትም ተናግረዋል፡፡
ሌላኛው አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ነዋሪ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ጦርነት ከተነሳ በሚል እያደረገ የሚገኘውን ቅድመ ጥንቃቄን ጠቅሰዋል፡፡ እሱም ገንዘብ ከባንክ በማውጣት ማስቀመጥ ሲሆን በዚህም በባንክ ቤቶች አካባቢ ረዣዥም ሰልፎች እና መጨናነቆች እንደሚታዩ ገልጸዋል፡፡
ከባንኮች በኩልም “ ጥሬ ገንዘብ (ካሽ) የለም ” የሚሉ ምላሾች እየተሰጡ መሆኑን የጠቀሱት ነዋሪው ይህ ደግሞ ስጋት ማጫሩን አስረድተዋል፡፡
ይህን የጦርነት ደመና በመስጋትም ገንዘብ የሌለው ጭምር ከዚሀም ከዚያም ተበዳድሮ አስቤዛ ለመግዛት እየሞከረ መሆኑን ምሬት በተጫነው ድምጸት ተናግረዋል፡፡ “ የትግራይ ህዝብ ጦርነትን በውል ያውቀዋል፤ ዳግም እንዲቀሰቀስ አይፈልግም፤ ወጣቱም ራሱን ከዚህ እንዲያገል ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
“ ያለን ቁስል ይበቃናል፤ ሌላ አትጨምሩበን ” ያሉት ነዋሪ ሁሉም አካላት ጦርነቱ በማስቀረት፣ ወደ ስምምነት መምጣት በሚችልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ መምከር አለባቸው ሲሉ ምክረሃሳበቸውን ለግሰዋል፡፡
የዚህ ስጋት መነሻ የሆነው ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ላይ በህወሓት ተፈጽሟል የተባለው ጥቃት ቢሆንም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ግን መሠረተ ቢስ ሲል ውንጀላውን ውድቅ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡
የፌደራሉ መንግስት ቢያንስ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የሁለቱን ክልሎች ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ያለው ነገር የለም፡፡

አጣሪ ኮሚቴው በአርሲ ዞን “ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ የምርመራ ሪፖርቱን ይፋ ሊያደርግ ” ነው‼️
የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን የተፈጸመውን ግድያ እንዲያጠራ ያሰማራው አጣሪ ኮሚቴ የደረሰበትን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት በነገው ዕለት ይፋ እንደሚያደርግ አዲስ ማለዳ ለማወቅ ችላለች።
ጉባኤው፣ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አራት ወረዳዎች “ የተከሰተውን ችግር ” ሲል የገለጸውን ግድያ በቦታው በአካል በመገኘት የማጣራት ሥራ ለመሥራት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተወከሉበት አንድ አጣሪ ኮሚቴ በአስቸኳይ በማቋቋም ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም “ ችግር ወደተከሰተባቸው ሂዶ የማጣራት ሥራ እንዲሠሩ ማድረጉን ” አስታውሷል።
በዚህም አጣሪ የልዑካን ቡድኑ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ይፋ እንደሚያደርግ፣ ጉባኤው ለመገናኛ ብዙኃን ያሰራጨው የጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ ያመላክታል።
በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና ሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች መገደላቸውን ቤተ ክርስቲያኒቱን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጣቸውና ድርጊቱን ማውገዛቸው ይታወሳል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጉባኤው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር “ ኃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነትና አብሮነት ” በሚሉ መሪ ቃላት አምስተኛውን ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ህዳር 3 እና 4 ቀን 2018 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ገልጧል።
በነገ መግለጫው ከሪፖርቱ በተጨማሪ ጉባኤው በዚህ ኮንፈረንስ ላይም ገለጻ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አበባው ደሳለው በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን የተፈጸሙትን ግድያዎች በጽኑ አውግዘው፣ “ የአካባቢው አመራሮችና የፌደራሉ መንግስት ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው” ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡
“ ኃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንዲቆም እኔም ብሆን ቀደም ብዬ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ጥያቄ አቅርቤ ነበር ” ሲሉ ያስታወሱት የምክርቤት አባሉ ይህን መሰል ጥቃት በአካባቢው በተደጋጋሚ እንደሚፈጸም ገልጸዋል፡፡
ለዚህም ዋነኛው ምክንያት “ የአካባቢው አመራሮች ችግሩን ለመቅረፍ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ስለሌላቸው ነው ” ባይ ናቸው፡፡
ጥቃቱን በሚፈፀሙት አካላት ላይም ተጠያቂነትን አለማረጋገጥና እርምጃ ሲወሰድ አለመታየቱ ችግሩ እንዲባባስ ሌላኛው ምክንያት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
አበባው አክለውም በኢትዮጵያ የነበረው የመተሳሰብና አብሮ የመኖር እሴት በዚህ መሰል ድርጊት እንዲሸረሸር ያደረገዉ የህግ የበላይነትን ማስከበር አለመቻል መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን “ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ላይ ከመጡበትና ከዚያ ጥቂት ጊዜያት ቀደም ብሎ እስካሁን ድረስ እንደ ፖሊስና መከላከያ ” ሲሉ የዘረዘሯቸው የመንግስት የጸጥታ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ አለመሆናቸው ችግሩን አባብሶታል ብለዋል፡፡
የፓርላማ አባሉ አሁንም ቢሆን ገለልተኛ አካል በስፍራው ገብቶ በማጣራት ጥፋተኞቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አበባው በቀጣይ ግን መንግስት ችግሩን መፍታት ካልቻለ “ ሰዎች ተፈጥሯዊ የሆነውን ራሳቸውን የመከላከል መብት ተጠቅመው ራሳቸውን እንዲከላከሉ ሊያስታጥቃቸው ይገባል አልያም በራሳቸው እንዲታጠቁ ማድረግ ይኖርበታል ” ሲሉ አሳስበዋል፡፡
Via Addis Maleda

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በአስር ቀናት ልዩነት፣ ለሁለተኛ ጊዜ “ የባህር በር ጥያቄን እናሳካለን ” ሲሉ ተናገሩ
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ በኢ-ፍትሐዊነት አጥታዋለች ያሉትን “ የባህር ጥያቄ እናሳካዋለን ” ሲሉ በትናንትናው ዕለት ታስቦ በዋለው አምስተኛ ዓመት የመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ጥቃት መርሐ ግብር ላይ ተናግረዋል፡፡
ፊልድ ማርሻሉ ከአስር ቀናት በፊት፣ ጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በተከበረው 118ኛው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምስረታ ቀን ላይ በተመሳሳይ የባህር በር ጥያቄን እንደሚያሳኩ ተናግረው ነበር፡፡
ኢታማዦር ሹሙ በመድረኩ ኢትዮጵያ ሦስት ነገሮች እንደሚያስፈልጓት የጠቀሱ ሲሆን እነርሱም ሰላም፣ ልማትና የባህር በር ናቸው፡፡ ከአስር ቀናት በፊት ባደረጉት ንግግር “ 30 ዓመት ተኝተናል፤ አሁን ነቅተናል፤ ጥያቄችንን እንቀጥላለን፤ ሰላምም፣ ልማትም፣ የባህር በርም እናሳካለን ” ብለው ነበር፡፡
ትናንት በተካሄደው መድረክ ላይም በተመሳሳይ ጉጅሌ ሲሉ የገለጹት ጥቂት የህወሓት ኃይል በክህደት አሳጥቶናል ያሉትን የባህር እንደሚያሳኩት ገልጸዋል፡፡
ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ መልዕክታቸው፣ በትናንት ንግግራቸውም ሰላምና ልማት እንደሚያስፈልግ አጽዕኖት የሰጡት ኢታማዦር ሹሙ “ እኛ ጥያቄችን አሁን አድጓል፤ ሲታፈን የነበረ ጥያቄ ወደ አደባባይ ወጥቷል ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ፊልድ ማርሻሉ ሦስቱን ጉዳዮች
አያይዘው ማስረዳት ሲቀጥሉ “ እያለማን ነው፤ ሰላም ለማምጣት መከላከያ ሠራዊት እየታገለ ነው፤ ሰላም መምጣቱ አይቀርም፤ ሀገር መልማቱ አይቀርም፤ ህዳሴም ተገድቧል፤ የቀረን ጥያቄ አለ(የባህር በር)፤ የቀረንን ጥያቄ ደግሞ እንሳካዋለን ”ሲሉ እርግጠኝነት በተጫነው ድምጸት ተናግረዋል፡፡አዲስ ማለዳ

ፊልድ ማርሻሉ ሦስቱን ጉዳዮች አያይዘው ማስረዳት ሲቀጥሉ “ እያለማን ነው፤ ሰላም ለማምጣት መከላከያ ሠራዊት እየታገለ ነው፤ ሰላም መምጣቱ አይቀርም፤ ሀገር መልማቱ አይቀርም፤ ህዳሴም ተገድቧል፤ የቀረን ጥያቄ አለ(የባህር በር)፤ የቀረንን ጥያቄ ደግሞ እንሳካዋለን ” ሲሉ እርግጠኝነት በተጫነው ድምጸት ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል፣ በሦስት መጠሊያ ጣቢያዎች ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለመንግስት ጥሪ አቀረቡ፡፡
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ሰርቼዋለሁ ባለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ የዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ከ27 ሚሊዮን ወደ 3 ሚሊዮን ወርዷል ብሏል፡፡
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደብረ ብርሃን ከተማ ቻይናና ወይንሸት እንዲሁም በሰሜን ጎንደር፣ ዳባት ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች “ ከዕለት ደራሽ ሰብዓዊ እርዳታ ባለፈ በዛላቂነት ራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ ” ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለደህንነታችን ሲባል ስማችን አይገለፅ ያሉ በደብረ ብርሃን ከሚገኙ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች እንዱ በሆነው ቻይና ካምፕ እንደሚገኙ የገለፁት ተፈናቃይ እንደተናገሩት እርሳቸው በተጠለሉበት ካምፕ ብቻ ከ11 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ፡፡
ከቀደመ ቀዬያቸው ተፈናቅለው መጠሊያ ጣቢያ ውስጥ ከገቡም አምስት ዓመታትን እንዳስቆጠሩ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደምም ድጋፍ የሚያደርጉላቸው መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ባለሀብቶች ነበሩ ያሉት አስተያየት ሰጪው የጊዜው መርዘምን ተከትሎ “ ለጋሾቹ መሰልቸታቸውን ” ተናግረዋል፡፡
“ አሁን ላይ ምንም ዓይነት የምግብ እርዳታ እየቀረበልን አይደለም ” ያሉት ተፈናቃዩ “ ከአምስት አመታት በፊት የተሰሩት መጠለያ ጣቢያዎችም በጊዜ ሂደት ከአገልግሎት ውጪ ለመሆን እንደተቃረቡ ” አስረድተዋል፡፡
በተደጋጋሚ ጉዳዩን ከማሳወቃቸው የተነሳ መሰላቸት ውስጥ እንደገቡም በምሬት ተናግረዋል፡፡ “ ምንም እንኳን የነቀዘና ለምግብነት ለማዋል የሚከብድ ቢሆንም ከዚህ ቀደም 15 ኪሎ በቆሎ ይሰጣቸው እንደነበረ ” ግን አስታውሰዋል፡፡
በዚሁ ደብረብርሃን ከተማ፣ ወይንሸት እየተባለ የሚጠራው ሌላኛው የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችም በተመሳሳይ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን በስፍራው ተጠልለለው የሚገኙ ተፈናቃይ ለአዲስ ማለዳ ነግረዋታል፡፡
በመጠሊያ ጣቢያው ውስጥ ከ8 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ የተናገሩት አስተያየት ሰጪው እንደ ቻይና ካምፕ ሁሉ ከዚህ በፊት ይደረግላቸው የነበረው የተበላሸ በቆሎም ጭምር ከቀረበላቸዉ ከሁለት ወር በላይ ማስቆጠሩን ገልጸዋል፡፡
ካምፑ ከዚህ በላይ ቁጥር ያላቸዉን ተፈናቃዮች ይዞ እንደነበር የሚናገሩት ተፈናቃዩ ከሰሞኑ ባቄሎ ወደተሰኘው ሦስተኛ የመጠለያ ጣቢያ መወሰዳቸውን አመልክተዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ እንደገለጹት ወደ መጠለያው ከመግባታቸው በፊት በኦሮሚያ ክልል አራቱም የወለጋ ዞኖች ውስጥ ይኖሩ ነበር፤ ይሁንና በአካባቢዎቹ በተፈጠረው የሰላምና ፀጥታ እጦት ተፈናቅለው ወደአማራ ክልል መጥተዋል፡፡
በተመሳሳይ በክልሉ ሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ የሚገኙና ለአዲስ ማለዳ አስተያየታቸውን የሰጡ ተፈናቃይ በትግራይ ይመሩት ከነበረው ኑሯቸው ተፈናቅለው ወደ አካባቢው መሄዳቸውን በመግለፅ በዛም ልክ እንደ ደብረ ብርሃኑ ሁሉ በርካታ ችግሮች እየገጠሟቸዉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
“ የሚቀርብላቸው በቆሎ በወፍጮ እንኳን አይፈጩልንም የሚሉት ተፈናቃዩ አልፎ አልፎም ቢሆን የዉጭ ተራድኦ ድርጅቶች ብቻ ድጋፍ እያደረገላቸዉ እንደሚገኝ ” ገልጸው፣ “ ስንት ነገር የለመድን ቤት ንብረት የነበረን ሰዎች ነን ” ሲሉ ስለቀደመ ህይወታቸው ያወሳሉ፡፡
ካምፕ ዉስጥ እርዳታ ሳይሆን የምንቋቋምበትን መንገድ ነው መንግስት እንዲያመቻችልን የምንፈልገው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአማራ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊን በስልክ ምላሻቸውን ለማካተት የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የገዢው የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አደም ፋራህ፣ መንግስታቸው ሰርቶታል ባሉት የግንዛቤ ስራ በተለያዩ የደጋፊ ማዕቀፍ ታቅፈው ሲረዱ የነበሩ “ ዜጎች እራሳችንን እንችላለን፤ የራሳችንን ገቢ እንፈጥራለን ” ማለታቸውን ተከትሎ በርካታ ዜጎች ከተረጂነት መውጣታቸውን ከአንድ ሳምንት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል፡፡
በ2013 የዕለት ደራሽ ምግብ ፈላጊዎች በምግብ መልክ የሚቀርብላቸው 27 ሚሊዮን ደርሶ የነበረ ቢሆንም በተያዘው ዓመት ግን አሽቆልቁሎ ሦስት ሚሊየን ገደማ መድረሱን አስታውቀዋል፡፡

መንግስት ለአርሲው ግድያ “ ይቅርታ እንዲጠይቅና ካሣ እንዲከፍል ” ኢሕአፓ ጠየቀ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ይህንን ያለው ዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣውና ለአዲስ ማለዳ በላከላት መግለጫ ላይ ነው፡፡
ፓርቲው በመግለጫው “ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር እና ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በጉና እና በመርቲ ወረዳዎች 17፣ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሽርካ ወረዳ 3፣ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳ 5 በድምሩ 25 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ” ብሏል፡፡
ኢሕአፓ በምዕመኑ ላይ የተፈጸመው ግድያና አካላዊ ጉዳትን አውግዞ መንግስት ተጠያቂነቱን እንዲያምን እና ወንጀሉን የፈጸሙት አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ አሳስቧል፡፡
ለደረሰው ግድያና አካላዊ ጉዳት የተሰማውን ሐዘን የገለጸው ፓርቲው መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅና አስፈላጊ ያለውን ካሳ ለሚመለከታቸው ሁሉ እንዲከፍል ጠይቋል፡፡ የፓርቲው መግለጫ ሲቀጥል ጉዳት ከደረሰባቸው ባለፈም የዕምነቱን ተከታዮች፣ የእስልምና ተከታዮች ላይ ለደረሱት ጉዳቶች በተመሳሳይ ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስቧል፡፡
ከጥቂት አመታት ወዲህ የተባባሱት መጠነ-ሰፊ በዕምነትና በዘር ልዩነት ላይ የተመሠረቱ ግድያዎች፤ አፈናዎች፣ እገታዎች፣ ማፈናቀሎች፣ የንብረት ንጥቂያዎችና ውድመቶች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤት ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ መንግስት የዜጎችን የመኖር መብት እንዲያረጋግጥ ጠይቋል፡፡

1 year ago
ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋት በአፍሪካ ቀዳሚ ናት - ጥናት
#ethiopia | ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋትና የኢንተርኔትን ነጸነት በመገደብ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በብሉምስበሪ አሳታሚ የታተመ ጥናት አመለከተ።
“የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ” በሚል ርእስ በፊሊሽያ አንቶኒዮ እና ቶኒ ሮበርትስ የተጠናውና መቀመጫውን በእንግሊዝ ባደረገው ብሉምስበሪ አሳታሚ ድርጅት በመጸሐፍ መልክ ታትሞ የወጣው ጥናት፣ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 በአህጉረ አፍሪካ በሀገራት የተፈጸመውን የኢንተርኔት መዘጋት ገምግሟል።
በዚህም ከ2016 እስከ 2024 ባሉት በለፉት ዘጠኝ ዓመታት 193 የኢንተርኔት መዘጋቶች በአፍሪካ አህጉር መመዝገቡን ገልጿል።
በተጠቀሱት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ በተፈጸሙ የኢንተርኔት መዘጋት ድግግሞሽ መጠኖች ሀገራትን በደረጃ ያስቀመጠው ጥናቱ፤ ኢትዮጵያን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ሰላሳ ጊዜ ኢንተርኔት የዘጋች በሚል፣ ከ55ቱ የአፍሪካ ሀገራት በአንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።
በእርስ በእርስ ጦርነት እየታመሰች የምትገኘው ጎረቤት ሀገር ሱዳን፣ በተጠቀሱት ዓመታት 21 ጊዜ ኢንተርኔትን በመዝጋት በአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ስትቀመጥ፤ ባለፉት ዓመታት በሰላም እጦትና በግጭት ውስጥ ያለችው ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር አልጀሪያ ደግሞ 14 ጊዜ ኢንተርኔትን በመዝጋት በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።
ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በአህጉሪቱ የተፈጸመው የኢንተርኔት መዘጋት ሁኔታና የድግግሞሽ መጠኑ ከሀገር ሀገር ከፍተኛ ልዩነት የሚታይበት መሆኑንም የጥናቱ ውጤት አመላክቷል። በዚህም ምንም እንኳን በብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት የኢንተርኔት መዘጋት የነበረ መሆኑን የጠቆመው ጥናቱ፤ በዚያው ልክ ደግሞ በ14 የአፍሪካ ሀገራት አንድም የኢንተርኔት መዘጋት አለመመዝገቡን፤ በሌሎች 14 ሀገራት ደግሞ የኢንተርኔት መዘጋት የገጠመው አንድ፣ አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑን አስታውሷል።
በአህጉሪቱ የተፈጸመው የኢንተርኔት መዘጋት ክስተት በመጠንና በድግግሞሽ ብቻ ሳይሆን ለድርጊቱ መፈጸም መንስኤ በሆኑ ገፊ ምክንያቶች ጭምርም ሰፊ ልዩነት የሚታይበት መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል።
የመንግሥታት ሕዝባዊ አመጽን መፍራት፣ በሀገራቱ ውስጥ የሚኖሩ ግጭቶችና ጦርነቶች፥ ምርጫን ተከትለው ሊቀሰቀሱ የሚችሉ አመጾች፥ የፈተና መሰረቅንና መጭበርበርን ለማስቀረትና የፖለቲካ ተቃውሞን ለማፈን የሚወሰዱ እገዳዎች ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በአህጉሪቱ ለተፈጸሙ የኢንተርኔት መዘጋትና በኢንተርኔት ነጻነት ላይ ለተፈጸሙ ገደቦች ዋነኛ መንስኤ ሆነው መለየታቸውንም ጥናቱ ገልጿል።
ኢትዮጵያን በተመለከተም የኢንተርኔት መዘጋት በተለይም በግጭትና በጦርነት ወቅት ሊኖረው የሚችለው ውጤትና በዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ላይ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖ በጥናቱ መካተቱን አዲስ ማለዳ በዘገባዋ አመልክታለች፡፡

ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋት ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ መቀመጧን ጥናት አመለከተ
ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋትና የኢንተርኔትን ነጸነት በመገደብ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በብሉምስበሪ አሳታሚ ላይ የታተመ የጥናት መጽሐፍ አመላከተ።
“የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ” በሚል ርእስ በፊሊሽያ አንቶኒዮ እና ቶኒ ሮበርትስ የተጠናውና መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ባደረገው ብሉምስበሪ አሳታሚ ድርጅት ላይ በመጸሐፍ መልክ ታትሞ የወጣው ጥናት በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 በአህጉረ አፍሪካ በሀገራት የተፈጸመውን የኢንተርኔት መዘጋት ገምግሟል።
በዚህም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 ባሉት በለፉት ዘጠኝ ዓመታት 193 የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ አህጉር መመዝገቡን ገልጿል።
በተጠቀሱት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ በተፈጸሙ የኢንተርኔት መዘጋት ድግግሞሽ መጠኖች ሀገራትን በደረጃ ያስቀመጠው ጥናቱ ኢትዮጵያን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ሰላሳ ጊዜ ኢንትርኔት የዘጋች በሚል ከ55ቱ የአፍሪካ ሀገራት በአንደኛ ደረጃ አስቀምጧታል።
በእርስ በእርስ ጦርነት እየታመሰች የምትገኜው ጎረቤት ሀገር ሱዳን በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ 21 ጊዜ ኢንተርኔትን በመዝጋት በአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ስትቀመጥ፤ እንደዚሁ ባለፉት ዓመታት በሰላም እጦትና በግጭት ውስጥ ያለችው ሰሜን አፍሪካዊቷዓ ሀገር አልጀሪያ ደግሞ 14 ጊዜ ኢንተርኔትን በመዝጋት በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።
ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በአህጉሪቱ የተፈጸመው የኢንተርኔት መዘጋት ሁኔታና የድግግሞሽ መጠኑ ከሀገር ሀገር ከፍተኛ ልዩነት የሚታይበት መሆኑንም የጥናቱ ውጤት አመላክቷል።
በዚህም ምንም እንኳዓን በብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት የኢንተርኔት መዘጋት የነበረ መሆኑን የጠቆመው ጥናቱ፤ በዚያው ልክ ደግሞ በ14 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ አንድም የኢንተርኔት መዘጋት አለመመዝገቡን፤ በሌሎች 14 ሀገራት ደግሞ የኢንተርኔት መዘጋት የገጠመው አንድ፣ አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑን አስታውሷል።
በአህጉሪቱ የተፈጸመው የኢንተርኔት መዘጋት ክስተት በመጠንና በድግግሞሽ ብቻ ሳይሆን ለድርጊቱ መፈጸም መንስኤ በሆኑ ገፊ ምክንያቶች ጭምርም ሰፊ ልዩነት የሚታይበት መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል።
የመንግሥታት ሕዝባዊ አመጽን መፍራት፣ በሀገራቱ ውስጥ የሚኖሩ ግጭቶችና ጦርነቶች፥ ምርጫን ተከትለው ሊቀሰቀሱ የሚችሉ አመጾች፥ የፈተና መሰረቅንና መጭበርበርን ለማስቀረትና የፖለቲካ ተቃውሞን ለማፈን የሚወሰዱ ሴንሰርሽፖች ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በአህጉሪቱ ለተፈጸሙ የኢንተርኔት መዘጋትና በኢንተርኔት ነጻነት ላይ ለተፈጸሙ ገደቦች ዋነኛ መንስኤ ሆነው መለየታቸውንም ጥናቱ ገልጿል።
ኢትዮጵያን በተመለከተም የኢንተርኔት መዘጋት በተለይም በግጭትና በጦርነት ወቅት ሊኖረው የሚችለው ውጤትና በዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ላይ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖና በጥናቱ ተካቷል።

ኢትዮጵያ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የባህር በር የማግኜት መብቷን እንደግፋለን ሲሉ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ገለጹ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ከአል አረቢያ ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የባህር በር መውጫ የመፈለግና የማግኜት መብቷን እንደግፋን ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም “የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት በዓለም አቀፍ ሕግ ማዕቀፍ ውስጥ አዲስ አይደለም። ማንኛውም ሀገር ዓለም አቀፍ ሕጎችን እና አህጉራዊ ስምምነቶችን እስካከበረ ድረስ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሊጠቀምባቸው የሚችላቸው እውቅና ያላቸው ዘዴዎች እና አካሄዶች አሉ" ሲሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ እነዚህን ሕጋዊ መንገዶች በሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ከተከተለች ሃሳቧ ማሳካት የምትችል መሆኗን ሶማሊያ እንደምታምንና ሀሳቡንም እንደምትደግፍም ነው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸክ መሀመድ
የገለጹት።

🚚🚓🚍ሁሉንም የተሽከርካሪ ዓይነቶች ጥራት ለመቆጣጠር የሚያስችል ሀገራዊ ስታንዳርድ ተዘጋጀ
ከዚህ በፊት ቀድመው የገቡትንም ሆነ በቀጣይ ወደሀገር ውስጥ የሚገቡ ማናቸውም ዓይነት ተሽከርካሪዎችን ጥራት ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ሀገራዊ የተሽከርካሪዎች ጥራት መቆጣጠሪያ ስታንዳርድ ማዘጋጀቱን የትራስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ።
ከሰሞኑ “ሲኖትራክ መኪና ወደሀገር ውስጥ እንዳይገባ ተከለከለ” ከመባሉ ጋር ተያይዞ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚንስቴር የሕዝብ ግንኙነት እና ኮምዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አመለወርቅ ሕዝቅኤል፤ ሲኖትራክ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ ያሉ ወደሀገር ውስጥ የሚገቡና ከዚህ በፊትም የገቡ ማናቸውም ዓይነት ተሽከርካሪዎችን ጥራትና የቱክኒክ ብቃት ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ሀገራዊ ስታንዳርድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ስታንዳርዱን የሚያሟላ ከሆነ ደግሞ ሲኖትራክም ሆነ ማንኛውም መኪና መግባት ይችላል ብለዋል።
በአዲስ መልክ የተዘጋጀው ሀገራዊ የሽከርካሪዎች ጥራት መቆጣጠሪያ ስታንዳርድ የቴክኒክ ብቃት ብቻ ሳይሆን ወደሀገር ውስጥ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ለአየር ንብረትና ለአባቢ ብክለት፥ ብሎም ለትራፊክ አደጋ መንስኤ መሆን የማይችሉ መሆናቸውንም ጭምር የሚቆጣጠር መሆኑንም አመላክተዋል።
ለዚህም በስታንደርዱ ላይ ተከታታይ ግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱንና ከአስመጪዎች እና የካምፖኒ ተወካዮች ጋር ውይይት መካሄዱንና መግባባት ላይ መደረሱን የሕዝብ ግንኙነት እና ኮምዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚዋ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
(#አዲስ_ማለዳ)

ሁሉንም የተሽከርካሪ ዓይነቶች ጥራት ለመቆጣጠር የሚያስችል ሀገራዊ ስታንዳርድ ተዘጋጀ
ከዚህ በፊት ቀድመው የገቡትንም ሆነ በቀጣይ ወደሀገር ውስጥ የሚገቡ ማናቸውም ዓይነት ተሽከርካሪዎችን ጥራት ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ሀገራዊ የተሽከርካሪዎች ጥራት መቆጣጠሪያ ስታንዳርድ ማዘጋጀቱን የትራስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ።
ከሰሞኑ “ሲኖትራክ መኪና ወደሀገር ውስጥ እንዳይገባ ተከለከለ” ከመባሉ ጋር ተያይዞ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚንስቴር የሕዝብ ግንኙነት እና ኮምዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አመለወርቅ ሕዝቅኤል፤ ሲኖትራክ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ ያሉ ወደሀገር ውስጥ የሚገቡና ከዚህ በፊትም የገቡ ማናቸውም ዓይነት ተሽከርካሪዎችን ጥራትና የቱክኒክ ብቃት ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ሀገራዊ ስታንዳርድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ስታንዳርዱን የሚያሟላ ከሆነ ደግሞ ሲኖትራክም ሆነ ማንኛውም መኪና መግባት ይችላል ብለዋል።

Comments